ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Freshman Tutorial

Freshman Tutorial

前往频道在 Telegram

This channel is Created For University Newbies and we also created a channel for senior university students, join us: @ethio_exams2 #mid #final #AAU #exams

显示更多
未指定国家教育39 729
3 904
订阅者
+324 小时
-127 天
-1230 天
帖子存档
Repost from Ethio Exams
#Medicine ስለ ሜዲስን ትንሽ ልበላቹህ 📡 ጥሩ ውጤት ማምጣት እስከቻላችሁና ግቢያቹህ ሜዲስን እንደሚሰጥ እርግጠኛ እስከሆናቹህ ድረስ ያለምንም ጥርጥር ህክምና ማጥናት ትችላላቹሁ ሀገራችን ውስጥ እንደሚታወቀው ከፍተኛ የሆነ የሀኪሞች እጥረት ያለ ቢሆንም የስራ እድሉ ግን ብዙዎቻቹህ እንደምታስቡት እንደልብ አይደለም በተለይ በዚህ ወቅት በህክምና የተመረቁ ዶክተሮችን እንደድሮው መንግስት ሳይሆን ራሳቸው ናቸው ስራ ፈለገው የሚቀጠሩት ቢሆንም ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የግል ስራ ለመስራት ጥሩ እድል አለው ። ምንም ጥያቄ የሌለው ነገር ሜዲስን ለመግባት ጥሩ ውጤት ሊኖራቹህ እንደሚገባ ነው ፤ ግቢ ስትገቡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ጥሩ ግሬድ ሊኖራቹህ ግድ ይላል(50%) ፤ ኢንትራንስም ከ20% ዋጋ አለው የሜዲስን መግቢያ COC ደግሞ 30% ግቢያቹህ በሚቀበለው ኮታ ልክ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎቹን ሜዲስን በምርጫቸው እንዲማሩ ይደርጋል ፈጣሪ ረድቷቹህ ሜዲስን ለምትገቡ Full year Course 🧿 Pre-medical modules (16 weeks) 📌 Basic English Skills 📌 Communicative Skill 📌 Basic Writing skills 📌 Computer Application in Medicine 📌 Medical Psychology 📌 Medical Sociology and Anthropology 📌 Civics and Ethics ♨️ Vacation: 2 ▶️ Pre-clinical Year I (Year 1) 📌 Body structure, Organization and Functions – I 📌 Body structure, Organization and Functions – II 📌 Metabolic Homeostasis and Molecular Genetics 📌 Basic concepts of Disease and Therapy ♨️Vacation: 2 weeks 📌 Measurment of Health and Diseases 📌 Blood and Immunity 📌 Neoplasia and Molecular Basis of Cancer 📌 Musculoskeletal, Integumentary and Craniofacial Regions ▶️ Pre-Clinical Year II (Year 2) 📌 Cardioipulmonary System 📌 Nutrition, Metabolic diseases and the GIT 📌 Urinary system and Toxicology 📌 Infectious Disease ♨️Vacation: 2 weeks 📌 Determinents of Health and Disease and research Methodology 📌 Endocrinology and Reproduction 📌 Neurosciences and Behavior ▶️1. Clinical Year I (Year 3) 📌Clinical Methods 📌Medical ethics and law I Internal Medicine I 📌Surgery I Obstetrics and Gynecology I Paediatrics and Child Health I ▶️1. Clinical year II (Year 4 and 5) 📌Health Promotion and Disease Prevention 📌Health Management and Policy 📌Otorhinolaryngology (ENT) 📌Ophthalmology 📌Dentistry 📌Dermatology 📌Introduction to Gender ♨️Vacation: 2 weeks 📌 Paediatrics and Child 📌 Health I 📌Obstetrics and Gynecology II 📌 Diagnostic Radiology 📌 Medical Ethics and Law II 📌 Rural community Health Practice ♨️Vacations: 2 weeks 📌 Internal Medicine II 📌 Surgery II 📌 Psychiatry 📌 Emergency Medicine 💎 ይህ ከላይ የተጠቀሰው የትምህርት ካሪኩለም የጥቁር አንበሳ ሆስፒቲል ተማሪዎች የሚማሩበት የትምህርት ስርዓት ሲሆን ከዩንቨርሲቲዎች ጋር አንዳንድ መዋቅሮቹ ቢለያዩም ብዙ ነገሮቹ ግን ተመሳሳይ ናቸው 💰ስለ ስራ እድሉ እና ተያያዥ የህክምና ትምህርት መረጃዎችን በሌላ ጊዜ የምንዳስስላቹህ ይሆናል ። 💌 Caution በጣም ግን አደራ ልላቹህ የምፈልገው ነገር ፍሬሽማን ኮርስ ላይ ጥሩ ውጤት ስላመጣቹህ ብቻ አልያም ሜዲስን የመማር ዕድል ስላላቹህ ብቻ ወይም ቤተሰብ ደስ እንዲለው ብላቹህ ሜዲስን ለመግባት እንዳትወስኑ ምክንያቱም ይህ የትምህርት መስክ ከሁሉም በላይ OVER LOAD ስላለው ብዙ ተማሪዎች ትምህርቱን መቋቋም አቅቷቸው ከመጫርም በላይ ስለሚጨልሉ አቅማችሁን አውቃቹህ ከፍላጎታቹህ ጋር ለማስማማት ሞክሩ ፤ በተለይ በተለይ ሶስቱን ተከታታይ አመታት የሚሰጡት ኮርሶች ከምታስቡት በላይ ጫና ሊኖራቸው እንደሚችል አውቃቹህ ከወዲሁ አቅማችሁን ፣ ችሎታችሁን እንዲሁም ተነሳሽነታችሁን ፈትሹ!! Source - Atc 📌 Join and share 👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2

