ch
Feedback
ከፍልስፍና ዓለም™

ከፍልስፍና ዓለም™

前往频道在 Telegram

A wise man is one who has learned to restrain his desires.The lowest level of life is to live only within the bounds of desire.Most people have many desires but little knowledge wisdom belongs to those who have much knowledge and few desires -Schopenhauer

显示更多

📈 Telegram 频道 ከፍልስፍና ዓለም™ 的分析概览

频道 ከፍልስፍና ዓለም™ (@philosophyofworld1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 23 936 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 3 188,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 395

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 23 936 名订阅者。

根据 10 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 966,过去 24 小时变化为 34,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 15.13%。内容发布后 24 小时内通常能获得 5.68% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 619 次浏览,首日通常累积 1 359 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 19

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
A wise man is one who has learned to restrain his desires.The lowest level of life is to live only within the bounds of desire.Most people have many desires but little knowledge wisdom belongs to those who have much knowledge and few desires -Schopen...

凭借高频更新(最新数据采集于 11 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

23 936
订阅者
+3424 小时
+1947
+96630
帖子存档
የጥናቱ ረቂቅ።

ከልጅነት ሃይማኖታቸዉ ለቀዉ የወጡ ኢአማኞች(apostate/analytical atheists) ከሃይማኖተኞች እና ከልጅነታቸዉ ጀምሮ ኢአማኝ ከነበሩ ሰዎች በላይ ጥልቅ የማሰብ እና የማገናዘብ ችሎታ አላቸዉ። የካምብሪጅ ዩንቨርስቲ ፕረስ ባወጣዉ የጥናት ግኝት ላይ ይህ ዉጤት ቁልጭ ብሎ ሰፍሯል፤ ጥናቱ ከ70,000 በላይ ተሳታፊዎችን በማካተት በ ጥልቀት ማሰብ(reflective thinking) እና በእምነት መካከል ያለዉን ትስስር አጥንቷል። የሰዎችን የማስላሰል ብቃት ለመለካት Cognitive Reflection Test (CRT) የተባሉ ጥያቄዎችን ተጠቅመዋል። እነዚህ ጥያቄዎች መጀመሪያ ላይ ለአእምሮ ቀላልና ትክክል የሚመስል ግን ደግሞ ስህተት የሆነ "የደመነፍስ (Intuitive)" መልስ የሚመጣባቸው ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት ግን ቆም ብሎ ማሰላሰል (Reflection) የሚጠይቁ ናቸው። ተመራማሪዎቹ ውጤቱ አስተማማኝ መሆኑን ለማረጋገጥ 4 የተለያዩ ንዑስ ጥናቶችን አካሂደዋል። ​በ CRT ፈተናዎች ላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ (ማለትም በደመነፍሳዊ ስህተቶች ሳይታለሉ ቆም ብለው ያሰቡ) ሰዎች፣ ለአምላክ ያላቸው እምነት አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ጥናቱ እንደ ሂሳብ ችሎታ ወይም አጠቃላይ የትምህርት ደረጃ ያሉ ሌሎች ተጽዕኖዎችን ወደ ጎን በመተው፣ "የማሰላሰል ብቃት" ራሱን ችሎ ለአምላክ-አልባነት (Atheism) አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አረጋግጧል። ግኝቱም በጥልቀት የሚያስቡ እና ምክንያታዊ የሆኑ ሰዎች ከልጅነት እምነታቸዉ የመዉጣት እድላቸዉ ከ 1.6 እጥፍ ይበልጣል፤ ይህም ክስተት analytical apostasy በመባል ይጠራል። ሌላዉ ይሄ ጥናት ያስታወቀዉ ነገር ከልጅነታቸዉ ጀምሮ ኢአማኝ የነበሩ እና ሃይማኖተኛ ሰዎች ተመሳሳይ የማሰብ ደረጃ እንዳላቸዉ ነዉ፤ ማለትም የዉጤት ልዩነት የታየዉ በ apostate/analytical atheists ላይ ብቻ ነዉ። በተጨማሪ ይህ correlation one way መሆኑን ወይም deconversionን ላይ እንጂ conversionን(ወይም ከ ኢ-አማኝነት ወደ አማኝነት) መምጣት ላይ እንደማይሰራ ጥናቱ አረጋግጧል። Well the "atheist-smart" turns out to be a myth but an "apostate atheist-smart"? Well yeah! That turns out to be evidential lol!

አንድ ወጣት በዉስጥ መጥቶ አንድ ለወጣቱ የሚጠቅም ፅሁፍ እንደከተበ እና እኔም አንብቤዉ ከተመቸኝ እንዳጋራለት ጠየቀኝ። ፅሁፉንም አንበብኩት እና አሪፍ ሆኖ ስላገኘዉት ላጋራዉ ወደድኩ። ፅሁፉ በፀሃፊው ዘአብ ዘሚካኤል አጭር ግለ ታሪክ መባቻዉን ሲያረግ በመቀጠል የተለያዩ የ ህልዉና ፍልስፍናዎች(existential philosophy) እና የስነ ልቦና ጉዳዮችን ያትታል። ፀሃፊዉ በሃገራችን በነበረዉ የሰሜኑ እርስ በእርስ ጦርነት መሃል ያለፈ በመሆኑ ስለ ጉዳዩ ሲፅፍ ከረቂቅ እሳቤዎች ባሻገር ለነገሮቹ ጥልቅ መረዳትን ይዞ እንዳፃፈ ያስታዉቃል፤ ብታነቡት ታተርፉበታላቹ። የልጁ የግል አካዉንት፦ @Nages_Desta

