ch
Feedback
ETHIO FREE INTERNET 🌐

ETHIO FREE INTERNET 🌐

前往频道在 Telegram

All NETWORK FREE INTERNET 🌐

显示更多
1 932
订阅者
无数据24 小时
-147 天
-5430 天
帖子存档
IP address
10.29..... 10.51..... 10.46....... 10.47..... 10.48...... 10.49........ 10.59...... 10.72...... 10.73..... 10.152.... 10.155.... 127.29......

+1
2 Day unlimited FREE.ehi0.11 KB

Free internet 00BIRR

+2
MAYA Fast 🛩️4Daay.ehi0.12 KB

sticker.webp0.17 KB

+1
TG ⚡ UNTD⚡🚀.tls0.01 KB

sticker.webp0.22 KB

ትንሽ ስለQR code Quick-response code ወይም በተለምዶ QR code በመባል የሚታወቀው በማሽን የሚነበብና በውስጡ የተለያዩ መረጃዎችን የያዘ two- dimensional matrix ነው።
ትንሽ ስለQR code Quick-response code ወይም በተለምዶ QR code በመባል የሚታወቀው በማሽን የሚነበብና በውስጡ የተለያዩ መረጃዎችን የያዘ two- dimensional matrix ነው። QR code በ1994 በJapan ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈለሰፈ ሲሆን ይህም የመኪና ክፍሎችን ለመሰየም ታስቦ ነበር አገልገሎት ላይ የዋለው። QR code በውስጡ link, text, email, sms, wi-fi network information, social media information, Download link እና የመሳሰሉ መረጃዎችን መያዝ ይችላል። QR Code አራት አይነት encoding modes አሉት። ⚫Numeric mode: Encodes digits and can store up to 7,089 characters, but doesn't support negative numbers. ⚫Alphanumeric mode: Extends numeric mode to include upper case letters, spaces, and symbols, and can store up to 4,296 characters. ⚫Byte mode: An extension of alphanumeric mode that supports lowercase letters. ⚫Kanji mode: Stores double-byte characters to encode Japanese characters. የQR code ጥቅሞች:- ⚫የተለያዩ Online ክፍያዎችን በቀላሉ ለመክፈል ⚫ለተለያዩ ኢቨንቶችና ፕሮግራሞች እንደ Digital ticket ያገለግላሉ። ⚫Scan አድርጎ ወደ አንድ web page ለመግባት ⚫የተለያዩ  መሳሪዎችን wireless connect ለማድረግ ⚫ለቢልቦርድና ለተለያዩ ትንንሽ የማስታወቂያዎች ስራዎች አገልግሎት ላይ ይውላል። አንዳንድ ስልኮች በራሳቸው built-in QR code scanner ሲኖራቸው አንዳንድ ስልኮች ላይ ደግሞ scan ለማድረግ የግድ scanner application download ማድረግ ይጠበቅብናል። ©@bighabesha_softwares