Repost from Ethio Exams
🗣🗣 ዩኒቨርሲቲ እና ተግዳሮቶቹ 🔰 ክፍል 1 ✍✍በ Concise ቻናል የቀረበ። ✍መነሻ ሀሳብ ኢትዮ ዩኒቨርሲቲ። 🤗 ዩኒቨርሲቲ ላወቀበት ተማሪ እጅግ በጣም ብዙ መልካም የሆኑ ገፀ በረከቶች አሉት፡፡ እነዚህን መልካም ገፀ በረከቶች ስትገቡ ታጣጥሙታላችሁ🤓። እኛ ግን የምንፈልገው እናንተ ተግዳሮቱቹን አውቃችሁ ፡ ራሳችሁን እንድትታደጉ ነው። 😥ተማሪዎች ግቢ ላይ መጥፎ የተባሉ ነገሮች ይገጥማቸዋል። እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት 1ኛ) 🥺 ብዙን ግዜ ዩኒቨርስቲዎች ከከተማ ዉጭ በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ራቅ ብለው ነው የሚገነቡት። ከከተማ ውጭ ስለሆኑ fresh air የተትረፈረፈበት ፡ ራስን ለማዝናናት ና ለመመሰጥ እንድሁም ለማንበብ ምቹ የሆኑ ጫካዎች ና የተፈጥሮ መስህቦች አሉ።ስለዚህ ተማሪዎች ለመዝናናት ፡ ለማንበብ እንድሁም walk ለማድረግ ወደ ጫካዎች ና ሰው ወደማይበዛበት ቦታዎች ሊሄዱ ይችላሉ። በዚህ ምክንያት ፡ 📌 ሴቶች የመደፈር አደጋ ያጋጥማቸዋል። 📌 ወንዶች ደግሞ የ መሰረቅ አደጋ ያጋጥማቸዋል ምክንያቱም ሌቦች( የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም የአካባቢው ሰው ሊሆን ይችላል) ከ ግቢ ተማሪዎች ስልክ ፡ ብር ና ላፕቶፕ በማስፈራራት መውሰድ ለምደዋል። ስለዚህ ፡ ከላይ የጠቀስናቸው ቦታዎች ላይ ስትሔዱ ተሰባስባችሁ መሔድ ወይም ደግሞ አለመሔድ🙅‍♂🤷‍♀። 2ኛ) ይኸ ደግሞ በሴቶች ላይ የሚስተዋል ሲሆን በፈቃደኝነት ስህተት በመስራት የማይመለስ ፀፀት ዉስጥ የምትገቡበት ነው። ገና ወደ ግቢ ስትገቡ ፡ ለግቢው አዲስ ናችሁ ፡ ለአካባቢው ና ለማህበረሱ አድስ ናችሁ ፡ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ና ግቢ ውስጥ ስለሚሰሩ ነገሮች አድስ ናቸው። ስለዚህ ነባር(senior) ተማሪዎች ይኸን ደካማ ጎናችሁን( አዲስነታችሁን) ተጠቅመው የህይወት መስመራችሁን ያስቷችሗል☹️። ምን መሰላችሁ ሴቶችዬ 🤔 ገና ዩኒቨርስቲ ስትገቡ ነባር ወንዶች ተማሪዎች አፋቸውን ከፍተዉ😂 እጃቸውን ዘርግተው ይቀበሏችሗል። ምክንያቱም የመጀመሪያ አመት ሴት ተማሪዎች ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትገቡ ነባር(senior) ወንድ ተማሪዎች ሴት ይፈልጋሉ። ስለዚህ ምን ያደርጋሉ መሰላችሁ 😎 መጀመሪያ ልክ ግቢ ስትገቢ ያይሻል። ሻንጣሽ ትልቅ ስለሆነ ይመጣና ላግዚሽ ይላል....ከዛን ይሸከምና እስከ ተመደብሽበት ዶርም #Dorm(setoch_gibi) ድረስ ያወራሻል...ከዛን ግቢውን እንዳላምድሽ ስ.ቁ ስጪኝ ይልሻል። አንቺም ለሁሉም ነገር አድስ ስለሆንሽ ስ,ቁ ትሰጭዋለሽ.....ነገሩ አለቀ🥺። 😴ከዛ ምዝገባ ላይ ተሯሩጦ ያስመዘገብሻል....እሱም በዚሁ.... ይቀጥላል። 🤗ከዛ ግቢውን ያስጎበሽኛል ፡ ከተማውን ያሳይሻል ፡ ላውንች( Lounge) ይጋብዝሻል። 😴.....ከዛ ቡሃላ ምን ይፈጠራል መሰለሽ.......አንድ ቀን #Over እንዉጣ ይልሻል ፡ ከዛም🥃🍷🥂🍻 ትጠጣላችሁ። ከዛም በመጠጥ ሀይል አብረሺዉ ታድሪያለሽ። ካደርሽ ቡሃላ ምክንያት በመፍጠር ካንቺ ይርቃል ሌላ ይጠብሳል። በቃ ይሄው ነዉ🤢🤨☹️። ☹️ ማርገዝ የምባል ነገር አለ ፍቅር ያሳየሽ መስሎ አታሎ...... ህይወትሽን ያጨልማል። ከ ገጠር የሚመጡ ሴቶች በጣም ደስ ይላሉ ለምን ብትሉኝ አላማቸው አንድ ብቻ ነዉ። ፍቅረኛ አያቁ በትዳር ያምናሉ። የከተማ ልጆች ደግሞ ስታስጠሉ😂😂 ሁሉንም አይደለም። 🥺 ስለዚህ ሴቶችዬ ጠንካራ ፡ ፅኑ ፡ አላማችሁን የምታስቀድሙ መሆን አለባችሁ💃💃። 3ኛ) Over🕺💃🕺💃🕺 የዩኒቨርሲቲ ተማሪ over ካልወጣ oxygen እንዳጠረው የሚታሰብበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። እንደ ሰደድ እሳት የ ግቢ ተማሪዎችን ህይወት እያበላሸ ያለው over ነው። over ከጥቅሙ ጉዳቶች ያመዝናሉ ምክንያቱም ፡ 📌#over በወንዶች ተማሪዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ። የግቢ ተማሪዎች over ወጥተው ይጠጣሉ ። ከዛም ሞቅ ይላቸዋል ፡ ከዛም በ ደረቅ ሌሊት ከ አካባቢው ወጣቶች ጋ ይጣላሉ ፡ ከዛም በጩቤ ይወጋሉ አልያም በጠርሙስ ይመታሉ ። ከዛም በሌሊት 6 ወይም 7 ሰአት ወደ ሆስፒታል😏። ከ አካል ጉዳት እስከ ህይወት መጥፋት የሚያስከትል ችግር በ #over ምክንያት። እንደታደል ሁኖ ካልተጣላችሁ ፡ በ ደረቅ ሌሊት 8 ሰአት ምናምን ወደ ግቢ ዘበኛ ለምናችሁ ትገባላችሁ። ከመጥን በላይ ቀላቅላችሁ ስለምትጠጡ በየ ሽንት ቤቱ ሻታ🤮🤮🤮። 👷‍♂ ወንዶችየ ተጠንቀቁ ነፃነት አገኘን ብላችሁ ነፃነታችሁን እንዳታጡ🤨። 📌 #over በሴቶች ተማሪዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ ። በተለይ የ ከተማ ሴቶች shameless ናቸው☹️። ሲጠጡ ራሱ😴😴። ሴቶች #over ይወጣሉ ፡በ ወንዶች ጋባዥነት ይጠጣሉ🥂🍻🍷 ፡፡ ከዛ ይሰክራሉ ። ከዛ ደግሞ አልጋ ይዘው ለማደር ብር ላይኖርቸው ይችላል። ስለዚህ ጎዳና ላይ ማደር ስለማትፈልጊ ፡ ከአንዱ ጋር ታድሪያሽ🙁። ከዛ ያልተፈለገ ዕርግዝና ሊከሰት ይችላል። ከዛ በሗላ የሚመጣውን ጣጣ አስቡት😱😱። ሴት ልጅ ሰክራ በየ አስፓልቱ ስትወድቅ ምን ይባላል 🙈🙈 ይሄን የሚያደርጉት.... አወቅን ባይ የከተማ ልጆች ናቸው። 👷‍♀ሴቶችዬ ተጠንቀቁ። ነፃነት አገኘን ብላችሁ ነፃነታችሁን እንዳታጡ። 😈 ክፍል ሁለት ይቀጥላል😈 🗣🗣🗣 ማሳሰቢያ 👆👆 ከላይ የዘረዘርናቸው የግቢ ተግዳሮችን ለመፃፍ እና ለ እናንተ ለማጋራት ያሰብንበት ዋና ምክንያት ግቢ እንደዚህ አይነት ነገር ስለሚኖር ካሁን አውቃችሁት ፡ እንድትጠነቀቁ ነው እንጅ ስለ ግቢ መጥፎ ነገር መናገር ፈልገን ወይም እንድትሳቀቁ ፈልገን አይደለም። 🕺 ራሳችሁን በአግባቡ መምራት ከቻላችሁ ግን ግቢ ላይ ምርጥዬ ህይወት ይኖራችሗል። ለ አስተያየት እና ጥያቄ👇👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group Join and share 👇👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2