የሚከለክል እና የሚፈቅድ የበላይ አካል ከሌለ ሁሉም ነገር ተፈቅዷል ማለት ነዉ? አልበርት ካሙ በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ከደረሰዉ  The Just assassins ከሚሰኘዉ ተዉኔት መካከል ሁለት የፍልስፍና ዘርፍ ሃሳቦችን የሚያስተጋቡ የሁለት ገፀ ባህሪያት ምልልስ ይገኝበታል። እነዚህ ገፀባህሪያት የሩሲያ ሶሻሊስት አቢዮት እንቅስቃሴ አባላቶች ሲሆኑ፤የአንድ አንባገነን መሪን ግድያ ልያስፈፅሙ በተጓዙበት ወቅት ላይ የተፈጠረ ኩነት በመካከላቸዉ አለመግባባትን ይፈጥራል ትዕይንቱም እንዲህ እያለ ይቀጥላል፦ ​(ቦታው በአንድ ሚስጥራዊና ጨለማ ክፍል ውስጥ ነው። ያኔክ [ኢቫን ካልያዬቭ] ግራንድ ዱክን ለመግደል የያዘውን ቦምብ ሳይወረውር፣ በሐዘንና በተስፋ መቁረጥ ተሞልቶ ወደ ክፍሉ ይመለሳል። ስቴፓን ፊቱ በንዴት ቀልቶ ይጠብቀዋል። ሌሎቹ የአብዮቱ አባላት በዝምታ ተቀምጠዋል።) ​ስቴፓን፦ (በቁጣ ወደ ያኔክ እየቀረበ) ቦምቡን ሳትወረውረው ተመለስክ? ለምን? ለምን ሳትወረውረው ቀረህ ያኔክ? ​ያኔክ፦ (በመድረክ ላይ በረዥሙ እየተነፈሰ፣ እጆቹ እየተንቀጠቀጡ) ሰረገላው አጠገቤ ሲደርስ... ልጆቹን አየኋቸው። የግራንድ ዱክ የወንድም ልጆች ሰረገላው ውስጥ ነበሩ። ሁለት ትናንሽ ሕፃናት። እርስ በርሳቸው እየተያዩ ይስቃሉ... ፊታቸውን እያየሁ ያንን ቦምብ መወርወር አልቻልኩም። አእምሮዬ ፍቃደኛ አልሆነልኝም። ​ስቴፓን፦ (በፌዝ ይስቃል) ሕፃናት? ለአምባገነኑ ቤተሰብ አዝነህ የሺዎችን ነፃነት አሳለፍክ? እነዚያ ሕፃናት ነገ አድገው ልክ እንደ አጎታቸው እኛን ከመጨቆንና ከመግደል ወደኋላ አይሉም። በዚህ ምድር ላይ ከነፃነት በላይ ምንም የተቀደሰ ነገር የለም፤ አንተ ግን በስሜት ተሸነፍክ! ​ያኔክ፦ (ቀና ብሎ እያየው፣ በጽናት) እኔ የመጣሁት ሰዎችን ነፃ ለማውጣትና ሕይወትን ለመጠበቅ ነው ስቴፓን፤ ሕይወትን ዝም ብሎ ለማጥፋት አይደለም። የሰውን ልጅ ሕይወት ዋጋ ካሳጣነው፣ የምናመጣው ነፃነት ራሱ ትርጉም አልባ ባዶ ይሆናል። ​ስቴፓን፦ (ድምፁን ከፍ አድርጎ) ሕይወት? ዋጋ? እነዚህ እኮ የድሮ የሃይማኖትና የሞራል ተረቶች ናቸው ያኔክ! ከእኛ በላይ ሰማዩ ባዶ ነው። የሚጠብቀን አምላክም ሆነ ፍትሃዊ ዕጣ ፈንታ የለም። በዚህ ፍጹም ትርጉም በሌለውና ጨካኝ በሆነ ዓለም ውስጥ ፍትህን መፍጠር ያለብን እኛው ራሳችን ነን። ፍትህ ደግሞ በደምና በኃይል እንጂ በስሜታዊነት አትመጣም። ​ያኔክ፦ ሰማዩ ባዶ ስለሆነ ብቻ እኛ ራሳችንን 'አምላክ' አድርገን መሾም የለብንም ስቴፓን። አምላክ የለም ብዬ ማመኔ እኮ ሰዎችን እንዳሻኝ እንዳርድ መብት አይሰጠኝም። ይልቁኑ በዚህ ምድር ላይ ያለነው እኛው ብቻ ስለሆንን፣ እርስ በርሳችን ልንረዳዳና የሰውን ልጅ ክብር ልንጠብቅ ይገባል። ሕፃናትን በመግደል የምናመጣው ነፃነት እኛኑ ወደ አውሬነት ይቀይረናል። ​ስቴፓን፦ (ወደ ያኔክ ተጠግቶ፣ዓይን ዓይኑን እያየ) አንተ ገና አልገባህም! እውነተኛ አብዮተኛ ሕይወትን አይሳንስም። እኔ ሰዎችን የምወደው አሁን ባሉበት ደካማና ባሪያ ማንነታቸው ሳይሆን፣ ወደፊት በምናመጣላቸው ፍጹም ነፃነት ውስጥ ነው። ለዚያ የወደፊት ነፃነት ሲባል አሁን ያለውን ትውልድ መስዋዕት ማድረግ ካስፈለገ እናደርጋለን። ከእኛ በላይ ማንም ሕግ ሊሰጠን አይችልም፤ እኛ ራሳችን ነን የበላይ አካላት! ​ያኔክ፦ (በቁጭት) ጨቋኞቹም የሚያስቡት ልክ እንደ አንተ ነው ስቴፓን። እነሱም ለራሳቸው ዓላማ ሲሉ ሰዎችን ይገድላሉ። እኔ ለነፃነት ስል ለመሞት ዝግጁ ነኝ፣ ነገር ግን ለነፃነት ስል ንጹሐንን አልገድልም። ያንን ካደረግኩ ከእነሱ በምን ተለየሁ? እኔ ሰውን የምወደው አሁን ባለው ሕያው ማንነቱ ነው፤ ወደፊት በሚመጣ ረቂቅ ሃሳብ አይደለም። ​(በክፍሉ ውስጥ ጥልቅ ዝምታ ይሰፍናል... ስቴፓን ፊቱን አዙሮ በቁጣ ይርቃል፣ ያኔክ ግን የያዘውን የሞራል ሸክም እያሰበ በሃሳብ ይዋጣል) በዚህ ተዉኔት ላይ ያኔክ አምላክ ኖረም አልኖረም የሰዉ ልጆችን ተፈጥሯዊ ክብር መጠበቅ ሊመነጭ የሚገባዉ ከሰዋዊ ማንነት ነዉ በማለት የsecular Humanism እሳቤን ሲያሳይ ስቴፓን ደሞ በተቃራኒዉ አፅናፈ አለም ወጥ የሆነ መተዳደሪያ ስለሌለዉ ቅድሚያ ልንቆም የሚገባዉ እራሳችን ላቆምነዉ አላማ ነዉ ከዛ የዘለለ ሃላፊነትም ሆነ ግዳጅ የለብንም በማለት የ Radical nihilism እሳቤን ያንፀባርቃል።

