ch
Feedback
ከእንቁ በላይ

ከእንቁ በላይ

前往频道在 Telegram

ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል?? ልባም ነሽ? ልባምነት ምንድነው? ሴት በመሆንሽ ብቻ ልዩ ነሽ አታስቢ ልባምነት ምን እንደሆነ በዚህ channel በደንብ እናያለን።

显示更多
未指定国家未指定类别
197
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
"10፤ ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል። " (መጽሐፈ ምሳሌ 31:10፤)

ከእንቁ በላይ..... ሻሎም ውድ እህቶቼ የጌታ ሰላም ባላችሁበት ቦታ ይድረሳቹ ዛሬ ደ'ሞ ጌታ ፈቅዶ ስለ አንዲት ልባም እና ከእንቁ በላይ የሆነች ሴት ልንማር ነው። ዝግጁ? በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በሴት ስም የተፃፉት መፀሐፍት ሁለት ናቸው እነሱም የሩትና የአስቴር መፅሀፍ ሲሆኑ ዛሬ ከአስቴር ልንማር ከምንችለው ጥቂቱን ልበላቹ። የአስቴርን ታሪክ ሁላችንም የምናውቅው እና ብዙ ጊዜ የሰማነው ታሪክ እንደሆነ አልጠራጠርም። አስቴር ህዝበዋን(አይሁዳዊያንን) ልትታደግ የቻለች ጀግኒት እና የእግዚአብሔር ሞገስ ያላባት ልባም ነች። በምእራፍ 1፥18 ላይ እንደምንመለከተው ንግስት አስጢን የንጉሱን ታዛዝ ስላልተቀበለች ንግስናዋን ከእሷ ለተሻለችው እንድታሰረክብ የሚያደርግ ህግ ሲደነገግባት እናያለን። አስቴር ንግስት አስጢንን ተክታ ሳይሆን ንግስት የሆነችው ከንግስት አስጢን ተሽላ የተገኘች በመሆኗ ነው። ከሰነፍ ሴት ተሽላ ተግኝታለች-አስቴር። ምእራፍ 2፥13 ላይ እንደምንመለከተው አስቴር በንጉሱ ፊት ወድያው ሞገስ አገኘች ይላል። አስቴር የተመረጠችው ቆንጆ ስለሆነች ሳይሆን ሞገስ ስለነበራት ነው። ይሄንን ደሞ በዚሁ ምእራፍ የመጀመርያ ቁጥሮች ላይ ለንግስና የተሰበሰቡት ሴቶች ሁሉ መልከ መልካምና ቆንጆ እንደሆኑ ስለሚናገር መረዳት እንችላለን። አስቴርን ያስመረጣት ከሁሉ የሚበልጠውና የሚማርከው ውጫዊ ውበቷ ሳይሆን ሞገሷ ነበር። አስቴር ያገኘችው ሞገስ በንጉሱ ፊት ብቻ የሚታይ ሳይሆን በሚያዩኣት ሁሉ ዘንድ የነበረ ነው።(2፥15-17) ንጉሱም አስቴርን ስለወደዳት የመንግስቱን ዘውድ በራሷ ላይ አደረገ። አስቴር:- 1-በምርኮ ሀገር የምትኖር አይሁዳዊ 2-እናትና አባቷ ያላሳደጓት በመርደኪዮስ እጅ የደገች ሴት ነበረች። 3-በሁሉ ፊት ንጉሱንም ጨምሮ ሞገስና መወደድ ያገኛች ልባም ሴት ነበረች። 4-የንጉስን ትእዛዝ የናቃችውንና ለብዙ ሴቶች መጥፎ ምሳሌ ከምትሆነዋ አስጢን ተሽላ የተገኘች ሴት ናት። የአስቴር ለንግስና መመረጥ በሷ ላይ ከነበረው ሞገስ የተነሳ እንጂ በውጫዊ በሚታየው ነገ በሚጠፋውና በሚረግፈው ውበት አይደለም። የተመረጥሽው በምንሽ ነው? ሰዎች ፊት መወደድ አለሽ? ካለሽ ይሄን መወደድ ከምን የተነሳ ነው ያገኘሽው? መወደድ መልካም ነገር ሆኖ ሳለ የተወደድንበት ነገርና መንገድ ግን ህይወታችንን እንኳን ሊያጠፋ ይችላል። ውጫዊ ዉበትሽን አይቶ የወደደሽ ይሄ ውበትሽ ሲጠፋ ይጠላሻል። ( ኢሳይያስ 40፥7:-ሳሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል። ) በውጫዊ ውበት መወደድ የምትሺ እና ያ ደሞ ልክ እንደሆነ የምታስቢ ከሆነ አንቺ ልባም አይደለሽም! (ምሳሌ 30፥31:-ውበት ሀሰት ነው ደምግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች።)ውበትም ሞገስም መወደድም በጌታ ነው። ይቅጥላል... For any comment @sumuniye Share the below links for ur friends and sisters @libamset @libamset @libamset Forward it please🙏🙌🙌🙌

Ifa kee fi dhugaa kee ergi, isaan anatti karaa haa argisiisan; tulluu kee isa qulqulluutti, iddoo buufata keettis ana haa geessan! 4 Gara iddoo itti Waaqayyoof aarsaa dhi'eessanii, gara Waaqayyoo isa ani itti gammaduu nan dhaqa; kiraaraanis sagalee gammachuu dhageessisee sin jajadha, yaa Waaqayyo, yaa Waaqayyoo ko!

