425
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
425
#በሬን_ስበር
፧
አይደክምህም? ማንኳኳቱ
የማይከፈት ቁልፍልፍ በር፤
እስከምከፍት አትጠብቅ
እጅ የለኝም በሬን ስበር፤
እጅ የለኝም ለመክፈቻ ተገንጥሏል በሀጢአቴ፣
እስከምከፍት አትጠብቅ ሰብረህ ግባ ወደቤቴ፣
ስታንኳኳ ብሰማህም ብፈልግም ልከፍትልህ፣
እግር የለኝም ለመነሳት ምናባቴ ልሁንልህ፣
ወዳጄ ነው ብለህ ናፍቀኸኝ ብትመጣም፣
የቆለፍኩት በሬ ወዳንተ አያስወጣም፣
ኳ ኳ ኳ...
አይደክምህም? ማንኳኳቱ
የማይከፈት ቁልፍልፍ በር፤
እስከምከፍት አትጠብቅ
እጅ የለኝም በሬን ስበር፤
ባክህ ግባ የኔ ጌታ እስከምከፍት አትጠብቅ፣
በተዘጋ መግባት ታውቅ የል? ወዳጅህን ስትናፍቅ፣
ካሻህም ስበረው በር አይኑረው ግቢው በር
አይኑረው ቤቴ፤
አንተ ካለህልኝ የድንግል ማርያም ልጅ
ይገደላል ሞቴ፤
ኳ ኳ ኳ...
አይደክምህም? ማንኳኳቱ
የማይከፈት ቁልፍልፍ በር፤
እስከምከፍት አትጠብቅ
እጅ የለኝም በሬን ስበር።
ገጣሚ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#እጅ_ለሌለው
፧
መጥቼልሻለሁ ሁለት እጄን ትቼ፤
ቆሚያለሁ ከበርሽ ማንኳኳት ፈርቼ፤
"ለምን ፈራህ?" ካልሺኝ፣
አማላይ ቁመና ማራኪ ደም ግባት፤
እግርና ጭንቅንላት ልብና ኩላሊት፤
እጅ ለሌለው ሰው ትርጉም የላቸውም፤
እንኳን ለአንቺ ለበሩ አይመቸውም፤
ስለዚህ ተመለስኩ በረዘመው እግሬ፤
እጅ አጥሮ እንደገፋኝ ለልቤ ነግሬ፤
ሄጃለሁ ከበርሽ መንገዱን አልይዝም፤
ለኔም ቀን ወቶልኝ እጄ እስከሚረዝም።
#መታሰቢያነቱ_ለገንዘብ_ሲሉ_ፍቅርን_ለረገጡ_ሰዎች_ይሁንልኝ
ገጣሚ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ልኑር_እየፈሰስኩ
፧
የማይገኝ ዕድል ታውቂያለሽ መክሊቴ፤
የምድር ገነት ነው በፍቅርሽ መሞቴ፤
ካጠገብሽ ሳልሄድ ከጎኔ ሳትርቂ፤
ፍቅርሽ መቼ አነሰኝ ናፍቆት አትመርቂ፤
ተይ ግን እዘኚልኝ፣
እያለሽ አትናፍቂኝ፣
ስመሽ እያቀረብሽ ስቀሽ አትራቂኝ፤
ከማህተብሽ ስር ዘላለም ደብቂኝ፤
የመኖር ጉጉቴ ከፀሀይ ዕድሜ እኩል፤
ሲመሽ እንዳልጠፋ.....
ቆሜ ተማከርኩኝ በጨረቃ በኩል፤
በክረምት እንዳልሸሽ ደመናን ተጠጋው፤
ካንቺ እንዳልለያይ....
ዘላለም ለመኖር ተፈጥሮን አወጋው፤
ጨረቃና ፀሀይ ኮከብም ደመና፤
አልጨከኑም በኔ ስላንቺ ነውና፤
ሁሌም አለሁ አልኩኝ አንቺጋ ለመድረስ፤
ዘወትር ኖርኩልሽ ናፍቆት ለመቀነስ፤
ናፍቆት መቀነሻ መፍትሄ ሰብስቤ
አስቤ እንደጨረስኩ፤
ፀሀይ ጨረቃና ደመናን ስጠብቅ
ዝናብ ሆኜ ፈሰስኩ፤
ግን ደሞ አላዘንኩም እንደሰው አሮጥሽም፤
ታድያለሁና ከኔ ለመጠለል ጥላ አልዘረጋሽም፤
ልዩዬ የኔ አለም፥
ከፀሀይ ጨረቃ ከኮከብ ደመና እየተቀናነስኩ፤
ካንቺ ሳልለያይ በፀአዳ ገላሽ ልኑር እየፈሰስኩ።
ገጣሚ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ኖረዋል
፧
ከኔ ጋራ ሆነሽ፥
ለምን ትስቂያለሽ?