Telegram secret chat ቴሌግራምን መጠቀም የአብዛኞቻችን የዕለት ተለት ተግባር በሆነበት ዘመን ቴሌግራም ላይ የምንላላካቸው ነገሮች ሚስጥራቸው የተጠበቀ መሆን አለባቸው። አንዳንዴም የላክናቸ
Telegram secret chat ቴሌግራምን መጠቀም የአብዛኞቻችን የዕለት ተለት ተግባር በሆነበት ዘመን ቴሌግራም ላይ የምንላላካቸው ነገሮች ሚስጥራቸው የተጠበቀ መሆን አለባቸው። አንዳንዴም የላክናቸው መልእክቶች ወዴትም እንዳይተላለፉ እና ቶሎ እንዲጠፉ እንሻለን። ቴሌግራም እርስበርስ ሚስጥር ተጠባብቀን የምናወራበት አንድ feature አለው። Secret chat ይሰኛል። ሰዎች መረጃ እርስ በርስ ብቻ የሚቀባበሉበት feature ነው። ማለትም ያ መረጃ ከሰዎቹ መካከል አፈትልኮ እንዳይወጣ የሚያደርግ ነው። ከቴሌግራም Secret chat አገልገሎቶች መካከል፦ ⚫የተላላክነውን መልዕክት ከላኪው እና ከተቀባዩ በስተቀር ማንም ማየት አይችልም። ⚫Screenshoot ማንሳት አይቻልም። ⚫forward ማድረግ አይቻልም። ⚫በቴሌግራም ሰርቨሮች ላይ የተላላክናቸው መረጃዎች አይቀመጡም። ⚫ማንኛውንም መልዕክት ስንላላክ በራሱ ጊዜ እንዲጠፋ ሰዓት set ማድረግ እንችላለን። ⚫የላክነውን መልዕክት በምናጠፋበት ወቅት በላኪውም በተቀባዩም ዘንድ ይጠፋል። ከሰዎች ጋር secret chat ለማድረግ ወደ ምትፈልጉት ሰው ፕሮፋይል ውስጥ ገብታችሁ 3 ነጥብ በመንካት እና start secret chat የሚለውን በመንካት secret chat ማድረግ ትችላላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ ለማንም ሰው ቢሆን ማንነታችንን የሚያጋልጡና 3ኛ ወገን እጅ ላይ ቢገቡ ሊያሳፍሩን የሚችሉ የፅሁፍ፣ የድምፅ እንዲሁም የፎቶ መረጃዎችን ከመላክ መቆጠብ። ከላክንም ነገ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለማይታወቅ ከሁለቱም ወገን በፍጥነት ማጥፋት። ©bighabesha_softwares

የጎግል ክሮም መጠለፍ ከስድት መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን ለዳታ ስርቆት እንዳጋለጠ ተገለጸ የጎግል ክሮም (Chrome Extension) መጠለፍ ከስድት መቶ ሺ (600,000) በላይ የሚሆኑ ተ
የጎግል ክሮም መጠለፍ ከስድት መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን ለዳታ ስርቆት እንዳጋለጠ ተገለጸ የጎግል ክሮም (Chrome Extension) መጠለፍ ከስድት መቶ ሺ (600,000) በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን ለዳታ ስርቆት እንዳጋለጠ ተገለጸ፡፡ ጥቃቱ ያነጣጠረው በክሮም ድር ማሰሻ ቅጥያዎች (Chrome Extension) ላይ ሲሆን ጥቃቱ የተፈጸመበት መንገድ በአስጋሪ (phishing) ዘመቻ ነው፡፡ በዚህም ኩኪዎችን እና የተጠቃሚ መዳረሻ (access) ቶክኖችን ለመስረቅ ተንኮል-አዘል ኮድ ወደ ህጋዊ ቅጥያዎች ለማስገባት የመዳረሻ ፈቃዶቻቸውን መጠቀሙን ተገልጿል። በጥቃት መጋለጡ የታወቀው የመጀመሪያው ኩባንያ ሳይበርሃቨን (Cyberhaven) የተሰኘው የሳይበር ደህንነት ድርጅት ነው። በፈረንጆቹ ዲሴምበር 27፣ ሳይበርሃቨን (Cyberhaven) ይፋ እንዳረገው ጥቃት የሰነዘረው አካል የአሳሹን ቅጥያ እንደጣሰ በዚህም ከውጭ ያለ አካል በሳይበርሃቨን ሰርቨር የተመዘገበ ዶሜይን ላይ ትእዛዝ እንዲሰጥ እና እንዲቆጣጠር፣ ፋይሎችን እንዲያወርድ እና የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲያወጣ የሚያስችል ተንኮል አዘል ኮድ መላኩን ገልጿል፡፡ ሳይበርሃቨን ድርጅት ጥቃት እንደደረሰበት ይፋ ካደረገ በኋላ ሌሎች የክሮም ማሰሻ ቅጥያዎች በጥቃቱ እንደተጋለጡ የተጠረጠረ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ፡ AI Assistant - ChatGPT and Gemini for Chrome፣ Bard AI Chat Extension፣ Search Copilot AI፣ VidHelper Video Downloader እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