Repost from Ethio Exams
🕺 በዚህ አመት ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ተፈጥሮ ሳይንስ( Natural science) ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ። ✍✍ በ Concise ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ። የመጀመሪያ አመት የመጀመራያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች👇👇👇 📌 MATHEMATICS ( for natural science) 📌 GENERAL PHYSICS 📌 GEOGRAPHY 📌 LOGIC & CRITICAL THINKING 📌 COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL 📌 PSYCHOLOGY 📌 PHYSICAL FITNESS 🥺 እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች እንመልከት። ❇️ MATHS 11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው አብዛሀኞቹ ፡ የተወሰነ ለውጥ( modification) ነው ያለው። ስለዚህ ብዙም አትቸገሩበትም ፡ አሪፍ ውጤት መስራት ትችላላችሁ👌። A+ 🙈 ❇️ General Physics ይኸም 11 ኛ እና 12 ኛ የተማራችሗቸው ናቸው አብዛኞቹ👌። ❇️ Logic and critical thinking ይህ course ለእናንተ አድስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ concept ተማሪ ከሆናችሁ እና English ቋንቋ የምትሞክሩ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል ፡ እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው🙈። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል ። ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም☹️። ለማንኛውም ለ logic and critical thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ። 1ኛ) Concise introduction to logic 2ኛ) freshman logic 📌 Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት😴። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን ፈተና ትሰሩታላችሁ😸 ምክንያቱም የከባድ ጥያቄዎች ጣሪያ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። ኸረ እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል🙈🙈። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው👏👏። 📌 Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ👏😘። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ ( concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት😴😍። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ 1ኛ) መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት ፡ ፒዲኤፍ ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት። 2ኛ) freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው። 3ኛ) Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ🕺 ፡ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት😴። ከዛ A+ ታመጡና መቀወጥ🕺💃🕺💃😁😁። ❇️ Communicative English skill ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡ ግቢ ላይ ውጤታችሁን ከሚያነሱ ኮርሶች መካከል ነው🙈። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ🤔 📌 Speaking skill ( ራሳችሁን በ እንግሊዝኛ ማስተዋወቅ🙈 ፡ ከዛ መምህሩ የሆነ ርዕስ ይሰጣችሁ እና ስለዛ ነገር በ እንግሊዝኛ presentation ማቅረብ (የሆነ ማርክ%) 📌 Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%) 📌 Writing skill ( letter , descriptive , narrative,argumentative , expository ከነዚህ ባንዱ ትፅፋላችሁ( ከዛ የሆነ ማርክ) Grammar ( Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው ፡ Concise ላይ የተለቀቁ ኖቶችም ሊጠቅማችሁ ይችላል።) ❇️ Geography ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ❇️ Psychology ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል ፡ ግን biology ማንበብ ስለለመዳችሁ አትቸገሩም። theory ነው ፡ ከእናንተ የሚጠበቀዉ ማንበብ ብቻ ኘው። ❇️ Physical fitness ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው😁። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ😂። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም ዝም ብላችሁ ሜዳ ወታችሁ ትሰራላችሁ እንጅ Grade ( A , A- , B+ ,B , C ....) የለውም። pass or fail ነው የምትባሉት። Attendance ወይም በዚህ ኮርስ ክፍለ ጊዜ ካልቀራችሁ pass ትሆናላችሁ። እሽ እስከአሁን የ natural science ተማሪዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸውን ኮርሶች አየን። 🥺 ነገር ግን አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ በ Logic and critical thinking ቦታ emerging technology የሚያስተምሩ አሉ ። ከዛ second semester ላይ ደግሞ logic and critical thinking ያስተምራሉ። ብቻ ምንም ለውጥ የለውም ፡ እንድታውቁት ያክል ነው። ❇️ Emerging technology ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ አይደለም። ከ 9 - 12 የተማራችሗቸው የ Ict ትምህርቶችን ያካትታል ( Ms word , Ms PowerPoint, Ms excel , database ..... ወዘተ) በቃ አለቀ። እነዚህን ኮርሶች ወስዳችሁ እንደጨረሳችሁ ህክምና ( Medicine , Dental Medicine , Veterinary medicine , pharmacy...) መግባት የምትፈልጉ ቴክኖሎጂ( Engineering, Architecture, Computer science, It , software engineering...) መግባት የምትፈልጉ Coc exam ተፈትናችሁ ትገባላችሁ ማለት ነው። ለማስታወስ ያክል First semester ( 50%) Coc exam ( 30%) Entrance exam( 20%) computational science ( Physics , Chem , bio , maths , biotechnology...) Other health ( medical laboratory, nursing , midwifery....) መግባት ለምትፈልጉ ደግሞ የመጀመሪያውን አመት( የመጀመሪያ ሴሚስተር አይደለም) እንደጨረሳችሁ ትገባላችሁ። በመጨረሻም የ natural science ተማሪዎች የመጀመሪያ ሴሚስተር የምትወስዷቸውን ኮርሶች እና አጋዥ መፅሀፍ በ PDF ቀጣይ እንልክላችሗለን። በቀጣይ ደግሞ የ social science ተማሪዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች እንለቃለን:: 📌 Join and share 👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2

