ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
603
订阅者
-324 小时
-87 天
-1730 天
帖子存档
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፲ (10) ቀን። ✝ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት #ለተላስስና_ለአልዓዛር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍት በዓል፣ ከታናሽ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ታኅሣሥ ፲ (10) ቀን። ✝ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት #ለተላስስና_ለአልዓዛር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍት በዓል፣ ከታናሽነቱ ጀምሮ ጃንደረባ ለሆነ #ለአባ_ጥዋሽ ለዕረፍት በዓል፣ ከቊጥስጥንጥንያ አገር ለከበሩ ሰዎች ልጅ ለሆነች #ለቅድስት_ሱርስት ለዕረፍት በዓል፣ ለአንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለነበረ #ለቅዱስ_አባ_ሳዊሮስ ከእስክንድርያ አገር ወጪ ወደሆነች ደብረ ዝጋግ ገዳም ሥጋው ለፈለሰበት በዓልና ለከበረ አባት ጻድቅ ኤጲስቆጶስ የስሙ ትርጓሜ የሕዝብ አሸናፊ ለሆነ #ለአባ_ኒቆላዎስ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ አገር ስልሣኛ ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ታውፋኔዎስ ዕረፍት፣ ከቅዱሳን #ከሜልዮስና_ከታውፍያ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ አባል ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ ታሠሩ ። ታኅሣሥ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የዕ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ አባል ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ  አያሌው ቢታኔ ታሠሩ ። ታኅሣሥ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የዕለት ችሎት ሥራቸውን አከናውነው ከባለቤታቸውና እና ከእህታቸው ጋር  ሜክሲኮ በሚገኘው ነዳጅ ማደያ ነዳጅ በመቅዳት ላይ ሳሉ ሲከታተሏ በነበሩ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ተወስደው የታሠሩ መሆኑ ታውቋል። ጠበቃ አያሌው ቢታኔ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴን በመምራት ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ቤተክርስቲያንን ወክለው የሕግ አገልግሎት እያበረከቱ እንዳለ ይታወቃል። ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፱ (9) ቀን። ✝ እንኳን #ያለደምን_መፍሰስ_ሰማዕትነት ለተቀበለ ታማኝ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_በአሚን ለዕረፍት
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ታኅሣሥ ፱ (9) ቀን። ✝ እንኳን #ያለደምን_መፍሰስ_ሰማዕትነት ለተቀበለ ታማኝ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_በአሚን ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳ #ከበድላም_ከአርምያና_ከዘካርያስ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                         ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_በአሚን፦ እርሱም በደቡብ ግብጽ በእስሙናይን አውራጃ ለአገረ ቴርሳ አቅራቢያ ከሆኑ ከሐፂብ ተወላጆች ወገን ነው ለአንድ ባለጸጋም በጅሮንድ ሆኖ ሳለ ስለ ንጽሕናውና ስለ ቅድስናው በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ሆነ የባለ ጸጋውም ሚስት አባ በአሚንን እጅግ የምትወደውና የምትተማመንበት ሆነች። ✝ እርሱ ግን የዚህን ዓለም ፍጻሜ አሰበ የባለ ጸጋውንም አገልግሎት ትቶ ወደ ገዳም ሒዶ መነኰሰ ባለጸጋውም መሔዱን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም ይዞ አባ በአሚን ወዳለበት በአንድነት ሔዱ ወደ እርሳቸው እንዲመለስም ለመኑት √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨ ስደተኞች  ክፍል  ሦስት ፫ ✨✨ ተዋንያን      ሳሙኤል ገዛኸኝ      አቤል ለታ     ረድኤት ብርሃኑ     አብርሃም ሙላቱ ምንጭ ከ ቪኒሲያ መፅሐፍ