መጀመሪያ ሳውቅሽ.....
ፈገግ ብለሽ ነው ልቤን የማረክሺው፤
ለማን ነው ምትስቂው?
ከንፈርሽ ይከደን ጥርስሽን መልሺው፤
ከኔ ጋራ ሆነሽ፥
ለምን ታለቅሻለሽ?
ተክዘሽ እኮ ነው ሆዴን የበላሽው፤
ላባብልሽ ብዬ ልቤን የረታሽው፤
ዝም በይ ከኔጋ ማንም እንዳይመኝሽ፤
መሳሳቱ አይቀርም ከሳቅሽ ወይ ካለቀስሽ፤
አትሳቂ አታልቅሺ የዛኔ አይሟገቱም፤
ዝም ብለው ዝም ያሉ ኖረዋል አልሞቱም።
ገጣሚ ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#አውቃለሁ
፧
እሾህ በሞላው ማሳ አውቃለሁ ማራኪ አበባ፣
በጦርነት ሜዳ ላይ አይቻለሁ አንጀት ሲባባ፣
ከብዙ ክፉዎች መሀል ደጋግ ልብ ይበቅላል፣
እንደው ምናልባት አንዳንዴ...
ከብዙ ድመቶች መሀል አይጥ በሰላም ይውላል፣
ይገላል የተባለ መርዝ መድሀኒት ሆኖ ያድናል፣
ቆሻሻ መሀል ተጥሎ ሲፈተሽ አልማዝ ይሆናል፣
እንደው ምናልባት አንዳንዴ...
ሀጥአን በሞሉት ዓለም እንደ ኖህ ፃድቅ ይገኛል፣
በክህደት የደማው ልቤ "እሷ ታማኝ ነች" ይለኛል።
ገጣሚ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ቀንቼኮ_አይደለም
፧
የሳመሽን ሁሉ "አትሳሟት"
እያልኩኝ የምሟገትልሽ፤
ዘመድ ጓደኛሽን "እንዳትነኳት"
እያልኩ ካንቺ ማርቅልሽ፤
..............
ቀንቼ'ኮ አይደለም
..............
ላንቺው አስቤ ነው
የሚያገኙሽ ሁሉ ጉንጭሽን ሲያለፉ፤
ስለምሳሳ ነው እየደጋገሙ
በሳቅሽ ስር ሲያልፉ፤
..............
ቀንቼ'ኮ አይደለም
..............
አትሳሟት እያልኩኝ ካገኘሁት ሁሉ
ከሰው የምጣላው፤
ስለምፈራ ነው፥
ፈገግ ስትዪ ስርጉድ የሚለውን
ከንፈር እንዳይሞላው።
ገጣሚ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ድፍረት
፧
አይሰለችህ እኔን መማር በየለቱ፤
አይሰበርም?
በቃልህ ሀይል ልቤ አለቱ፤
ማረኝ ብዬ የምበድል፤
እያዳንገከኝ የምገድል፤
ስትፈልገኝ፥
የማልገኝ አንድ ግልገል፤
ኮብልያለሁ አንተን ትቼ
ሀጢያቶቼን ለማገልገል፤
ሳገለግል ኖሬ ሀጢአትን በብዙ፤
ለሞት አስረከበኝ ይህ ነበር ደሞዙ፤
ወዮ የኔ ጌታ በምን አንደበቴ ማረኝ እልሀለሁ፤
አስገባኝ ከቤትህ ብዬ አልጠይቅህም
በደሌን አውቃለሁ፤
ባክህ አባቴ ሆይ ባክህ የኔ ጌታ፤
ከገነት በሩ ላይ ይኖር ይሆን ቦታ፤
ማን ፈራጅ አረገኝ በየትኛው ሀይሌ፤
እዛስ በምን ፅድቄ ድፍረት ነው ይህ ቃሌ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#መድሃኒቴ
፧
አለች ደሞ መድሃኒት አንገት ስማ የምታክም፤
ቃል ከአንደበት የምትሰውር ስቃ ምታደክም፤
***
ግልፅ የሆነች ለኔ ምንም የማትደብቅ፤
አጠገቤ ሆና እያየችኝ የምትናፍቅ፤
መጨነቄ የሚጨንቃት መደሰቴ ለሷ ደስታ፤
ቀን ሞላ ጎደለ አትርቀኝም ሁኔታ አይታ፤
የሆነችኝ ለኔ ፅናት ያቆመችኝ ተንበርክካ፤