Repost from Ethio Exams
❇️ ዩኒቨርሲቲ እና ተግዳሮቶቹ 💆‍♂🤦‍♀TENSION🤦‍♂🙆 📗📘📙ጭለላ📖📚❌ ♈️ግቢ ላይ ከሚያጋጥሙን ጥቂት ችግሮች ውስጥ አንዱ ከልክ ያለፈ ጭንቀት ወይም በግቢ ስሙ #Tension ብለን የምንጠራው ነገር ነው። ይሄ ችግር ብዙውን ጊዜ በአንደኛ አመት ተማሪዎች ላይ በስፋት የሚስተዋል ቢሆንም በሁሉም ዘንድ ማለትም ተመራቂ ተማሪዎችንም ሳይቀር የሚያጦዝ ደስ የሚል ሙድ ያለው ጭለላ ነው። 💯እኔ ግን ጥሎብኝ የሚሰማኝ ሰው ሳገኝ ብዙ አወራለሁና ዛሬም ከሰማችሁኝ ትንሽ ስለ ግቢ Stress or Tension ባካፍላቹህ ደስ ይለኛል ፤ በተጨማሪም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለቴንሽን አዲስ በመሆናቸውና ከሁሉም በይበልጥ የታላላቆቻቸውን ምክር ስለሚቀበሉ ይቺን ምክር እንድታደርሱልኝ አደራ ማለት እወዳለሁ አይይ እንግዲህ ብዙ አታቅራራ ፡ ወደ ገደለው ግባ ‼️Tension ብዙውን ጊዜ የሚገጥመን የሆነ ክስተት አንጎላችንን ሲቦጠብጠው እንደሆነ የአንጎል ስፔሻሊስትና የሳይኮሎጂ ሊቅ ለመሆን የሚመኙት Dr abz ይገልፃሉ አስከትለውም ጭንቅላታችን በጣም በሚጨናነቅበት ጊዜ የሚገጥመን failure ነው ይላሉ ። ስልካችንን አንዳንዴ busy ሲሆን stack እንደሚያደርገው ማለታቸው ነው።😂 🦋በግቢ ተማሪዎች ሳይኮሎጂ ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉት ኢንጂነር muja እንደጠቀሱት ደግሞ " ግቢ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች በተለይም አንደኛ አመት ተማሪዎች ፈተና በሚቃረብበት ወቅት የሚገጥማቸው ከፍተኛ መጨናነቅ መንስኤው አስቀድመው ተገቢውን ዝግጅት አለማድረጋቸው ነው" በማለት ይጠቅሳሉ ። 🔹እኔም የኢንጂነሩን ጥናት ዋቢ በማድረግ የተወሰኑ ገጠመኞቼን ላካፍላቹህ *አንደኛ አመት ተማሪ እያለሁ Drawing ኮርስ አጨልሎኝ አድሮ ጥዋት ከፈተና በፊት ካፌ ላይ የተፎገርኩት ፉገራ እስካሁን ሳስታውሰው ያስቀኛል ፤ ምን መሰላቹህ pictorial drawing የሚሉት ነገር አልገባህ ብሎኝ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ወረቀት ላይ አፍጥጬ ስላደርኩ መሰለኝ ከምላቹህ በላይ ጭልል ብዬ ነበር እናም ምንም ቁምነገር ሳልይዝ ነጋና ቁርስ መብያ ሰዓት ደርሶ ሁሌም አብሮኝ የሚበላው ጓደኛዬ ጋር በመሆን ወደ ካፌ ሄድን ፡ ስንደርስም ያን ጨርቅ የመሰለ ፊቴን ታጥቤ ወደ ሆድ ሸንቁሬው አዝግ ሰልፍ አመራን ፥ የማይደርስ የለምና ተራችን ደርሶ ባንደኛው እጃችን ትሪና ኩባያ ይዘን በሌላኛው ደግሞ binder( for drawing exam) ይዘን ወደ ጨላፊዎች ተጠጋን ጨላፊዋም ትሪህን አስጠጋ ስትለኝ ትሪዬን' ሰጠኋት ፨ የሚገርማቹህ ትሪ ብዬ ፍርፍሩን የተቀበልኩት በ binderu ነበር እሷም አውቃ ይሁን እንደኔ ጨልላ ባላቅም ጭልፋ ሙሉ ፍርፍር በትሪዬ' ሞላችልኝ kikikikikiki በBindeሬ ፍርፍር ማስደረጌን ያስተዋልኩት አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ በሳቅ ፍርፍር ብሎ ፍርፍሩ ሲደፋበት ነበር ። 😀😀😀😀😀 ብዙ ተማሪ እየሳቀብኝ እንደሆነ ሳይ ደግሞ ይብስኑ የምገባበት ጠፋኝ ( ሳሳዝን)😖😖😖😖 እንዴትም ብዬ ከዛ ደባሪ ሙድ በመውጣት ፍርፍሬን ወደ ትሪዬ ገልብጬ ወደ መቀመጫዬ በመሄድ በእልህ ምግቡን ስበላው እሱም ለካ ቂም ይዞብኝ ነበር 😬 አነቀኝ ፡ ባክህ አልሰማህም በሻይ ድራሽህን ነው ማጠፋው ብዬ ወደ ኩባያዬ እጄን ስሰድ አለወትሮዋ ኩባያዋ ቀለለችኝ ምንሼ ነው ብዬ ወደ ኩባያዬ ሾፍ ሳደርግ ሻይም ሳላስቀዳ ነበር የተቀመጥኩት ( አይ drawing) ድጋሚ ይስቁብኛል ብዬ ባልፈራ ኖሮ ተነስቼ ሻይ አስቀዳ ነበር ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ከጓደኛዬ እየተዋስኩ ታሪካዊ ቁርሴን በላሁ ። 🐒ከካፌው ወጣ ብለን እጃችንን በመታጠብ ላይ ሳለን ሳላስበው ጧ ብዬ ሳቅኩ አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ በመገረም " ይሄ ልጅ ዛሬ ምን ነካው" ሲል ባሰብኝ .... እንዴት ብዬ ልንገረው ገና ት ብዬ ስጀምር ሳቄ ይቀድመኛል 😀😀😀😀😀 እንዴትም ብዬ በምልክት ወደ ትሪው ጠቆምኩት ፥ ደንግጦ ትሪውን ይዞ ወደ ካፌ ሲሮጥ ህዝቤ ፈተናዋን ረስታ ሳቀችበት ብድር በምድር አሉ ፥ ለካስ freind ከኔው ብሳ ትሪዋን ይዛ ወደ ፈተና ልትገባ ነበር😄😄😄 🐓የሚገርም ግጥምጥሞሽ እያልኩ ፏ ብልጭ ብዬ ተፈተንኩ እላቹሃልው ። ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ* 🍞😷😷😷😷😷😷😷😷😷🍞 🍄Final exam ሲቃረብ እንደዚህ አይነት የካፌ comedy መመልከት የተለመደ ነው ምክንያቱ ደግሞ ቅድም ኢንጅነሩ የጠቀሱት ቅድሚያ አለመዘጋጀት ነው። ፈተና ሲደርስ ከሚስተዋሉ ገጠመኞች ውስጥ ጥቂቶቹ⚡️ 👉 ካፌ ላይ መፎገር 🤧 👉 ስልክን library, class, cafe etc መርሳት ወይም መጣል 👉 Calculator መርሳት / መጣል 👉 PC መርሳት ለዛውም space ( class) 👉 ያነበቡትን መርሳት 👉 ራስን መሳት ( በተለይ ሴቶች) 👉 ወዘተ.... ታድያ ምን ይሻላል⁉️ የሚሻለውማ 📌ፈተና ሳይደርስ ሁሉንም course cover ማድረግ 🙅‍♂ 📌 ከጭንቀታም ጓደኛ መራቅ ( በሰላሙ ሰአት እናንተ ስታነቡ ከማያነበው ማለቴ ነው)💃 📌 ከጎበዝ ተማሪ ጋር መጎዳኘትና አብሮ ማንበብ🙇‍♀🙇 📌 ጥያቄዎችን በgroup መስራት 👨‍👨‍👦‍👦👨‍👨‍👧‍👧 📌 ስለ ፈተና አወጣጥ ከታላላቆቻችን መጠየቅ ( from seniors)🕵‍♀ 📌 Information gather ማድረግ 🔚🔝🔛🔜 📌 ከበግ ተራ በመራቅ ሴቶችን info መጠየቅ ( affirmative ምናምን ብለው ....)🙈🙉🙊 🌹በተረፈ Tension መጠኑ ይለያይ እንጂ አይቀሬ ነገር በመሆኑ ፈታ በሉ። እንደኔ እንደውም Tension ምንም የማይዘው ተማሪ ካሮት አምራች ገበሬ ይመስለኛል፤😭 ምክንያቱም አንብቦ ሳይሆን የሚፈተነው position አስተካክሎ ነው ። ☃ሲበዛ ነው እንጂ የማይነፋው ተማሪ ካነበበ እስከሚፈተን ድረስ Tension Normal ነው።👍 የመረጃ ምርጭ - Atc 📌 Join and share 👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2

