1 036
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
+1130 天
帖子存档
Repost from N/a
ርዕስ፡ የመልካምነት ጉዞአችንን እናጠናቅቅ!
ውድ የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ፣
ለወገን እንድረስ እናግዝ በሚል መርህ ብዙ ወገኖቻችን የሚረዱበትንና የሚታከሙበትን ሆስፒታል በጋራ ለመገንባት ከመቄዶንያ በቀረበልን ጥሪ መሰረት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስናካሂድ ቆይተናል።
በዚህም በእናንተ ደግና ሩህሩህ ወላጆች፣ አስተማሪዎች፣ ተማሪዎች እና በመላው የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ባደረጋችሁት ልዩ ትብብር ከዕቅዳችን 500,000 ብር ውስጥ 360,000 ብር ማሰባሰብ ችለናል። ይህም 72% የዕቅዳችንን ግብ ማሳካት እንደቻልን ያሳያል።
ለዚህ ታላቅ ድጋፍ እና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን።
ይህን ውጤት ያስመዘገብነው በሁላችሁም ድጋፍ እና በግሪን በጎ ክለብ አባላት ያላሰለሰ ጥረት ነው። አሁንም የቀረውን 140,000 ብር በአንድነት፣ በትብብር እና በቅንነት እንደምናሟላው ሙሉ እምነት አለን።
ስለዚህ ሁላችሁም የግሪን ማህበረሰብ አባላት እና ነገ በኔ ብላችሁ የምታምኑ ወገኖች ከዚህ ታላቅ ዓላማ ጎን በመቆም አስተዋጽኦዎን እንድታበረክቱ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ወላጆችም ለልጆቻችሁ አርአያ በመሆን ድጋፋችሁን በሚከተለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ማድረግ ትችላላችሁ።
💳 CBE Account
1000748130358
(Mulusewu Muniye – Mekodonia
Kaleb Demissaw – Green School (Green Bego))
“መስጠት አያጎድልም!”እናመሰግናለን።።
ቀን 19/09/18
ለግሪን ቅድመ አንደኛ ት/ቤት ወላጆች በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ለኢድ አል አድሀ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን
ማሳሰቢያ
1.ኢድ አል አድሀ በዓል ምክንያት ማግስቱን ነገ ማለትም 20/09/18 ትምህርት ዝግ ይሆናል::
2. በሀገራዊ ምርጫ ምክንያት ትምህርት ከሰኞ 24/09/18 -ረዕቡ 26/09/18 ዝግ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን::
Repost from N/a
+9
🟢 የግሪን በጎ ፌስቲቫል፡ ከልብ የመነጨ ምስጋና! 🟢
ውድ የግሪን ኒው ጄኔሬሽን ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ወላጆች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ አስተዳደር እና በቦታው ተገኝታችሁ የነበራቹ በሙሉ፤
ባለፈው ቅዳሜ (ግንቦት 8) በታላቅ ድምቀት የተካሄደው የግሪን በጎ ፌስቲቫል (Green Bego Festival) በማይታመን ስኬት መጠናቀቁን በታላቅ ደስታና ትህትና እንገልጻለን! 🌟
የእናንተ ከፍተኛ ተሳትፎ፣ መነሳሳት እና እውነተኛ ደግነት ታክሎበት በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ180,000 ብር ማሰባሰብ ችለናል! 💸🎉
ይህ ትልቅ ስኬት ወደ ዋናው የገቢ ማሰባሰብያ ግባችን አንድ ግዙፍ እርምጃ ያቀረበን ሲሆን፥ እንደተለመደው 100% የተገኘው ገቢ በሙሉ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር የግንባታ እና የእንክብካቤ ፕሮጀክቶች ድጋፍ በቀጥታ የሚውል ይሆናል።
ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ለ፡
• ለትምህርት ቤታችን አስተዳደር እና መምህራን — በራዕያችን አምነው ስላበረታቱንና ቦታውን ስለፈቀዱልን።
• ለግሪን በጎ የስራ ክፍሎች እና በጎ ፈቃደኞች — ከበስተጀርባ ሆነው የቪአር (VR) ጌሞችን፣ የመዝናኛ ቦታዎችን እና አጠቃላይ የፌስቲቫሉን እንቅስቃሴዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላስተባበሩ።
• ለእያንዳንዱ ታዳሚ — በቦታው ተገኝታችሁ፣ አቅማችሁ የፈቀደውን አስተዋጽኦ አድርጋችሁ ቀኑን ልዩ ስላደረጋችሁልን።
እናንተ ፌስቲቫል ላይ መገኘት ብቻ ሳይሆን እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን ተስፋ ሆናችኋል። የርህራሄን እና የአንድነትን እውነተኛ ኃይል ስላሳያችሁን እናመሰግናለን።
የፌስቲቫሉን ይፋዊ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች እንዲሁም ቀጣይ ስራዎቻችንን በቅርቡ በዚህ ቻናል የምናጋራ ይሆናል፤ ይጠብቁን!