ሌባ ዳኛ FIFA ቆሻሻ ነው 🙌
ሌባ ዳኛ FIFA ቆሻሻ ነው 🙌

Astral Projection በ Insidious እና Behind her eys በሚሉት ፊልሞች ውስጥ እንዴት ተገለፀ የሚለውን እንመልከት። Behind Her Eyes 6 ክፍሎች ያሉት ሲሆን Astral Projection የተገለፀበት መንገድ ትንሽ የሳሳና ብዙውን እውነት የማያሳይ ነው። በፊልሙ ውስጥ Astral Projection ነብስ ከ አካል ውስጥ በመውጣት ከዚህ በፊት በምታውቃቸው ቦታ ብቻ እየተዘዋወረች የሚከናወነውን የምትታዘብበትን የሚተርክ ነው። ፊልሙ ላይ በህልማቸው በ ቅዥት አለም የሚቸገሩና በእንቅልፍ ልባቸው ስለሚነሱ ሰዎች (sleep walker) ያትታል። እና የ አዕምሮ ህክምና ማገገሚያ የገቡ ሁለት ካራክተሮች እናያለን። እንቅልፍ መተኛት የሚቸገሩና በህልማቸው ሁል አስፈሪ ተመሳሳይ ህልሞችን የሚያዩ ናቸው። በሂደት አንዷ ካራክተር በ Astral projection በልምምድ ህልሟን መቆጣጠርና ማዘዝ ስትችል ያሳያል። ቤቷ ተኝታ ነብሷ (ንቃተ ህሊናዋ) ከዚህ በፊት የምታውቃቸው ቦታዎች እየተዟዟረች ባሏ ቢሮ ምን እንደሚሰራ ትከታተለዋለች። አብራው ያለውን በቅዥት የሚቸገር ጓደኛዋን ስለ Astral projection ታሳየውና አብረው ልምምዱን ማድረግ ይጀምራሉ። በፊልሙ ላይ ከ አስትራል በፊት መደረግ ስለሚገባቸው ዝግጅቶች ያሳያል። ጣትን መቁጠር ተመስጦ ማድረግና ከመተኛታችን በፊት ያለች በሰመመን የምናያት የራሳችን የህልም አለም (Lucy dreaming) አስፈላጊ መሆናቸውን ያትታል። ሌላው ስለ አስትራል የተነሳው ጉዳይ በ Astral projection ነብሳችን መሄድ የምትችለው ከዚህ በፊት በምናውቀው ቦታ ብቼ መሆኑን ያትታል። ከዚህ በፊት ያልሄድንበት ቦታ ላይ መሄድ እንደማንችል አፅንዖት ይሰጣል። በተወሰነ መልኩ የነብስ ነጠቃም እንዳለ ያትታል። ሁለት የ አዕምሮ ማገገሚያ ማዕከል ያሉ ጓደኛሞች Astral projection ካሳየችው በኋላ እየተገበሩት ነብሳቸው ከሰውነታቸው ተነጥሎ በሚገዟዟሩበት ጊዜ አካል ተቀያይረው ለመሞከር ይፈልጋሉ። በመሀል የሷ ነብስ የሱ ውስጥ የሱ ነብስ የሷ ውስጥ እንዳሉ ጓደኛዋ የሷን አካል ሲነጥቃትና እሷ የሱ አካል ውስጥ እንዳለች ሲገላት ያሳየናል። ከዛም የሱ ነብስ በሷ ነብስ ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀስ ያሳያል። ፊልሙ በተወሰነ መልኩ ስለ Astral projection የሚያሳይ ሲሆን የተሳሳቱ ነገሮችንም ይናገራል። ለምሳሌ በ Astral real መጓዝ የምንችለው የምናውቀው ቦታ ብቻ ነው የሚለው ድምዳሜ ከእውነታው የራቀ ነው። አንዳንድ ቦታዎች ለማየት እንደሞከርኩት ነብስ አይታ የማታውቀው ቦታ እንደምትጓዝ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ። Insidious በሚለው ፊልም ውስጥ ይሄ ፊልም ስለጉዳዩ የተሻለ የሚገልፅ ሆኖ አጊኝቼዋለሁ ፊልሙ chapter 2 chapter 3 እያለ 4 ክፍሎች ያሉት ነው። የመጀመሪያው ክፍል