🗣🗣 በዚህ አመት ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ሰላም ሰላም🙌🙌 ወደ ግቢ ለመግባት ዝግጅት ላይ ናችሁ ኣ🕺🕺🕺🕺💃💃💃💃🕺🏿🕺🏿🕺🏿💃🏿💃🏿💃🏿💃🏿💃🏿💃🏿 የ በሶ ፡ ዳቦ ቆሎ ፡ ኩኪስ ፡ የለውዝ ቅቤ እና ሌሎችም የማቆያ ምግቦች ዝግጅት ተጧጡፏል አሉ። 😋😋😋😋🙈🙈🙈 በ ስነ - ልቦና ስ ዝግጁ ናችሁ???☹️☹️ አዎ በስነ ልቦና ዝግጁ መሆን አለባችሁ።🥺🥺 ምክንያቱም 1ኛ) ከቤተሰብ ቁጥጥር እና ተፅዕኖ ናችሁ። ራሳችሁን የምትመሩት ና የምታስተዳድሩት ራሳችሁ ናችሁ። ስለዚህ ይኸን ነፃነት እንዴት በአግባቡ እንጠቀምበት🤔? ቅድሚያ ትኩረት መስጠት ያለባችሁ ለ ትምህርታችሁ ና ለአላማችሁ ነው። 2ኛ) የጓደኛ ተፅዕኖ( peer influence) ጓደኛን ለመምሰል ብሎ ፡ ለመቀላቀል ተብሎ ፡ ወደ አልባሌ ሱስ መግባት ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ ነን ፡ ነፃነት አገኘን ብላችሁ 📌 የማታነቡ ከሆነ 📌 ትምህርታችሁን በአግባቡ የማትከታተሉ ከሆነ 📌Over( ጭፈራ ቤት) መውጣት የምታበዙ ከሆነ 📌 ቺክ የምታሳድዱ ከሆነ ወይም ወንድ የምታሳድጂ ከሆንሽ 🙈🙈 📌 አልባሌ ሱስ ውስጥ የምትዘፈቁ ከሆነ 📌 እና ሌሎችም መጥፎ ወይም ትምህርታችሁን የሚያስተጓጉሉ ነገሮች የምታደርጉ ከሆነ ጊዜያችሁን አባክናችሁ☹️ ፡ ቤተሰብን ላልተገባ ወጪ ና ኪሳራ ዳርጋችሁ😣 ፡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ሻንጣችሁን ጠቅልላችሁ ወደ መጣችሁበት ትመለሳላችሁ🙅‍♂🤷‍♀። ግቢ ላይ እየቀለድኩ እያሾፍኩ እማራለሁ ማለት ዘበት ነው ምክንያቱም ኩረጃ በፍፁም የማይታሰብ ነው። ስለዚህ ግቢ ገብታችሁ 📌 ለማንበብ 📌 ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም 📌 ራሳችሁን በአግባቡ ለመምራት 📌 አላማችሁን ለማሳካት 📌 የሚደርስባችሁን ጫና ለመቋቋም ራሳችሁን በ ስነ ልቦና በደንብ ማዘጋጀት ይጠበቅባችሗል። ይኸን ስንል ግቢ ገብታችሁ አትዝናኑ ማለት አይደለም። ኸረ ፈታ በሉ please enjoy 🕺💃🕺🕺💃🕺💃🕺💃🕺። ግን እኛ የምንመክረው ትምህርታችሁን በማይጋፋ መልኩ ፡ እናንተን ለመጥፎ ሱስ በማይዳርግ መልኩ። ኸረ ፈታ በሉ ብዙ መዝናኛ ሞልቷል🕺🕺🕺💃💃💃🕺🕺🕺💃💃💃💃። ሌላኛው አንገብጋቢ ጉዳይ ደግም የምትፈልጉትን department ማግኘት ነው። 😌 Department ስትመርጡ 📌 የእናንተን ፍላጉት ፡ የእናንተን skill (ክህሎት) ፡ ዝንባሌ ፡ አቅም መሰረት ያደረገ መሆን አለበት። 📌 በቤተሰብ ተፅዕኖ ፡ በጓደኛ ተፅዕኖ ወዘተ መሆን የለበትም። እዚጋ ብዙዎች ጋ የሚስተዋለው ነገር ብዙ ብር ክፍያ አገኛለሁ ብሎ በማሰብ ፡ ቶሎ ስራ አገኛለሁ ብሎ በማሰብ አንዳንድ ተማሪዎች ያለ ዝንባሌያቸው ዲፓርትመንት ሲመርጡ ይስተዋላሉ። ስለዚህ 📌 ፍላጎታችሁን ፡ የትምህርት ክህሎታችሁን ፡ ጫናዎችን የመቋቋም ዝግጁነታችሁን ና አቅማችሁን መሰረት አድርጋች ብትሞሉ አሪፍ ነው። የምፈልገውን Department እንዴት ማግኘት እችላለሁ🤔? ጥሩ ውጤት ከሰራችሁ የምትፈልጉት ዲፓርትመንት መግባት ትችላላችሁ። ጥሩ ውጤት እንዴት እንስራ🤔? 1ኛ) ግቢ ገብታችሁ የምትወስዱት የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት እጅግ በጣም በጣም በጣም ጠቃሚ ነው። 50% ከመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ። የመጀመሪያውን ሴሚስተር ቅጥቅጥ አርጋችሁ ማንበብ ነው። 🕺🕺 እንመታደል ሁኖ የመጀመሪያ ሴሚስተር የምትወስዷቸው ኮርሶች 11 እና 12 የተማራችሗቸው ናቸው። ስለዚህ ያላችሁን አጋዥ መፅሀፍ ፡ PDFs እና የተለያዩ ማቴሪያሎችን እንዳትጥሏቸው፡ ወደ ግቢ ይዛችሁት ሒዱ። 2ኛ) COC exam ነው። የመጀመሪያውን ሴሚስተር ከጨረሳችሁ በሗላ COC exam ትፈተናላችሁ። 30% ከ coc exam ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ። 😴😴 እንደመታደል ሁኖ coc exam የምትፈተኑት 11 ና 12 ኛ የተማራችሗቸውን ነው። ስለዚህ 11 ና 12 የተማራችሁባቸውን ማቴሪያሎች ወደ ግቢ ይዛችሁ መሔድ ነው። 3ኛ) Entrance exam ነው። 20% ከ Entrance ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ። ስለዚህ የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤት እና COC ን በደምብ መስራት አለባችሁ ፡ አዲስ የተቀየረ ነገር ከሌለ። Join and support us!! @ethio_exams2 @ethio_exams2