ግሪን በጎ —
በጎ በጎውን 💚
2026
Instagram | TikTok | Telegram
Repost from N/a
🚨 1 ቀን ብቻ ቀረው! 🚨
ነገ ማንም እንዳይቀር! በደስታ እና በፈገግታ የሚሞላ፣ ልዩ እና የማይረሳ ጊዜ አብረን እናሳልፋለን። ✨
🗓️ ዋና ዋና መረጃዎች፦
• 🕒 የመግቢያ ሰዓት፦ ነገ ጠዋት ከ2:00 ጀምሮ በሮች ክፍት ይሆናሉ።
• 🎫 የቲኬት ማረጋገጫ፦ የገዛችሁት ቲኬት በSMS (በፅሁፍ መልዕክት) መድረሱን ያረጋግጡ። ካልደረሶት እባክዎ በፍጥነት ያነጋግሩን።
• 🎟️ የዕለቱ ቲኬት፦ አስቀድመው መግዛት ካልቻሉ፣ በዕለቱ በሩ ላይ መግዛት ይቻላል።
🎈 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እና ዋጋቸው፦
የሚከተሉት አገልግሎቶች ከተጨማሪ ክፍያ ጋር የቀረቡ ናቸው፦
• 🎨 ፌስ ፔይንት (Face Paint)፦ 100 ብር
• 🍦 አይስክሬም እና ኮተን ካንዲ፦** 100 ብር
• 📸 ፎቶ ቡዝ (Photo Booth)፦ 350 ብር
ቲኬት ለመቁረጥ፦ https://chapa.events/to/green-bego-festival
ነገ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! እንዳትቀሩ! 🎉
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የማበራዊ ድረገፆቻችንን ይቀላቀሉ፦
Instagram | TikTok | Telegram
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን
Repost from N/a
ONLY 3 days left🔥
🎉 Don’t miss the Green Bego Festival
📍 ቅዳሜ May 16 @ Green new generation school
🎟️ Get your tickets now on:
👉 chapa.event
Your weekend plans are officially set 😎
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የማበራዊ ድረገፆቻችንን ይቀላቀሉ፦
Instagram | TikTok | Telegram
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን
Repost from N/a
🎉 Green Bego kids Festival 🎉
📅 ቀን: ቅዳሜ ግንቦት 8, 2018 (May 16, 2026)
መረጃ ፦
• 📍 ቦታ:- ግሪን ስኩል (Green School)
• 💰 ዋጋ፦ 325 ብር (ለአንድ) | 899 ብር (ለ3) | (New)1200ብር(ለ4) | 1450 ብር (ለ5)
🎟 ቲኬቶች በኦንላይን በ Chapa Events ይገኛሉ👇
https://chapa.events/to/green-bego-festival
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
🔗 https://t.me/Greenbego
Our TikTok account: https://vt.tiktok.com/ZS9ned7nL
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን@greennewgenerationschool #greenschool #greenbego #kidsfestival #kidsfestivale #kidsfestivaleaddisabeba
Repost from N/a
📣 ሁለተኛ የጊዜ ማራዘሚያ ማሳሰቢያ፡ የፌስቲቫሉ ቀን ተቀይሯል!
ውድ ወላጆች፣
ቀደም ብለን የፌስቲቫሉን ቀን አራዝመን የነበረ ቢሆንም፣ በርካታ ወላጆች ቀኑ ከግንቦት ልደታ በዓል ጋር በመገጣጠሙ ምክንያት እንዲቀየርልን ባቀረባችሁልን ጥያቄ መሰረት፣ የተሳታፊዎቻችንን ፍላጎት በማክበር ቀኑን በድጋሚ ለማራዘም ወስነናል።
ልጆቻችሁም ሆኑ እናንተ ወላጆች በበዓሉ ቀን ቤተሰባዊ ግዴታችሁን እንድትወጡና በፌስቲቫሉ ላይም ያለምንም ስጋት እንድትገኙ ስንል አዲሱን ቀን እንደሚከተለው አስተካክለናል፦
🗓 አዲስ የጊዜ ሰሌዳ
• የነበረው ቀን፦ ግንቦት 1 (May 9)
• አዲሱ ቀን፦ ቅዳሜ ግንቦት 8 (May 16, 2026)
ሁሉም ዝግጅቶች (VR፣ ስዊሚንግ ፑል...) እንዳሉ ናቸው። ገቢውም ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት የሚውል ይሆናል።
መረጃ ፦
• 📍 ቦታ:- ግሪን ስኩል (Green School)
• 💰 ዋጋ፦ 325 ብር (ለአንድ) | 899 ብር (ለ3) | 1450 ብር (ለ5)
• 🎟️ ቲኬት፦ https://chapa.events/to/green-bego-festival
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
🔗 https://t.me/Greenbego
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን#greenbego #greenbegofestival #greennewgenerationschool #mekedonia
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