ሰላም ይብዛላቹ ልባም ሴት ምሳሌ ልትሆን የምትችል ሴት ናት። ሁሉም ሰው ልባምም ሆነ ሰነፍ የሚወክለው ምሳሌ ይኖረዋል። ሰነፎች በስንፍናቸው ምሳሌ መሆን ሲችሉ ልባሞችም በልባምነታቸው ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ። አብዛኛው ሰው በብዛት የሚከተለው (role model) አድርጎ የሚያስቀምጠው ሰው ይኖረዋል። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በስንፍናዋ ምሳሌ ሆና ከተጠቀሱት ሴቶች መካከል ዛሬ አስጢንን እንመልከት። አስጢን ማን ናት? እንዴትስ በስንፍናዋ ልትጠራ ቻለች? ንጉሱ አርጤክስስ ይገዛ በነበረበት ዘመን አስጢን የንጉስ ሚስትና ንግስት ነበረች።(መጽሐፈ አስቴር 1፥10-13) በክፍሉ ላይ እንደምንመለከተው ንጉሱ ብዙ የወይን ጠጅ ባበዛ ጊዜና ልቡ እጅግ ደስ ባለው ጊዜ የሚስቱን ዉበት ሌሎች እንዲመለከቱለት በመሻት ለንግስቷ ትእዛዝ አስተላልፏል። ቢሆንም ንግስት አስጢን የንጉሱን ትእዛዝ ቸል ስትልና አልቀበልም ስትል እንመለከታለን።በዚህን ጊዜ የንጉሱ ቁጣ በአስጢን ላይ ስለነደደ አማካሪዎችን ጠርቶ ምን አይነት ቅጣት ልትቀጣ እንደሚገባ ከጠየቃቸውና ከተማከሩ በኋላ ንግስቲቱ ከንግስናዋ እንድትሻርና በርሷ ፋንታ አሷን ተክታ ንግስት የምትሆን ሴት በሀገሪቷ እንድትፈለግ ይደረጋል። ንግስት አስጢን እጅግ ውብ ነበረች ነገር ግን በንግስናዋ ልትቆይ አልቻለችም። ለምን? 1-የንጉስን ትእዛዝ ስለተላለፈች። የንጉስን ትእዛዝ መተላለፏ ይሄን ሁሉ ቅጣት ለምን አደረሰባት? (አስቴር 1፥16-21) ንግስቲቱ ትእዛዝ በመተላለፏ ንጉስን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ሰው የበደለች ነበር። ምክንያቱም የንጉስን ትእዛዝ እንደናቀች የሰሙ ሴቶች ከሷ የሚማሩት የተሳሳተ ትምህርት ይኖራልና። 1-በሌሎች ሴቶች ዘንድ ባሎቻቸው በአይኖቻቸው ፊት የተናቁ ይሆናሉ። 2-ነገሩ በተሰማ ጊዜ ንቀትና ቁጣ ይበዛል። የንግስት አስጢን ንጉስን አለመታዘዟ እኚህን መልካም ያልሆኑ ነገሮች ያስከትላል። ይሄ ማለት በሃገሪቱ ያሉት ሴትች ከሷ የሚማሩት መልካም ነገር ሳይሆን ክፉውን ነገር ነው። በዚህ ምክንያት ነበር ንግስት አስጢን የስንፍና ወይም የሰነፍ ሴት ምሳሌ ሆና ልትነሳ የቻለችው። ባለመታዘዟ ብቻ? አለመታዘዝ እኮ መብቷ ነው ይሄ ትክክለኛ ፍርድ አይደለም መብቷን መጋፋት ነው ምናምን የሚባል ሃሳብ ሊነሳ ይችላል ነገር ግን እውነታው አንድ ነው:- አግዚአብሔር ከኛ ታዛዥነትን ይፈልጋል።(1ኛ ሳሙ.15:22) አለመታዘዟ መጥፎ ምሳሌ እንድትሆን ያደረጋት ንግስት ንግስናዋንም ያጣችው እና ስፍራዋን ሌላ ሰው እንዲተካ የተደረገው ባለመታዘዟ ነበር። ንግስትነቷን እንድታጣ መደረጉ:- *ሴቶች ሁሉ ባሎቻቸውን ታናሹንም ታላቁንም እንዲያከብሩ ያደርጋል። ሌሎች ሴቶች ካንቺ ምን እየተማሩ ነው? በተቀመጥሽበት ስፍራ መሆን የሚገባሽን ሆነሻል? የምን ምሳሌ ነሽ? የሰነፍ ወይስ የልባም ሴት? @libamset @libamset For comment @sumuniye

"1፤ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ሰማኝም። " (መዝሙረ ዳዊት 120:1፤)

(የሐዋርያት ሥራ �?ዕራ�?? 9) ---------- 32፤ ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ። 33፤ በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ። 34፤ ጴጥሮስም። ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ አለው። 35፤ ወዲያውም ተነሣ። በልዳና በሰሮናም የሚኖሩ ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ዘወር አሉ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ የሚሰራው ስራ ሁሉ ሰዎች ፊታቸውን ወደ ጌታ ዘወር እንዲያደርጉ እንጂ ለኛ ክብርና ዝና መሆን የለበትም። በሁሉ በኩል የሰዎችን ትኩረት ወደ ኢየሱስ እንጂ ወደ ራስህ/ሽ እንዳይሆን ተጠንቀቅ/ቂ። "ዋጋችንን በምድር እንዳንቀበል!"

(መጽሐፈ ኢዮብ �?ዕራ�?? 2) ---------- 9፤ ሚስቱም። እስከ አሁን ፍጹምነትህን ይዘሃልን? እግዚአብሔርን ስደብና ሙት አለችው። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው) ዳግመኛ እግዚአብሔርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠናዋለሁ፤ ዳግመኛም መከራውን እታገሠዋለሁ፥ የቀድሞ ኑሮዬንም ተስፋ አደርገዋለሁ ትላለህን? አለችው። እንደዚህሳ እንዳትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠራርህ ጠፋ፤ ሴቶች ልጆቼና ወንዶች ልጆቼም ሞቱ እኔስ ዘጠኝ ወር ሳረግዝ ሳምጥ ስወልድ ሳይረቡኝ ሳይጠቅሙኝ በከንቱ ደከምሁ አለች። አንተም በመግል ተውጠህ በትል ተከብበህ ትኖራለህ፤ ሌሊቱን ሁሉ ስትዛብር ታድራለህ። እኔ ግን እየዞርሁ እቀላውጣለሁ። ከአንዱ አገር ወደ አንዱ አገር ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት እሄዳለሁ፤ ከድካሜ በእኔ ላይ ካለ ከችግሬም አርፍ ዘንድ ከጧት ጀምሮ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ እጠብቃለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔርን የማይገባ ቃል ተናግረኸው ሙት አለች። 10፤ እርሱ ግን አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን? አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።

ስንቶቻችን ነን ህይወት ባስጠላን ቁጥር መኖርን ባንገሸገሸን ልክ ተስፋችንን ባጣን ጊዜያት ሁሉ እግዚአብሄርን ለመሳደብ የደፈርን? "እግዚአብሄርማ እኔን አያስታውሰኝም እሱማ ለሌሎቹ እንጂ ለኔ መች ራርቶ ያውቃል? እሱ እኔን አይወደኝም፣፡እኔን ረስቶኛል፣እሱም እንደሰው ያዳላል፣እግዚአብሄር የለም..." እስከማለት ያደረስሽ ችግር ይኖር ይሁን? እግዚአብሄር ያልሆነውንና ያላደረገውን ነገር ነው ብሎ መፈረጅ በራሱ የሱን ቃል መጻረር ስልሆነ ይሄም ስድብ ነው። ያም ሆነ ይህ እንዲህ ባስባለሽ ነገር ሁሉ ላይ ግን እግዚአብሄር መልካም ነው። የእግዚአብሄርን መልካምነት በስኬቶቻችን ግዚያት ብቻ መናገር ያለብን ጉዳይ ሳይሆን በህይወት ዘመናችን ሁሉ ልናስተውለው የሚገባ ጉዳይ ነው። #ተስፋ ቆርጠሻል? #ረዳት አጥተሻል? #ሁኔታው ከባድ ነው? #መኖርሽን ጠልተሻል? እግዚአብሄር ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ መንገድ አለው። ለሚያልፍ ቀን ያማያልፍ ቃል አትናገር እንደሚባለው ለሚያልፍ መከራና ችግር የስንፍና ንግግር ባንደበትሽ አይገኝ! ለኢዮብ ከ41 የህይወት ምእራፍ ጉዞ በኋላ ምርኮ እንደተመለሰለት ያንቺም የምርኮ ጊዜ እንደሚመጣ አምነሽ ልባም ሁኚ። "ተሳድበሽ የስንፍናን ምክር መክረሽ ሰነፍ ከመሆን እራስሽን ጠብቂ።" "አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበም። ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና።"ገላቲያ6፥7 ሰነፍ ከመሆን ተጠበቂ። @sumuniye for comment @libamset @libamset ☝️☝️join for more

ሰላም የጌታ ፀጋና መንፈስ ባላችሁበት ቦታ ከእናንተ ጋር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱሳችን ስለ ልባም ሴት ብቻ ሳይሆን ስለ ብዙ ሰነፍ ሴቶችም ጭምር ያስተምረናል። ብልህ የሆነ ከልባሟ ሴት ብቻ ሳይሆን ከሰነፏም ሴት ይማራል። አስተውይ:-'ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል ሞኝ ከራሱ ስህተት ይማራል።' ከሰነፏ ሴትም መማር ይቻላል። ዛሬ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ሰነፍ ተብለው ከተጠሩት ሴቶች መካከል ስለ አንዷ እንማረለን። ይህቺ ሰነፍ ሴት የኢዮብ ሚስት የነበረች ናት። በመጽሐፈ ኢዮብ 2፥9 ጀምሮ እንደተገለጸው ይቺ የኢዮብ ባለቤት ለባሏ መጥፎ ምክርን በመምከሯ ሰነፍ ልትባል ችላለች። ኢዮብ እግዚአብሔርን እንዲሰድብ ከመናገሯ በፊት የኢዮብ ሚስት እንዲህ ያለ ድፍረት ውሳጥ እንድትገባ ያደረጋት ምን እንደነበር እንመልከት። የኢዮብ ሚስት የገባችበት የህይወት ውጥውረድ እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ያደረገችው ነገር ወይም የተናገረችው ንግግር በሰውኛ ሲታሰብ "እውነቷን ነው ምን ታድርግ ታድያ? አይፈረድባትም ልክ ናት"ምናምን የሚያስብል ቢሆንም እውነታው ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር ሲታይ ያ አይደለም። ኢዮብና ባለቤቱ ከምእራፍ 1፥ 14ጀምሮ እንደምንመለከተው በጣም ከባድ በሆነ ኑሮ ውስጥ ወይም የህይወት ውጥውረድ ውስጥ ያሳለፉ ናቸው። ያላቸውን ሀብትና ንብረት ባንድ ቀን ውስጥ ከማጣታቸውም በላይ 10 ልጆቻቸውን ባንድ ቅጽበት ውስጥ ያጡ ቤተሰቦች ናቸው። ላንዲት እናት ባንድ ጊዜ ውስጥ 10 ልጆቿን ማጣት ማለት ምን ያክል ሊከብድ እንደሚችል መገመት ቀላል ነው ብለን የምናልፈው ጉዳይ ሳይሆን ካልደረሰብን በቀር ልንረዳው የምንችለው ጉዳይ አይደለም። አንዲት እናት 1 ልጇን ብታጣ ልቧ ከመሰበሩ በላይ ከማዘኗም በላይ አእምሮዋን እስከመሳትም ልትደርስ ትችላለች ጌታ ካልረዳት በስተቀር ደግሞ እራስን እስከማጥፋት ድረስ እርምጃ የምትወስድ ሴት ጥቂት አይደለችም። ለኢዮብ ሚስት የቀረላት መጽናኛ ቢኖር አንድ ባሏ ብቻ ነው። በምእራፍ 1 ውስጥ የኢዮብ ሚስት ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደነበረች ምን እንደተናገረች እንዴት እንዳሳለፈች የተገለፀልን አንዳች ነገር ባይኖርም በምእራፍ 2 ውስጥ ግን ሁሉ ነገር ከአቅሟ በላይ ሆኖባት እግዚአብሔርን ተሳደብ ብሎ እስከመናገር የሚያደርስ መከራና ችግር ውሳጥ እንዳለች ማወቅ ይቻላለ። #ሃብትና ንብረቷን በሙሉ አጥታለች #ልጆቿን አጥታለች #ባሏ በከባድ ቁስል ተመቷል ኢዮብ ከደረሰበት መከራ የተነሳ (ቁስሉ እስከሚተላ ድረስ) ሚስቱ ለሱ *መድሃኒት ፍለጋ ልትንከራተት ትችላለች *ሁልጊዜ ያዘነች ናት *መኖሯ ሰቀቀን ሆኖባታል *ተስፋ አጥታለች ይሄ ሁሉ ነገር ሲደራርብባት እግዚአብሄርን መሳደብ እንደ መፍትሄ የቆጠረች ሴት ናት:-የኢዮብ ሚስት።