Repost from Ethio Exams
ASTU አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መገኛ ፡ አዳማ በውስጡ ያሉ ግቢዎች፡ አንድ ለናቱ ነው የአየር ሁኔታ፡ ሞቃታማ በተለይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ትንሽ ይሞቃል ፤ ይህን እንጂ ማታ ማታ ደግሞ ያልተጋነነ ብርድ ስለሚኖር ሹራብ ነገርም ያስፈልጋቹሃል ። ይህን info ለሰጣችሁኝ ለ@ethio_exams2 ቤተሰቦች ላቅ ያለ ምስጋና ይድረስልኝ። Fields and Departments ASTU ላይ ብዙዎቻቹህ እንደምታውቁት ሁለት የትምህርት መስኮች ብቻ ይገኛሉ። ➡ Engineering & ➡ Applied science ከሌላው ግቢ ትንሽ ለየት የሚያደርገው pre- engineering የሚያስተምረው ሁለት ሴሚስተር መሆኑ ነው ( department and school የምትመርጡት ሁለተኛ አመት ላይ ነው ማለት ነው) Pre-engineering courses ▶ -General Chemistry(🙄) ▶ - General Physics 1 ▶ - Applied Maths 1 ▶ - Communicative english. ▶ - Introduction to computing( Python). ▶ - Civic or Logical reasoning. ▶ - HPE( 0 ch) Second semister courses ⏭ - Applied Maths 2 ⏭ - Technical drawing ⏭ - General physics 2 ⏭ - Computing ( c++) ⏭ - English writing ⏭ - Civic or Logic ⏭ - HPE(0 ch) Under Applied science pre-engineering courses ♒ Almost the same as Engineering except one course Departments of Applied Natural Sciences are *.Applied Biology *.Applied Chemistry *.Applied Geology *.Applied Mathematics *.Applied Physics Under Engineering there are 3 schools 1. Electrical 2.Mechanical 3.Civil Under electrical engineering or CSE there are 3 streams A) Electrical and computer engineering B) Electronics and communication engineering C) Power and control engineering Under Mechanical engineering A. Chemical B. Mechanical C. Material Under civil and arc school. A.Architecture B. Civil C. Water resource management and hydrolic Engineering D. Geomatics (next lijemr yichlal), Note* Engineering ላይ Aerospace engineering and software engineering አሁን ላይ አይሰጥም ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታቸው ላይ በመግባት ያረጋግጡ <www.astu.edu.et> Note * በነገራቹህ ላይ የመግቢያ ፈተናው ብዙም አይከብድም፤ ፈተናው ከEntrance exam ጋር ተመሳሳይነት አለው። Content of exam subjects are ▶ Chemistry ▶ Biology ▶ Mathematics ▶ Physics and ▶ English ASTU and AASTU JOIN ማድረግ ለምትፈልጉ ሰሞኑን ማስታወቂያ ተከታተሉ። ለማንኛውም አምና መመዝገቢያ ነጥብ ለሴቶች 420እና ለወንዶች430 ነበር Engineering ማለት ነው። applied ትንሽ ይቀንሳል መመዝገቢያ ነጥቡ 390&410 ነበር ሌላው የምግብ ቤቶች ዋጋ ነው የምግቤቶቹን Menu ማግኘት አልቻልኩም ግን ከብዙ ነባር ተማሪዎች እንደደረሰኝ ከሆነ የምግብ ቤቶች ዋጋ ከ25-40 ብር ባለው range ይጠቃለላሉ። ይህን ሁሉ መረጃ በመስጠት ለተባበራችሁኝ የastu(adama) ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገባቹህ ደግሞ አሪፍ ሽልማት ይበረከትላቹሃል በ2011 ከ3.76 በላይ ላመጡ 59 ተማሪዎች PC💻 ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። እምናና ካቻምናም በተመሳሳይ ብዙ ተማሪዎች ተሸልመዋል ፤ ከ3.5 በላይ ያመጡም የተሸለሙበት ጊዜ ነበር ። ብቻ እናንተ ጠንክሩ እንጂ ለሽልማቱ አለንላቹህ.....from Astu እኔን የገረመኝ ምን መሰላቹህ ? የሆን ተማሪ ለተከታታይ አመታት የግቢውን ሽልማት ጠራርጎ ወስዷል አስቡት አራት (PC) በየአመቱ ተሽልሞ ቀጣይ ካለም አለህላቹህ እያል መሆኑን ሰምቼ ድንቅቅቅ አለኝ ። (2012 batch ተማሪዎች እንደ ልጁ ሁሉንም ኮምፒውተር ለመውሰድ ያሰበ ካለ እንዳይረሳኝ ንገሩልኝ😁😁) ሌላም surprise አለ Engineering ለምትገቡ የአምስት ዓመቱን ትምህርት በአራት አመት የመማር ዕድል ሊያጋጥማቹህ ይችላል ግን በጣም ትልቅ ጥረት ያስፈልጋል (ፈተና አለው) ለApplied science ተማሪዎችም የአራት ዓመቱን ትምህርት በሶስት ዓመት ማጠናቀቅ የሚችሉበት መንገድ በተመሳሳይ መልኩ ማለትም በቅድመ ፈተና ተፈትነው በማለፍ ብቻ pre Engineering ሳይማሩ መመረቅ ይችላል። ♻️ለአስተያየት ፣ ለጥቆማ አልያም ለጥያቄ👇👇👇 @ethio_exams2 🔔ትምህርት ነክ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🌹✾🌹✦🌹✾🌹 (((((((((((((((((())))))))))))))))))) @ethio_exams2 @ethio_exams2 @ethio_exams2 @ethio_exams2 ((((((((((((((((()))))))))))))))))))) 🌹✾🌹✦🌹✾🌹 #SHARE🙏🙏🙏

