ch
Feedback
Nova'

Nova'

前往频道在 Telegram

ከባርነት ነፃነት ትከብዳለች። ብዙዎች ነፃነትን ሽጠው እስትንፋስ ይገዛሉ። እኔ ግን እስትንፋሴን በነፃነት እለውጣታለሁ። !

显示更多
526
订阅者
无数据24 小时
-57 天
-1730 天

数据加载中...

吸引订阅者
十二月 '24
十二月 '24
+5
在0个频道中
十一月 '24
+7
在0个频道中
Get PRO
十月 '24
+4
在0个频道中
Get PRO
九月 '24
+5
在0个频道中
Get PRO
八月 '24
+3
在0个频道中
Get PRO
七月 '24
+5
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+5
在0个频道中
Get PRO
五月 '24
+38
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+239
在0个频道中
Get PRO
三月 '24
+169
在27个频道中
Get PRO
二月 '24
+140
在21个频道中
Get PRO
一月 '240
在0个频道中
Get PRO
十二月 '230
在0个频道中
Get PRO
十一月 '230
在0个频道中
Get PRO
十月 '230
在0个频道中
Get PRO
九月 '230
在0个频道中
Get PRO
八月 '230
在0个频道中
Get PRO
七月 '230
在0个频道中
Get PRO
六月 '230
在0个频道中
Get PRO
五月 '230
在0个频道中
Get PRO
四月 '230
在0个频道中
Get PRO
三月 '230
在0个频道中
Get PRO
二月 '230
在0个频道中
Get PRO
一月 '230
在0个频道中
Get PRO
十二月 '220
在0个频道中
Get PRO
十一月 '220
在0个频道中
Get PRO
十月 '220
在0个频道中
Get PRO
九月 '220
在0个频道中
Get PRO
八月 '220
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+1
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+1
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+1
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+14
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+314
在0个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
09 十二月+1
08 十二月+1
07 十二月0
06 十二月+1
05 十二月0
04 十二月0
03 十二月+1
02 十二月+1
01 十二月0
频道帖子
መሬት, ፀሓይና ጨረቃ የዘመን መለወጫ ይሠራሉ:: የዘመን መቁጠሪያ ከሰው አቅም ውጭ ነው:: ጨረቃ በ28 ቀናት 12 ከዋክብትን ተከትላ ትዞራለች:: ይህ ወራትና ሳምንታትን ይፈጥራል:: መሬት እና ፀሓይ በ365 ደረጃዎች (ቀናት) የሚዘዋወሩበት ምሕዋር አላቸው:: እነዚህ ሁሉ ያለመዛነፍ ያለማንም ፍጡር ጣልቃ ገብነት ምሕዋራቸውን ጠብቀው ይዞራሉ:: የዓመታት መቁጠሪያ ቀርቶ ሰዓትና ሰኮንድ ከእነዚህ ነው የሚቀዳው:: ምክንያቱም perfect ስለሆኑ:: ሦስቱ አራት ወቅቶች (ክረምት, ፀደይ, በልግና በጋ) ይፈጥራሉ:: ዛሬ የነበሩበት ትይዩ ላይ ለመድረስ አራት ዐመታት ወይም 1,460 ሲደመር 1 ቀን (ዲግሪ) ይፈጅባቸዋል:: ሦስቱም አካላት የማንም የግል ንብረት አይደሉም:: እምነት ቢኖርም ባይኖርም ቆጣሪ ቢፈጠርም ባይፈጠርም ይኸው ሁኔታ ለሚሊዮኖች ዐመታት ነበር:: ይቀጥላል:: በሂጅሪያም ቁጠር በግሪጎሪያ, በሕንድም ቁጠር በዞሮስትሪያ ቆጣሪዎቹ ሰዎች ሳይሆኑ እነዚህ ግዙፍ ፍጡራን ናቸው:: መጋጨት አትችልም:: አይንጋ ብትል ፀሓይ ባንተ እጅ አይደለችም:: ከ12 