photo content
+1

ሁዋዌይ ያስተዋወቀው የመጀመሪያው 3 ቦታ የሚታጠፍ ስልክ ምን የተለየ ነገር ይዟል? የቻይናው ሁዋዌይ 10.2 ኢንች ስክሪን ስፋት ያለው 3 ቦታ የሚታጠፍ ስማርት ስልክ ይፋ አድርጓል አል-ዐይን Published on: 2024/9/16 11:24 EAT ሁዋዌይ ሜት (Mate XT) ስማርት ስልኩ በ2 ሺህ 800 ዶላር ወይም ከ300 ሺህ ብር በላይ ዋጋ የተቆረጠለት ሲሆን፤ ይህም አነጋጋሪ ሆኗል የቻይናው ሁዋዌይ ኩባንያ በአይነቱ ለየት ያለ እና ሶስት ቦታ የሚተጣጠፍ አዲስ ስማርት ስልክ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል። አሁን ላይ ሁለት ቦታ የሚታጠፉ ስማርት ስልኮች እየተለመዱ የመጡ ሲሆን፤ ሁዋዌይ ይፋ ያደረገው ሶስት ቦታ ተጣጣፊ ስማርት ስልክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። አዲሱ የሁዋዌይ ሜት (Mate XT) የሚል ስያሜ ያለው ስማርት ስልኩ 3 ቦታ የሚተጣጠፍ ሲሆን፤ 10.2 ኢንች የስክሪን ስፋት አለው። ሁዋዌይ ሜት (Mate XT) ከስልክነት በዘለለ እንደ ላፕቶፕ በመሆን መደበኛ የሆኑ ስራዎችን መከወን እንደሚያስችልም ኩባንያው አስታውቋል። በዚህም ሶስት ቦታ የታጠፈውን ስክሪን ሙሉ በሙሉ በመዘርጋት ድረ ገጾችን ለመከፈት እና ለማንበብ እንዲሁም የጥናት ስራዎችን ለማከናወን ያስችላል ተብሏል። በተጨማሪም የስማርት ስልኩ ግዙፍ ስክሪን ኢሜል ለመላላክ፣ የፋይናንስ አስተዳደሮ ተግባራትን ለማከናወን እንዲሁም ቪዲዮዎችን ለማጫወት የሚስችል ነው። ሶስት ሌንሶች ያሉትና ከፍተኛ የካሜራ ጥራት አለው የተባለው ስማርት ስልኩ፤ 50 ሜጋ ፒክስል የምስል ጥራት ማንሳት የሚችል እንደሆነም ተነግሯል። አዲሱ የሁዋዌይ ሜት (Mate XT) ምን ይዟል? የሁዋዌይ ሜት (Mate XT) ስማርት ስልክ ሁለት ናኖ ሲም ካርዶችን የሚቀበል ሲሆን፤ GSM / CDMA / HSPA / CDMA2000 / LTE / 5G ኔትዎርት የሚያስተናግድ ቴክኖሎጂ አለው። ሃርሞኒ (HarmonyOS 4.2) የተባለ እና በቻይና የተሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀም መሆኑንም ሁዋዌይ ኩባያ አስታውቋል። የመረጃ ማከማቻ ወይም ሜሞሪውን ስንመለከትም፤ ከ1 ቴራ ባይት ጀምሮ በሶስት አይነት የቀረበ መሆኑ ተነግሯል። በዚህም መሰረት 256 ጊጋ ባይት (GB) በ16 ጊጋ ባይት GB RAM፣ 512 ጊጋ ባይት (GB) በ16 ጊጋ ባይት (GB) RAM እንዲሁም 1 ቴራ ባይት (TB) 16 ጊጋ ባይት (GB) RAM ነው የቀረቡት ተብሏል። በካሜራም ከፍተኛ ጥራት አለው የተባለ ሲሆን፤ እስከ 50 ሜጋ ፒክስል የምስል ጥራት ማንሳት የሚችል ካሜራ ተገጥሞለታል። በስልኩ ጀርባ ላይ የተገጠሙ ሶስት የካሜራ ሌንሶችም፤ የመጀመሪያ ካሜራ 50 ሜጋ ፒክስል ሲሆን፤ እያንዳንዳቸው 12 ሜጋ ፒከስል የሆኑ ሁለቱ ሌንሶች ደግሞ የቴሌፎቶ እና ርቀትላይ የሚገኝ ነገርን ማንሳት የሚያስችሉ ናቸው። 8 ሜጋ ፒክስል የፊትለፉት (ሰልፊ) ካሜራም የተገጠመለት ሲሆን፤ 5600 mAh ባትሪም ተገጥሞለታል። በቀይ እና በጥቁር ቀለም ለገበያ ይቀርባል የተባለው ስማርት ስልኩ ከአራት ቀናት በኋላ ማለትም መስከረም 10 ቀን ለገበያ እንደሚቀርብ ይጠበቃል። ለስማርት ስልኩ የተቆረጠው የመሸጫ ዋጋ 2 ሺህ 800 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ300 ሺህ ብር በላይ ሲሆን፤ ዋጋው እጅግ እያነጋገረ ነው።

