ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多606
订阅者
-224 小时
-57 天
-1430 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን #ውዳሴ_ማርያውና ከ 14 ሺህ በላይ ድረሳናትንና ተግሣጻትን ለደረሰው ለታላቁ ሊቅ #ለአፈ_በረከት_ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ_ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሶርያው_ሊቅ_አፈ_በረከት_ቅዱስ_ኤፍሬም፦ ይህም ቅዱስ ከዋክብት የሚያመልኩ ሰዎች አገር ነው አባቱ ክብር ይግባውና የክርስቶስን አምልኮት የሚጠላ የጣዖት ካህር ነበር። በዚያን ጊዜም የእግዚአብሔር ቸርነት ቀሰቀሳቸውና አነሳስታ የንጽቢን ጳጳስ ወደ ሆነው ወደ አባ ያዕቆብ ወሰደችው እርሱም የቤተ ክርስቲያን ትምህት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው በእርሱ ዘንድ በጾምና በጸሎት ያለማቋረጥ እየተጋደለ ለብዙ ዘመናት ኖረ።
❤ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት አሕዛብን ተከራክሮ ይረታቸው ነበር። ኒቅያ በሚባል ከተማ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከአባ ያዕቆብ ጋር ወደ ቅዱሳን ጉባኤ ሔደ። ከሀዲው አርዮስንም አውግዘው ከለዩት በኋላ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም በዚያች ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ አየ ከዚህ ራዕይ የተነሳ አደነቀ ይገልጽለትም ዘንድ ወደ ጌታ ጸለየ "ይህ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው" የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ።
❤ ቅዱስ ኤፍሬምም ያየው ዘንድ ወዶ ወደ ቂሣርያ አገር ተጓዘ በደረሰም ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በማዕዘኑ በኩል ቆመ ቅዱስ ባስልዮስም ወንጌልን ሊያነብ በወጣ ጊዜ ዋጋው ብዙ የሆነ ከወርቅ የተሠራ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ አየው። ሦስት ምልክቶችን እስኪያይ ድረስ ተጠራጠረ ምልክቶችም እኒህ ናቸው። ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች። ሁለተኛም በልብሱ ላይ የሚያርፉ ተዋሐስያን ይቃጠሉና ይረግፉ ነበር። ሦስተኛም ከአፉ የእሳት ነበልባል ወጥቶ በምዕመናን ላይ ያድር ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱስ ኤፍሬምን በስሙ ጠራውና እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ተለዋወጡ። በአስተርጓሚ ይነጋገሩ ጀመር። የየራሳቸውን ቋንቋ ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስ ለመነው። በጸለየም ጊዜ ተገልጾላቸው ያለ አስተርጓሚ ተነጋገሩ።
❤ ከዚህ በኋላም ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁና ሾመው ከጥቂት ወራት በኋላ ቅስና ሾመው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ተገለጡ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ተጋደለ።
❤ አንዲት በወገን የከበረች ባለ ጸጋ ሴት ነበረች እርሷንም ለካህን ለማስመርመር ታፍር ነበር ከታናሽነቷ ጀምራ የሠራችው ኃጢያቷን ሁሉ ጽፍ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አመጣች። "አባቴ ሆይ በዚህ ክርታስ ውስጥ ያሉት ኃጢያቶቼ ይደመሰሱ ዘንድ ተናገር ብላ ለመነችው እርሱ እንዳልሽው ይሁንልሽ" አላት። እርሷ ክርታሱን በገለጠች ጊዜ ከአንዲት ኃጢያቷ በቀር ኃጢያቷ ሁሉ ተደምስሶ አገኘች ያችም ኃጢአት አስጨናቂና ታላቅ ኃጢአት ነበርች።
❤ በአገኘቻትም ጊዜ ያቺን የቀረች ኃጢአቷን ያጠፋላት ዘንድ አልቅሳ ለመነችው እርሱም "ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሒጂ እርሱ ይቺን የቀረች ኃጢአትሽ ያስተሠርይልሻል" አላት። ወዲያውም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሒዳ እርሷ የሆነውን ሁሉ ነገረችው። እርሱም እንዲህ አላት "ፈጥነሽ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሒጂ ግን ሙቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኚዋለሽ ሳትጠራጠሪም ይቺን ክርታስ በላዩ ጣይ ይደመስስልሻል።
❤ ያቺም ሴት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ተመለሰች ሙቶ ተሾክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱትም አገኘችው። ያንንም ክርታስ በአስክሬኑ ላይ ጣለችው ወዲያውኑ ተደመሰሰላት።
❤ ይህም ቅዱስ ኤፍሬም ብዙ ተአምራቶችን አድርጓል በዘመኑ ዲዳን የሚባል አንድ ከሃዲ ተነሳ ይህም አባት ኤፍሬም ተከራክሮ ረታው።
❤ እጅግም ብዙ የሆኑ ዐሥራ አራት ሺህ ድርሳናትና ተግሣጻትን ደረሰ ከእርሳቸውም ውስጥ አምላክ የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያው ውዳሴዋ ነው። "አቤቱ የፀጋህን ማዕበል ግታልኝ" እስከሚል ደረስ ድርሳናት ደርሷል።
