ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多600
订阅者
-124 小时
-97 天
-1930 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ #የተባረከ_የሰኔ_ወር ቀኑ_ዐሥራ_አምስት_ሰዓት ነው። ከዚህም በኋላ ይጐድላል።
❤ #ሰኔ ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን #እስራኤል_ለተባለው_ለያዕቆብ ልጅ #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ዮሴፍና_ለሚስቱ #ለቅድስት_አሰኔት_ለዕረፍት_ቀን_መታሰቢያ_በዓል፣ ከእርሱ ተአምራት ለተገለጡ #ለሶርያ_ሰው_ለሆነ #ለቅዱስ_ለውንትዮስ_ለቤተ_ክርስቲያኑ_ለቅዳሴ ቤቱ በዓልና ለመስተጋድል ለሰማዕት #ለቅዱስ_ቢፋሞን_ለዕረፍቱ_መታሰቢያና በስሙ ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የመጀመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ ቤቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከላይኛው ግብፅ ከጣሀ አውራጃ ከሆኑ ከባልጀራሞች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ #ከሰማዕት_ቆዝሞስ_ከዕረፍቱ መታሰቢያና፣ #ከእስክድርያ_ከተማ_ሰማዕታትና #ከሊቀ_ጳጳሳት_ቶማስም_ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ #የቅዱስ_ለውንትዮስ_የቤተክርስቲያ_ቅዳሴ ቤት፦ ይኸውም ቅዱስ ለውንትዮስ በሐምሌ ወር በሃያ ሁለተኛው ቀን በሰማዕትነት በዐረፈ ጊዜ ከታላላቅ መኳንንቶች የአንዱ መኰንን ሚስት መጣች ለወታደሮቹም ብዙ ገንዘብ ሰጠች የቅዱሱንም ሥጋ ወሰደች በባሏም ልብስ ገነዘችው በሣጥንም አድርጋ በቤቷ ውስጥ አስቀመጠችው በቀንና በሌሊትም የሚያበራ መብራት በፊቱ አኖረች። እንሆም ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በመኰንኑ ባሏ ላይ በሆነ ሥራ ምክንያት ተቈጣ። በአንጾኪያም ከተማ በወህኒ ቤት አሠረው።
❤ ቅዱስ ለውንትዮስም ለሥጋው መልካም ለሠራች ለመስፍኑ ሚስት መልካም ወጋዋን ሊከፍላት ሽቶ በዚያች ሌሊት በወህኒ ቤት ለባልዋ ተገለጠለት በወህኒ ቤቱም ብርሃን ወጣ ለመኰንኑም የራሱ የሆነውን በቤቱ ያለውን የሚያውቀውን የወርቅ ልብስ ለብሶ በጐልማሳ ፈረሰኛ አምሳል ተገለጠለት።
❤ ከዚህም በኋላ እንዲህ አለው "አትዘን አታልቅስም ዛሬ ከዚህ ወጥተህ ከንጉሥ ጋር በማዕዱ ትቀመጣለህና ከዚያም ወደ ቤትህ በሰላም ትሔዳለህ"። የታሠረው መስፍንም ይህን ጐልማሳ ፈረሰኛ ስለ አየው በላዩም ስለ ወጣው ብርሃን የወህኒ ቤቱም ደጅ እንደ ተዘጋና እንደ ተቆለፈ ወደ ርሱ ስለ መግባቱ ደግሞም የራሱ የሆነውን በቤቱ ውስጥ የተወውን የወርቅ ልብስ ለብሶ ስለ ማየቱ በዚህ ሁሉ ሥራ ያደንቅ ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለውንትዮስ በዚያች ሰዓት ወደ ንጉሡ ሔደ በመኝታውም ተኝቶ ሳለ ረገጠው እጅግም ደነገጠ ለንጉሡም እንዲህ አለው "ንጋት በሆነ ጊዜ መስፍን ዕገሌን ከወህኒ ቤት አውጣው አክብረውም በክፉ አሟሟትም ሙተህ እንዳትጠፉ ወደ ቤቱ ይሔድ ዘንድ ተወው"። ንጉሡም ከግርማው የተነሣ እየተንቀጠቀጠ "እሺ ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብሎ መለሰለት። በነጋ ጊዜም ንጉሡ ወደ ወህኒ ቤት ልኮ መስፍኑን አወጣው ታላቅ ክብርንም አከበረው መልካም ልብሶችንም አልብሶ ከእርሱ ጋራ በማዕዱ አስቀመጠው። ፈረሰኛም እንደ ተገለጠለትና ይፈታው ዘንድ እንዳዘዘው ነገረው መስፍኑም አደነቀ። ንጉሡም የሥራይ ሥራ እንደሆነ አድርጎ አሰበ መስፍኑም "እኔ መጠበብንና ሥራይን አላውቅም ከእሊህ ከምትለኝም ነገሮች ማን እንደተገለጠልህ ምንም አላውቅም"። ንጉሥም ከተገለጠለት ራእይ ፍርሀት የተነሣ ክፉ ነገርን ሊናገው አልደፈረም ነገር ግን ወደ አገሩ በታላቅ ክብር ሰደደው።
❤ መስፍኑም በጎዳና ሲጓዝ ሁለተኛ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ወደ አገሩ ጠራብሎስም እስኪደርስ እያነጋገረው ያጽናናው ነበር ከዚህም በኋላ ተሠወረው። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ቤተሰቦቹን ሰላም አላቸው የእርሱን የወርቅ ልብስ የሚመስል ልብስ ለብሶ ፈረሰኛ ጐልማሳ እንደ ተገለጠለትም ነገራቸው ከወህኒ ቤትም እሥራት ያድነው ዘንድ ቃል እንደገባለት ነገራቸው። ሚስቱም ያዳነው ቅዱስ ለውንትዮስ እንደሆነ አውቃ "ብታየው ታውቀዋለህን" አለችው "አዎን" አላት ከዚያም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥዕል ወደ አለበት ቦታ አስገባችው አይቶም "የተገለጠልኝ በእውነት ይህ ነው" አለ።
❤ ሁለተኛም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥጋ ያለበትን ሣጥን ከፈተች ያንንም የርሱን የወርቅ ልብስ እንደለበሰ አየው። የፊቱንም መሸፈኛ ገለጠ የተገለጠለትና ከእሥራት ያዳነውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ። መስፍኑም ማን እንደሆነ ስለ እርሱ ሚስቱን ጠየቃት እርሷም የቅዱስ ለውንትዮስን ገድል ነገረችው መስፍኑም ይህን መልካም ሥራ ስለ ሠራች ሚስቱን አመሰገናት መረቃትም የተመሰገነ እግዚአብሔርንም በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ሥራ ስለሚሠራ አመሰገነው። መብራትና ማዕጠንትም እንዳይለየው ሚስቱን አዘዛት ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስን ጌታችን እስከ አጠፋው ድረስ እንዲሁ የምትሠራ ሆነች።
❤ ከዚህም በኋላ መልካም ቤተ ክርስቲያን አንፀው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ በዚች ዕለትም ሰኔ 1 አከበሩዋት ከሥጋውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለውንትዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ #የሰኔ_1_ስንክሳር።
+ + +
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እስመ ናሁ ዘእንተ ሠራዕከ እሙንቱ ነሠቱ። ወጻድቅሰ ምንተ ገብረ። እግዚአብሔር ውስተ ጽርሐ መቅደሱ። መዝ 10፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥42-ፍ.ም።
+ + +
