ch
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

前往频道在 Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

显示更多
1 875
订阅者
-224 小时
-97 天
-5530 天
帖子存档
እኔ የምላው Facebook ትተን ለምን Ummalife አንጠቀምም!? Mark Zuckerberg አላማረራችሁም.....!?⁉️ 😄
እኔ የምላው Facebook ትተን ለምን Ummalife አንጠቀምም!? Mark Zuckerberg አላማረራችሁም.....!?⁉️ 😄

ዴቪን የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሶፍትዌር ማበልፀግና ኮድ መጻፍ የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ተዋወቀ። ኮግኒሽን በተባለው የቴክኖሎጂ ኩባንያ የበለፀገው ዴቪን፤ የመጀመሪያው የሰውሰራሽ አስተውሎት
ዴቪን የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሶፍትዌር ማበልፀግና ኮድ መጻፍ የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ተዋወቀ። ኮግኒሽን በተባለው የቴክኖሎጂ ኩባንያ የበለፀገው ዴቪን፤ የመጀመሪያው የሰውሰራሽ አስተውሎት የሶፍትዌር ኢንጅነር ነው ተብሎለታል፡፡ ሞዴሉ የሚቀርብለትን ጥያቄ (Prompt) በመጠቀም ኮድ መጻፍ፣ ድረ-ገጾችን እና ሶፍትዌሮችን ማልማት እንደሚችል ዊዮን ዘግቧል፡፡ ዴቪን ውስብስብ ስራዎችን የማቀድና በሺዎች የሚቆጠሩ ውሳኔዎችን የመወሰን አቅም አለው፥ በጊዜ ሂደትም ከስህተቱ በመማር እና ራሱን እያሻሻለ በመሄድ ወደላቀ አፈጻጸም ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቴክኖሎጂው ሰዎችን ከመተካት ይልቅ የተለያዩ ተግባሮችን በትብብር  በአንድ ጊዜ በመከወን ስራ ማቅለልን ዒላማው ማድረጉ ተነግሮለታል፡፡ ይህ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት በዘርፉ የተሰማሩ ሶፍትዌር አበልፃጊዎች ይበልጥ ውስብስብ በሆኑ ችግሮች ላይ እንዲያተኩሩ በማበረታታት በሶፍትዌር ልማት ውስጥ አዲስ የፈጠራ ዘመን እንዲመጣ መንገድ ይከፍታል።

✳️ የዓለማችን ትልቁ 3ዲ ማተሚያ❗️ 🔺ፋክትሪ ኦፍ ዘ ፊዩቸር (Factory of the Future) የተሰኘ የዓለማችን ግዙፍ 3ዲ ማተሚያ በአሜሪካው ሜይን ዩኒቨርሲቲ ይፋ ሆኗል፡፡ መሣሪያው በ20
+2
✳️ የዓለማችን ትልቁ 3ዲ ማተሚያ❗️ 🔺ፋክትሪ ኦፍ ዘ ፊዩቸር (Factory of the Future) የተሰኘ የዓለማችን ግዙፍ 3ዲ ማተሚያ በአሜሪካው ሜይን ዩኒቨርሲቲ ይፋ ሆኗል፡፡ መሣሪያው በ2019 በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ከተሰራዉና ማስተር ፕሪንት (Master Print) ከተሰኘዉ 3ዲ ማተሚያ በአራት እጥፍ የሚልቅ ነዉ፡፡ 🔺ማተሚያው 29 ሜትር ርዝመት፣ 10 ሜትር ስፋት እና 5 ሜትር ቁመት ያላቸውን ቁሳቁሶች ማተም የሚችል ነው። በተጨማሪም በሰዓት 227 ኪሎ ግራም የማተም አቅም አለው። 🔺በትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሳተፈዉ ይህ መሣሪያ እንደ ድልድይ ግንባታ፣ የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና መርከብን የመሳሰሉ ግዙፍ ቁሶችን በማምረት ሂደት ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የማምረቻ አማራጭ ይዞ መምጣቱን ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ #Tech_News