ላይ ፊልሙ ሲጀምር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ህፃን ልጃቸው ኮማ ውስጥ ሳይሆንም ሳይነቃ በእንቅልፍ አለም ውስጥ በኦክስጅን ብቻ የሚቆይበትን ሂደት ያስቃኛል። በዚህ ግራ መጋባት ወስጥ እንዳሉ ሀኪሞችም ሳይኮሎጂስቶችም መላ ሊሰጧቸው አልቻሉም። በዚህን ጊዜ አያቱ አንድ ሴት ታናግራለች። ሴትየዋ ለሰው የማይታይ የምታይ መንፈሳዊ ጥበብ ያላት ናት። ልጁንም ካየችው በኋላ ለቤተሰቡ አንድ ነገር ነገረቻቸው ህፃኑ Astral projection መሆኑን ሳይረዳ በህልም አለም ያለ መስሎት ሳያስበው ሌላቸፈኛው አለም ውስጥ Astral plane ሄዷል። እናም ሳያውቀው ነብሱ ከሰውነቱ በጣም እየራቀ በመሄዱ ለመመለስ እንዳይችል ሆኗል። ነብስ ነጣቂ የሚባሉ (parasite) ዴሞን ክፉ ለሰው የማይታዩ መናፍስት ከዚህ በፊት ኖረው የሞቱ ሰዎች ነብሱን ከአካሉ አርቀዋት በህፃኑ ሰውነት የነሱን ነብስ ለመክተት የሚያደርጉትን ትግል ያሳያል። ህፃኑንም ለመመለስ አባቱ በ Astral ሄዶ ሲመልሰው ያትታል። ይህች መንፈስ የምታየው የ psychic power ያላት ስለ ጉዳዩ chapter 3 በሚለው ክፍል ላይ አንድ ነገር ትናገራለች። Astral projection ሁለት አለም አለው ትላለች። አንደኛው white ጥሩ ቦታ የምንሄድበትና መንፈሳዊ ጥቅምና እውቀት የምናገኝበት መልካሙ አለም እና መልካም መናፍስት ያሉበት ሲሆን የ Black የሚባለው ክፍል ግን ነብሳችንን ከአካላችን አርቀዋት የነሱን ነብስ በሰውነታችን ለማስገባት የሚጥሩበት ሰዎችን ለማሰቃየት የሚፈልጉ ክፉ መናፍስት ያሉበት ነው። ፊልሙ አንድ ሰው አስትራል ከማድረጉ በፊት አንድ ትልቅ አላማ ሊኖረው ይገባል የሚል መልእክት ይናገራል። አላማ ካለን ነብስ ነጣቂዎቹ የሙት መንፈሶቹን የመታገል አቅም ይኖረናል የሚል ይናገራል። እነዛን ነብስ ነጣቂዎች አለመፍራትም ዋነኛው ነገር ነው። እነሱ የሞቱ በመሆናቸው ከኛ ጋር በሀይል አይጣጣሙምና። በጥቅሉ የ አስትራልን ትክክለኛ መልክ የሚያሳይ ነው። ሳጠቃልለው ያለምንም መንፈሳዊ ልምምድ እና ሙከራዎች እንዲህ አይነት ልምምድ የሚሞክር ሰው ትልቅ ቀውስ ውስጥ እንደሚገባ ነው። ከ YouTube ብዙ ቪዲዮ ማግኘት ትችላላቹህ በዚህ ልምምድ ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሚያደርጉትን ትግልና ስቃይ። አንድ ጊዜ Astral projection የሞከረ ሰው ሰውነቱ የመንፈሳዊውን አለም የሚከፍት በመሆኑ የጭለማው አለም ነብስ ነጣቂዎች እስከለተ ሞታችን ድረስ ያሳድዱናል። ብዙ ያየኋቸው ይሄን ልምምድ ያደረጉ ሰዎች ወደ ጭለማው አለም ነው የሚገቡት። ከዛም እንቅልፍ መተኛት እስካይችሉ ድረስ መንፈሳዊው አለም ከ እውነተኛው አለም ጋር ይቀላቀልባቸዋል። ለኛ ባይን የማናያቸው መናፍስት ሙታኖች ለነሱ ይታያቸዋል። የብሳችን ያኛውን አለም ከገባችበት መውጫዋ ሀይማኖታዊ መንገድ ያልታገዘ ከሆነ ውጤታማ የመሆን እድሉ ዝቅ ያለ ነው። ፊልሙን እንድታዩት እጋብዛለሁ። @ourrthought