Repost from Freshman Tutorial
The word "psychology" is derived from two Greek words 'psyche' and "logos‟. Psyche refers to mind, soul or sprit while logos means study, knowledge or discourse. Therefore, by combining the two Greek words the term "psychology" epistemologically refers to the study of the mind, soul, or sprit and it is often represented by the Greek letter ᴪ (psi) which is read as ("sy"). psychology ከሁለት የግሪክ ቃላት የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የህይወት፣ የአይምሮ እና የመንፈስ ጥናት ማለት ነው። - Psychology is the scientific study of human behavior and the underlying mental In the above definition, there are three aspects; science, behavior and mental processes: *Science: psychology uses scientific methods to study behavior and mental processes in both humans and animals. This means psychologists do not study behavior with commonsense rather they follow scientific procedures and use empirical data to study behavior and mental processes. psychology ሁልጊዜም ቢሆን scientific ሒደቶችን የሚከተል ነው። *Behavior: refers to all of our outward or overt actions and reactions, such as talking, facial expressions, movement, etc. There is also covert behavior which is hidden, non-observable and generally considered as a mental process behavior የምንለው ደግሞ የምናደርጋቸው ተግባራት ናቸው። *Mental processes: refer to all the internal, covert activities of our minds, such as thinking, feeling, remembering, etc. ይሄኛው ደግሞ በአይምሯችን የምናከናውናቸው ተግባራት ናቸው። Be with us! join and share!😊😊😊 @freshman_tutorial @freshman_tutorial Let's work together!😊😊