❤ መልካም የሆነ ገድሉንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ወደደው ወደ እግዚአብሔር ሐምሌ 15 ቀን ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በብፁዕ ቅዱስ ኤፍሬም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 15 ስንክሳር።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን ልክ እንደ #ቅዱስ_ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሊሰቃይ ሲሔድ #ጌታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ተገልጾ ለመለሰው #ለቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለመነኰሳት አለቃ #ለታላቁ_አባት_አባ_መቃርስ_ለመታሰቢያ_በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_አሞንዮስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_አብሮኮሮንዮስ፦ የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ከኢየሩሳሌም ነው የአባቱ ስም ክርስቶፎሮስ ነው ትርጓሜውም ክርስቶስን የለበሰ ማለት ነው ክርስቲያንም ነበረ የእናቱም ስም ቴዎዶስያ ነው እርሷ ግን ጣዖትን ታመልክ ነበረች።
❤ አባቱም በዐረፈ ጊዜ እናቱ ወሰደችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ገንዘብ ይዛ ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደች ልጅዋንም በእስክንድርያ ከተማ ገዥ አድርጎ ይሾመው ዘንድ ለዲዮቅልጥያኖስ እጅ መንሻ ሰጠችው እርሱም ሾመው የሹመት ደብዳቤውንም ጽፎ ክርስቲያኖችን እንዲአሠቃዩ አዘዘው።
❤ ከአንጾኪያም ከተማ ወጥቶ ጥቂት እንደ ተጓዘ ወደእርሱ የሚያስፈራ ቃል ከሰማይ መጣ በስሙ ጠርቶ እንዲህ አለው "ከሀዲው ዲዮቅልጥየኖስ እንዳዘዘህ ብታደርግ አንተ በክፉ አሟሟት ትሞታለህ። እርሱም "ራስህን ትገልጥልኝ ዘንድ ጌታዬ ሆይ እለምህሃለሁ" አለው ወዲያውኑም የብርሃን መስቀል ታየው ዳግመኛም "በኢየሩሳሌም የተሰቀልኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ" የሚለውን ቃል ሰማ።
❤ ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ተመልሶም ከአንጥረኛ ዘንድ የወርቅ መስቀል አሠራ ከዚያም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ተጓዘ በጒዞውም ውስጥ ሊገድሉት ዐመፀኞች አረማውያን ተነሡበት እርሱም በእነርሱ ላይ በርትቶ ክብር ይግባውና በጌታ ክርስቶስ መስቀል ድል አደረጋቸው። እናቱም "በጦርነት ላይ ለረዱህና ላዳኑህ አማልክት መሥዋዕትን ሠዋ" አለችው እርሱም እንዲህ አላት "እኔስ አዳኝ በሆነ በመስቀሉ ኃይል ላዳነኝ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ"። ይህንንም በሰማች ጊዜ ልጅዋ አብሮኮሮንዮስ ክርስቲያን እንደሆነ ወደ ዐመፀኛው ዲዮቅልጥያኖስ ልካ ነገረችው። ዲዮቅልጥያኖስም ጭፍራ ልኮ ወደ ቂሣርያ ከተማ አስወሰደው የቂሣርያውንም ገዥ ስለ ርሱ እንዲመረምርና እንዲአሠቃየው አዘዘው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ በአቀረቡት ጊዜ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ለመሞት እስቲደርስም ጽኑዕ ግርፋትን ገረፈው ከዚህም በኋላ አሠረው። በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ብርሃን ውስጥ ታየው ከእርሱም ጋራ ብርሃናውያን መላእክት ነበሩ ከማሠሪያውም ፈታውና በመለኮታዊ እጁ ዳሰሰው ከቍስሎቹም ሁሉ አዳነው።
❤ በማግሥቱም መኰንኑ ስለ ቅዱሱ ዜና ሙቶ እንደሆነ ወይም አልሞተ እንደሆነ ጠየቀ ለእርሱ የሞተ መስሎት ነበረና። ቅዱሱም በመጣ ጊዜ ጤነኛ ሁኖ አየውና መኰንኑ አደነቀ በዚያ የነበሩ ሕዝቡም አይተው እጅግ አደነቁ እንዲህም እያሉ ጮኹ "እኛ በግልጥ ክርስቲያን ነን በቅዱስ አብሮኮሮንዮስ አምላክ እናምናለን"። ከእነርሱም ጋራ ሁለት መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች እናቱ ቴዎዶስያም ነበሩ መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ። እነርሱም ቆረጡአቸው። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ሐምሌ ስድስት ቀን ተቀበሉ።
❤ ቅዱስ አብሮኮሮንዩስን ግን ምን እንደሚያደርግበት እስቲአስብ ድረስ ሦስት ቀን አሠረው ከዚህም በኋላ አውጥቶ እንዲህ አለው "ልብህ እንዲመለስ ነፍስህንም እንድታድን ለአማልክትም እንድትሠዋ እነሆ በአንተ ላይ ሦስት ቀናት ታገሥኩ"። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "መኰንን ሆይ የለም ልቤ ወደ ስሕተት አይመለስም ክብር ይግባውና ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ አውቄ ተረድቼአለሁ ጣዖታቱም ሁሉ ከዕንጨትና ከደንጊያ በሰው እጅ የተሠሩ ፍጡራን ናቸው እንጂ አማልክት አይደሉም አይጐዱም አይጠቅሙም"።
❤ መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ጐኖቹንም በሰይፍ እንዲሰነጣጥቁ አዘዘ አርኬላዎስ የሚባል ባለ ሰይፍም የቅዱሱን ጐኖቹን ሊሠነጥቅ እጁን ዘረጋ ያን ጊዜም እጁ ደረቀች ወድቆም ሞተ። መኰንኑም ተቆጥቶ በምድር ጥለው ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እንደ አዘዘም ገረፉት በሰይፍም ጐኖቹን ሠንጥቀው በቍስሉ ውስጥ መጻጻ ጨመሩ እስከ ወህኒ ቤትም ድረስ በእግሩ ጐተቱት በዚያም ሁለት ቀኖች ኖረ ከዚህም በኋላ አውጥቶ እሳትን በተመላች ጕድጓድ ውስጥ ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችንም አዳነው ምንም ምን አልነካውም።
❤ ብዙ ከማሠቃየቱም የተነሣ መኰንኑ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአብሮኮሮንዮስ_በኢየሩሳሌም ዘተወልደ። እምለባሴ ክርስቶስ አቡሁ በአርዑተ ወንጌል ዘተጸምደ። በትእዛዘ ንጉሥ ሠዊዐ ሶበ ለጣዖት ፈቀደ። ቃል ዘይከልኦ እምሰማይ ወረደ ወበቊስላቲሁ አንበረ መለኮት እደ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_14።
" #የጾሙ_ዐዋጅ_ለገዳማውያን_ብቻ_ነው"
ሐምሌ 22 ቀን የሚጀመረውን የገዳማውያን ጾምን አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ ማሳሰቢያ!!!
ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም
አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመናን እያቀረቡት ካለው የግንዛቤ ጥያቄ አንጻር ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠውን መግለጫ በተመለከተ አጭር ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መሠረት ከላይ በተጠቀሰው ቀን የተሰጠው መግለጫ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በሚል ገላጭ ርዕስ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም ለሚገኙ #ገዳማውያን_ብቻ የታወጀ የምሕላ ሱባኤ መሆኑን እየገለጽን በዚህ የሱባኤ ሳምንት ከቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን የሚጠበቀው ለገዳማውያኑ ጸጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉት ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ ሆኖ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ይሰጥልን ዘንድ በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ በጸሎት ብቻ እንድትተጉ የቋሚ ሲኖዶስን ውሳኔ በማስታወስ አደራ እያልን የፈቃድ ጾም ግን ለኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የማይከለከል መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ_፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለአገረ_ቅፍጥ_ኤጲስቆጶስ ከነቢያት ትንቢትም አንዳንዱን መጽሐፍ በሚነብ ጊዜ ትንቢቱ የሚነበብለት ነቢይም ወደርሱ መጥቶ ንባቡን እስቲፈጽም ይቆይ ለነበረ፤ እጆቹን አንሥቶ በሚጸልይ ጊዜ ጣቶቹ እንደ ፋና ይበሩ ለነበር ለታላቁ አባት #ለአባ_ብስንድዮስ_ለዕረፍቱ_መታሰቢያ በዓልና በግብፅ ደቡብ ከቡና አውራጃ ከጡሕ ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_አሞን_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአገረ_ቅፍጥ_ኤጲስ_ቆጶስ_አባ_ብስንድዮስ፦ ይህም ቅዱስ ሰው መንኵሶ በታላቅ ገድል ተጠምዶ ቅዱሳት መጻሕፍትንም አጠና ከቅዱሳት መጻሕፍትም ውስጥ የዳዊትን መዝሙርና የነቢያትን መጻሕፍት አጥንቶ ነበር። ከነቢያት ትንቢትም አንዳንዱን መጽሐፍ ያነብ ነበረ። ትንቢቱ የሚነበብለት ነቢይም ወደርሱ መጥቶ ንባቡን እስቲፈጽም ይቆይ ነበር።
❤ ስለርሱ እንዲህ ተባለ እርሱ እጆቹን አንሥቶ በሚጸልይ ጊዜ ጣቶቹ እንደ ፋና ይበሩ ነበር እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ። እርሱም በዕድሜው ዘመን ሁሉ የሴት ፊት አላየም። ራሱን ወደ ምድር ያዘነብል ነበር እንጂ። በሆድዋ ውስጥ ታላቅ ደዌ የነበረባትም አንዲት ሴት ነበረች ከበዐቱ ደጅ ጠበቀችውና በድንገድ አገኘችው። እርሱም ሮጠ እርሷም ተከትላው ሮጠች ወደ እርሱ መድረስም በተሳናት ጊዜ እግሩ የረገጠቻትን አንዲት እፍኝ አፈር ዘግና በእምነት በላች ከደዌዋም ፈጥና ተፈወሰች።
❤ በአንዲት ዕለትም የሚያበሩ ሦስት ሰዎች አየ እነርሱም "አንተ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ትመግባት ዘንድ አለህ" እያሉ መክፈቻ ቅልፍን ሰጡት። ከዚህ በኋላ ቅፍጥ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ የቊርባን ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜም ጌታችንን እጆቹ በመሠዊያው ላይ ሆነው ይመለከተው ነበር። መላእቶቹንም በዙሪያው ቁመው ያያቸው ነበር።
❤ በአንዲት ዕለትም አንድ ቄስ ሊቀድስ ገባ በቅዳሴ እኩሌታ ላይም በመሠዊያው ፊት እያለ ምራቁን ተፋ። ቅዳሴውም በተፈጸመ ጊዜ ይህ አባት ገሰጸው እንዲህ አለ "በሚያስፈራው ወሠዊያው ፊት በምትቆም ጊዜ ከእግዚአብሔር ጌትነት የተነሳ አትፈራምን የተፈኸውስ ምራቅ በመሠዊያው ዙሪያ በቆመ ኪሩብ ክንፈች ላይ እንደረሰ አታውቅምን"። ያን ጊዜም ያንን ቄስ መንቀጥቀጥ ያዘው ተሸክመውም ወደ ቤቱ ወሰዱትና ታሞ ሞተ።
❤ ይህም ቅዱስ አባት አንደበቱ ጣዕም ያለው ነበር በሚያነብ ጊዜ በሚያስተም ጊዜ በሚመክርም ጊዜ አይጠገብም ነበር። የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና አስተማራቸው መከራቸውም በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጠ።
❤ ከሥጋውም ብዙ ተአምር ተገለጠ ደቀ መዝመሩ ከመግነዙ ጥቂት ቁራጭ ወስዶ በእምነት በሽቶኞችን ሁሉ ይፈውስ ነበር። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ብስንድዮስ ጸሎቱ ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_አሞን፦ ይህም ቅዱስ ከግብጽ ደቡብ ከቡና አውራጃ ጡሕ ከሚባል አገር ነው። ለዚህም ቅዱስ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጸለት ከእርሱ የሚሆነው ሁሉ ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ሒዶ አውግስጦስ የሚባል መኰንን ፊት ክብር ይግባው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም በመንኰራኵር ውስጥ በእሳት ላይ በመጣል በእሳት በአጋሉት በብረት አልጋ ላይ በማጋደም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ በመጨመር ጽኑዕ ስቃይም አሰቃዩት። የራሱንም ቆዳ ገፈው በራሱ ላይ የእሳት ፍም አኖሩ እግዚአብሔርም ያጸናው ነበር ያለምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ ያስነሳው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባው እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በጎልማሳ አምሳል በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ተገለጠለትና አጽናናው እንዲህም አለው "ወዳጄ አሞን እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለው ስምህን የሚጠራውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ፣ ወይም ገድልህ የሚጽፈውን ሁሉ እኔ በመንግሥቴ ውስጥ አስበዋለሁ ኃጢያቱንም እደመስሳለሁ አገርህም እጠብቃለሁ" ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጥቶ ከእርሱ ዘንድ አረገ።