ወራት በላይ ልጨምር ብትልም አይመጣም:: የሦስቱ አካላት ሽግግር ወደ ቁጥር ለመቀየር የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል:: በጀትም ይሁን ጸሎት ጋብቻም ይሁን ውልደት ሳይቀር የእነዚህ ጥገኛ ናቸው:: 12ቱንም የጨረቃ መዞሪያ ቡሩጆች እኩል 30 ቀናት ከሰጠን 5 ዲግሪ (ቀናት) ክፍት ይመጣል:: Perfect ዙር ግን 4 ዓመታት ይፈጃል:: ይህ እንዴት ይቻቻል የሚለው የተለያዩ ሀገራት የተለያየ ዘዴ ተጠቅመዋል:: በአንድ ክብ ላይ የሚመጣው ክፍተት አለ:: ማትስ ጂዖሜትሪ ውስጥ ይወስደናል:: የሦስቱ ክብ አካላት ክፍተት ደግሞ ጳጉሜ አድርገው የሄዱ አሉ:: በየወራቱ የሸጎጡም አሉ:: ለዘመን መለወጫ እየጠፉ ብቅ የሚሉ ከዋክብት የተጠቀሙ ብዙ ናቸው:: ባነበብኩት ግብጾችና ፋርሶች እንዲሁም ከፊል ዐረቦች ሺዕራ (ሲሪየስ) የሚባለውን የንጋት ኮከብ ይጠቀሙና ያመልኩም ነበር:: ግብጾች ሺዕራ ኮከብ ስትቀርብ የዓባይ መነሻ ሀገራት ላይ ክረምት እንደገባ አውቀው ይዘጋጁና ይገብሩ ነበር:: ከሦስቱ አካላት አልፎ ከዋክብትም ምሕዋሩን ጠብቀው ይንቀሳቀሳሉ:: የሕዋው ቋንቋ ቁጥር ነው:: እኛ ሕዳር እንበል ጁላይ ፕላኔቶቹ አያውቁም:: ሰው በ28 ፊደላትና በ7 አናባቢ ይተረጉማቸዋል:: በሌላ አነጋገር እኛ ነን እነርሱን ፕላኔቶቹን ተርጉመን የምንከተለው:: ኢትዮጵያ የምትከተለው ቀመር one of the perfect and ideal ቀመር ነው ይባላል:: የሰዓት አቆጣጠራችንም ልዩ ነው:: ፀሐይ ስትወጣ ጀምረን 1 እንልና ስትጠልቅ 12 እንላለን:: ፈረንጆች ከእኩለ ሌሊት ይጀምራሉ:: የእኛ perfect ነው:: ይህንን ቀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀመር ሆኖ ያገለግላል:: የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ዓመቱ የሺዕራ ኮከብ ለምድር መቃረቢያ ሐምሌ ላይ ሲሆን የዘመን መለወጫው ክረምት ሲወጣ መስከረም 1 ላይ ነው:: ጉራጌዎች አሁን ሕዳር አጋማሽ ላይ ናቸው:: እንኳን ለ2017 አደረሳችሁ:: 2018ን በሰላም አደረሳችሁ ለማለት ያብቃን:: በሰላም ስንል በጦ^ርነት የከረሙት ይከፋሉ:: Hassen Injamo

2
ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ዙሪያ Fb ላይ ሲመላለሱ በነበሩ ቪድዮዎች በአንዱ ላይ ይህ ወንድማችን ሊገለጽ የማይችል እና ሌሎችን የሚያስቆጣ ሀሳብ በመጻፉ ብዙዎች ቁጣቸውን ሲገልጹለት
ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ዙሪያ Fb ላይ ሲመላለሱ በነበሩ ቪድዮዎች በአንዱ ላይ ይህ ወንድማችን ሊገለጽ የማይችል እና ሌሎችን የሚያስቆጣ ሀሳብ በመጻፉ ብዙዎች ቁጣቸውን ሲገልጹለት (አለፍ ሲልም ሲዝቱበት ነበር) የልጁ አገላለጽ እጅግ መረን የለቀቀ እና ጤነኞችን የሚያሳምም ለመሆኑ አብዛኞቻችንን የሚያስማማ ነው። በዚህ መሰሉ ጋጠወጥነት ላይ የተቆጡት ለምን ተቆጡ ማለት አንችልም(እኔም ያ ስሜት ተሰምቶኛል) ከዚህ አልፈን በዚህ መሰሉ ክፉ ተግባርን የሚያበረታቱን አደብ ለማስያዝ የተሻለው አማራጭ እንዲያዝ አድርጎ ለሚመለከተው የህግ አካል አሳልፎ መስጠት ነው የነበረብን።ከዛ ውጪ ያለው ተግባራችን ከሄቨን ገዳይ እኛ በምን ተሻልን? ይህንን ልጅ ተከታትለው የያዙት ወጣቶች ግን የፈጸሙት እንደ አንድ የተደራጀ ማፊያ ቡንድ አፍነው ጫካ ውስጥ በሚዘገንን ሁኔታ እየደበደቡት ቪድዮ ቀርጸው ነው የለቀቁት። ይህን የተመለከቱ ብዙዎች ጥሩ እንዳደረጉ በደስታ እየገለጹም ተመልክተናል።