Netflix እንደዚ አይነት Psychological Thriller የሚገርም Plot Twist እንደሰራ ለምን አልነገራቹንም እስካሁንም Worth to Watch ያላያቹት ካላችሁ 👏
Netflix እንደዚ አይነት Psychological Thriller የሚገርም Plot Twist እንደሰራ ለምን አልነገራቹንም እስካሁንም Worth to Watch ያላያቹት ካላችሁ 👏

photo content

ጥበብ የገመደቺዉ ፍቅር ታሪኩ የሚጀምረው በ1924 ዓ.ም በጀርመኗ የማርቡርግ ከተማ ነበር። በወቅቱ ሀይደገር የ35 ዓመት ጎልማሳ፣ ባለትዳር፣ የሁለት ልጆች አባት፣በሀሳብ ጥልቀቱ በአውሮፓ ዝነኛ የነበረ ፈላስፋ እና ፕሮፌሰር ሲሆን፤ ሀና አረንድት ደግሞ ገና የ18 ዓመት ወጣት እጅግ ብልህ አይሁዳዊት ተማሪው ነበረች። ሀይደገር በተማሪው ልዩ አእምሮአዊ ብስለት ሲማረክ፤ እሷም በአስተማሪዋ ጥልቅ እውቀት ተሳበች። በመካከላቸው የነበረው ግንኙነት በፍጥነት ወደ ስሜታዊ የፍቅር ግንኙነት ተቀየረ። ነገር ግን የሀይደገር ትዳር እንዳይፈርስና በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ቅሌት እንዳይፈጠር ሲሉ ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ሚስጥራዊ ለማድረግ ተገደዱ። ​ለአራት ዓመታት ያህል አብረው የቆዩ ሲሆን፤ አሰራራቸውም ሙሉ በሙሉ በምስጢራዊ ደብዳቤዎች ላይ የተመሰረተ ነበር። ሀይደገር ለሀና በሚፅፋቸው ደብዳቤዎች ላይ የሚገናኙበትን ሰዓት እና ቦታ በምስጢር ኮድ ያስቀምጥ ነበር፤ ለምሳሌ በክፍሏ መስኮት ላይ የምታበራው መብራት ወይም የምታስቀምጠው ምልክት እሱ ወደ እሷ መምጣት መቻሉን ወይም አለመቻሉን የሚጠቁምበት አሰራር ነበራቸው። በሚገናኙበትም ወቅት ግንኙነታቸው ከስሜት ባለፈ በጥልቅ የፍልስፍና ውይይቶች፣ በግሪክ ስነ ግጥም እና በሃሳብ ልውውጥ የተሞላ ነበር። ሆኖም ይህ ግንኙነት በስውር መቀጠሉ ስላስቸገራቸውና ሀናም የራሷን የትምህርት መስመር መያዝ ስለነበረባት በ1928 ዓ.ም ግንኙነታቸውን በስምምነት አቁመው በጓደኝነት ለመቀጠል ወሰኑ፤ ሀናም ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ተዛወረች። ​ነገር ግን በ1933 ዓ.ም አዶልፍ ሂትለር በጀርመን ስልጣን ላይ ሲወጣ ያልታሰበዉ የታሪክ ነዉጥ መጣ። ሀይደገር የፍራይቡርግ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለመሆን ሲል የናዚ ፓርቲ አባል ሆነ። ስልጣኑን እንደያዘም የናዚን መፈክሮች የሚያስተጋቡ ንግግሮችን ማድረግ የጀመረ ሲሆን የራሱን አይሁዳውያን መምህራንና ጓደኞቹን የሚያገል የፖለቲካ እርምጃዎችን ወሰደ። ይህ ክህደት በሀና ላይ ታላቅ የሞራል ስብራት ፈጠረ። አይሁዳዊት በመሆኗ የጀርመን ዜግነቷ ተገፎ በናዚ ታሰረች፤ በመጨረሻም በጓደኞቿ እርዳታ በስደት መጀመሪያ ወደ ፈረንሳይ ከዚያም በ1941 ዓ.ም ወደ አሜሪካ አመለጠች። በዚህ የፖለቲካ ማዕበል ምክንያት በመካከላቸው ለ17 ዓመታት ያህል ፍፁም ዝምታ ሰፈነ። ​ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አብቅቶ ናዚ ሲሸነፍ ሀይደገር ናዚን በመደገፉ ምክንያት ከዩኒቨርሲቲ ተባረረ፣ የማስተማር መብቱ ተከለከለ እና በክህደት ተወግዞ ተገለለ። በአንጻሩ ሀና አረንድት በአሜሪካ ውስጥ ስለ አምባገነንነት ስርዓት ምንነት የምትፅፍ ታዋቂ የፖለቲካ ፈላስፋ ሆነች። እ.ኤ.አ. በ1950 ዓ.ም ሀና ለስራ ጉዳይ ወደ ጀርመን በተመለሰችበት ወቅት በነበረችበት ሆቴል አቅራቢያ የሚኖረውን ሀይደገርን ልታየው ወሰነች። ካለፉት 22 ዓመታት የስደት እና የፖለቲካ ቁስል በኋላ አይን ለአይን ሲገናኙ ሀና ያደረሰባትን የግል ክህደት ወደ ጎን በመግፋት ሀይደገር ያጠፋውን የፖለቲካ ጥፋት እና የፍልስፍና እውቀቱን ለይታ ለመመልከት ወሰነች። ​የእርሱን ድንቅ የፍልስፍና ስራዎች ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም ለአሜሪካና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብም አስተዋወቀች፤ ስሙና እውቀቱም ከታሪክ ገፅ እንዳይጠፋ ትልቅ እገዛ አደረገችለት። እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ ድረስም በደብዳቤዎች እየተፃፃፉ የነበረውን የድሮ የፍቅር ትዝታ እና የፍልስፍና ትስስር በክብር በመጠበቅ ታሪካቸውን አጠናቀቁ።