❤ ይህም ቅዱስ በሥጋው ሳለ ታላላቅ ታምራቶችንና ድንቆችን አደረገ ወዲያውንም በሠይፍ ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። ቅዱስ ዮልዮስም በዚያ ነበር ሥጋውን ወስዶ በመልካም ልብስ ገነዘው ከሁለት አገልጋዮቹም ጋር ወደ አገሩ ላከው በላይኛው ግብጽም ታላላቅ የሆኑ ድንቆችንና ተአምራቶች እያሳየ እስከ ዛሬ አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ሰማዕት በቅዱስ አሞን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 13 ሰንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለብስንድዮስ_ዘይኔጽር_ነቢያት። እስከ ይፌጽም ኣንብቦ ጸሐፍ ትንቢተ። ወሰሚዓ ካዕበ ዘገብረ ትእምርተ። ብእሲት ጥዕየት እምደዌሃ ወሐይወት ሕይወተ። እምአሠረ እግሩ ቅድስት በሊዓ መሬተ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_13።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ 1፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥18-35፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 19፥11-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥32-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለከ_ረዳኤ_ቅዱሳን_ሰማዕት። ወሐዋጼ ጻድቃን ዘውስተ ጾማዕት። #ሚካኤል_ፀሐይ_ጥዒና ቈሪራን አዝርዕት። ያንቅሐኒ ወያንሥአኒ እምዳግም ሞት። ውስተ ክነፊከ ዘሀሎ ሕይወት"። ትርጉም፦ #ቅዱሳን_ሰማዕታትን_በተጋድሎአቸው ጊዜ የምትራዳቸው ስለጽድቅ ድንጋይ ተንተርሰው ጤዛ ልሰው በዱር በገደል የሚኖሩ ጻድቃንን የምትጎበኛቸው ላንተ #ለሚካኤል_ሰላም_እላለሁ። ሚካኤል ሆይ የለመለሙ አዝዕርቶችን አብስለህ ለመከር የምታበቃቸው ፀሐይ አንተ ነህ። አሁንም በክንፍህ በሥልጣንህ ሥር ያለ ሕይወት ከዳግም ሞት እንቅልፍ ያንቃኝ ያትጋኝ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_12።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረ መልአክ ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_ሚካኤል_የፋርስ_ንጉሥ ወደ ሆነ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት እግዚአብሔር ለላከበት ቀን #ንጉሥ_ሕዝቅያስን ረድቶ በአንድ ሌሊት ከሰናክሬም ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞች ለገደለበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓልና ስርያቆስ ከሚባል አገር ለሆነ #ለአባ_ሖር ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #የአባ_ሖር_ማኅበር_ከመቶ_ሰባት_ወንዶችና_ከሃያ_ሴቶች_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፡፡
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ #የቅዱስ_ሚካኤል_የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን የፋርስ ንጉሥ ወደ ሆነ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት እግዚአብሔር ላከው ከሰናክሬም ሠራዊት ከሰናክሬም ሠራዊትም መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞች ገደለ።
❤ ይህም እንዲህ ነው ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን በከበባት ጊዜ ሕዝቅያስንና ፈጣሪው እግዚአብሔርን እየዘለፈ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ እንዲህም አለ "እግዚአብሔር ያድናችኋል እያለ ሕዝቅያስ አያስታችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ ማን ነው"።
❤ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እጅግ አዘነ ወገኖቹንና አገሩ ኢየሩሳሌምንም ያድን ዘንድ ማቅ ለብሶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀበሎ ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ላከለት። ድንቅ ሥራንም ሠርቶ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ሰዎች ሁሉ አዳናቸው።
❤ ስለዚህም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ በዚች ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
✝️ #አባ_ሖር፦ ይህም አባት ስርያቆስ ከሚባል አገሩ ነው። አባቱም አንጠረኛ ነበር አንዲት እኅቱም ነበረችው። ጎልማሳም በሆነ ጊዜ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደ አገረ ፈርማ ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ከሥቃዩም ድኖ ተነሣ። መኰንኑም በእጁ ላይ ጌታችን ያደረገውን ይህን ተአምር አይቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ አመነ። በሌላ መኰንን እጅም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ በሰማዕትነት ሞተ።
✝️ ቅዱስ አባ ሖርን ግን ወደ እንዴናው ላከው በዚያም በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃዩት በመንኰራኵሮችም አበራዩት ዘቅዝቀውም ሰቅለው በእሳት በአጋሉት የብረት በትር ደበደቡት። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነትን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 12 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
✝️ "#ሰላም_ለሖር_በኀበ_እግዚኡ_ዘተመዝገነ። አመ ጽዕለተ ተወክፈ ወበትረ ኀፂን ርሱነ። ወሶበ እምኔሁ ነጸረ ዕበየ ተአምር ዘኮነ። ምስለ ብእሲቱ ወደቂቁ ከዊኖ ፍልጣነ። በእደዊሁ መኰንን አምነ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_12።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦"ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታምእሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥30-36።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ኢይድኅን ንጉሥ በብዝኀ ሠራዊቱ። ወያርብህኒ ኢድኅነ በብዝኃ ኃይሉ። ወፈረስኒ ሐሰት ኢያድኅን"። መዝ 32፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥17-30፣ ይሁ 1፥7-14 እና የሐዋ ሥራ 10፥3-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 18፥1-9። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው። መልካም የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል የወራዊ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከቅዱሳን መካናት ተባረከ በዚያም በቅድስት ትንሣኤ በተሰየመች ቤተ ክርስቲያን በጳጳሱ በአባ ሚካኤል እጅ ቅስና ተሾመ። ከዚያም ወደ ምስር አገር ተመልሶ በማዕልቃ ባለች በእመቤታችን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን እየጻፈ ተቀመጠ።
❤ በዚያም ወራት ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ቄርሎስ ዐረፈ። የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ መንበርም ያለ ሊቀ ጳጳሳት ነበር። ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት የአገር ሽማግሌዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰበስበው ይሾሙት ዘንድ በአንድ ምክር ተስማሙ ሰይጣን ግን ክፉዎች ሰዎችን አነሣሥቶ ተቃወሙት። ሹመቱንም አልፈቀዱም። ነገር ግን መንሳዊ አባት የነበረውን የከሊል ልጅ አባ አትናቴዎስን ሾሙት። እርሱም መንጋውን በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ።