ከፀሐይ ፍም ያዳነችኝ አስጠልላኝ እንደ ዋርካ፤
***
አለች ደሞ መድሀኒት አንገት ስማ የምታክም፤
ቃል ከአንደበት የምትሰውር ስቃ ምታደክም፤
***
ተቀብታ የፍቅር ናርዶስ ፍቅር ፍቅር የምትሸት፤
አለች ደሞ አንቺን አይነት የምትማርክ እንቡጥ እሸት።
ገጣሚ
#ካሳሁን_ክንፈ
አሪፍ ግጥሞችን ከፈለጋችሁ
Join👇
@getemk2g
425
#ስልክ_መግዛት_የምትፈልጉ
ዋጋ 7,800 ብር
INFINIX SMART 6
RAM 2
Storage 32 GB
Android 10
0902414335 ሳያመልጣችሁ ደውሉልኝ ወይም በውስጥ አናግሩኝ
👉 @kaseshart
425
#ገለሽኛል
፧
በታመንኩኝ ዝቅ ባልኩኝ ለፍቅር ስል፤
አደማሽው ያዳንሺውን ክፉ ቁስል፤
ፍቅር እውር ነው ተታለልኩኝ፤
በሙሉ ልብ ካንቺ ዋልኩኝ፤
ቁልቋል ሆኜ ኖሬ ካ'ጋም፤
ምርጫ ያለው ለካ አይረጋም፤
አንቺ ምን አለብሽ ሁለት እናት አለሽ፤
አንዱ ሲሞትብሽ በአንዱ ታለቅሻለሽ፤
የሞትኩት እኔ ነኝ ሳምንሽ ክደሽኛል፤
ለመኖር ስጓጓ ዋሽተሽ ገለሽኛል፤
አመሰግናለሁ በክደት ቢላ ስለገደልሺኝ፤
ብሞትም እንኳን
ወደተሻለው የፍቅር ገነት ስላስገባሺኝ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#በእንባዬ_እንዳጠፉ
፧
ትላንትናን እያሰብኩኝ ለምን ብዬ እንባ ላፍስስ፤
በሀዘኔ ለሚያለግጡ የጠላቴን አንጀት ላርስ፤
በሆዴ ቻል ዋጥ አድርጌ ህመሞቼን ሽፍንፍንፍን፤
በመድማቴ ስቄ ቁስሎቼን ሽፍን፤
ለምን ሲባል ተሰንሰቅስቄ ደም ማንባቴ፤
ለምን ሲባል ወዳጆቼ ይታመሙ በጉዳቴ፤
ከላይ በፈገግታ በሳቅ ስንከተከት፤
ጥርሶቼ እስከኖሩ አይኔን አይመለከት፤
ተከትሮ የቆመ እንባ ተጠራቅሞ ዓይኖቼ ስር፤
ቅርቡን እንጂ ጨልሞብኝ ሩቅ አላይም እንደንስር፤
እንባዬ ጎርፍ ሆኖ ሀገር እንዳይጠፋ፤
ወንዝ ዳር አቁሙኝ እጅጉን ስከፋ፤
የዛን ጊዜ ይውረድ ከውሃው ይደብለቅ፤
ጨው ካለው ባህር ላይ በውቅያኖስ ይጥለቅ፤
ውሃ ጣዕም የለውም እስከነፃ ድረስ፤
እንደኔ የከፋው የአንድ ሰው እንባ ነው
ጨዋማ ውቅያኖስ፤
ሲቀላቀል የኔ የተገደበ እንባ መውረድ ከጀመረ፤
ሊቀጥል አይችልም የተዋበው ሁሉ ሰርክ እንደሰመረ፤
በሳቅ የታጀበ የታመቀ እንባ የደቀቀ ተስፋ፤
ድጋሜ እንዳቶጉኝ አቅቶኝ አልቅሼ ዓለም እንዳጠፋ።
ገጣሚ
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ገጣሚው_የት_ጠፋ
፧
ብዕሩ ጠፋበት ብራና አለቀበት?
ብርሀን ሲጠብቅ ጨልሞ ቀረበት?
ወይስ ቃላት አጣ?
በሀሳብ ገረጣ?
ገጣሚው የት ጠፋ?
አጥቶ ይሆን ተስፋ?
አቅሙ ደቃቆ ተሰባብሮ ይሆን?
ሕይወት ሰነከለው መሆን አለመሆን?
ከራሱ ተጣላ?
ወይንስ ከሌላ?
ወይ ስራ ቀየረ?
በግጥሙ አፈረ?
የት ጠፋ ገጣሚው ምንስ ተፈጠረ?
ግጥምን ከራቃት ቀናት ተቆጠረ፣
ይህ ሁሉ ጥያቄ ተፈጥሮ ሲያበቃ፣
የገጣሚው ግጥም እንዲ ነበር በቃ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