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወሤሞ መልአከ አሕዛብ። ወረሰዮ እግዚአ ለቤቱ። ወአኰነኖ ላዕለ ኵሉ ጥሪቱ"። መዝ 104፥21-22። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥21-32፣ 1ኛ ጴጥ 4፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥9-23። የሚነበበው ወንጌል 24፥45-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የቅዱስ ዮሴፍና የሚስቱ የቅድስት አሰኔት የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘሰኔ #አንድ (፩)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
አስቸኩዋይ የሥራ ማስታወቂያ (ሥራ ለሌላቸው ሴት የሰንበት ት/ቤት አባላት)
የንግድ ሥራ ስልጠና በመስጠት የግል ሥራቸውን እንዲጀምሩ የሚያደርግ ጅርጅት ነው፡፡
የግል ሥራቸውን እስኪጀምሩ የድርጅቱን ስራ እየተከፈላቸው ይሰራሉ፡፡
እድሜ ገደብ የለውም
የተማሪዎቹን ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥራቸውን በቴሌግራም (0941227969) ይላኩልኝ
ቦታዎች ሳይያዙብን በፍጥነት እድሉን እንጠቀም ፡፡
❤ ከዚያም ከመሰቀል ያዳነችው ወጣት ልጅ አባት ቀረበና፣"ልጄ ዐይነ ሥውር ኹኖብኛልና ስለርሱ ለምነሽ አድኝልኝ" አላት። እርሷም ኃጢአቱን እንዲናዘዝ ጠየቀችው። ያም ወጣት መቶ ዲናር ሰጥታ ከመሰቀል ያዳነችውን አንዲት ሴት ፈቃዱን እንድትፈጽም ሲጠይቃት ባይኾንለት በግፍ ለመርከበኞች እንደሸጣትና ከነርሱም ተለይቶ እንደተመለሰ ወዲያውኑ ዐይነ ሥውር እንደኾነ ተናዘዘ። እርሷም "እንዲህ ያለህ ቀጣፊ ነህ፣ ኾኖም አሁን ግን እግዚአብሔር በግልጥ እንድትናገር አድርጎሃል" ብለ ገሠጸችውና በዐይኖቹ ላይ ጸልያ አዳነችው። ግብጻዊውም ከዕብራዊ አገልጋዩ ጋር ቀረበና እንድትፈውሰው ጠየቃት። እርሱም ከመቃብር ውስጥ ያወጣት አርሷ እንደኾነች፡ከቶ አላወቃትም ነበር። እርሷም ዕብራዊው የሠራውን ክፉ በደል ከተናገረ እንደምትፈውሰው ነገረችው። ያም፡ግብጻዊ "ያደረግኸውን ፈጥነህ ተናገር፣ አለዚያ ግን እዚሁ ጥዬህ እመለሳለሁ" አለው። ዕብራዊውም "አንዲት እስራኤላዊት ሴት እኛ ዘንድ መጣች። ከእኔ ጋርም አንድ እንድትኾን ጠይቅኋት፣ አይኾንም ባለችኝም ጊዜ የአንተን ልጅ ከእናቱ ወስጄ በወቅለምት ገደልሁና ከአጠገቧ አደረግሁ፣ ወቅለምቱምንም እጇ ከሚደርስበት ቦታ አኖርሁት፣ ይህንም ማድረጌ ፈቃዴን ስላልፈጸመችልኝ አንተ እንድትገድላት ብዬ ነው" አለው። ከዚህም
በኋላ ጸለየችለትና አዳነችው።
❤ ከዚህም በኋላ የዚያች ደሴት ሰዎች ኹሉ የሚሹትን ካገኙ በኋላ ኹላቸውም ኼዱና ቅድስት አርዋ እና ባልዋ ቀሩ። ከዚያም ትጠይቀው ጀመረች። "እንዲህ የምትናገርላት ሚስትህ እኔን ትመስላለችን?" አለችው። እርሱም "አፍንጫዋ ዐይኖቿ ኹሉ አንቺን ይመስላሉ። እርስዋ ካልሞተች አንቺ እርሷ ትኾኝን?" አለ። እርስም መልሳ ሚስቱ አርዋ እንደኾነች ነገረችው። ከዚህም በኋላ የቅድስት አርዋ ባል ወደርሷ ሊደርስ ወደደ። እርሷ ግን "እዚህ አይኾንም፣ ታጥቤ እመጣለሁ ወደ ቤታችን" አለችውና እርሱ ወደ ቤት ኼደ። እርሷም ወደ ዋሻዋ ተመለሰችና ሰውነቷን ታጥባ ንጹሕ ልብስ ከለበሰች በኋላ ከዋሻው ወጣች። ቀድማ ግን ጌታችንን እንዲህ ስትል ተማጸነች። "ጌታዬ አምላኬ ከወደድኸኝ ነፍሴን ተቀበላትና ዳግመኛ ከወንድ ሳልገናኝ ልሙት" በማለት ጸለየች። ወዲያውም ሰገደችና ዐረፈች። ባልዋም መጣና ዐርፋ አገኛት። ወስዶም ቀበራት። ከእናታችን ከቅድስት አርዋ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን ጸሎቷ ይማረን!። ምንጭ፦Dn Melaku Yifru Zewulude Birhan.