For freshman students used, especially polynomial and logarithm functions 🩸Join and share our channel👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2 👩‍👩‍👧‍👦👩‍👩‍👧‍👦Join and Share our group👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group

Physics mid exam for freshman student's different university colection 🩸Share and join our channel Ethio Exams ለተማሪዎች በቀላሉ የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, ሁሉንም በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው:: https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2

hawasa University physics mid exam 🩸Join and share our channel👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2 👩‍👩‍👧‍👦👩‍👩‍👧‍👦Join and Share our group👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group

physics mid exam for freshman students 🩸Join and share our channel👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2 👩‍👩‍👧‍👦👩‍👩‍👧‍👦Join and Share our group👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group

Psychology unit 2 prepared by Prof.million ♦️Join and Share our official group 👇👇👇👇👇👇👇 @ethio_exams_discussion_group 🩸Share and Join our channe👇👇 Ethio Exams ለተማሪዎች በቀላሉ የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, ሁሉንም በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው:: https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2

Geography freshman from unit 1-4 🩸Share and join our channel 👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2 👨‍👨‍👧‍👧👨‍👨‍👧‍👧Share and join our group 👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group

Geography freshman from unit 5-8 🩸Join and share our channel👇👇 @ethio_exams2 @ethio_exams2 👩‍👩‍👧‍👦👩‍👩‍👧‍👦Join and Share our group👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group

Fallacy that translated to oromic language 🩸Share and join our channel 👇👇 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 👨‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👦‍👦Share and join our group 👇👇 @ethio_exams_discussion_group @ethio_exams_discussion_group

Fallacy that translated to amaric language 🩸Share and Join our channe👇👇 Ethio Exams ለተማሪዎች በቀላሉ የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, ሁሉንም በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ቻናል ነው:: https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2 https://t.me/ethio_exams2

#Answer 1. True 2. False 3. True 4. True 5. True 6.D 7.C 8.D 9.B 10.C 11.B 12.C 13. No answer 14.D 15.A 16. Immediacy, Consistency and Intensity 17. Attention, Retention, Motor Reproduction, Motivation 18. Is the ability to remember(recall) the first(primacy effect) and the last(recency effect)... 19. 7plus or minus 2 20. a. Electric shock b. Frighten and cry c. Toy d. Fear (Frighten and cry) Any ቅሬታ on😎👇 https://t.me/ASHU_PROMOTION Plus ፈተናውን እንዴት አያችሁት share idea @freshman_tutorial ©@freshman_tutorial

shows fear when his mother gives him the toy and he refuses to play with it. What is @freshman_tutorial a) UCS(Unconditioned stimulus)_____________ b) UCR(Unconditioned Response) _____ @freshman_tutorial c) CS(Conditioned Stimulus)_______________ d) CR(Conditioned Response)______________ መልስ ለመላክ👇 @freshman_tutorial ©A+ Tutorial Class