◉ አትፍረድ ! ➊ ይህ «Aattam» (The Play) የተሰኘው የMalayalam  ፊልም በተለየ መልኩ እወደዋለሁ። ከራሴ ጋር እንዳወራ አድርጎኛል። ታሪኩ የሚያተኩረው Arangu በተሰኘ የአንድ የቲያትር ቡድን አባላት ዙሪያ ነው። በዚሁ የቲያትር ቡድን ውስጥ ብቸኛ ሴት ተዋናይ አለች። እና ይቺ ሴት ከአንድ ትርኢት በኋላ በተዘጋጀ የምሽት ግብዣ ላይ በቡድኑ ውስጥ ካሉ ወንዶች በአንዱ የጾታ ትንኮሳ ጥቃት ይደርስባታል። ​ድርጊቱ ይፋ ከወጣ በኋላ በቡድኑ ውስጥ ያሉትን 11 ወንዶች ያካተተ አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራል። ታሪኩ ሙሉ በሙሉ የሚያተኩረው እነዚህ ወንዶች ጥቃቱን በሰሙበት ወቅት በሚያሳዩት የተለያየ ባህሪና በሚያደርጉት ሙግት ዙሪያ ነው። ወንዶቹ መጀመሪያ ላይ ለሴቷ ሙሉ ድጋፍና አጋርነት ያሳዩ ቢመስሉም፣ ቀስ በቀስ የራሳቸው የግል ጥቅም፣ ዝና እና የሚያገኟቸው የገንዘብ እድሎች ጥያቄ ውስጥ ሲገቡ አቋማቸውን መለዋወጥ እና ጥቃቱን ማሳነስ ይጀምራሉ። ❷ ይህን ፊልም ካየሁ በኋላ በቀጥታ ታዋቂው የሆሊውድ ክላሲክ ፊልም "12 Angry Men" ነው ትዝ ያለኝ። በቅርፅም ሆነ በይዘት እጅግ በጣም የሚቀራረቡ ናቸው።  በ12 Angry Men ውስጥ 12 የዳኞች ማህበር አባላት የአንድን ልጅ እጣ ፈንታ ለመወሰን እንደሚከራከሩት ሁሉ፣ በAattam ውስጥም 11 የቡድኑ ወንዶች በአንዲት ሴት ላይ በደረሰው ጥቃት ዙሪያ ይከራከራሉ። በሁለቱም ፊልሞች መጀመሪያ ላይ ሁሉም ሰው በአንድ ወገን የተሰለፈ ቢመስልም፣ ውይይቱና ክርክሩ እየጠነከረ ሲሄድ ግን የሰዎች አቋም እንደ ፍላጎታቸውና ጥቅማቸው ሲዋዥቅና ሲቀያየር ይታያል። ❸ ​Aattam የ12 Angry Menን መዋቅር ቢወስድም የስነ-ልቦና ብርበራውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ያሳድገዋል። ወንዶቹ ለሴቷ የቆሙ መስለው፣ በመጨረሻ ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ ተጎጂዋን ዳግመኛ እንዴት እንደሚበድሏት እናያለን። ፊልሙ ሲያልቅ ፍርዱን በቀጥታ ለተመልካች በመተው ነው። ፊልሙ መጨረሻ ላይ "ተጠርጣሪው ጥቃቱን በእርግጥ ፈጽሟል ወይስ አልፈጸመም? ወንዶቹስ ምን ሆኑ?" የሚለውን ፍርድ ቤት ወይም ፖሊስ ዘንድ አድርሶ በቁጥጥር ስር ሲውሉ አያሳየንም። ዳይሬክተሩ ይህንን ያደረገበት ምክንያት ፊልሙ ትኩረት እንዲሰጠው የፈለገው በአንድ ወንጀለኛ ላይ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላው ማህበረሰቡ ራሱን እንዲፈትሽና እንዲመለከት ስለፈለገ ይመስለኛል ። ● ፊልሙ ለእኛ የተወልን ጥያቄ ሲመስለኝ ይሄ ነው... ​"አንድ በደል ሲፈጸም፣ ለተበዳዩ የምንቆመው እውነትንና ፍትህን ፈልገን ነው ወይስ የራሳቸውን ጥቅም እስካልነካ ድረስ ብቻ?" የፊልሙ ደራሲ ወይንም አዘጋጅ በታሪኩም ጭምር መፍረድ የፈሩት ክብደቱን ስለተረዱ ይሆናል።  ❹ ያው የሰው ልጅ ፍፁም ነፃ (እንደ ነጭ ወረቀት) ሆኖ አይፈርድም። እያንዳንዱ የሚያሳልፈው ውሳኔ፣ ፍረጃ ወይም አቋም ከውስጣችን ማንነት፣ ከኖርንበት ህይወት፣ ካለን ፍርሃትና ከግል ጥቅማችን የሚቀዳ ነው። ለዚህ ነው በህግና በፍትህ ሥርዓት ውስጥ Objective Truth ላይ መድረስ እጅግ ከባድ የሚሆነው። አንድ ዳኛ ፍፁም ፍትሃዊ ለመሆን መጀመሪያ የራሱን ውስጣዊ ጭፍን ጥላቻ፣ ፍላጎትና ስሜት  ድል ማድረግ አለበት። ይሄ ደሞ ሲሲፈስ ከዛ አለት ጋር እንደሚታገለው ትግል ሆነ ማለት ነው። ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር መታገል ማለት ስለሆነ አስቸጋሪ  ነው። ● ከ 12 Angry Men ምሳሌ እንስረቅ ◉ ፊልሙ መገባደጃ ላይ 11ዱም ዳኞች ማስረጃዎቹን አንድ በአንድ እየመረመሩ ሲመጡ "ልጁ ጥፋተኛ አይደለም " ወደሚለው አቋም ይሻገራሉ። መጨረሻ ላይ የቀረው ብቸኛው ሰው ዳኛ ቁጥር 3 ይሆናል።  "Not Guilty" ለማለት ያንቀዋል። ልጁ እንዲሰቀል ነበር የፈለገው። እስከመጨረሻው ሰከንድ ድረስ በንዴትና በእልህ ልጁ ጥፋተኛ ነው እያለ ይሞግታል። ነገር ግን መጨረሻ ላይ በንዴት ውስጥ ሆኖ የራሱን ልጅ ፎቶግራፍ ከኪሱ አውጥቶ ሲቀደው ሽሽግ ምስጢሩ ይገለጣል። ዳኛው ልጁን ሊቀጣ የፈለገው  ከራሱ ልጅ ጋር ባለው የግል ጠብና ቂም ምክንያት እንደነበረ ይረዳል። በራሱ ስሜት ተሸንፎ  ስቅስቅ ብሎ ካለቀሰ በኋላ "ጥፋተኛ አይደለም!" ብሎ ድምፁን ይሰጣል። በዚህም 12ቱም ዳኞች በአንድ ድምፅ ልጁን ነፃ ያደርጉታል። ❺ ​ “አትፍረድ ይፈረድብሃል!” የሚለው አባባል በትክክልም የሰው ልጅን ጉድለትና የስነ-ልቦና ሀቅ የሚፈትሽ መርህ ነው። በአንድ ሰው ላይ የምንሰነዝራት ፍርድ ወይም የምንወረውራት ትችት ስለ ተከሳሹ ሳይሆን ስለ እኛ  ውስጣዊ ማንነት የሚናገረው ነገር ይበልጣል። በ12 Angry Men ላይ ያለው ዳኛ በተከሳሹ ልጅ ላይ በጭካኔ ሲፈርድ የነበረው በራሱ ህይወት ውስጥ ካለው ቁስልና ቂም የተነሳ እንደነበረው። መፍረድ ከባድ ነገር ነው። ምክንያቱም እውነተኛ ፈራጅ ለመሆን መጀመሪያ ከራስ ጥቅም፣ ከራስ ስሜት፣ ከራስ ታሪክና ጥላቻ ነፃ መሆንን ይጠይቃል። አለዚያ አንዷን ጣት ስትቀስር አራቱ ወደ ራስ ያመለክታል እንደሚባለው ይሆናል። ባጭሩ ሁለቱም ፊልሞች የሚያሳዩን በሸንጎ ስለሚቆሙት ተከሳሾች ሳይሆን፣ በፈራጆቹ ወንበር ላይ ተቀምጠን ስለምንፈርደው ስለ እኛ ማንነት ነው። ▭▭ ©መስዑድ