"3፤ የወደደውን ሁሉ ያደርጋልና ከፊቱ ትወገድ ዘንድ አትቸኵል፥ ክፉንም በማድረግ አትጽና። " (መጽሐፈ መክብብ 8:3፤)

3- ተማርሽ? 1-ቅድስት እንደነበረች 2-ጸጋን የተሞላች እንደነበረች 3-ታዛዥ እንደነበረች 4-መንፈስ ቅዱስ ያድርባት ወይም ይሰራባት እንደነበር 6-ትውልድ ሁሉ ከሷ የሚማር ምርጥ ምሳሌ የምትሆን ሴት እንደሆነች. . . . ልባም መሆን ትፈልጊያለሽ? ጌታ የተማርነውን እንድንተገብረውና እንድንኖርበት ፀጋውን ያብዛልን። ጌታ ልባም ሴት ያርግሽ ትውልድ ካንቺ ህይወት መልካምን ነገር ይማር እንደማርያም የተቀደስ ህይወት ይኑርሽ አንደበትሽ ምስጋናውን ለመናገር የተከፈተ ይሁን ቤተሰብሽን ጓደኛሽን ያንቺ የሆነው ነገር በሙሉ በደሙ ይሸፍንልሽ ዘመንሽ በቤቱ ይለቅ አሜን። ተምረሽበታል? ተባርከሽበታል? ፡አንተስ? ሃሳባችሁንና አስተያየታችሁን በ @sumuniye አድርሱኝ። እህታቹ ሜላል ነበርኩ።በጣም እንደምወዳቹ ደሞ አትርሱ ተባረኩልኝ። መልካም በአል ላንተም ላንቺም ለኔም ለሁላችንም!