ይህ ተግባር ግን ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። mob justice ያጠፋናል እንጂ ፈጽሞ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። በዚህ መሰል ቅጽበታዊ የቡድን ፍርድ ጥፋታቸውን ያላወቁ ሰዎች በህይወት እያሉ በእሳት ተጨምረው ሲጠበሱ ፣ በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ፣ አፈሙዝ ጭንቅላታቸው ላይ ተደግኖ አንጎላቸውን ሲበትኑ ፣ ሲሰቀሉም ጭምር ተመልክተናል። ይህ ሰውኛ ያልሆነ አውሬያዊ ባህሪይ መጠፋፊያ ካልሆነ ፈጽሞ አስተማሪ ሊሆን አይችልም🙏
0
3
ኦሾ  .. የዚህን ሰውዬ መፅሃፍ ካነበብክማ ታብዳለህ (የሚባልለት) ኦሾ  ያነበበዉን  ያክል  መጽሐፍ  ባይጽፍም  ነገር ግን ከ 100 ሺህ በላይ መፅሃፍትን አንብቤያለሁ! በቀን  ውስጥ ቢያንስ ከስድስት ያላነሱ መፅሃፍትን እጨርስ ነበር!  ይላል! "  "Enlightenment" ይለዋል ! የሰው ልጅ ጥልቅ ሃይል እንዳለው በራሱ መንገድ እውነትን ፈልጎ ማግኘት እንደሚገባው በነፃነት መኖር እና ፍቅርን በነፃ ሰጥቶ መቀበል እንዳለበት ያምናል ያስተምራል። ወሲብ ነፃ መሆን እንዳለበት እና አንድ ሰው ካሻው ከማንኛው ሰው ጋር መመቻቸት እንዳለበት ያምናል "ትዳር" የሚባል ተቋም በጭራሽ እንደማያስፈልግም ያስተምራል ብችል "ትዳር" የሚባለው ተቋም ከምድረ ገፅ ባጠፋው ደስ ይለኛል ይላል! አብዛኛዎቹ የዓለማችን ችግሮች የሚመነጩት ትዳር ከሚባል ቆሻሻ ተቋም ነው ብሎ ሽንጡን ገትሮም ይከራከራል!።   "Meditation" እና "Therapy" የሰው ልጆች ቁልፍ መዳኛ መንገዶች እንደሆኑም ያምናል! ለዚህ ሰውዬ እዚህ መድረስም መውደቅም ትልቁን አስተዋፅኦ ያበረከተች አንዲት ገራሚ ሴት አለች! "Sheela" ትባላለች በትውልድ ህንዳዊት ናት! ለሷም ፀለየላት "Meditate' አስደረጋት የህይወት ፍልስፍናውን አስተማራት እሷ ግን በነዚህ ነገሮች ብዙም አልተመሰጠችም ሰውየው ያለውን አቅም "ዓለም አቀፋዊ እንዲያደርገው ፈለገች የሰውየው የህይወት ፍልስፍና በወቅቱ ከነበረው የህንድ መንግስት ጋርም ብዙ ሰጣ ገባ ውስጥ እየከተተው ስለነበር ደህንነቱ አሳሳቢ ሆነ! "Sheela" እንዲህ አለችው! ". ... ለምን ወደ ነፃነቷ ምድር "አሜሪካ" አንሄድም? ለምን "አሜሪካ" ውስጥ ሰፊ መሬት ገዝተን የራሳችንን የተቀደሰች ከተማ አንገነባም? ፍቅር፣ ርህራሄ እና መካፈል የበዛባት ማንም ምንም ነገር ባለቤት የማይሆንባት፣ ስግብግብነት ፅዩፍ የሆነባት፣ የቃል ኪዳን ከተማን አንገነባም? " ብላ መከረችው! ተስማሙ! በአሜሪካ "Oregon" ግዛት "Antelope" የምትባል መንደር ውስጥ 64 ሺህ ሄክታር መሬት ገዙ! አብዛኛዎቹ የ "osho" ፍልስፍና ተከታዮች የተማሩ እና ሀብታም ስለነበሩ ከተማዋን ለመገንባት ብዙ ግዜ አልፈጀባቸውም። የሰውየው "ቃል አቀባይየሆነችው  "Sheela" "osho"ን ለመከተል የመጡትን ባለሃብቶች፣ ኮንትራክተሮች እና አርክቴክቶች አሰባስባ ያለመችውን ከተማ አስገነባቻቸው። የከተማዋን ስምም የ" Rajneesh ከተማ" አሏት። ቀስ በቀስ የራሳቸውን ባንክ፣ የራሳቸውን አየር ማረፊያ፣ ግድብ፣ አውሮፕላኖች፣ ግዙፍ ዘመናዊ እርሻዎች፣ እንስሳት ማርቢያዎች እና ሰው ሰራሽ ሃይቆች ሳይቀር ሰሩ!.....