✳️ መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት መጠቆም የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ሆነ❗️ 🔺ተመራማሪዎች የልብ ምት መዛባት (Cardiac Arrhythmia) በመባል የሚታወቀውን መደበኛ ያልሆነ የልብ
✳️ መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት መጠቆም የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ሆነ❗️ 🔺ተመራማሪዎች የልብ ምት መዛባት (Cardiac Arrhythmia) በመባል የሚታወቀውን መደበኛ ያልሆነ የልብ ምትን አስቀድሞ መጠቆም የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ማድረጋቸውን Wion TV ዘግቧል፡፡ 🔺የሉክሰምበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት በተውጣጣ ቡድን የበለፀገው ሞዴል ከመደበኛ የልብ ምት ወደ መደበኛ ያልሆነ የሚደረገውን ሽግግር በ80 በመቶ የትክክለኛነት መጠን መተንበይ መቻሉ ተመላክቷል፡፡ 🔺ሞዴሉ በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኘው ቶንግጂ ሆስፒታል በ24 ሰዓት ውስጥ የተወሰዱ 350 የታማሚ ናሙናዎችን በግብዓትነት በመጠቀም በዲፕ ለርኒንግ የማሽን ማስተማር ሂደት የበለፀገ ነው፡፡ 🔺ቴክኖሎጂውን ሰዎች ከሚጠቀሟቸው የተለያዩ ተለባሽ ስማርት መሳሪያዎች ጋር በማቀናጀት ለታካሚዎች ስለልብ ምታቸው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎችን መስጠት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች ሲኖሩም በአማካይ በየ30 ደቂቃ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የቅድመ መከላከል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስችላል፡፡ 🔺ሞዴሉ ሰዎች የልባቸውን ደህንነት በየሰዓቱ ክትትል እንዲያደርጉና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ተጠቅመው ጤናቸውን እንዲጠብቁ በማስቻል ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ #Tech_News

የ2016 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ጊዜ ታወቀ የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ታውቋል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3-5  ለማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ል ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ል እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ  6-7/2016 ዓ/ል ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

✳️ ሀሰተኛ ፎቶዎችን ወይም ምስሎች እንዴት መለየት እንችላለን❗️ 🔺በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠራጥራችሁን ፎቶ ስትመለከቱ በቀላሉ የትኛውንም ሚዲያ ወይም ግለሰብ እንዲያጣራላችሁ ሳትጠብቁ በእጅ
✳️ ሀሰተኛ ፎቶዎችን ወይም ምስሎች እንዴት መለየት እንችላለን❗️ 🔺በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠራጥራችሁን ፎቶ ስትመለከቱ በቀላሉ የትኛውንም ሚዲያ ወይም ግለሰብ እንዲያጣራላችሁ ሳትጠብቁ በእጅ ስልካችሁ ማረጋግጥ ትችላላችሁ። 🔺በቅደሚያ ሀሰተኛ የመሰላችሁን ፎቶ/ምስል ወደ ስልካችሁ Save አድርጉት። 🔺በቀላሉ ስልካችሁ ላይ "Google Chrome App" ክፈቱት፦ -ወደ Desktop Site ቀይሩት -በቀኝ በኩል ከላይ Image የሚለውን ምረጡ -በመቀጠል የካሜራ ምልክቱን ተጫኑ ለማጣራት የፈለጋችሁትን ፎቶ Choose file የሚለው ላይ ፎቶውን Upload አድርጉት፤ ከዛ ውጤቱን አጣርቶ ይነግራቹኋል።

ብዙ የሚጠይቀው ነገር አለ! እናም ኢንተርኔት ቤት ወይም የኮምፒውተር ባለሙያዎች ይመዝግቧችሁ!
+4
ብዙ የሚጠይቀው ነገር አለ! እናም ኢንተርኔት ቤት ወይም የኮምፒውተር ባለሙያዎች ይመዝግቧችሁ!

*ተከፍተው ይሁን* ብለህ ትጨነቃለህ ለካ እነሱ አንተ ላይ ፊታቸውን አዙረውብህ ነው። እኮ ብቻ ጌታ ፊቱን አያዙርብህ፤ የሰውስ ነገር ቀላል ነው። ummalife.com/ReshadMuzemil
*ተከፍተው ይሁን* ብለህ ትጨነቃለህ ለካ እነሱ አንተ ላይ ፊታቸውን አዙረውብህ ነው። እኮ ብቻ ጌታ ፊቱን አያዙርብህ፤ የሰውስ ነገር ቀላል ነው። ummalife.com/ReshadMuzemil

#ጥቆማ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል። እነማን ይመዘገባሉ? የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦
#ጥቆማ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል። እነማን ይመዘገባሉ? የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም ስልጠናው መቼ ይጀምራል? ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም (ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት) ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦ ➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ➭ ሮቦቲክስ፣ ➭ ፕሮግራሚንግ፣ ➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም። ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦ 👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8 👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ @tikvahuniversity

