ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 406
订阅者
+124 小时
+407 天
+33730 天
帖子存档
#NOMORE ON ETHIOPIA #MORE FOR ENDF ✍️በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣልያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሠልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አደረጉ። ✍️በድጋፍ መድረኩም ሁሉም ሰራተኛ ከደሞዝ ባሻገር ስንቅ በማዘጋጀት እንዲሁም ልዩልዩ የአይነት ድጋፎች ለማድረግ ተነሳሽነቱንና ቁርጠኝነቱን አሳይቷል። ✍️በማጠቃለያውም የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና አየር ሀይል አባል የነበሩ የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር ለመዝመት በዝግጅት ላይ ለሚገኙ የኮሌጁ ሰራተኞች የሞራል ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ህዳር 09/03/2014 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም ለሚከናወኑ ተግባራት/እቅድ ቅንጅታዊ አሰራር ማስፈንና በየተቋማቱ የሚገኙ የሰዉ ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅሞችን በጋር መጠቀም ስለሚቻልበት፤ ስለቴ/ሙ/ት/ስ ፣ ስለፈጠራ ስራዎች ፣ ስለቴክኖሎጂ ሽግግርና ስለSTEM እውቀቶች በተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ግንዛቤ ማስጨበጥና ምቹ ሁኔታ መፍጠር ስሚቻልበት ከትምህርት ቤቶች ዋና ር/መ/ር ፣ ም/ር/መ/ራን እና አስተባባሪዎች ጋር ስልጠናዊ መድረክ በማዘጋጀት ውይይት አደረገ፡፡ በዚህ መሰረት የ18 ትምህርት ቤት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፤ በመድረኩም አዲሱ የቴ/ሙ/ት/ስ ፖሊሲና ስትራቴጅ ገለጻ የሳቴምሒ ፕሮግራም ድጋፍ የአሰጣጥ ስልትና ጠቀሜታን በማስገንዘብ የ2014 በጀት ዓመት የሳ/ቴ/ም/ሒ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ የጋራ እቅድ ገለጻ በማድረግና በማወያየት ስምምነቱን የማጽደቅ ስነ ስርዓት ማካሄድ ተችላል።

"ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር" በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም በጀት አመት የዝግጁነት ምዕራፍ በዕቅድ ተይዞ እየተሰራበት የሚገኘው የስራ አካባቢን ምቹነት የማሻሻል ስራ የቴክኒክና ሞያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊዎችን እንዲሁም የአቻ ኮሌጅ አመራሮችን ማስጎብኘት ተችሏል በጉብኝቱም ላይ የኮሌጁ ዲን ይህ ጅምር ስራ ሰፍቶና ዳብሮ በቀጣይ የኮሌጁን አገልግሎት ለማሻሻል ከሚሰሩ ስራዎች ጋር ጎንለጎን በሁሉም የስራ አካባቢዎች የሚቀጥል እንደሆነ ተናግረዋል። ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም

"የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም" በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2013 ዓ.ም በጀት አመት የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም አጠቃላይ የኮሌጁ አሠልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ። በፕሮግራሙም ላይ የቴክኒክና ሞያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በተለያየ ደረጃ ያሉ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ለፈጻሚዎች፣ ክፍሎች እና የስራ ሂደቶች ላስመዘገቡት የተሻለ የስራ አፈጻጸም እና ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅናና ምስጋና ተበርክቶላቸዋል። ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም

ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመደበኛ ነባር የምሽት ሰልጣኝ ተማሪዎች የተላለፈ ጥሪ።

በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የ2014 ዓ.ም እቅድ ላይ ተወያዩ። ……………………………………………… የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች የ2013ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት እና 2014ዓ.ም እቅድን አስመልክቶ አጠቃላይ የተቋሙን ሰራተኛ ያሳተፈና ሰፋ ያለ መድረክ በማዘጋጀት እንዲወያዩበት አድርገዋል። በመድረኩ በቀዳሚነት ለተሳታፊዎች የቀረበው የ2013ዓ.ም አፈፃፀም ሲሆን በዚህም የተቋሙ የስራ ሂደቶች በቅደም ተከተል የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን ያቀረቡበት ነበር። በመቀጠልም የ2014 ዓ.ም የተቋሙ ዕቅድ በኮሌጁ ዲን እና ምክትል ዲኖች ለተሳታፊዎች የቀረበበት ነበር። በመጨረሻም ተሳታፊዎች በቀረቡላቸው የአፈፃፀም ሪፖርቶች እና ቀጣይ ሊተገበር በታቀደው ዕቅድ ላይ እንደ ክፍተት ያዩትንና ቢሻሻሉ ያሏቸውን ገምቢ ሀሳቦችን ለቤቱ በማቅረብ በቀጣይ የታቀደው እቅድ መሬት ወርዶ ግቡን እንዲመታ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የገለፁበት መድረክ ሆኖ አልፏል።