❤ እርሱም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆሳትና የሕዝቡ አለቆች ዳግመኛ ተሰበሰቡና በእጃቸው ጽፈው አባ ገብርኤል እንዲሾም ፈቀዱ ሁለተኛም በሕቡም መካከል ሁከት ተነሳ ከሌሎችም ጋር እጣ ያጣጥሉት ዘንድ ተስማሙ ስሞቻቸውንም ጽፈው በመንበሩ ላይ አኖሩ በላዩም እየጸለዩና እየቀደሱ ሦስት ቀኖች ሰነበቱ። ከዚህም በኋላ ታናሽ ብላቴና አምጥተው በውስጡ የአባ ዮሐንስ ስም ያለበትን ክርታስ አወጣላቸው። ያም አባ ዮሐንስ ተሾመ ይህ አባ ገብርኤል ግን ለማዕልቃ ቤተ ክርስቲያን ተከራካሪ አድርገው ሾሙት።
❤ በዚያም ወራትም በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሁኖ ነበር። ይህ አባ ገብርኤልም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሒዶ በጾምና በጸሎት በሥግደትም በቀንና በሌሊት ሲጋደል ኖረ። ከቅዱሳን መነኰሳት ብዙዎች መልካም ራእይን አዩለት ከእርሷቸው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ልብስን እንደሚአለብሱት ብዙዎች ከአሕዛብ የተመለሱ ክርስቲያኖችም እንደሚያጅቡት ያየ አለ። ደግሞም ይሾምባት ዘንድ ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ሲሔድ ያየለት አለ። ቁጥር የሌላቸውንም መክፈቻዎችን ሲቀበል ያዩ አሉ።
❤ ከገዳሙም ሊወርድ ብዙ ጊዜ ይሻ ነበር ነገር ግን አልተቻለውም። ከዚህ በኋላ አባ እንጦንስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዚህ ገዳም ትወርድ ዘንድ እኔ አልፈቅድም ጊዜው ሳይደርስ አትውረድ" አለው።
❤ ከሦስት ዓመት በኋላም አንዱ አረጋዊ የከበረ መልአክ እንግዲህስ አባ ገብርኤልን ወስደው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙታል እያለ እንደሚያነጋግረው ራእይ አየ። በዚያችም ቀን የሀገረ እንጣፊ መኰንን መጣ ከእርሱም ጋር ብዙዎች መሳፍንቶች ነበሩ። አባ ገብርኤልን አምጥተው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ የሚያዝዝ የንጉሥ ደብዳቤም ከእርሱ ጋር ነበረ።
❤ ከዚህም በኋላ ያለ ፈቃዱ ወስደው በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስናን ሾሙት። ቀን እርሱ ለኢየሩሳሌም አንድ ጳጳስና ሌሎችንም ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመ። ከዚህም በኋላ ሦስት ጊዜ ሜሮን አከበረ ባረከ እንደዚህም አድርጎ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኖረ። በዚያን ጊዜም አባ እንጦንስ ተገልጦ እንዲህ አለው "እነሆ ዕረፍትህ ቀርቦአል ከዐሥራ ስምንት ወሮች በኋላ ወደ እግዚአብሔር ትሔዳለህ የዘላለም ሕይወትንም ትወርሳለህ"።
❤ ከዚህም በኋላ በክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራ ሆነ። ይህም አባት ወገኖቹን ያድን ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ሕዝቡን ይቅር አለ።
❤ ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ከመንበረ ሢመቱ ወጥቶ በምስር አገር ዓመት ሙሉ ተሠወረ። ከአንድ ምእመን በቀር ማንም አላወቀበትም በቀንና በሌሊት በገድል ከመቀጥቀጡ የተነሣም መልኩ ተለወጠ ሥጋውም ደረቀ።
❤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እርሱን ለሚፈራው ለአንድ ምእመን ሥራውን ገለጠ። እርሱም ከዚያ ቦታ አውጥቶ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አስቀመጠው በጸሎትና በቅዳሴ እያገለገለ ኖረ። ድኆችንም ይጐበኛቸው ነበር። የሚሹትንም ይሰጣቸው ነበር። ወደ ርሱ የሚመጡትንም ሕዝቦች ያስተምራቸውና ያጽናናቸው ነበር።
❤ በአንዲት ዕለትም ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስ በግልጽ ታየው እንዲህም አለው "ስለዚህ ፈጽሞ አትዘን ከዚህ ብዙ ድካምና መከራ እግዚአብሔር ያሳርፍሃልና አነሆ ምድራዊ ኑሮህን የሚፈጽም ደዌ በአንተ ላይ ይመጣል ነገር ግን ደስ ይበልህ ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብለሃልና። የዘላለም ሕይወትንና የማያልቅ ተድላ ደስታንም ትወርሳለህና" አለው።
❤ በዚያን ጊዜም በሚያስጨንቅ ደዌ ታሞ እየተጨነቀ ኖረ። ስለ ነፍሱም መውጣትና በእግዚአብሔር ፊት ስለ መቆሙ ይፈራና ይደነግጥ ነበር የእመቤታችን ማርያም ሥዕልም በዚያ ነበረ። ወደርሷም አዘውትሮ ይማልድ ነበረ በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ራሱ እግዚአብሔር በብሩህ ገጽ "ተገለጠለት መንግሥተ ሰማያትን አግኝተሃልና ደስ ይበልህ እንጂ አትፍራ እስከ ሦስት ቀንም ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ትወጣለህ" በማለት አረጋጋው። ይህንንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ በሦስተኛውም ቀን ሐምሌ 11 ቀን በሰላም አረፈ። በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ክብር ተቀበረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ገብርኤል በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 11 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለኢሳይያስ_ቀሲስ። ወግኍሥ ባሕታዊ ዘደብረ መቃርስ። ከመ አአምኀከ ዘልፈ በመሥዋዕተ ስብሐት ሐዲስ። አጒይይ እከይየ መንፈስ ቅዱስ። እስመ ለኃጥእ ተብህለ መሥዋዕቱ ርኵስ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_11።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ተፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር። ወለራትዓን ይደልዎሙ ክቡር። ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ"። መዝ 32፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 2፥1-9፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-17፣ የሐዋ ሥራ 14፥20-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ6፥20-27። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን #ለመርባስ ከሚባል አገር ሰዎች ለሆኑ #ለቅዱሳን_ዮሐንስና_ለአባቱ_ወንድም_ልጅ_ለስምዖን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና #ለእስክንድርያ_ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ ለሆነው #ሊቀ ጳጳሳት_ለቅዱስ_ለአባ_ገብርኤል ለዕረፍቱ በዓል በሰላሞ አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ በአስቄጥስ ገዳም ከነበረው ከቅዱስ አባት ኢሳይያስና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ዮሐንስና_የአባቱ_የወንድም_ልጅ_ስምዖን፦ የዚህም ቅዱስ ዮሐንስ እናቱ መካን ነበረች አባቱም ልጅን ይሰጠው ዘንድ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይለምነው ነበር ከዚህም በኋላ ልጁን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ሊአደርገው ተሳለ።