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ ሰላም ለእናተ ይሁን። እንዴት ናችሁ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች (አባሎች)⁉️ #የሚቸግራችሁ ነገር አለን፤ ፈልጋችሁ ያጣችሁት ነገር አለን!? እገዛ ካስፈለጋችሁ በግል አካውንቴ አሳውቁኝ!! በአላህ ፍቃድ የምችለውን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ በዚሁ አጋጣሚ ቻናሉ ለሌሎች እንዲዳረስና ከዚህም የተሻለ ጠንክሮ ለመስራት በሐሳብም ሆነ በሌላ ነገር ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በሩ ክፍት ነው❗️❗️ ➤ በአላህ ፍቃድ በ2017 E.C ልክ እነደዚህኛው ቻናል ከፍቼ ከ9-12 ክፍል ላሉ ተማሪዎች የምችለው እገዛ እንደማደርግ ከወዲሁ ላሳውቃችሁ። [[በአላህ ፍቃድ]]አሁን ላይ ከ1-8ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች ድጋፍ እንደምናደርገው ማለት ነው። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ⭕️ ትውልድን ❝ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው በዚህ መንገድ ሂዱ ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ለትክክለኛው መንገድ (ለስኬት) ማዘጋጀትም ተገቢ ነው ባይ ነኝ❞ ! ▬▭▬▭▬▭▬▭▭▬▭▬ ⭕️ ለማስታወስ ያህል:- ▮ነገ ለምትፈተኑት ሞዴል እገዛ እንዲሆናችሁ ከላይ በ2016 E.C Secon Semester የተዘጋጀ ሞዴል ለቅቄያለሁ። t.me/ReshadMuzemil

Business Plan Preparation & Vision Setting.pptx1.81 MB

Amharic_Version_Annex_8,_Preparing_a_Business_Plan_Adopted_from.pdf6.44 KB

የቢዝነስ ፕላን/ 4 Pages Business Plan በ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?፦ በቀላሉ ሁሉንም መስፈርት ባሟላ መልኩ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል በምሳሌ በ100ሺ ብር የሚሰራ የምርጥ ቡና ቢዝነስ ፕላን በአማርኛ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተመልከቱት፤ ናሙናውን በመጠቀም ወደ የምትፈልጉት ቢዝነስ አይነት መለወጥ እንዲሁም ለሌሎች ማጋራት ትችላላችሁ። ✅ የቢዝነስ ፕላን/ 4 Pages Business Plan በ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል ✅ የዩኒቨርስቲ የመወጫ ፈተና(Exit Exam) ማግኘት ይችላሉ! ✍ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን ይፈልጋሉ? ✔️ዩኒቨርስቲ የመወጫ ፈተና(Exit Exam) የፈለጉትን መጽሀፍት በPDF በቴሌግራም ቻናላችን ታገኛሉ! 👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇 https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary አሁኑ ይቀላቀሉ! ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን በስልካችሁ ማግኘት ትችላላችሁ! የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library) ጊዜው የቴክኖሎጂ ነው አብረው ከቴክኖሎጂ ጋር ይጓዙ! https://youtu.be/7R9GyixR59s ©The Ethiopian Economist View

+1
ቢዝነስ ፕላን Business Plan Form

የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ዝግጅት ✅ የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ምን ማለት ነው? ▪ ማንኛውም አንተርፕራይዝ ሊተገብር ያሰበው የንግድ ስራ ግብና ዓላማ ምን እንደሆነ፣ የስራው ሂደት ምን እንደሚመስልና እንዴት እንደሚሠራ እንዲሁም እያንዳንዱ ክንውን መቼ እንደሚሰራ የሚያስረዳ ዶኩመንት (ሰነድ) ነው፡፡ ▪ የታለመውን ግብ ለመምታት የሚያስችል የአሰራር መመሪያን የያዘ ነው፡፡ ▪ የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ /የንግድ ስራ አሰራር ፍኖተ ካርታ ያሳያል፡፡ ▪ የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ/የንግድ ስራ ያለውን እድል ለገንዘብ ተቋማትና ባለሀብቶች ሊያስረዳ የሚችል ሰነድ ነው፡፡ ▪ የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ/የንግድ ስራ ሊኖረው የሚችለውን ማንኛውንም እድል /ሁኔታ በመዘርዝር የሚታቀድበት በቂ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት ነው፡፡ ✅ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) ለምን ይዘጋጃል? ▪ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) በተዘጋጀው ግብና ዓላማ ላይ ትኩረት / አጽንኦት በመስጠት ስራን ለማከናወን ይረዳል፡፡ ▪ የገንዘብ አቅምን ከተለያየ ምንጭ ለማግኘት ይረዳል፡፡ ▪ ቢዝነሱ/የንግድ ስራው የሚጀመርበትንና ሊመራበት የሚገባውን ስርዓት በማሳየት አቅጣጫ ጠቋሚ ይሆናል፡፡ ▪ በተነደፈው የቢዝነስ /የንግድ ስራ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ይረዳል፡፡ ▪ የተነደፈው የቢዝነስ /የንግድ ስራ የስኬት እድል ያለው መሆኑን ለማሳየት ይጠቅማል፡፡ ▪ በኢንተርፕራይዙ ውስጥ ቢዝነሱን /የንግድ ስራውን ለማስተዳደር የሚያስፈልገው በቂ ችሎታ እንዳለ መኖሩንና ለሚመረተው ምርትና አገልግሎት የገበያ እድል መኖሩን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡ ▪ ስራው ከተጀመረ በኃላ በጊዜ ሂደት ውስጥ በእቅድ ደረጃ የተቀመጠውን ውጤት በተግባር ከሚሆነው ጋር ለማወዳደር የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) እንዴት ይዘጋጃል? ▪ በቢዝነስ / በንግድ ስራ ውስጥ የሚጠየቁ ማንኛውንም ጥያቄዎች በመዘርዘርና ለጥያቄዎቹ መልስ በመስጠት ▪ ከተጠየቁት / ሊጠየቁ ከሚችሉት ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ በማሰባሰብ ▪ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በሙሉ በማሰባሰብ ▪ የተለያዩ አማራጮችን በማወዳደርና የተሻለውን አማራጭ ለመውሰድ በመወሰን። ✅ በቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ምን ሊደረግ ይችላል? ▪ የቢዝነስ/ የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) አስቀድሞ ማዘጋጀት ለክትትል ይረዳል፡፡ ይህም ማለት በእቅድ የተያዘውን ስራ ከተከናወነው ስራ ጋር በማነጻጸር ለመገምገም ይጠቅማል፡፡ ▪ ከገንዘብ ተቋማት እንዲሁም ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ለሚደረግ ውይይት የመነሻ ሃሳብ ይሆናል፡፡ የቢዝነስ / የንግድ ስራ እቅድ ለጅምላ ንግድ፣ ለችርቻሮ ንግድ፣ አገልግሎት የሚሰጥ የንግድ ድርጀት፣ ምርት የሚያመርት (አምራች) ድርጅት፣ ማንኛውም የንግድ ድርጅት፣ ለገንዘብ ተቋማትና ለንግድ ዘርፍ ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ ✅ የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ገጽታ ምን ይመስላል? ▪ የተተየበና በጥራዝ የተቀመጠ፣ በንጽህና የተጠበቀ/የተያዘ፣ ማጠቃለያና እዝል ያለው (ዋናውን እቅድ ላለማስረዘም ማለት ነው)፣ እያንዳንዱ ገጽ የገጽ ቁጥር የተሰጠው፣ በሚመለከተው አባል የተፈረመ መሆን የተገባው ሲሆን የቢዝነስ እቅድ መድብል ብዙ ወይም ጥቂት መሆን የሚወሰነው እንደ ንግዱ የዘርፍ ዓይነት ነው፡፡ ✅ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) ማንን ያካትታል? ▪ የንግድ ዘርፉ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችን፣ በዘርፉ የሚሰሩ ተወዳዳሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ አቅራቢዎች፣ ተቀጣሪዎች፣ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች፣ የንግድ ስራው የሚካሄድበት ስፍራ ወይም አድራሻ፣ ለንግዱ ስራ የሚያስፈልገው ቁሳቁስ. ወዘተ (ከአማራ ክልል የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የተገኘ) ሙሉ ቢዝነስ ፕላን PDF ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን Amharic version Preparing business plan የሚለውን ይጠቀሙ።

ከF1 እስከ F12 ያሉ # የዊንዶውስ ቁልፎች አገልግሎት በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function Key እንላቸዋለን፡፡ በዋናነትም ከሌሎች # ቁልፎች ጋር በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡ 📍 F1 ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን # የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡ 📍 F2 # የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt + Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡ 📍 F3 ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift + F3 መጫን # የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡ 📍 F4 አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 # መጫን ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ #የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4 ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt + 📍 F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት ነው፡፡ 📍 F5 አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5 መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡ 📍 F6 በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን # ወደቀጣዩ የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡ 📍 F7 ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ #Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡ 📍 F8 ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ # Startup menu ለመግባት የጠቅማል፡፡ 📍 F9 በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን #Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { } ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ ለማጥፋት 📍 F10 አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን # ራይት ክሊክ እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡ 📍 F11 በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡ 📍 F12 ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ # የ Save as ማስኮትን ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡

​​✳️ በአለማችን ትልቁ የCreation Software Developing ካምፓኒ Adobe ሲሆን የአዶቤን ሶፍትዌር የማይጠቀም ፕሮዲውሰር ፣ Studio ፣ ዲዛይነር ፣ TV Company የለም ማለት ይቻላል። ከትላልቆቹ Hollywood እስከ ጀማሪዎቹ Art ባለሙያዎች ሁሉም ስፘቸውን የሚሰሩት በAdobe ነው። ◽️ በአለም ዙሪያ ብዙ ተጠቃሚ ያላቸውና በብዙ ሰዎች የሚወደዱ የAdobe ሶፍትዌሮች፡ 🔺Adobe Photoshop | ፎቶና ግራፊክስ መስሪያና ማቀናበሪያ 🔺Adobe Premiere Pro | ቪዲዮ ማቀናበሪያ 🔺Adobe After effect | Motional ግራፊክስ መስሪያ 🔺Adobe Lightroom | የፎቶ ከለር ማቀናበሪያ 🔺Adobe illustrator | ዲጂታል ስዕልና ሎጎ መስሪያ 🔺Adobe xD | interface ዲዛይን ማድረጊያ 🔺Adobe InDesign | Logo, Banner, Mesh መስሪያ 🔺Adobe Premiere Rush | all In one ቪዲዮ ማቀናበሪያ 🔺Adobe Dimension | 2D እና 3D ነገሮች Design ማድረጊያ 🔺Adobe Character Animator | 2D Animation መስሪያ 🔺Adobe Bridge | file organize ማድረጊያ 🔺Adobe Dreamweaver | ዌብሳይት መስሪያ 🔺Adobe Acrobat | Pdf መፍጠሪያና ማቀናበሪያ 🔺Adobe Animate | Vector ግራፊክስ እና Animation መስሪያ 🔺Adobe Audition | ድምፅ ማቀናበሪያ

+2
Window 7 installation steps.pdf6.54 KB

ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተር USB WiFi Adapter ምንድን ነው? *ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተር የብሮድባንድ ገመድ ሳያስፈልግ በቀላሉ ኮምፒውተራችንን እና የዲሽ ሪስቨራችንን ከ ዋይፋይ ኔትዎርኮች ጋር በማገናኘት ኢንተርኔት ያስጠቅመናል ፡፡ ይህም በዩኤስቢ መሰኪያ ላይ በመሰካት ነው:: *እስከ 150Mbps ድረስ የማስጠቀም አቅም አለው:: * ከ15 - 20 ሜትር  እርቀት ላይ ሆነው መጠቀም  ይችላሉ:: *ለ Win 7, 8, 8.1, 10, Mac እና Linux ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ይሆናል:: *WLAN Driver አብሮ ያለው *በሌላ ኮምፒውተር ላይ ለመጠቀም በሚፈለግበት ጊዜ ነቅለው መውሰድ ይችላሉ ፡፡ ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተርን መጠቀም ብዙ ጥቅሞች አሉት! 1.ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተርን ፈጣን የኢንተርኔት  ግንኙነት በማቅረብ ለኮምፒተርዎ አዲስ ሕይወት ይሰጣል፡፡ ኮምፒተርዎ በዝቅተኛ የግንኙነቱ ፍጥነቱ ኔትወርክን እያሰናከለ ነበር ፣ ስለሆነም ፍጥነት እንዲጨምር መደረጉ  ቀሪውን የቤት/መስርያ ቤት ውስጥ ኔትዎርኮችን ለፈጣን ግንኙነት ነፃ ያደርጋቸዋል ፡፡ 2. ዩቲዩብ እና አይ.ፒ.ቪ ቻናሎችን በሳተላይት ዲኮደር (ዲሽ ሪሲቨር) አማካኘነት ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተሩን በመሰካት በቀላሉ  መመልከት ይቻላል፡፡ 3.ምንም አይነት የውስጣዊ ሃርድዌር መጫን  ዘዴ የለውም - ስለዚህ ለዝቅተኛ የቴክኖሎጂ እውቀት ላለው ተጠቃሚ እንኳን ቀላል ነው:: #አስተዉሉ የብሮድባንድ ገመድን በመሰካት ብቻ ይሰሩ የነበሩ ኮምፕዩተሮች (ዴስክቶፕም ሆነ ላፕቶፕ) ይሄ  ሁነኛ ዘላቂ መፍተሄ  ነው! 🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskills Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil ╚═══📌Share📌════