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፰ (8) ቀን ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለደብረ ድማሕ(ዲማ) ገዳም አበምኔት በፊትም በኋላም የሚያዩ ለሆኑ #ለታ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝            ✝ #ታኅሣሥ ፰ (8) ቀን ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለደብረ ድማሕ(ዲማ) ገዳም አበምኔት በፊትም በኋላም የሚያዩ ለሆኑ #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ለተክለ_አልፋ ለዕረፍት በዓል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ማልኝ ብለው በአባይ ወንዝ ውስጥ ለዘጠኝ ዓመት ለጸለዩ #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ_ለልደት በዓል፣ በክርስቶስ ለሚታመንየሰማዕታትንና የጻድቃንን በየዕረፍታቸው ቀን ለእያንዳንዳቸው ርኁባንን በማጥገብ የተራቆቱትን በማልበስ መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ ለነበረ #ለቅዱስ_ገብረ_ማርያምና፣ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ኪሮስና ከግብጽ ለኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ተሾመው ለመጡ በኢትዮጵያ ብዙ የዋሻ ቤተ ክርስቲያንን ላነጹ #ለብጹዓዊ_ለአቡነ_ሙሴ_ዘድባ ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                           ✝ ✝ ✝ ✝ #ስለ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ_ልደት፦ (የተወለዱበት) ቦታ ዳውንት ፀወን ዓባይ ይባላል። በአካባቢውም በገዳሙ አንፃር በሰሜን በኩል የእናታቸው አገር ደብረ ድባ የቄርሎስ ቦታ ይባላል የአባታቸውም አገር የእግዚአብሔር አብ ደብር √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝተው የሕንፃ ግንባታው ሒደት ጎበኙ። ዘጋቢ ሰላም ኣምባዬ (#EOTCTV  ታኅሣሥ 7 ቀን 2016 ዓ.ም) ታኅሣሥ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ  (ዶ/ር)  የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሓፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ጅንካ ፣ የአሪ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ሰላማ የምዕራብ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም መልአከ ምሕረት ዘካርያስ ሐዲስ የየካና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ  ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሪ ምሥራቀ ጸሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተገኝተው የሕንፃ ግንባታው ሒደት ጎብኝተው መንፈሳዊ አገልግሎት ሰጥተዋል።   የደብሩ አስተዳዳሪ እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሰ/ት /ቤት ወጣቶች እና ምእመናን በተገኙበት ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረውን ታላቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ላይ በብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት ትምህርተ ወንጌል በማስተማርና በተለያየ መንፈሳዊ  አገልግሎት አበርክተዋል። ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ  ከተጀመረ አንድ ዓመት እንደ ሆነ በተገለጸው አዲሱ የሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታን ጎብኝተዋል። በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዮሐ.1፥ 44  ተጽፎ የምናገኘው ኃይለ ቃል " ነቢያት ስለ እሱ የተናገሩትን መሴ ስለሱ የጻፈለትን አግኝተነዋል " በሚል ርእስ ያስተማሩ ሲሆን ወደ ቤተክርስቲያን ስንቀርብ እውነተኛውን አምላክ ነቢያት ስለእሱ ብዙ ያሉለትን እናገኘዋለን ብለዋል። በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ  አብርሃም  የምእመናኑ አስተዋጽኦ ለሕንጻ ግንባታ የላቀ መሆኑን በመጥቀስና በ1ኛ ዜና መዋእል 28፥6 ያለውን ኃይለ ቃል " እርሱም ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና እኔም አባት እሆነዋለሁ ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል " በማለት  እኛ የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን የማይጠፋ ለዘለዓለም ሕይወት  ስንቅ የሚሆነን ቤተ እግዚአብሔር በመሥራት አምላካዊ ቃሉን  ልንተገብር ይገባል በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የደብሩ አስተዳዳሪ ጉባኤ ሊቀ ብርሃናት ናሁ ሰናይ ነጋ  በሀገር ውስጥም በውጭ ዓለም ያሉ የሥላሴ ወዳጆች  የተጀመረውን የሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ መደገፍ እንደሚገባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት EOTC TV

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በትላንትናው ዕለት በደብራችን በግራር ደብረ አባይ
+9
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በትላንትናው ዕለት በደብራችን በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ የእናታችን የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤት ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የተለያዩ የቤተክርቲያን ሊቃውንት አባቾች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል!!! 🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊 📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸   ከሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ከምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለአመቱ በሰላም ያድርሰን አሜን🙏🙏🙏