❤ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስም እግዚአብሔር ልጅን እንደሚሰጠው በራእይ ተገልጦ ነገረው። ይህን ቅዱስም በወለደው ጊዜ ዮሐንስ ብሎ ጠራው በመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስም ስም ቤተ ክርስቲያን ሠራ።
❤ ከዚህም በኋላ አድጎ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ የበጎች እረኛ አደረገው ምሳውንም ለእረኞችና ለመንገደኞች ሁል ጊዜ ይሰጥ ነበር እርሱ ግን እስከ ምሽት ይጾም ነበር። አባቱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ስለዚህ ሊአረጋግጥ ወደ እርሱ ሔደ አባቱንም በአየው ጊዜ ዮሐንስ ፈርቶ ሊሸሽ ወደደ። አባቱም "የዛሬ ምሳህን አሳየኝ" አለው ብላቴናውም "ታይ ዘንድ ግባ" አለው ወደ መጠለያውም በገባ ጊዜ አገልግሉን ትኩስ እንጀራን ተመልቶ አገኘው እጅግም አደነቀ ከልጃቸው የሆነውንም ለሚስቱ ነገራት።
❤ ከዚያችም ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ጸጋ እንደ አደረችበት አወቁ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲማር አደረጉት እንጂ በጎችን የሚጠብቅ እረኛ እንዲሆን አልተዉትም።
❤ ከዚህም በኋላ አባቱ ሊአጋባው ወደደ። እርሱ ግን ይህን አልወደደም። ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነውም ጊዜ ቅስና ተሾመ የአባቱ የወንድም ልጅ የሆነ ስምዖንም በጎቹን ትቶ መጥቶ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆነ። እርሱም ስለ ተአምራቱ የተናገረ ነው። እግዚአብሔር በእጆቹ ላይ ድንቆችንና ተአምራቶችን ገልጧልና። ደዌ ያለባቸውንም ሁሉ ያመጡአቸው ነበር እርሱም በዘይቱ ላይ ይጸልይና ይቀባቸው ነበር ወዲያውኑም ከደዌያቸው ይድኑ ነበር። እርሱም ወደርሱ የሚመጡትን ከኃጢአት ይርቁ ዘንድ ያስተምራቸው ነበር። ይመክራቸውና ይገሥጻቸውም ነበር። ከተአምራቱም አንዱ ይህ ነው በአንዲት መበለት የተሸከመችውን ገብስ ቀምቶ ለፈረሱ አበላት ያችም መበለት በዚህ ቅዱስ ዘንድ ከሰሰችው ቅዱስ ዮሐንስም ረገመው ያን ጊዜም ፈረሱ ሞተች።
❤ ዳግመኛም የንጉሥ የጭፍራ አለቃ ግብር ሊሰበስብ መጣ አንድ ዐይኑ የታወረች አንድ አገልጋይም ነበረው። ከእርሱም ተባርኮ ወዲያውኑም የታወረች ዐይኑ ተገለጠች በእርስዋም ደኅና አድርጎ አየ። ይህም ቅዱስ የሰዎችን ሥራቸውን በግልጽ ያይ ነበር ስለ ኃጢአታቸውም ንስሓ ይገቡ ዘንድ ይገሥጻቸው ነበር።
❤ ዜናው በንጉሥ ማርያኖስ ዘንድ ተሰማ ለእርሱም አንዲት ሴት ልጅ ብቻ ነበረችው ወደ ሆድዋም ከይሲ ገብቶ ለሞት ተቃረበች ከዚህም በኋላ ያድኗት ዘንድ ገንዘቡን ለባለ መድኃኒቶች ሰጠ ነገር ግን አልተቻላቸውም። ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃው የባሪያውን ዐይን እንደ አዳነ የቅዱስ ዮሐንስ ዜና ነገረው ንጉሡም ጭፍራ ልኮ ወደርሱ ሊአስመጣው ወደደ ቅዱስ ዮሐንስም በመንፈስ ዐወቀ እርሱ ግን የመንገዱን ድካምና ባሕሩን ይፈራ ነበር ያን ጊዜም ደመና መጥታ ነጠቀችው ሰርመላስ ከሚባል አገርም ወደ አንጾኪያ ከተማ አደረሰችው። ንጉሡም ዐልጋ ላይ አቆመችው ንጉሡም ደነገጠ ቅዱስ ዮሐንስም "ወደዚህ ወዳንተ ልታስመጣኝ የተመኘኸው ምስኪን ሰው እኔ ነኝ" ብሎ ነገረው። "አሁንም ልጅህን አምጣት" አለው ልጁንም አመጣ። በላይዋም በጸለየ ጊዜ ከይሲው ሳያሳምማት ከሆድዋ ወጣ። ንጉሡም ከቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሁሉ ጋር ከእርሱ ተባረኩ። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ጸጋ የሚሰጥ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።
❤ እጅ መንሻውንም ብዙ ገንዘብ አቀረበለት እርሱ ግን ምንም አልወሰደም። ንጉሡም በእርሱ ዘንድ ሊያኖረው ወደደ ቅዱሱ ግን አልወደደም ንጉሡም እንዳይሔድበት ቀሚሱን ያዘ ያንጊዜም ንጉሡ ቀሚሱን እንደያዘ ደመና ነጥቆ ወሰደው ቀሚሱም ተቆርጦ በንጉሥ እጅ ላይ ቀረ ቅዱስ ዮሐንስም በዚያች ሰዓት ወደ አገሩ ደረሰ።
❤ ንጉሡም ቤተ ክርስቲያ ሠርቶ የቀሚሱን ቊራጭ በውስጧ አኖረ ቤተ ክርስቲያኒቱም እስከ ዛሬ ድረስ የፊቃር ቤተ ክርስቲያን ተባለች። የቊርባን ቅዳሴ በሚቀደስ ጊዜም ሥጋውንና ደሙን መቀበል የሚገባቸውንና የማይገባቸውን ጻድቃንና ኃጥአንን ያያቸዋል።
❤ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ የጣዖትን አምልኮ በአቆ ጊዜ ለአባቱ ወንድም ልጅ ለስምዖንም ይህን አስረድቶት ወደ እስክንድርያ ከተማ ሔዱ በመኰንኑ ፊትም ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይም አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን ሐምሌ 11 ቀን በሰይፍ አስቈረጣቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ከሥጋቸውም ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ ለበሽተኞችም ታላቅ ፈውስ ተገኘ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ዮሐንስና ስምዖን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ትድረስን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ገብርኤል፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ ነው። የዚህም ቅዱስ ወላጆች እግዚአብሔር ሕግ የጸኑ ደጋጎች ፈቃዱንና ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ነበሩ። ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት።
❤ በአንዲት ዕለትም ቅዱሳን መነኰሳት ወደርሱ መጡ ከውስጣቸውም መልካም ገድል ያለው አንድ አረጋዊ ነበረ። እርሱም ብዙዎች ኤጲስቆጶሳት ሕፃኑን ከበው እጃቸውን እንደሚጭኑበት እንደሚባርኩትና ይሁን ይሁን ይገባዋል እንደሚሉ ራእይን አየ።
❤ ሽማግሌውም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ሕፃኑ ታላቅ እንደሚሆን አሰበ ለአባቱም "ይህን ሕፃን አስተምረው ለብዙዎች ሕዝቦች አለቃ ይሆን ዘንድ አለውና" አለው። አባቱም ሰምቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው "ከዚህ ሕፃን ምን ይደረግ ይሆን" አለ።
❤ ሕፃኑ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ አባቱ ዐረፈ። ብህና በሚባል አገርም በገድሉ የተደነቀ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ብሉያትንና ሐዲሳትንም የሚያውቅ የእናቱ ወንድም ስሙ ጴጥሮስ የሚባል ጴጲስቆጶስ ነበረ ሕፃኑንም ወስዶ አስተማረው ከተሰጠውም ጸጋና ዕውቀቱ የተነሣ ያዩት ሁሉ ያደንቁ ነበር ዲቁናም ተሾመ።
❤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሆነው ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ይህንም ኃላፊውን ዓለም ናቀ ኢጴጲስቆጶሱ አባ ጴጥሮስም በገድል ተጸምዶ ለሚኖር ለቀሲስ አባ ጴጥሮስ ሰጠው እርሱም በጥቂት ቀኖች የምንኵስናን ገድል አስተማረው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ታዩ።