#የጥንቃቄ_መልዕክት ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎ
#የጥንቃቄ_መልዕክት ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት እናሳስባለን!! ከዚህ በፊትም በSMS በርካታ የማጭበርበሪያ links ወደ በርካቶቻችን ስልክ መሰራጨታቸው አይዘነጋም። መረጃው የINSA ነው።

Photoscan by google አብዛኞቻችን የdocument ፎቶዎችን በምንልክበት ጊዜ ላይነበብ አንግሉ ሊዛባ እና የለተያዩ ግድፈቶች ሊፈጠሩ እንዲሁም print የሆኑ ፎቶዎችን ስናነሳ ከሞላ ጎደል
Photoscan by google አብዛኞቻችን የdocument ፎቶዎችን በምንልክበት ጊዜ ላይነበብ አንግሉ ሊዛባ እና የለተያዩ ግድፈቶች ሊፈጠሩ እንዲሁም print የሆኑ ፎቶዎችን ስናነሳ ከሞላ ጎደል ብዥታ እና የጥራት ማነስ ይፈጠራሉ። ይህንን ችግር የሚቀርፍልን መተግበሪያ እናስተዋውቃችሁ። photoscane ይሰኛል። photoscan በ google የተሰራ መተግበሪያ ሲሆን ማንኛውንም ፎቶ scan በማድረግ ዋና ክፍሉን ከጥራት ጋር እና ከበርካታ feature ጋር ፎቶ የምታነሱበት መተግበሪያ ነው። ከnormal photo camera app በተቃራኒው photoscan high-quality digital scans ለመፍጠር በርካታ advanced technology ይጠቀማል። ይህንን መተግበሪያ ከplaystore https://play.google.com/store/apps/details?id=com.google.android.apps.photos.scanner ማውረድ ትችላላችሁ።

#National_id_printing ብዙ ሰው በአቅራቢያው ፖስታ ቤት ባለመኖሩ ምክንያት Original national id print ለማድረግ ሲቸገር ይስተዋላል። ታዲያ ኢትዮ ቴሌኮም ለዚህ ነገር መፍትሄ የሚሆን አዲስ አሰራር አስጀምሯል። ይህም አሰራር ከዚህ ቀደም የተመዘገብነውን national ID ቴሌብርን ተጠቅመን አቅራቢያችን ባሉ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መቀበል የሚያስችለን ነው። National id print ለማድረግ ቴሌብር መተግበሪያችንን update አድርገን ወደ መተግበሪያው ከገባን በኋላ አዲስ ወደ ተካተተውና national ID print ወደ ሚለው እንገባለን። በመቀጠልም የመታወቂያችንን FIN (Faida Alias number) እናስገባለን። ከዚያም ሙሉ የመታውቂያው መረጃ ትክክል መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ I agreed to the Terms and conditions የሚለውን confirm እናደርጋለን። በመጨረሻም ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት ስለኛ የሚጠይቀንን የተለያዩ መረጃዎችን ካስገባን በኋላ ከፍለን እንደጨረሰን ወዲያው message ይላክልናል። አሁን ቴሌብር ላይ national id print ለማድረግ ሶስት አይነት ፓኬጅ አሉ። እነርሱም:- ⚫Standard፡ በሶስት ቀን ውስጥ የሚደርስ ሲሆን ዋጋውም 345 ብር ነው። ⚫Primium፡ በሁለት ቀኑ ውስጥ የሚደርስ ሲሆን ዋጋውም 600 ብር ነው። ⚫Express፡ በስድስት የስራ ሰአት ውስጥ የሚደርስ ሲሆን ዋጋውም 800 ብር ነው። መረጃው የኢትዮ ቴሌኮም ነው።

Usb killer አይተን ከምንገምተው በላይ አደገኛ የሆነ አንድ መሳሪያ አናስተዋውቃችሁ። USB killer ይሰኛል ይህ መሳሪያ ስንመለከተው ትንሽ ይሁን እንጂ በርካታ ስራዎችና ጥፋቶችን ያደርሳል።
Usb killer አይተን ከምንገምተው በላይ አደገኛ የሆነ አንድ መሳሪያ አናስተዋውቃችሁ። USB killer ይሰኛል ይህ መሳሪያ ስንመለከተው ትንሽ ይሁን እንጂ በርካታ ስራዎችና ጥፋቶችን ያደርሳል። USB KILLER ወደ ተገናኝበት ማንኛውም መሳሪያ የመረጃ መስመሮች (data lines) ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ሃይልን ለመልቀቅ በሰከንዶች ልዩነት ሙሉ በሙሉ አሊያም በከፊል ማውደም ይችላል። መሳርያው በውስጡ በርካታ ካፓሲተሮችን ስለያዘ ከማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃ ጋር በUSB ሲገናኝ እያንዳንዱ capacitor 5 ቮልት charge ያደርጋሉ። ካፓሲተሮቹ ሙሉ በሙሉ ሲሞሉ መሳሪያው በተራው 2ዐዐ ቮልት ወደ USB ፓርቱ ኤሌክትሪክ በመልቀቅ ከጥቅም ውጭ ያደርጋቸዋል። ይህ መሳሪያ ተንቀሳቃሽ፣ ትንሽ እና ለአያያዝ ቀላል መሆኑ ብዙ ሰዎች እጅ ላይ እንዲገኝ አድርጎታል። Usb killerን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ያመረቱትን መሣሪያ ጥራት ለመለካት ይጠቀሙበታል። ከዚህም በተጨማሪም አላስፈላጊ electronic devices disable ለማድረግ እንጠቀምበታለን። በዚህ መሳሪያ ዙሪያ  ሀሳብ ስጡበት።

💎ዳታ ማይኒንግ ምን ዓይነት ጥቅም አለው❓ ✅ዳታ ማይኒንግ ብዙ መጠን ያለውን ዳታ በመመርመር እና በመተንተን በተለያዩ መስኮች ችግር ፈቺና ትርጉም አዘል መረጃዎችን ለይቶ ለማወቅ ትልቅ አበርክቶው
💎ዳታ ማይኒንግ ምን ዓይነት ጥቅም አለው❓ ✅ዳታ ማይኒንግ ብዙ መጠን ያለውን ዳታ በመመርመር እና በመተንተን በተለያዩ መስኮች ችግር ፈቺና ትርጉም አዘል መረጃዎችን ለይቶ ለማወቅ ትልቅ አበርክቶው አለው። ✅በዘርፉ አሜሪካ፣ ቻይና፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና እስራዔል ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እና ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ከሚሰሩ ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ ✅ተመራማሪዎች የንግድ ተቋማት እንዲሁም መንግሥታት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔን እንዲያሳልፉ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው የሳይንስ ዳይሬክት ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡ ✅ዳታ ማይኒንግ እንደ ጤናና ትምህርት ባሉት መስኮች የሚያጠነጥኑ መረጃዎችን በተገቢ መልኩ በመረዳት ዜጋ ተኮር ስራዎች ላይ ለመስራት ዕድል ይፈጥራል፡፡ አገልግሎት ሰጪ እና በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትም የደንበኞችን ፍላጎት በማወቅ እርካታን ለማሳደግ እንዲችሉ ጉልህ ሚና አለው፡፡ ©Artificial intelligence institute