የቀጠለ... መጽሀፍ ይነግረናል። በፍቅር ህይወትሽ ወይም ከትዳር በፊት ባለሽ ህይወት ምን ያክል የተቀደሽና እራስሽን የጠበቅሽ ነሽ? በፍቅር ህይወት ሊኖርሽ የሚገባ ቅድስና ምን እና እስከምን ድረስ ነው? መሳሳም(kissing)፡መዳራት፡ዝሙት፡ዘፈን፡ቅንአት፡ጥል፡ክርክር፡ርኩሰት...ወዘተ የፍቅር ህይወትሽን ቅድስና የሚያጎድሉ ነገሮች ወይም የስጋ ስራዎች ናቸው። እርግጥ ነው አንዳንዱ ላይ ሃጢአት ነው አይደለም የሚል ክርክር አለ። በሰፊው ሌላ ጊዜ ብመለስበትም በጥቂቱ ግን ለማንሳት ልሞክር፥- ከፍቅረኛሽ ጋር ሆነሽ የፍቅር ዘፈን ትስሚያለሽ? ወደማይሆን እርምጃ የሚውስድሽ አይነት ቅንአት አለብሽ? በመካከላቹ ጥል አለ? መሳሳምን እንደ ትክክለኛ ነገር ቆጥረሽ ወደ ተግባር ገብተሻል?(ከወንድሞች ጋር በተቀደስ አሳሳም ሰላምታ ተሳጣጡ)። ማርያም ቅድስት ናት ሲለን ፍቅረኛ (እጮኛ) እያላት ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ሁሉ እራሷን ጠብቃለች ማለት ነው። ለዚህም እኮ ነው እጮኛዋ ዮሴፍ ሊያሳፍራት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ የሚለው። ይሄ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሻል? ዮሴፍ ማርያም ከርሱ ጋር በነበራት የፍቅር ህይወት ቅድስት እንደሆነች ያውቅ ስለነበር ነው። ማርያም የተቀደስች እንደነበረች የሚያሳየን ወይም የሚያረጋግጥለን 1-መልአኩ ገብርኤል 2-ዮሴፍ እጮኛዋ 3-ኤልሳቤጥ ዘመዷ 4-ማርያም እራሷ ናት። ከማርያም ሌላ የምንማረው ነገር ፀጋን የተሞላችና ታዛዥ የነበረች መሆኗን ነው። "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደቃልህ ያርግልኝ" ስትል ለማመንና ለመቀበል የሚከብደውን የመልአኩን መልእክት ተቀብላለች። አስተውይ ዘካርያስ የኤልሳቤጥ ባል ግን የመልአኩን ቃል ባለመቃበሉና በመከራከሩ ምክንያት ለ9 ወር ከ2 ሳምንት ዲዳ ሆኗል ማለትም ዮሐንስ እስከሚወልድ ድረስ! ልባም ሴት መሆን ትፈልጊያለሽ ልክ እንድ ማርያም? እንግዲያውስ ታዛዥ ሁኚያ! ለጌታ ቃል፡ለቤተሰቦችሽ፡ለታላላቆችሽ እንዲሁም ለታናናሾችሽ፡ለቤ/ክ፡ለጓደኞችሽ... አሁንም አስተውይ መታዘዝ ከመስዋእትነት ስለሚበልጥ ነው ማርያም ልባም ሴት ልትሆን የቻለችው። ማርያም ፀጋን የተሞላች ከመሆኗም በላይ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁሌ የተገናኘች መሆኗን የምትረጂው ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስን እንደተሞላች ስትመለከቺ ነው! ሰዎች ያንቺን ሰላምታ ሲሰሙ መንፈስ ቅዷን ይሞላሉ ወይስ? ለምን? አንቺ የክርስቶስ ልጅ ከሆንሽ መንፈስ ቅዱስ በውስጥሽ ካደረ ሰላምታሽ ለሰዎች ለምን ፈዋሽ አይሆንም? የነጳውሎስ ጥላ ይፈውስ እንደነበር አትርሺ! ማርያም ለአምላኳ በሚገርም ቅኔ ዝማሬንና ውዳሴን አምልኮን ያቀረበችም ሴት ናት። አንቺስ? ዛሬ ከልባሟ ከብጽእቷ ከቅድስት ማርያም ምን

ሻሎም ልባም እህቶቼና ወንድሞቼ ባላችሁበት ቦታ ሁሉ የጌታ ፀጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን። በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለቤዛችን ለካህናችን ለጠበቃችን ለአባታችን ላፍቃሪያችን ... በቃ ባጠቃላይ ሁሉ ነገራችን ለሆነው ለኛ ሲል ክብሩን ጥሎ ስጋ ሆኖ ራሱን ባዶ አድርጎ ዝቅ ብሎ በረት ውስጥ ተወልዶ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ለወደደን ለጌታችንና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በኣል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን። አሜን። ወደ ዛሬዋ ልባም ሴት ከማለፌ በፊት የኢየሱስ ክርስቶስን ልድት በኣል ስናከብር አብዛኞቻችን ጋር ያለውን ስህተት ለማስተካከል ልሞክር። የኢየሱስ ክርስቶስ እድሜ እኛ እንደምንለውና እንደምናስበው 2013 ወይም 2021 አመቱ አይደለም። በጭራሽ! አቆጣጠሩ ልክም ይሁን የተሳሳት ዛሬ የምናክብረው የገና በኣል የጌታን እድሜ የሚነግረን ሳይሆን በእናቱ በቅድስት ማርያም ተፀንሶ ወደ ምድር ከመጣና የሰው ልጆችን አበሳና ኩነኔ አስቀርቶ ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን ካሻገረን 2000 እና ከዚያ በላይ ዘመናት መቆጠሩን ነው የሚገልፅልን! ጌታ ኢየሱስ ከመወለዱም በፊት የነበረ ዘልአለምን የፈጠረ ከአብ እና መንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ አምላክ ነው። የወደደን የመረጠን የተወለደልን ጌታ ስሙ ለዘልኣለም የተባረከ ይሁን። አሜን። ለ30! ሰከንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶ ባይሆን ኖሮ፡ምን ልትሆኚ እንደምትችይ ቆም ብለሽ አስቢ እስቲ! የዛሬዋ ልባም ሴት ማን ልትሆን እንደምትችል መገመት የሚያቅትሽ አይመስለኝም። . . . ልባሟ ሴት ቅድስት ማርያም ናት! ቅድስት ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ልባም ከመሆኗም በላይ እስከዛሬ ድረስ ትውልድ ሁሉ ብጸእት ብሎ የሚጠራት ድንቅና እጅግ አስገራሚ የእግዚአብሔር ፀጋ የበዛላት ለሁላችንም ምሳሌ መሆን የምትችል ሴት ናት! አዳምና ሔዋን አትብሉ የተባሉትን ፍሬ በመብላታቸው ምክንያት ሃጢአት ወደ ሰው ልጆች ሁሉ ደርሷል። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በሴቲቱና በእባቡ መካከል ጠላትነትን አደረገ በዘሩና በዘሯም መካከል። እግዚአብሔር ከዘሯ(ከሴቷ) የሚወጣው የእባቡን አናት እንድሚቀጠቅጥ እንደተናገረው ከብዙ ሺህ አመታት በኋላ በማርያም በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ። ከላይ እንዳነበብነው ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስን ሳትፀንስ በፊት ለእጮኛዋ ለዮሴፍ ታጭታ እንደነበር ነው። በዚህ ውሳጥ አንድ ነገር ልብ እንበል እህቴ ትኩረትሽን ወደዚህ፥- ማርያም ታጭታ ነበር ማለት ፍቅረኛ ከዚያም አልፎ እጮኛ ነበራት ማለት ነው። ከማርያም ህይወት መማር ያለብን ትልቁ ነገር ይሄ ይመስለኛል። በእጮኝነቷም ሆነ ከዚያ በፊት በነበራት ህይወት የተቀደስች እንደነበር መ