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝                ✝ ታኅሣሥ ፯ (7) ቀን። ✝ እንኳን #የማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን_የቅዱስ_ያሬድ ዜማ አገልግሎት ላይ ለዋለበት ቀን መታሰቢያ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዐሉ #በአዲስ_አበባ_ደብረ_ይባቤ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን_ከወራዊ_በዐሉ ጋር ታቦተ ሕጉ ወጥቶ #ታኅሣሥ_11_ቀን_ይከበራል ሁላችንም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ተጋብዘናል እንዳንቀር አደራ።                               ✝ ✝ ✝ ✝ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ስለ መዋሉ፦ ዐፄ ገብረ መስቀል የቅዱስ ያሬድ ባሕረ ጥበባት ዜማን ጣዕም ሰምተው ከተረዱ በኋላ ሊቃውንትና ካህናቱን ሰብስበው "ይኽን የያሬድ ዜማ ተቀበሉትና ለቅድስት ቤተክርስትያን መገልገያ ይኹን" ባሉ ጊዜ ካህናትና ሊቃውንቱ "ምን ምልክት ዐይተን እንቀበለው? እንደሐዋርያት እጅና እግሩን ለተሳለ ቀኖት (ችንካር)፤ አፉን ለመረረ ሐሞት ሰጥቶ አላየነው?!" ብለው ሲመልሱላቸው ዐፄ ገብረ መስቀልም "እንግዲያውስ አንድ ሱባዔ እንያዝና እርሱ አምላካችን ይግለፅልን!" ብለው ሱባዔ ያዙ። ✝ ካህናት እና ሊቃውንት በታኅሣሥ ወር ከሰኞ እስከ እሑድ አንድ ሱባዔ ይዘው የአክሱም ጽዮን ማርያምን ቤተክርስቲያን እየዞሩ አራት መቶ እግዚኦታ እና አርባ አንድ በእንተማርያም እያደረሱ ምሕላውን አከናወኑ። ✝ በሰባተኛው ቀን በዕለተ እሑድ ልመናቸውን ጨርሰው ሲያሳርጉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዐርብ እንደተሰቀለ ኾኖ ስለካህኑ ቅዱስ ያሬድ ዜማ ሰማያዊነት ሊመሰክር በጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ ተገለፀ። ✝ አባታችን ቅዱስ ያሬድም ይኽንን አስመልክቶ ፦ ✝ "ዘበመስቀሉ ተቀነወ ወበነቢያት ተሰብከ መላእክት ወሊቃነ መላእክት ሰብሕዎ ኪያሁ ንሰብክ መድኅነ"። ትርጉም፦ በነቢያት ትንቢት የተነገረለትና በመስቀሉ ላይ የተቸነከረው ጌታ መላእክት እና የመላእክት አለቆች አመሰገኑት፤ እኛም እርሱ መድኃኒት እንደኾነ እንናገራለን። ✝ ቀኑም ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ዜማ ማስተማር የጀመረበት ፥ የነቢያት "ይወርዳል - ይወለዳል" ትንቢት የተፈጸመበት መኾኑን ለማጠየቅ "ስብከት" ተባለ። ✝ በዚያችም ቀን ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ የተቀበለው ዜማ ወደቤተክርስቲያን ገባ - የቤተክርስቲያን ብርሃኗ በራ!። ✝ "የመላእክትን እንጀራ የሰው ልጅ በላ፥ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠኻቸው" የተባለው የቅዱስ ዳዊት የትንቢት ቃል ተፈጸመ ምንኛ ይደንቅ!። ምንጭ፦ የቤተክርስቲያን ብርሃን ቅዱስ ያሬድ (ታደሰ ዓለማየሁ)። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ሙጃ ቅድስት አርሴማ ገዳም የመስቀል ቅርፅ የሚሰራው የንብ መንጋ በረከቷ ለእኛም ይድረሰን
+1
ሙጃ ቅድስት አርሴማ ገዳም የመስቀል ቅርፅ የሚሰራው የንብ መንጋ በረከቷ ለእኛም ይድረሰን

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል በቢሾፍቱ ቁርቁራ ደብረ አሚን ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በድምቀት ተከብ
+4
የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል በቢሾፍቱ ቁርቁራ ደብረ አሚን ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ ታኅሳስ6/2016 ዓ.ም