ቀሪውን ፊልሙ ላይ ማየት ነው ....... *** «ናፖሊዮን ሂል 'Think and Grow Rich' የተባለ መፅሐፉን በመሸጥ እንጂ እንደሚያወራው ቀና አስተሳሰቡ አልነበረም ያበለፀገው፡፡ የሀብቱ መነሻ በመላው አለም የሚገኙ የዋሆች መፅሀፉን ስለገዙለት ነበር።» ይለናል Bhagwan Shree Rajneesh Osho ህዝቦቼ አለምን በፌሽታ በደስታ በዳንስ በዜማ እንዲሞሉዋት እፈልጋለሁ። እኛ አንዳች መንግስተሰማያትን አይደለም የምንፈልገው እኛ የምንፈልገው መንግስተሰማያትን እዚሁ መፍጠር ነው ምክንያቱም እኛ ከሞት በኃላ ስላለ ነገር አይደለም ፍላጎታችን እዚሁ መንግስተሰማያትን መፍጠር ከቻልን በርግጠኝነት በገሀነም ከተገናኘን እዛም መንግስተሰማያትን መፍጠር አያቅተንም   osho
0
4
ለአሜን የተፈጠርን ( ካሊድ አቅሉ) ሰፈራቸው መታጠፍያ ጋር ሆኜ ወደ በራቸው ሳማትር ሰዎች ተባብረው ድንኳን ሲተክሉ አየው ። ምን ተፈጥሮ ይሆን ብዬ ለማጣራት ወደ ግቢያቸው ስጠጋ እልልታና ጭብጨባ በሙዚቃ መሳርያ ታጅቦ ሌላ ገፅታ አላብሶታል ፤ ለካ አጢነው ከሰሙት " አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ " የሚለው የሰርግ ዜማ ከሙሾ በላይ ያስነባል ነገሩ ዛሬያችን እራሱ ትናንታችን የገፋው ግሳንግስ የሚሆንበት ወቅት አለ አይደል ••• የወደፊትዋ ሚስቴ ብዬ በልቤ መዝገብ አድምቄ የፃፍኳት ልጅ " የአቶ እንትና ባለቤት " ለመባል በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶችን ምትጠባበቅ  እጩ ሙሽራ መሆንዋን ቤታቸው በዜማ ነገረኝ ብዙ ግዜ ያገኘሁት እሷ እስክትመጣ አተኩሬ ያየሁት ደማቅ ጥቁር በራቸው ብዙ እንዳንኳኳሁት አሻራዬን ያላሳረፍኩበት ለመምሰል አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬቱን እያየ "እኔ ምን ላርግ አልከፈትም አልንኳኳም ማለት አልችል !" ያለኝ መሰለኝ ነገሩ እኛስ ህይወት እንደ ከረንቡላ ኳስ ወዳሻት ጉርጓድ ምትወረውረን ከተዘጋጀልን ነገር የማንሸሽ ሰዎች አይደለን ከ "ለምን?"  ይልቅ "ለአሜን" የተፈጠርን። በራሴ እጅ የፃፍኩት ጉም ተስፋ ከተረት ተረት እንዳልዘለልን ተረዳውና ፈጣሪ የከተበልኝን አዲስ ምዕራፍ ለመግለጥ ቤታቸውን ትቼ እራሴን ለማግኘት ጉዞ ጀመርኩኝ ••••••
0
5
አንድ ቀን ቅዳሜ ደውዬላት ቤቴ መጥታ ሰፊ አልጋዬ ላይ እንደተቃቀፍን ... በስሜት እየቃተተች "በደንብ አባልገኝ አለችኝ" ቃሉ ቀፈፈኝ ... አባልገኝ! ... ፈፅሞ ከእሷ አንደበት የወጣ አይመስልም
አንድ ቀን ቅዳሜ ደውዬላት ቤቴ መጥታ ሰፊ አልጋዬ ላይ እንደተቃቀፍን ... በስሜት  እየቃተተች "በደንብ አባልገኝ አለችኝ" ቃሉ ቀፈፈኝ ... አባልገኝ! ... ፈፅሞ ከእሷ አንደበት የወጣ አይመስልም፤ የእሷ ቃላት ጠያይሞች ናቸው። ይሄኛው የተቃጠለ የመኪና ዘይት የመሰለ ጥቁር የከተማ ቃል ነበር። "እንደዚያ አትበይ ማሂ" አልኳት። "ለምን?" "ይደብራል!" "ይደብርህ! አባልገኝ!!" ዝም አልኳት። ከብዙ ግርምት ጋር ። በአራት አመት ቆይታችን አልጋ ላይ ከስሬ ተኝታ ከሚቆራረጥ ትንፋሿ ውጭ አንድ ቃል ስትተነፍስ ሰምቻት አላውቅም ነበር፣ የዚያን ቀን ግን ምርር ባለ ድምፅ ብዙ ብዙ ነገር አለች ... አልሰማም ብል እንኳ አስገድዶ በጆሮዬ የሚፈስ ነገር... "እንደማታገባኝ እያወቅሁ አብሬህ መተኛት ብልግና ነው ... ለመባለግ፣ ለመርከስ ፈቅጄ ነው ... ይሄ ፍቅር አይደለም፤ አባልገኝ! ... ሳሎን ውስጥ አባልገኝ፣ ሶፋህ ላይ አባልገኝ፣ ምንጣፍህ ላይ አባልገኝ፣ ኩሽናህ ውስጥ አባልገኝ..." ከኔ ጋር መተኛት እርኩሰቷ ነው። ግን እርኩሰቷን በሚቆራረጥ ትንፋሿ ውስጥ ባለው ፍቅር አጠበችው። ታፈቅረኛለች! ግን አላገባትም። እንደተሳሳተች ታውቃለች ግን ፍቅር አስሯታል።
0
6
አንድ ቀን ቅዳሜ ደውዬላት ቤቴ መጥታ ሰፊ አልጋዬ ላይ እንደተቃቀፍን ... በስሜት  እየቃተተች "በደንብ አባልገኝ አለችኝ" ቃሉ ቀፈፈኝ ... አባልገኝ! ... ፈፅሞ ከእሷ አንደበት የወጣ አይመስልም፤ የእሷ ቃላት ጠያይሞች ናቸው። ይሄኛው የተቃጠለ የመኪና ዘይት የመሰለ ጥቁር የከተማ ቃል ነበር። "እንደዚያ አትበይ ማሂ" አልኳት። "ለምን?" "ይደብራል!" "ይደብርህ! አባልገኝ!!" ዝም አልኳት። ከብዙ ግርምት ጋር ። በአራት አመት ቆይታችን አልጋ ላይ ከስሬ ተኝታ ከሚቆራረጥ ትንፋሿ ውጭ አንድ ቃል ስትተነፍስ ሰምቻት አላውቅም ነበር፣ የዚያን ቀን ግን ምርር ባለ ድምፅ ብዙ ብዙ ነገር አለች ... አልሰማም ብል እንኳ አስገድዶ በጆሮዬ የሚፈስ ነገር... "እንደማታገባኝ እያወቅሁ አብሬህ መተኛት ብልግና ነው ... ለመባለግ፣ ለመርከስ ፈቅጄ ነው ... ይሄ ፍቅር አይደለም፤ አባልገኝ! ... ሳሎን ውስጥ አባልገኝ፣ ሶፋህ ላይ አባልገኝ፣ ምንጣፍህ ላይ አባልገኝ፣ ኩሽናህ ውስጥ አባልገኝ..." ከኔ ጋር መተኛት እርኩሰቷ ነው። ግን እርኩሰቷን በሚቆራረጥ ትንፋሿ ውስጥ ባለው ፍቅር አጠበችው። ታፈቅረኛለች! ግን አላገባትም። እንደተሳሳተች ታውቃለች ግን ፍቅር አስሯታል።
0
7
🚦ማጽናኛ🚦 👉አንድ ወጣት ህይወቷን መቀየር ሰውነቷን መጠቀም ፈልጋ 😉. በአንድ አጋጣሚ ከባለሀብቶች ጋር አገናኘኋትና...ቀልጠፍጠፍ አለች.....አሁን እሷ ሱቅ ምናምን ከፍታ....ቻፒስት ሁናለች (ወንድ አርጎ ስለፈጠረን እንውቀሰው ይሆን🤔)...ባለሥልጣናት ማጫወት ጀምራለች..(የአገሪቷ ከባባድ መረጃ እጇ ላይ ነው)...በቅርቡ ቤተክርስትያን እርዳታ መሥጠት ፈልጋ...እንደደበራትና...የሀጥያተኝነት ስሜት እንደ ተሰማት...ነገረችኝ...እና ይህንን አጫወትኳት... 👉አንዴ The economist እያነበብኩ የኮሎምብያ...drug cartel..አስተዳዳሪዎች....በሚያገኙት ገንዘብ...በአካባቢያቸው የካቶሊክ ቤተክርስትያን ያሠራሉ..ለአጥቢያቸውም የቤተክርስትያኗን ንዋየ ቅድሳት የሚገዙት እነሱው ናቸው....አንድ ግዜ የካቶሊኩ ፖኘ...የዚህችን ቤተክርስትያን Bishop...እንዴት የሀጢያት ገንዘብ ለቤተክርስትያን አገልግሎት ታውላለህ ብለው...ወጥረው ይይዟቸዋል 👉በዚህ ግዜ Bishopፑ.. ''በመጽሀፍ ቅዱስ ዘማዊቷ ሴት የክርስቶስን እግር በውድ ሽቶዋ ስታጥብ እኮ...ክርስቶስ ሽቶውን ከየት አመጣሽው ብሎ አልጠየቃትም.''..ብለው ፖፑን ኩም አረጓቸው.....ይህንን ታሪክ ነግሬ አጽናንቻታለሁ...ወደ ኋላ ዙሮ ማየት የጫው ሀውልት አርጎ ያሥቀራል
0
8
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት ሊያደርግ ነው በተጨማሪም ቴሌግራምን ተወዳጅ ሊያደርጉት ከሚችሉ ነገሮች አንዱ ይህ ነው 🤩 ⭐️ አሱም MAJOR Telegram Stars ይሰኛል🔴 እን
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት ሊያደርግ ነው በተጨማሪም ቴሌግራምን ተወዳጅ ሊያደርጉት ከሚችሉ ነገሮች አንዱ ይህ ነው 🤩 ⭐️ አሱም MAJOR Telegram Stars ይሰኛል🔴 እንደሚታወቀው TikTok በፈጠረው የቲክቶክ ኮይን ጊፍት አማካኝነት ብዙዎቹ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ረድቷል። ቴሌግራምም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል ይህም የቴሌግራም ክሬተሮች የተሰጣቸውን ጊፊት ወደ ገንዘብ መቀየር እንዲችሉ ተደርጓል። ቴሌግራምም ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገል መጥቷል ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል። በተጨማሪም Verify የሆነ Airdrop ነው ከመጣም 5 ቀን አልሆነውም ይህንንም በደንብ የሰራ ሰው የTON ሽልማት እንዳለው አሳውቀዋል 1 ሰው invite ስታደርጉ 15 star ታገኛላቹ ⭐️⭐️ ይህንን እንደ ኤርድሮፕ እንዳትቆጥሩት ሊስት ብሎ ነገር የለውም ትክክለኛ ገንዘብ ነው ስለዚህ Guys አሁኑኑ ጀምሩት💥 👇🏻 https://t.me/major/start?startapp=6492379204
0
9
ባልና ሚስት የአንድ አርሶአደር የከብቶች ማርቢያን ሲጎበኙ በሬው ላሟን ሲሰር አዩ። ይህኔ ሚስትዮዋ አርሶ አደሩን... "ለመሆኑ በሬው በቀን ስንቴ ይሰራል?" ብላ ጠየቀችው። አርሶአደሩም... "ቢያንስ በቀን 6 ጊዜ ይሰራል" አለ። ሚስትዮዋም ወደባሏ ዞራ... "ሰማህ?" አለችው። ይህኔ ደግሞ ባልየው አርሶ አደሩን... "በሬው በቀን 6 ጊዜ የሚሰረው አንዷን ላም ነው?" ብሎ ጠየቀው። አርሶአደሩም.... "አይ የተለያዩ ላሞችን ነው" ሲል ባልየው ወደሚስቱ ዞሮ... "ሰማሽ?" 🙃 ሰማቹ
0
10
ፊት ለፊቴ ተቀምጣለች … ሸገር ባስ ውስጥ መጨረሻ አካባቢ ፊት ለፊት የሚያፋጥጠው ወንበር ተፋጠን ተቀምጠናል … በስርቆሽ ቀና እያለች ታየኛለች … አይኔን ተክዬባታለሁ …ቆንጅዬ ናት … “ሰዓት ይዘሻል !..” “እንዴ አንተኮ አስረሃል …!” እየሳቀች “ኦው …የኔን ሰዓት ስለማላምናት ነው …!” “እንዴዴዴዴዴዴ ካላመንካት ለምን እጅህ ላይ አሰርካት …!?” ፊቷ ላይ ግርምት ልትቀባ እያኮበኮበች… “ስለምታምር … ደግሞ በጣም የማከብረው ሰው ሽልማት ስለሆነ …” “ኦው እንደዛ ከሆነ ጥሩ … በጣም የምታከብረው ሰው መሆን አለበት …!” “አዎ …ኧረ እንደውም የቴዲ አፍሮ ስጦታ ናት … እሱ ነው ከእጁ አውልቆ የሸለመኝ …” ኮፈስ ብዬ … አይኗ ሲበለጠጥ አየሁ … እግሮቿን ወደኔ አዞረቻቸው … ከንፈሯን በምላሷ ማረጣጠብ … ምናምን ምናምን “እንዴ የምርህን ነው !.. እስቲ እስቲ … እንዴት ሸለመህ … ማለት አንተም ዘፋኝ ነህ …!” … እጄ ላይ ያለችውን ሰዓት እጄን እያገላበጠች አየቻት .. “እንደዛ ነገር ….” ኮፈስ ብዬ…” እሱ ባለበት መደረክ ላይ አንድ ሙዚቃውን ተጫወትኩ … መጣና ይህን እኔ በመዝፈኔ እንድቆጭ አደረከኝ …ዘፈኔ ትክክለኛውን ዘፋኝ አገኘ …ብሎ አቅፎኝ አለቀሰ..” “የምርህን ነው !” “ያ !... ከዛ እጁ ላይ አድርጓት የነበረችውን እቺን ሰዓት አውልቆ ሸለመኝ….”… አጠገቤ ያለው ሰውዬ ተነስቶ ሲወርድ ባዶ ቦታው ላይ ተሸቀዳድማ አጠገቤ ተቀመጠች … ጠረኗ መቼም ሙት ይቀሰቅሳል … ደስ አለኝ … “በናትህ ትንሽ አንጎራጉርልኝ …እ!” አይኖቿን በሃዘኔታ አንከባለለቻቸው ….ስታሳዝን “እዚህ !... ኧረ አይሆንም!... “ ተግደረደርኩ … “በናትህ አንዴ ብቻ እ!.. ትንሽ ለኔ ብቻ እንዲሰማኝ አድርገህ እ… ደሞ የማደርግልህን አታውቅም … “ (ጉንጭሽን አስሚኝ …ጡትሽን አስነኪኝ ብላት እሺ ትለኛለች …) “ ሄይ ሰውዬ አይንህን ገልጠህ ታንቀላፋለህ እንዴ !... መጨረሻው ነውኮ … “ የሚፈቀፈቅ ቆርቆሮ ያለው ድምፅ ከሃሳቤ አናጠበኝ … ብንን ብዬ ስነሳ ፊትለፊቴ ባዶዶደዶዶ የቆመ አውቶብስ ውስጥ እኔ ሹፌሩና ቲኬተሩ ተፋጠናል … (ይሄ አጉል ሃሳቤማ እንኳን ፌርማታ ህይወቴን ያዘልለኛል … የት ልሄድ ነበር የተሳፈርኩት!... ወይኔ ስልኳን ሳልቀበላት !)
0
11
ጣምራ ጦር @OLDBOOKSPDF.pdf
0
12
የመጽሐፍ ዳሰሳ 3 ጣምራ ጦር ደራሲ:- ገበየሁ አየለ ይዘት:- ታሪካዊ ልቦለድ የታሪክ እና የፖለቲካ መጻሕፍትን እወዳለሁ። የሰው ልጅ ሥነ ጥናት ምን አድማስን ቢዞር ... የመጨረሻ ግቡ ሰው ነው። ታሪክ እና ፖለቲካ ደግሞ መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸው ሰው ነው። " ጣምራ ጦር " የተሰኘው የገበየሁ አየለ መጽሐፍ ታሪክን መሠረት ያደረገ መጽሐፍ ነው። ታሪኩን ለተደራሲያን ውብ አድርጎ ለማቅረብ ታሪካዊ ልቦለድነትን ተላብሷል። ታሪኩ መሠረት የሚያደርገው በሃገራችን አቆጣጠር 1969 ላይ በተደረገው የኦጋዴን ጦርነት ላይ ነው። የዚአድባሬ ሱማሊያ ወደ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ወረራ እና የዘመኑን ጀግኖች የአይበገሬነት ትግል ያስቃኘናል። መጽሐፉ ሙሉ ጦርነቱን አልዘገበም። ከዚያ ይልቅ በሁለት ጓደኛሞች የደርግ ወታደሮች ውጣ ውረድ ላይ ነው ሙሉ ዳሰሳው። በሁለቱ ጀግኖች ሕይወት ላይ የዘመኑን የምስራቅ ኢትዮጵያ ሁኔታ፣ የወረራውን አስከፊነት፣ የህዝቡን ሰቆቃ፣ የመልክዓ ምድሩን አስቸጋሪነት፣ ታማኝነት፣ በወዳጅ መከዳት፣ የሀገር ፍቅር፣ መስዋዕትነት፣ የቤተሰብ ናፍቆት፣ በሞት ጥላ ስር መኖርን ... ያስመለክተናል። ጣምራ ጦር በውብ አጻጻፍ የተጻፈ፣ እንደ ሌሎች ታሪካዊ ልብወለዶች ማጋነን ያልበረዘው ድንቅ መጽሐፍ ነው። ገበየሁ አየለ በመጽሐፉ ... ወታደሮች በጦርነት እሳት ውስጥ በምን አይነት ሰቆቃ እንደሚያሳልፉ ቦታው ያለን እስኪመስለን ያሳየናል። ሲያዝኑ አብረን እንድናዝን ሲከፉ አብረን እንድንከፋ የሚያደርግ አስማታዊ አጻጻፍ አለው። የሰው ልጅ የትዕግስት ልክ የጽናት ጥንካሬ እስከምን እንደሚዘረጋ ስናይ ይደንቀናል።  ሚስቱ እና ልጆቹ በጨካኝ ወታደሮች እጅ የወደቁበት ወታደር ልቡ ምን ያህል እንደሚታመም ... ናፍቆት እንዴት እንደሚያቆስለው ከእውነተኛው ታሪክ በብዕሩ ተቀንጭቦ ስናነብ እናዝናለን። ለዓላማ ከሚከፈል መስዕዋትነት ትንሽ እርምጃ ራቅ ብሎ አሸናፊነት እንዳለ ስንገነዘብ ... አንዳንዱ ምነው ባልሞተ እና የድል ጣፋጭ ጽዋን ቀምሶ በነበረ ብለን እንመኛለን። በስተመጨረሻ የኦጋዴን በረሃ ጀግኖች ጽናት ያልተነገረ ያልተዘከረ ታሪካችን ሆኖ እናገኘዋለን። ድንቅ ታሪክ፣ ፅኑ ልብ፣ አይበገሬ መንፈስ፣ ጀግና ትውልድ፣ ናፍቆት እና መስዋዕትነት ... ሁሉን በውብ አጻጻፍ ከጀግና ወጣት ታሪክ ጋር ጣምራ ጦር ውስጥ እናገኛለን። አንብቡት። ጋበዝኳቹ። Pdf ከስር ይለቀቃል። Nova.
0
13
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ የምወደው ጥቅስ አለ! " ላለው ይጨመርለታል። ለሌለው ግን ያው ያለውም ይወሰድበታል። " .