❤ ከዚህም በኋላ መምህሩ ቀሲስ አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ከዚያ ተነሥቶ ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሔደ በዚያም በጾምና በጸሎት በስግደት በመትጋት እየተጋደለጨ ያለ ማቋረጥ ብዙ ዘመናት ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አባ መቃርስ ደብር ሔደ። ደብረ ማርስ ባለች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን አበምኔት አደረጉት። ሕንፃዋንም አደሰ።
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
ሐምሌ 14 የሰንበት ትምህርት ቤታችንን 12ኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቶቻችንን አጠናቀን እናንተ ወንድም እህቶቻችንን በመጠባበቅ እንገኛለን በዕለቱም ሁላችንም ነጭ በመልበስ 7:00 ሰዓት በሰንበት ትምህርት ቤታችን በመገኘት እንድናከብር እና በተለያዩ ምክንያት ለራቁን ወንድም እህቶቻችን ባሉበት ድረስ ሄደን በመጥራት በመንገር አብረን እንድንመጣ በሰዓት እንድንገኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ_፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን #ለቅዱስ_ናትናኤል_ለተባለው ለሐዋርያው #ስምዖን_ቀለዮጳ_ሰማዕትነት_ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክንድርያ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_ከላድያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት መላእክት ይጎበኙት ለነበረ ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ለነበረ #ለአባ_ብስንዳ የዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከምትታሰበው፦ ከሐዋርያው #ቅዱስ_ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) አብራ ሰማዕትነት ከተቀበለች #ከቅድስት_ቴዎና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ)፦ ይህንንም ሐዋርያ አይሁድ ጌታችንን ወንድም ያዕቆብን ከገደሉት በኋላ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሐዋርያት ሾሙት። እርሱም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ ከአይሁድ ብዙዎችን ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው ተአምራትንም አድርጎአልና በሽተኞችንም አድኗልና።
❤ ንጉሡ እንድርያኖስም ሴቶችን ከባሎታቸው እንደሚለይ ንጽሕናቸውንም እንዲጠብቁ እንደሚአዝዛቸው ስለ እርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ሐምሌ 10 ቀን እንዲቆርጡ አዘዘ ከእርሱም ጋር ቴዎና የምትባል አንዲት ድንግል ተገደለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ቅዱስ ስምዖን ቀለዮጳ) በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁላችንም የክርስቲያን ወገኖች ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ከላድያኖስ፦ ይህም ቅዱስ አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዘጠነኛ የሆነ ነው። በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ መንበር ዐሥራ አራት ዓመት መንጋውን እየጠበቀ ከኖረ በኋላ ሐምሌ 10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ከላድያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_አባት አባ_ብስንዳ፦ ይህም ቅዱስ ጥልቅ በሆነ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቆሞ ሲጋደል ኖረ መላእክትም ይጎበኙትና ዘጠኝ ክንድ ያህል በሠረገላ ከፍ ከፍ ያደርጉት ነበር። ከዚህም በኋላ ሐምሌ 10 ቀን በሰላም ዐረፈ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 10 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ናትናኤል_ዘቃና። እስራኤላዊ ንጹሐ ሕሊና። ሐዋርያ ሐዲስ ሠናየ ርሥእና። በረከተከ ከዐው ለሕዝብከ መንገለ ይትፈቀድ ፍና። ከመ ዝናማተ ይክዑ ደመና"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_10።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እስመ ናሁ ጽድቀ አፍቀርከ። ዘኢይትነበብ ኀቡዐ ጥበበከ አይዳዕከኒ። ትነዝኀኒ በአዛብ ወእነጽሐ"። መዝ 50፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ24፥13-34።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 1፥10-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥17-20 የሐዋ ሥራ 8፥14-18። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥44-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀለዮጶ) የዕረፍት በዓልና የአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ_፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ታላቁ_ገዳም #ደብረ_ወገግን_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳምን_ለመሰረቱት #ለአባታች_ለአቡነ_ሳሙኤል_የልደት (ለተወለዱበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘወገግ፦ "የአባታቸው ስም እንድርያስ የእናታቸው ስም አርሶንያ ይባላል። እነዚህ የበቁ ደጋግ ወላጆቻቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው። የወላጆቻቸው በጎ ምግባር ተክለ ሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል።
❤ ልጅም ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው "እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብለው ትንቢት ነግረዋቸውል።
❤ በትንቢቱም መሰረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ፡በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል። አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በአባቱ እድርያስ በኩል የሥጋ ዘመድ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክረስትናውን "ሳሙኤል" አሉት። ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ" ማለት ነው። ከሕፃንነትም ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኵሰውታል..."። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ።
❤ ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው።
❤ ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 9 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ዕብል_ለብእሲ_ምእመን። እንተ ይሰመይ ኅልያን። ከመ ግዕዘ ምስለ ፫ቱ ዕደው ኅብረ ፀዓዳ ልቡሳን። ያብርህ ሎቱ በውስተ መጽልም መካን። እምበረ እዴሁ ወጺኦ መስቀል ዘብርሃን"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_9።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 3፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 13፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ_፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን #ለአምስቱ_አገርኤጲስቆጶስ_ለቅዱስ_ቴዎድሮስ ለዕረፍት በዓል፣ #ለመስተጋድል_ለአባ_ኅልያን ዕረፍት በዓልና #ለቆጵሮስ_አገር_ለሆነ_ለቅዱስ_ታኦድሮስ ከእርሱም ጋር #ሦስት_ሴቶችና ያሠቃዩት ለነበሩ ለሁለት መኳንንት #ለሉክያኖስና_ለድግናንዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመብራጣንና_ከቀፈጠላ_ኤጲስቆጶስ_ከንድራኦስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከግብጻዊው_ከቅዱስ_ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሴ ቤት ከከበረችበት፣ #ከአባ_ኤሲ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ #ከአምስት_ሽህ_አምስት_መቶና_ከአራት_ጭፍሮች ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ደምረነ_ምስለ_ኵሎሙ_ቅዱሳኒከ ምስለ እለ ገብሩ ፈቃደከ እለ እምዓለም አሥመሩከ፡፡ እለ ዐቀቡ በንጽሕ ሥርዓተ ቤትከ (ወእለ ሰበኩ በሠናይ)/፪/ በሠናይ ዜናከ"። ትርጉም፡- ፈቃድህን ከሠሩ በሕይወታቸውም ካስደሰቱህ የቤትህንም ሥርዓት ከፈፀሙ ዜናህንም በመልካም ካስተማሩ #ቅዱሳንህ_ሁሉ_ጋር_ደምረን፡፡
✝ ✝ ✝
❤ #የአምስቱ_አህጉር_ኤጲስቆጶስ_ቅዱስ
#አባ_ቴዎድሮስ፦ ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር። ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው።
❤ ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም"። መኰንኑም "በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ የምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን?" አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ "አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው" አለው።
❤ መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን ሐምሌ 9 ቀን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ቴዎድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #መስተጋድል_አባ_ኅልያን፦ የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው።
❤ በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ "ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም" አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም "አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ" አላት።
❤ ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ።
❤ ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም።
❤ ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር። የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው።
❤ ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው "አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም" አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።
❤ ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኅልያን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ከቆጵሮስ_አገር_የሆኑ_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ታውድሮስ ከእርሱም ጋራ ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት #ሉክያኖስና_ድግናንዮስ፦ ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ሐምሌ_፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለኢትዮጵያዊው_ለጻድቁ ለአባታችን #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ በዐባይ ባሕር ውስጥ ስለ አገራችን ኢትዮጵያ #ለዘጠኝ_ዓመት ከጸለዩ በኋላ #ከጌታችን_ቃል ኪዳን_ለተቀበሉበት_ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባታችን_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
#በዓባይ_ባሕር_ዘጠኝ_ዓመት_እንደ_ጸለዩና_ከጌታችን_ቃል_ኪዳን_እንደተቀበሉ፦ ከዚህም በኋላ ወደ ዋልድባ ደርሶ በዚያ በዋሻው ውስጥ እየጾመ ለገዳሙ እያገለገለ አራት ዓመት ቆየ፣ ከአራት ዓመት በኋላ ከአቡ ሳሙኤል ጋራ ተገናኘ አቡነ ሳሙኤልም "የአንተ ክፍል ይህ ነው" ብሎ ቦታውን ነገረው።
❤ ከአራት ዓመትም በኋላ አረጋውያን መነኰሳትን ተሰናበታቸው እነርሱም መርቀውት የኢትዮጵያን ገዳማት ተዘዋውሮ እየጎበኘ ገዚም ወደ ሚባል አገር ደረሰ ይኸውም ጎጃም (ጎዣም) ነው በዚያ እያስተማ፣ እያጠመቀ፣ የታመሙትን እየፈወሰ፣ የዕውራንን ዐይን እያበራ፣ ሙታንንን እያስነሣ፣ በዚያ ተቀመጠ ተአምራትንም እያደረገ በጾምና በጸሎት የምታታቸውን ዕፀዋት የጥንቁልናቸውን ሥራ ሻረባቸው። እነርሱም ምታታቸውን ጥለው ንስሓ ገቡ።
❤ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ባሕር ውስጥ ገብቶ ፱ (ዘጠኝ) ዓመት ለኢትዮጵያ ጸለየ። ከጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ "የመነኰሳት መጨረሻው ከመነኰሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ይህችን ሀገር እና የኢትዮጵያን ሰዎች ምሬልሃለሁና ከዚህ ባሕር ውጣ" አለው።
❤ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ከባሕር ውስጥ ወጥቶ ተንበርክኮ ለጌታችን ሰገደ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም "የማረፊያህ ቦታ የምትሆን ምሥራቅ ወደምትሆን ወደ ዳውንት ሂድ ዳግመኛም ዝክርህን የዘከረ፣ ስምህን የጠራ፣ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ፣ የጻፈውን፣ ገድልህን ያነበበ፣ የተረጎመ የሰማውን እስከ ሰባት ትውልዶ እምርልሃለሁ ስለድካምህ ብዛት ኃጢአታቸውንም ይቅር እላቸዋለሁ" ይህን ብሎ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ። ከአባታችን ከአቡነ እስትፋንሰ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ እስትፋንሰ ክርስቶስ 9፥9-13።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከናፍሪከ_ወለአፋከ_ዘጥዕመ። ዕክለ በረከቱ ለክርስቶስ በሥጋ ማርያም ዘሐመ። እስትንፋሰ ክርስቶስ መናኒ እንበለ ትበል ጌሠመ። በጌባል ምድረ መርገም አመ። በረከትከ ቆመ ፍሬ ዕፀ በለስ መሪር ተረክበ ጥዑመ"። #መልክዐ_አቡነ_እስትፋንሰ_ክርስቶስ።