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ ገዳም በፎቶ ! ታኅሣሥ 6 ቀን 2016 ዓ.ም
+3
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ ገዳም በፎቶ ! ታኅሣሥ 6 ቀን 2016 ዓ.ም

እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የጎጆዋ ቅድስት አርሴማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረች ትገኛለች
+2
እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የጎጆዋ ቅድስት አርሴማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረች ትገኛለች

ሰበር አራት ዐይና ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ጌጡ በጎንደር ከተማ የቅድስት ልደታ ለማርያም የታች ቤት ትርጓሜ የአራቱ ጉባዔ መምሕር እና የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ በኮማንድ
ሰበር አራት ዐይና ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ጌጡ በጎንደር ከተማ የቅድስት ልደታ ለማርያም የታች ቤት ትርጓሜ የአራቱ ጉባዔ መምሕር እና የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸው ተሰማ።

🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣📣🕊📣🕊📣 📣ታህሳስ 6📣 "እንኳን ለሰማዕቷ እናታችን ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል በሰ
🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣📣🕊📣🕊📣               📣ታህሳስ 6📣 "እንኳን ለሰማዕቷ እናታችን ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፤ የሰማዕቷ ረድኤት በረከት ምልጃና ጸሎቷ ከሁላችንም ጋር ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡" 🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣 ✨ፍኖተ ብርሃን✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፭ (5)። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለእግዚአብሔር ሕግ ለሚቀና ገድለኛ ለሆነ ለንጹሕ ድንግል ለቅዱስ አባት #ለ
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝             ✝ #ታኅሣሥ ፭ (5)። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለእግዚአብሔር ሕግ ለሚቀና ገድለኛ ለሆነ ለንጹሕ ድንግል ለቅዱስ አባት #ለአባ_ገብረ_ናዝራዊ_ለዕረፍት_ዓመታዊ ክብረ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_ገብረ_ናዝራዊ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በወገን የከበሩ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው አባቱም የቤተ ክርስቲያንን ሕጓንና ሥርዓቷን የሚጠብቅ ካህን ነው እናቱም ፈጣሪዋን የምትወድ ደግ ሴት ናት። ይህም ቅዱስ በተወለደ ጊዜ በዕውቀት እግዚአብሔርን በመፍራት በመማር አደገ ከዚህም በኋላ ዲቁናን በተሾመ ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን የሚያነብ ሆነ በኦሪትም ውስጥ "የሰንበትን ቀን የሻረና ሥራ የሠራባት በሞት ይቀጣ" የሚል አገኘ። ከወንጌልም ውስጥ እንዲህ የሚል አገኘ "ከእነዚህ ትእዛዛት ታንሳለች ብሎ የሚያስተምር አንዲቱን የሻረ ለሰውም እንዲህ ብሎ የሚያስተምር በመንግሥተ ሰማይ የተለየ ይሆናል √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፬ (4) ቀን። ✝ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያ አንዱ ለሆነው #ለሊቀ_ሐዋርያት_ለቅዱስ_ጴጥሮስ_ወንድም ለተመሰገነ #ለ
✝ በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ታኅሣሥ ፬ (4) ቀን። ✝ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያ አንዱ ለሆነው #ለሊቀ_ሐዋርያት_ለቅዱስ_ጴጥሮስ_ወንድም ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_እንድርያስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን #ከአባ_ጻዕ_ከአባ ያዕቆብ_ከዘካርያስ_ከስምዖን፣ #ከታዖድራና_ከታውፍልዖ እግዚአብሔር አምላክ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

የበዓታ ማርያም በዓለ ንግሥ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአድኣ ወረዳ ቤተ ክህነት የጥንታዊቷ ኤረር ደብረ ገነት በዓታ ለማርያም ገዳም በደማቅ ሥርዓት ተከበረ። ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም
+1
የበዓታ ማርያም በዓለ ንግሥ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአድኣ ወረዳ ቤተ ክህነት የጥንታዊቷ ኤረር ደብረ ገነት በዓታ ለማርያም ገዳም በደማቅ ሥርዓት ተከበረ። ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም