ETHIO CRYPTO ™
前往频道在 Telegram
Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟
显示更多3 571
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
-8230 天
帖子存档
3 571
ሰኔ 8
ለፈተና የቀራችሁት ትንሽ ቀን መሆኑን አውቃችሁ ካሁኑ ሰዓታችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ።
አብዛኛውን ጊዜ የትኛውም ተማሪ ለፈተና አንድ ሳምንት ከቀረው በኋላ ነው የሚጨነቁት ። ያ ልሆን አይገባም ።
የፈተና ቀናችሁን ላስታውሳችሁ 👇
1ኛ Group--Remedial ተማሪዎች ሰኔ 26 የ ማዕከሉ ፈተና ይጀመራል። ስለዚህ ካሁኑ ጀምራችሁ ዝግጅት መጨረስ አለባችሁ።
( Freshman ለመግባት ከ 50% በላይ ግድ ነው)
2ኛ Group--Exit Exam ተፈታኞኝ ሐምሌ 3 ይጀምራሉ ። Blue print ላይ ያሉትን Courso'ች ጨርሳችኋል?? ጉድ እኮ ነው እስካሁን ያልጀመረም አለ🤔
ልንገራችሁ ፈተናው ቀላል እና Common ነገሮች እንደሆነ ነው። ከ ብዙ Subject'ች ስለሆነ የሚመጣው ወሳኝ የተባሉ ነገሮችን መያዝ ነው።
ለምሳሌ :- Digital Communication ተምሮ ስለ Logic Gate, Binary ካላወቅክ ምኑን ተፈተንከው።
ሌሎችም እንደዛው ። Coursun ስትጠሩ አብሮ ብቅ የሚሉ ነገሮች ላይ Focus አድርጉ።
3ኛ Group-- የ 12ኛ ክፍል ፈተና ሐምሌ 19 ይጀምራል ። ስለዚህ ጥናት ጨርሳችሁ ጥያቄ እየሰራችሁ መሆን አለበት።
አጠሬራ የፃፋችሁትን፣ ጥያቄ የሰራችሁበት ወረቀቶች አትጣሉ። ዛሬ አንድ ጥያቄ ሰርታችሁ ካላፋችሁ ቀጣይ ሳምንትም ልጠፋ ይችላል። ነገር ግን ወረቀቱ ካለ በአንድ ታስታውሳላችሁ።
ለፈተና የሚሆኑ መረጃዎችን እና ጥያቄዎችን በዚህ ቻናል እየለቀቅን ነው።
3 571
#Grade 12
የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡
ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወንደወሰን ኢየሱስወርቅ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
ከተመዘገቡት ውስጥ 503,812 ተማሪዎች የሶሻል ሳይንስ እና 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።
የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡
3 571
" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር ሳይጋጭ እንደሚከናወን አሳውቋል።
በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ፣ ከመውጫና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲከናወን የሚረዳ ዕቅድ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ አስታውሰዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ዶ/ር ኤባ ፤ በዘንድሮው ዓመት 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸው ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡
የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱን አመላክተዋል።
ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በማዕከል ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና ሥርዓት ለመሞከር እንደ አገር ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቀው፤ በዚህም ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከልና ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።
ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደራጀ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ለመውጫ ፈተናው የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ጄኔሬተሮች ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
3 571
ተዘጋጁ
የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ከሁለት ወር በኋላ ይሰጣል። በዚህም መሰረት ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ ዝግጅት መጨረስ አለባችሁ።
ዘንድሮም ፈተናው በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ይሰጣል። እንደ ከዚህ በፊቱ ኩረጃ እና ስርቆት የሚባል ነገር አይኖርም።
በዛ ላይ ፈተናው ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁትን ያጠቃልላል። ስለዚህ ትኩረት አድርጋችሁ ማንበብ አለባችሁ።
አምና ያለፉ ተማሪዎች 3% ብቻ ነበሩ። ዘንድሮስ ለማለፍ ምን ያክል ዝግጁ ናችሁ??
የ 12ኛ ክፈል ተማሪዎች የሆናችሁ ሼር አድርጋችሁ ለጓደኞቻችሁ አድርሱ።
3 571
የትምህርት ማስረጃ ማጣራት
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለህ/ተ/ም/ቤት የተናገሩት ፦
" በሁሉም የፌደራል_ተቋማት የሰራተኞችን ማህደር መመርመር ጀምረናል። ምን ያህሉ እውነተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዞ ነው ? ምን ያህሉ አይደለም የሚል ምርመራ እያካሄድን ነው፤ ከራሳችን ጀምረን።
ማህበረሰቡ ልክ እንደፈተናው [የ12ተኛ ክፍል ፈተና] እንዲያውቅልን የምንፈልገው ከአሁን በኋላ በተጭበረበረ ድግሪ፤ በተጭበረበረ ዲፕሎማ የሚሰራ ስራ አይኖርም የሚለውን ለማሳወቅ ነዉ። በዚህ ዓመት እሱን እንጨርሳለን ብለን እናስባለን። "
3 571
የመውጫ ፈተና
ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።
በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት በአሁን ሰዓት ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ በ2015 በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ብሉ -ኘሪንት የተዘጋጀ መሆኑና የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል፡፡
የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም የገለፁት ሚኒስትሩ፤ የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብራርተዋል፡፡
በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) ተለይተው፤ በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮት የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል፡፡
@student_text
3 571
MOE
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜን በይፋ አሳውቋል።
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በልዩ ሁኔታ በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ተዘጋጅቶ እንዲላክና አጠቃላይ ሂደቱ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ተቀምጧል።
ፈተናውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተሰጠው ትምህርት መሠረት ከማዕከል በጋራ ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ተብሏል።
በዚህም መሰረት በሴሚስተሩ በተሰጠው ትምህርት የተቋማት የውስጥ ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና ውጤት 50 ከመቶ ይይዛል ተብሏል።
ተማሪዎችም በ2016 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ ሆነው ለመገኘት የሁለቱ ድምር አማካይ 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።
ዩኒቨርሲቲዎችም ፈተናውን በማስተዳደርና ውጤት በመግለጽ በ2016 የፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ለይተው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ የ2016 የትምህርት ካሌንደር የተስተካከለ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር
3 571
MOE
የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል።
ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
3 571
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የ2015 የ12ክፍል መፈተኛ ቀናት ተገለፀ
Social Science ሃምሌ 15-16
Natural Science ሃምሌ 25-28
3 571
Ministy Of Education
ExitExam
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል።
በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።
ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።
ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።
@student_text
3 571
Ministy Of Education
ExitExam
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል።
በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።
ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።
ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።
3 571
ማሳሰቢያ
ለሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት !
በ2015 ዓ.ም ከሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻችሁን መረጃ በተላከላችሁ የመረጃ መላኪያ ቅጽ መሠረት እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንድታቀርቡ እያሳሰብን እስከ ተጠቀሰው ቀን መረጃውን የማያቀርብ ተቋም ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን
ትምህርት ሚኒስቴር
3 571
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን አብራርተዋል።
ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡
ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
3 571
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኞች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አሳስቧል።
በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችን " ከነገ በኋላ አላስተናግድም " ሲል አሳውቋል።
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ከምዝገባው መጠናቀቅ በኃላ ይፋ ይደረጋል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ ተፈታኞች እስካሁን ድረስ የመፈተኛው ቀን ይፋ አለመደሩግን በማወቅ ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ በተጋጋ መንፈስ ዝግጅታቸሁን አድርጉ።
@student_text
3 571
#ብሔራዊ_ፈተና
" እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።
ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።
ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