(የሉቃስ ወንጌል �?ዕራ�?? 1) ---------- 26፤ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ 27፤ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። 28፤ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። 29፤ እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች። 30፤ መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። 31፤ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። 32፤ እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ 33፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም። 34፤ ማርያምም መልአኩን። ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው። 35፤ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። 36፤ እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ 37፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። 38፤ ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ። 39፤ ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥ 40፤ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት። 41፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ 42፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። 43፤ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? 44፤ እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። 45፤ ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት። 46፤ ማርያምም እንዲህ አለች። 47፤ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ 48፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ 49፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። 50፤ ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። 51፤ በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ 52፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤ 53፤ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። 54-55፤ ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።

#ልባም ከእንቁ ትበልጣለች! ከእንቁ በላይ ከሆንሽ እንዴት ለፈለገሽ ሁሉ የምትገኚ ቀላል ሴት ትሆኚያለሽ? የትኛው የከበረ እንቁ ነው በየሰው ቤት ሁሉ ያለው? የትኛው የእንቁ አይነት ነው በቀላሉ በየሰው እጅ የሚገኘው? ለፈለገሽ ሁሉ በቀላሉ የምትገኚ ከሆን አንቺ እንቁ ሳትሆኚ አርቴፊሻል ነሽ ማለት ነው! አዎ ሁሉም ሰው ጣት ወይም እጅ አልያም አንገት ላይ የሚገኘው አርቴፊሻል እቃ እንጂ የከበረ እንቁ አይደለም? ዳይመንድ ቀይ እንቁ በስንት ሰው ቤት አለ? ሁሉ ጋር የምትገኚ ርካሽና አርቴፊሻል እምዳትሆኚ እኮ ነው እግዚአብሔር "ልባምን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ እንቁ ይልቅ እጅግ ይበልጣል" ምሳለ 31፥10ያለው! ማን ሊያገኛት ይችላል ሲል ሁሉም ጋር የማትገኝ መሆኗን ነግሮናል። ከቀይ እንቁ ይበልጣል ሲል ቀይ እንቁ ከሚያስወጣው ብርና ሀብት በላይ አንቺ ውድ ነሽ ማለት ነው። እና እንደዚህ ከሆነ ብር እንዴት ያታልልሻል? አንቺ እንቁ ከሆንሽ ወርቅ እንዴት ልብሽን ይሰርቃል? በገንዘቡ ልክ ተምኖ ሊገዛሽ የሚፈልግ ወንድ እንዴት ሊያገኝሽ ቻለ??? እንቁነትሽን ጥለሽ ከሆነ እራስሽን ፈትሺ! እራስሽን ካስቀመጥሽበት ሚዛን ውረጂ አይመጥንሽምና! ልባም ሴት መሆን ትፈልጊያለሽ? እንግዲያውስ እንደ ሸቀጥ እዚም እዚያም አትገኚ! "በብርቱ ይፈልጓችኋል ግን ለመልካም አይደለም በብርቱ ትፈልጓቸው ዘንድ በውጪ ሊያስቀሯቹ ይፈልጋሉ" ገላቲያ 4፥17 ባስቸኳይ የፈለገሽ ለምንድነው? አጥብቀሽ ልብሽን ጠብቂ የህይወትሽን መውጫ ስታጠብቂ ነው ልባም ምትሆኚው ልብሽን ሳታጠብቂ ልባም እሆናለሁ ማለት ጤፍ ዘርቶ ስንዴ ለማጨድ መጠበቅ ማለት ነው! ተጠንቀቂ! @libamset @libamset እህትና ጓደኛሽን invite አርጊን ልባም አርጊያቸው። ፀጋው ይብዛልሽ ! For any comment @sumuniye