Best telegram bots @EmojiTitleBot የራሳችሁን የፅሁፍ sticker የምትሰሩበት bot ነው። በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው። @DevToolsForbot የ telegram bot developer ከሆናችሁ ይህንን bot ለብዙ ነገር መጠቀም ትችላላችሁ። @Txt2Filebot የላካችሁለትን ማንኛውንም file download ሊደረግ ወደምችል file format የሚቀይርላችሁ bot ነው። @stickercanvasbot ይህ webapp የፎቶ stickers የምንሰራበት webapp ነው። @korwordbot ይህንን bot በመጠቀም የkorea ቋንቋ መልመድና የምንፈልገው chat ላይ በEnglish የጻፍነውን ወደ ኮርያ ቋንቋ እየቀየረ ይልክልናል። @shortener_tiny_url_bot ማንኛውንም ሊንክ የምያሳጥርልን bot ነው። @CleaningToolboxBot የቻናል ወይም የግሩፕ content ለመቀየር አልያም መሸጥ ስትሹ ቻናላችሁ ወይም ግሩፓችሁ ላይ የተፖሰቱትን ሙሉ ማጥፋት አድካሚ ቢሆንም በዚህ bot መገላገል ትችላላችሁ።

Eye protection mode አሁን አሁን አብዛኞቻችን ስልካችን ላይ የምናሳልፈው የጊዜ መጠን እየጨመረ መጥቷል። ታዲያ እጃችን ላይ ያለው ስልክ ምንም ያክል በርካታ ጥቅም ቢኖረውም የተለያዩ ጉዳቶ
Eye protection mode አሁን አሁን አብዛኞቻችን ስልካችን ላይ የምናሳልፈው የጊዜ መጠን እየጨመረ መጥቷል። ታዲያ እጃችን ላይ ያለው ስልክ ምንም ያክል በርካታ ጥቅም ቢኖረውም የተለያዩ ጉዳቶች አሉት። የጤና ጉዳትም ስልክ ከሚያመጣቸው ጉዳቶች አንዱ ነው። ይህንን ጉዳት ለመቀነስ አንዳንድ የስልክ አምራች ድርጅቶች Eye protection mode የተሰኘ feature ካስተዋወቁ ሰነባብተዋል። Eye protection mode ከስልክ የሚለቀቀውን blue light ray በመቀነስ screen በምንጠቀምበት ጊዜ ምቾት እንዲሰማን የሚያደርግ እና አይናችን እንዳይጨናነቅ የሚያደርግ feature ነው። ይህ feature የአይን ጤናን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። Eye protection mode enable ለማድረግ notification bar ላይ በመሄድ Eye protection mode የሚለውን ማብራት አልያም ወደ Settings በመሄድ > Display > Eye protection mode የሚለውን turn on ማድረግ። ይሁን እንጂ እንደየ ስልኩ ስያሚውም ሊለያይ ይችላል።

ማያ ጥቅል(በ5 ብር 2GB) ወይም የቴሌግራም(በ12ብር 1.5GB) ጥቅል እየገዛችሁ ምትጠቀሙ ሰዎች በዚሁ ቻናል ብትቀላቀሉ ትጠቀማላችሁ።
አጠቃቀሙ ካልገባችሁ መጠየቅ ይችላሉ።
https://t.me/CYBERCRACKEX