0
14
[የታላቆችን ታላቅነት፥ የተሻገረው ታላቅነት] በምድር ታሪክ ውስጥ ብዙዎች የአማልዕክት ልጆች፥ ከሞት እንደሚነሱ በማወቅ ስለሰው ልጆች ሙተዋል፥ ተሰቅለዋል፥ ምናልባት ተከትፈውማል። አንዳንዶቹም ስለነገዋ የገነት ፀሃይ ዛሬ በሞት ጥላ መካከል አልፈዋል፥ እንደድንች ተልጠው፥ እንደሽንኩት ተከትፈዋል፥ በአውሬ ገደል ተጥለው፥ በአሲድ መፍጫ ተፈጭተዋል፥ በንፍር ውሃ ተቀቅለው፥ በሚንቀለቀል እሳት ተጥለዋል፥ ሁሉም ከሞት በላይ አንስቶ የክብርን አኪሊል የሚያቀናጃቼውን ታላቅ ህልው በመተማመን። በኮሚኒስት ሰፈር፥ በዲያሌክት መንደር ሞትን ኦሜጋ አድርጎ በማይነሱበት፥ ስለአንዱ ነፃነት ህይወቱን የሰጠ፥ የታላቆችን ታላቅነት የአዳኞችን አዳኝነት ወዲያ ጥሎ ያሳፈረ እነሆ የዛሬ 94 አመት ኤርኔስቶ 'ቼ' አለ። ቼን አንተ አዳኝ ነህን ስንለው መልሱ ቀላል ነበር እንዲህ ይለናል፥ በነፃአውጭነት መንፈስ ሳይኮፈስ... " I am not a liberator. Liberators do not exist. The people liberate themselves" ቼ ለእምነቱና፥ ለአመለካከቱ ፥ ለ'እውነቱ' የፀና ብረት ነበር። እውነትም ከታላቁ ስር ፊደል የቆጠረ የካስትሮ የመንፈስ ልጅ ነበር። ሁሌም 'Better to die standing, than to live on your knees' በሚለው ሃሳቡ እንደፀና፥ ተንበርክኮና ተዋርዶ ከመኖረን፥ ለሃሳቡ ፀንቶ ሞቱን መረጠ። ረስልን ስለዚህ ጉዳይ ብጠይቀው እንደ ፖሲፊስትነቱ 'እኔ ስለእምነቴም ሆነ ፥ ስለአቋሜ አልሞትም ስህተት ልሆን እችላለሁና' ቼ ግን የነፃ አውጭወችን፥ ሞት ከንቱ ሊያደርግ፥ ለሃሳቡ ሊሞትና በልባችን ፅላቱን ለማኖር እነሆ ዛሬ ተወለደ። ሊዩ ሳቅ፥ ከልዩው 'ቼ' © Sad Jonahist [Jun 14, 2022 ]
0
15
没有文字...
0
16
እስከ ቅርብ ጊዜ በጣም sociable ነበርኩ። ሰዎችን የመግባባት ምንም አይነት ችግር የለብኝም። ሰዎች በቀላሉ ይወዱኛል ያምኑኛል። የማንንም ሰው እምነት አጉድዬም አላውቅም። ከሁለት ዓመት ወዲህ ግን ሰው የመጨረሻ ነው የጠላሁት። ብቸኝነት ውስጥ ያለው ሰላም ያስደስተኛል። እውነተኛ ሕይወት ከራስህ ጋር ስትኖር ያለው ነው። አንዳንዴ ነገሮች ከባድ በሚሆኑበት ጊዜ አይዞህ የሚል ሰው እፈልጋለሁ። ከመቅጽበት ግን ይህ አይበገሬ መንፈሴ ኖቫ ሰው ተደግፈህ የምትቆም አይነት ሰው አይደለህም። የምን መልፈስፈስ ነው የሚል ድምፅ ያሰማኛል። ብቻዬን መሆን ... ከሰው በሸሸሁ ቁጥር ነው ሰላም ያገኘሁት። ልቤ ውስጥ ያለውን እሳት ያረገብኩት በብቸኝነት ጥላ ስር ተቀምጬ ነው።
0
17
ሶስቱ የእውቀት ደረጃዎች ----- • በመጀመሪያው የእውቀት ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ሁሉንም ነገር ያወቀ ይመስለዋል፡፡ • በሁለተኛው ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው የማወቅ ጉጉቱ በጣም ይጨምራል፡፡ • ሶስተኛው ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ግን ምንም ነገር እንደማያውቅ ይረዳል፡፡ ---- (ኢማም አቡ ሓሚድ አል-ጘዛሊ)
0
18
ሰንደል ሲያቃጥሉት መልካም ሽቶ ወጣው፤ ብረት ሲያቀልጡት ጠነከረ፤ የረጋ ውሃ ሳይሆን ትልቅ ማዕበል ብርቱ ዋናተኛን የሚፈጥረው፤ ጀግና በጦርነት መሃል ነው ሚወለደው። መቃጠልን፣ መቅለጥን፣ መገፋትን አትፍራ። መከራን ያሳወቀን ጦርነት ጠቀመን። ችግርን ያስለመደን ስደት ምስጋና ይገባው። ፅናትን ከነርሱ ተማርን። 📚 ርዕስ፦ ሶባሐል ኸይር ✍️ ፀሃፊ፦ ሙሐመድ ስዒድ
0
19
I need some reaction to my Birthday. ዛሬ እናቴ የመጀመርያ ልጇን ያገኘችበት እኔም የተወለድኩበት ቀን ነው። 22/9♊️
0
20
I can't😂😂
I can't😂😂
0