ሃሳብና አስተያየታችሁን በ @sumuniye ልታደርሱኝ ትችላላቹ ተባረኩ

ብዙውን ጊዜ ስለ ኢዮስያስ ተሰብከን ወይም ተተምረን ሊሆን ይችላል ግን ስለ ልባሟ ሴት ስለ ሕልዳና ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? ከጥንት በነበረው የአስተሳሰብ ችግር ምክንያት ስለ ሕልዳናም ይሁን ስለ ሌሎች ብዙ ልባም ሴቶች መጽሓፍ ቅዱሳችን ብዙ ቢለንም ማንም ማለት በሚቻልበት ሁኔታ የእነዚህን ጀግና ሴቶች ታሪክ አይነገርንም አይወራልንም! ያሳዝናል 😔😔😔 ይሄን አስተሳሰብ እና ልምድ ግን እኔና አንቺ ከዛሬ ጀምሮ ሰብረን እግዜአብሄር እንድንማርባቸው ያስቀመጠልንን ሴቶች እያነሳን ከነሱ ህይወት ተምረን ለብዙዎች የሚሆን ትምርትን እና ህይወትን እናተርፋለን። እኔ አምናለው ነገ በዚህ ህብረት ከራሳችን ባለፈ ትውልድን ሁሉ ሀገራችንን እና አለማችንን እንደምንወርስ! አሜን ጌታ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! ወደ ትምህርቱ ከመግባቴ በፊት ስለ ሴትነት ትንሽ ልበላችሁ እስቲ ስንቶቻችሁ ናችሁ ሴት በመሆናቹ የምትናደዱት የምትበሳጩት እና የበታችነት የሚሰማቹ? ምነው ወንድ አድርጎ በፈጠረኝ ኖሮስ አላላችሁም? መልሱን ለእናንተው እኔ ግን ከልጅነቴ ጀምሮ ሴት በመሆኔ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። አሁን ደሞ ጌታ በሴትነቴ ምን ያክል ሊጠቀምብኝ እንደሚችል ሳስብ እና እውነቱ ሲገባኝ. . . የምገልጽበት ቃል አጥሮኝ ባይሆንም ከተረዳችሁት ይበቃል ብዬ ነው። ከላይ በ2ኛ ዜና 34፥21 ጀምሮ የእግዚአብሄር ቃል እንደሚናገረው ሕልዳና ኢዮስያስ በነገሰበት ዘመን የነበረች ሴት መሆኗን ነው። ከመሳፍንት ዘመን ጀምሮ የእስራኤል ህዝብ አምላኩን በመርሳት ፊቱን ወደ ጣኦት ያዞረበት ከባርነት ከግብጽ ምድር ያወጣውን አምላኩን የዘነጋበት ዘመን ነበር። ለተወሰኑ ኣመታት ሳይሆን አጅግ ለረዝም አመት የእስራኤል ህዝብ አምላኩን በድሎ ኖሯል። ምንም እንኳን በነዚህ ዘመናት መካከል ኣንዳንድ የእግዚአብሄርን ክብር ወደ ቤቱ ያስመለሱ ትውልድ ፊቱን ወደ አምላኩ እንዲያዞሩ ያደረጉ የጌታ ነቢያት ቢኖሩም የእስራኤል ህዝብ ግን በጌታ ላይ ልበ ደንዳና ሆኖ እናገኘዋለን። ከመሳፍንት ጀምሮ ስንቆጥር 2ኛ ዜና 8ኛው መጽሀፍ ነው። ማለትም መሳፍንት ሩት 1ኛ &2ኛ ሳሙኤል የነገስት መጽሐፍ እና ዜና አለ። ኢዮስያስ ከመንገሱ በፊት የጣኦት አምልኮ የተስፋፋው ነገስታት እንዲሁም ህዝቡ ልጆቻቸውን በእሳት ውስጥ ለጣኦቱ መስዋእት እስከማድረግ ነበር! ወደ ጌታ ዘወር ያሉ ነገስታት እንኳን አንካሳ ነበሩ። አንካሳ ያልኩት መንፈሳዊ አንካሳ ሰለነበሩ ነው ምክንያቱም እራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለጌታ አሳልፈው ሲሰጡ አንመለከትም። ከኣባቶቻቸው የወረሱትን ሃጢአት እየተከተሉ በግማሽ ልባቸው ነበር ወደ ጌታ ለመመለስ ያሰቡት! አስተዉሉ የጌታ ቃል ሲናገር ግን "አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም ሀይልህ ውደድ" ይላል። እያነከሱ የጌታ መሆን የለም! እያነከሱ የጌታ ነኝ ማለት መጨረሻው ለመሰበር ነው🤷‍♀🤷‍♀ ለጊዜው ባይመስልም! ከአለምም ከመንፈስም እቋደሳለው ማለት ለሁለት ጌታ እገዛለው ማለት ነው ይሄ ደሞ ከቶ የማይታሰብ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ቃሉ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም ብሏል ። ከቃሉ ወዴት ፍንክች እንላለን! በዚህ ኣንካሳ ብቻ በሞላበት ዘመን ግን አንዲት ልባም የሆነች ከአልምም ከመንፈስም እየቀላቀለች ሳትዘል እዚም እዚያም እያለች ሳትባዝን አምላኳን ብቻ የምትከተል አካሄዷን ከጌታ ጋር ያደረገች ምርጥ የጌታ ሴት አለች። ማን ናት? ሕልዳና ናታ። ነቢይት መሆን ማለት በዚህ ዘመን ስሙ እንደቀለለብን ቀላል ጉዳይ አይደለም! 400 ሀሰተኛ ነብይ አለ ማለት ነብይነት የቀለለ የወረደ ዝቅ ያለ ጉዳይ ነው ማለት አይደለም! ከ400 መሃል ጌታ የራሱ 1 አለው። ሕልዳና ነብይት ናት ብሎ መጽሀፍ ቅዱስ ሲነግረን ከቃሉ ይቺ ሴት #የፅሎት ሴት #ጌታን የምትፈራና የምትታዘዝ #ቃሉን የምታነብ እና የምታሰላስል #ለጌታ የተለየች #ራሷን የቀደሰች #ዘመኑም ያልመሰለች #ሁሌም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምታወራ #ትንቢት የምትናገር #የጌታን ድምጽ የምትሰማ #የሰማችውን የምታስተላልፍ . . . እንደሆነች መረዳት እንችላለን ። አንድ ነገር ልብ እንበል- ይህቺ ሴት በብሉይ ኪዳን ዘመን ነበረች በብሉይ ኪዳን ደግሞ ለሴት ልጅ የነበረውን አመለካክት እና ስርአት ምን እንደሆነ ማስታወስ ቀላል ነው! ከሴትነቷም በላይ የጌታን መንገድ ትከተልና ነቢይት ትሆን ዘንድ ምሳሌ ወይም ሮል ሞዴል የሚሆናት ሰው አለመኖሩ እንዲሁም ህዝብ ሁሉ የባአድ አምልኮን የተለማመደበት ዘመን መሆኑን! በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ሕልዳን