"ለመጀመሪያ ጊዜ ከሙሉ ህይወት የሌላቸዉ ኬሚካላዊ ንጥረነገሮች የመጀመሪያዉን ሰዉ ሰራሽ ባይሎጂካል ህዋስ መፍጠር ተቻለ" በቤተ ሙከራ ውስጥ የተሰሩ 7 የዲኤንኤ ፕላዝሚዶችን (DNA Plasmids) በማገናኘት፣ 90 ኪሎቤዝ ጥንዶች (kbp) ብቻ የያዘና 36 ጂኖችን ብቻ የያዘ እጅግ አነስተኛ የህይወት ኮድ (Genome) በኮምፒውተር ቀረፁ። ​ይህን ዲኤንኤ፣ ቅባትና ፕሮቲን ብቻ ከያዘ ሰው ሰራሽ የፈሳሽ ከረጢት (Lipid Membrane)ውስጥ ከተቱት። ​ህዋሱም ራሱን ችሎ እንዲያድግና የራሱን ፕሮቲን እንዲያመርት የሚያስችሉ መሰረታዊ የኬሚካል ኢንዛይሞችን በውስጡ ጨመሩበት። ህዋሱ ራሱን ችሎ ማደግ፣መባዛት እና ከሞላ ጎደል አብዛኛዉ ህዋስ ሊያረገዉ የሚችለዉን ነገር ማረግ የሚችል ነዉ። አክለዉም ሳይንቲስቶቹ mutation happen እንዲያረግ በማረግ የ evolution ማሳያን ተጠቅመዋል mutate ያረጉት spudcellዎችም ቶሎ የሚያድጉ፣ቶሎ የሚባዙ እና መሰል መሰረታዊ ልዩነትን የያዙ spud cellዎች ሆነዋል። ይሄ ለ Abiogenesis 100% ማሳያ ይሆናል? well 100% የሚባል unfalsifiablity ሳይንስ ጋር የለም! ሳይንስ በማስረጃ እንጂ በብያለዉ ብያለዉ! አይደለም የሚሰራዉ ስለዚህ ይህ ህይወት እንዴት እንደጀመረ ለማሳየት abiogenesisን the only realistic,evidential and experimental ማብራሪያ ያረገዋል። ይህን አልቀበልም የሚል ሰዉ የ abiogenesisን evidential account የሚገዳደር ሌላ ዳጎስ ያለ ማስረጃ ማምጣት አለበት። የየሆነን theory ክፍተት እየጠቀሱ ስለዚህ ነብዬ ያለዉ ነዉ ትክክል ፈጣሪዬ ያለዉ ነዉ ትክክል የሚል Gap argument weight አይኖረዉም። ሆነም ቀረ ግን Nothing have been good at destroying the God hypothesis not even philosophy,revolution or violation but science. ሙሉዉን ለማንበብ ይሄን ይጫኑ