የጌታ ሴት ነበርች:-ልባም ሴት! በኛ ዘመን እንውሰደው👉👉 ሴትነት በረከሰበት በዚህ ዘመን ነብይ መሆን እንደ ውርደት በሚቆጠርበት በዚህ ዘመን መቀደስ እንድ ፋራነት በሚቆጠርበት በዚህ ዘመን የጌታ መድረክ በቀለለበት በዚህ ዘመን . . . ጌታን መከተል ማለት ነው። ይከብድ ይሁን? አከባቢን አለመምሰል እንደሌሎቹ አራዳ አለመሆን ከማያምኑት ጋር ህብረት አለመፍጠር አለመቀደስ ይከብድ ይሁን? ለመላው የእስራኤል ህዝብ የከበደው ነገር ለምን ለሕልዳና አልከበዳትም? የሷ ልብ ድንጋይ ስለሆነ ወይስ ልቧን አጥብቃ ስለያዘች? "አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የህይወት መውጫ ከእርሱ ነውና" ለዚህም እኮ ነው እንድ እባብ ልባም ሁን የተባልነው። ጌታ ልባም ያድርግሽ፡ ያድርገኝ፡ ያድርገን አሜን። ከላይ እንዳነበብነው ሕልዳና ለንጉሱ ለኢዮስያስ የተናገረችው ትንቢት ትንሽ ከበድ ይላል። ምክንያቱም ንጉሱን ለማስደሰት ወይም ለሰው ፊት ብላ ጌታ ያላላትን፡ነገር ኣልቀባጠረችም ነበር። እግዚአብሄር ክፉ ነገር ይማጣል ሲላት ለሰሚው እንዲመች ብላ ያጣመመችው ቃል የለም። ደስ አትልም? ክፉ ነገር አመጣለው በይ ሲላት ክፉ ነገር አመጣለው ቁጣዬ ይነዳል በይ ሲላት እንደዚያው.... ለኢዮስይስ ቁጣው ሳይመጣ እንደሚሞት ያለምንም ማንገራገር ተናግራለች። የሰው ፊት አይታ ለሰው እንዲመች ብላ ቃሉን የምታጣምም ሀጢያት የምትሰራ ከትውልዱ ጋር የምትመላለስ ሴት አልነበረችም -ሕልዳና። ይህቺ ናት ልባም ሴት ማለት። በስተመጨረሻ ሕልዳና የተናገረችው ትንቢት አንድም መሬት ላይ ጠብ ሳይል ተፈጽሟል። ሳጠቃልል ከሕልዳና ልባምነትን የተማርነው 1-የጌታን ድምጽ ለመስማት ወይም ፍቃዱን ፈልገው እርሷ ዘንድ እንደሄዱ #ለጌታ ነገር የምትፈለግ 2-በክፉ ዘመን ውስጥ ጌታን የምትፈራ የምትታዘዝ የምትሰማ 3-ለትውልድ መፍትሄ የሆነች 4-የተለየች 5-ቃሉን የማታጣምም ምርጥ የጌታ ሴት እንደሆነች ነው። ከልባምም ልባም አይደለች?? እኔ በጣም ነው የቀናሁባት አንቺስ? ያስተማረን መንፈስ ቅዱስ ስሙ የተባረክ ይሁን። እግዚአብሄር እንደ ሕልዳና የሚያስጀግን ስብእናን ያላብሰን። ልባርክሽ- ጌታ ልባም ያርግሽ ትውልድን ባንቺ ያስርፍ ጆሮሽን ቃሉን ለመስማት ይከፈት አይኖችስም ራእይን ይመልከቱ በህይወት ዘመንሽ አካሄድስ ሁሉ ከጌታ ጋር ይሁን እንድ ሕልዳና ልባም ያርግሽ ትውልድ ባንቺ ይረፍ ለትውልድ እናት እህት ሁሉ ነገር ያድርግሽ ዳርቻሽ ይስፋ ዘመንሽ በቤቱ ይለቅ። አሜን። በዛሬው ጸሎትሽ እንደ ሕልዳና ልባም እንዲያደርግሽ መፅልዩን አትዘንጊው በዚያውም ለዚህ ለልባም ሴት ቡድንም ፅልይ። አዎ አንቺኑኑ ነው😄😄😄 ተባረኩልኝ እህታቹ ሜላል ነኝ ሀሳብ አስታያየት እቃበላለሁ። እወዳችኋለሁ በጣም😍😘 @libamset @libamset Join it 👆👆👆👆 እንደዚህ አስተማሪ የሆኑ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች እና ምክሮች የሚለቀቅበት ምርጥ channel ነው

(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ምዕራፍ 34) ---------- 21፤ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቁ፥ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ለእኔ በእስራኤልና በይሁዳም ለቀሩት እግዚአብሔርን ጠይቁ ብሎ አዘዛቸው። 22፤ ኬልቅያስና እነዚያ ንጉሥ ያዘዛቸው ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቲቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በኢየሩሳሌም በከተማይቱ በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ይህንም ነገር ነገሩአት። 23፤ እርስዋም አለቻቸው። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት። 24፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ አመጣለሁ። 25፤ በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት ዐጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ይነድዳል፥ አይጠፋምም። 26፤ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ስለ ሰማኸው ቃል ልብህ ገር ሆኖአልና፥ 27፤ በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ ቃሌን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አለቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። 28፤ እነሆ፥ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፥ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ ዓይኖችህ አያዩም። ይህንም ለንጉሥ አወሩለት።