ነገረ ጢም ጢም በተባዐቱ ዘንድ ረጅም ታሪክን የያዘ ብዙ ማህበራዊ ትርጉሞችንም ያዘለ የአካል ክፍል ነዉ።ከጥንት የግብፅ እና የሱመሪያን ስልጣኔ ጀምሮ በግሪክ ሳይቀር አብርሃማዊ ሃይማኖቶች ተደምረዉ ጢም ለየት ያለ ቦታ ሲሰጠዉ ኑሯል።  በጊዜያት ዉስጥ የስልጣን፣የጥበብ፣የወንዳወንድነት፣የመብሰል እና የግርማ ሞገስ ማሳያ ሲሆን ቆይቷል። በሱመሪያኑ ስልጣኔ ጊዜ ጢማቸዉን በረጅሙ የሚያሳድጉት ነገስታት እና መኳንንቶች ሲሆኑ፤ ጢሙም እንደ ስልጣን፣ጥበብ እና ብስለት ተምሳሌት ተደርጎ ይወሰድ ነበር። በተቃራኒዉ ባርያዎች ጢማቸዉን እንዲያሳድጉ ስለማይፈቀድ ነፃዉን ህዝብ ማለትም መኳንንቱን እና ነገስታቱን ከባሪያዎቹ መለያ አንድ ምልክትም ተደርጎ ይወሰድ ነበር። በግብፆች ስልጣኔ ወቅት ደሞ ትልቁ ቦታ የሚሰጠዉ ንፅህና ስለነበር ብሎም ፂም እና ፀጉርን ማሳደግ ንፅህናን ያጓድላል ብለዉ ስለሚያስቡ እምብዛም አያሳድጉም ግን በተቃራኒዉ ነገስታቶቹ በይፋዊ ስነ ስርአቶች እና ሸንጎ ላይ የሙታንን የትንሳኤ አምላክ ኦሳይረስን ለመምሰል ሲሉ ሰዉ ሰራሽ ጢሞችን በአገጫቸዉ ላይ ያደርጉ ነበር።ይሄ ሴቷ ንግስት (ፈርኦንንም) የሚጨምር ሲሆን፤ጢሙም ስልጣኗን እና ንግስታዊ ግርማዋን ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል። ወደ ግሪኮች ስንመጣ በጥንት የግሪክ ስልጣኔ በወታደሮችም ሆነ በፈላስፋዎች ዘንድ ጢም ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል፤ በስፓርታዉያን ዘንድ ጢም እንደ ጀግንነት መለያ ነበር የሚወሰደዉ። አንድ ሰዉ ወኔ ቢስ መሆኑ ከታወቀ ጢሙ እንዲቆረጥበት ነበር የሚፈረጀዉ በጊዜዉም ይህ ትልቅ ማህበራዊ ዉርደትን ይዞ የሚመጣ ኩነት ነበር። በተጨማሪ በጥንት ግሪክ ፈላስፋዎች ዘንድም ቢሆን ከ ሶቅራጠስ ዘመን እስከ ስቶይኮች ጢም ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል የጥበብ እና የአሳቢነት ተምሳሌትም ተደርጎ ይወሰዳል። ታዋቂዉ የስቶይክ ፈላስፋ ኢፒክቲተስ እንደዉም "ፂሜን ከምቆርጠዉ አንገቴን ብቆርጠዉ ይሻለኛል" ብሏል። ወደ አብርሃማዊ ሃይማኖቶቹ ስንመጣ አይሁዳዊያን በኦሪት ዘሌዋውያን የተዛዘትን ትህዛዝ ለማክበር ሲሉ ሙሉ ፂማቸዉን አያነሱም፤ በክርስትናም በኦርቶዶክስ tradition ዘንድ የአለምን መናቅ፣የትህትና እና የክርስቶስ ሃዋሪያነትን ስለሚወክል ማሰደግን ይመርጣሉ በተመሳሳይ ሁኔታ በእስልምና ላይ ፂም ሱና ነዉ። በመካከለኛዉ ዘመን የጢም ማህበራዊ አስፈላጊነት እየደበዘዘ ቢመጣም በ 19ኛዉ ክፍለዘመን ላይ በነበረዉ በኢንዱስትሪዉ አብዮት የጢም ወጉ በፅኑ ተመለሰ፤ በአሜሪካ እና በብሪታኒያ ያሉ መሪዎች፣ባለሃብቶች፣እንደ ማርክስ ያሉ የጊዜዉ ፃህፍት እና ፈላስፋዎች ማጌጪያቸዉ ያረጉት ጀመር።በጊዜዉም የታማኝነት፣የስልጣኔ እና የጭምትነት ማሳያ ይሆን ጀመረ። በሃያኛዉ ክፍለዘመን ደሞ የወታደሮች የጋዝ ጭምብል ፊታቸዉ ላይ በአግባቡ እንዲቀመጥ ሲባል የግድ መላጨትን እንዲተገብሩ ታዘዘ፤ ይህን ተከትሎ የጢም መላጫ ኩባንያዎች በመስፋፋታቸዉ እና በስፋት ተፀህኖ ፈጣሪ ማስታወቂያዎችን በመስራታቸዉ ጢሙን ሙልጭ አርጎ የሚላጭ ሰዉ "የንፅህና እና የኮርፖሬት ስራ አስፈፃሚነት" መለያ መሆን ጀመረ። በሃገራችን ባህልም ቢሆን ከሞላ ጎደል ጢም የግርማ ሞገስ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፤ "ሰላቢ ይመስል ጢም የለዉም" አይነት የመሸንቆጫ ብሂሎችም የፈለቁት ከዚህዉ ጢም በማህበረሰባዊ እይታ ዉስጥ ከሚሰጠዉ ቦታ አንፃር ነዉ።