+ + +
❤ #አባ_ሚካኤል፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ለእስክንድርያ ጳጳሳት ስሳ ስምንተኛ ነው። የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ስለ ተማረ አዋቂ ነበር። በልቡም አጠናቸዌ በቃሉም አጠናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ንጸሕት ሰውነቱ ከአምላክ በተገኘ የምንኵስና መንገድ በመጋደል ክብር ይግባውና የክርስቶስ ጭፍራ ልትሆን ወደደች። ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በውስጡ ብዙ ዓመታት ኖረ ቅስናም ተሾመ።
❤ ከዚህም በኋላ በግጽ አገር ወደ አለ ወደ ሠንጋር ወጣ በዚያም በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደርጎ አርባ ዓመት ኖረ ከዚያም የሚበዛ ኖረ በዚያም ዋሻ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ። የትሩፋቱ የጽድቁምና የዕውቀቱ ወሬ በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ተስማሙ ወዲያውኑ ይዘው በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
❤ በተሾመም ጊዜ በጎ አካሔድን ሔደ የዚህን ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ ተወ። ከሚገባው ከሚአመጡለት ገጸ በረከት አንድ ዲናር ወይም አላድ ጥሪት አድርጎ አላኖረም። ከእርሱ በየጥቂት እየተመገበ የቀረውን ለድኃና ለጦም አዳሪ ይሰጣል ለአብያተ ክርስቲያናትም ለንዋየ ቅዱሳትና ለቅዱሳት መጻሕፍት መግዣ ያደርገዋል። ሕዝቡንም ያስተማራቸዋና ይገሥጻቸው ይመክራቸውም ነበር። አንድ ጊዜ ከመጻሕፍት አንድ ጊዜም ከቃሉ።
❤ መልካም አገልግሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው የሕይወትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ሊሰጠው ወዶ የአንዲት ቀንና የአንዲት ሌሊት ሕማም በላዩ አመጣ። ከቶ አልተናገረም በሚሞትበትም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን አመሰገነው ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ። ነፍሱንም ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ግንቦት30 ቀን ሰጠ መላ ዕድሜውም ዘጠና ዓመት ከስምንት ወር ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ሚካኤል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። የግንቦት ወር ንባብ ተፈጸመ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ለመንግሥተ ሰማያት የተዘጋጀን ያደርገን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የንግቦት30 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለቆሮስ ለወልደ ማርያም ዘተልእኮ። መጠነ ፫ቱ ዓመት በኢያውክኮ። ወእምድ ኅረዝ ዐርገ ካዕበ ምስለ ጳውሎስ ተወሲኮ። እምነ ሥቃይ ዘረከቦ ወእምንዳቤ ዘሆኮ። አመ ፍጻሜ ወርኅ አዕረፈ በሠናይ አምልኮ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_30።
+ + +
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ኃጢአትየ ዘበንእስየ ወዕበድየ ኢትዝክር ሊተ። ወበከመ ሣህልከ ተዘከረኒ። በእንተ ምሕረትከ እግዚኦ"። መዝ 24፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 7፥44-ፍ.ም።
+ + +
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ ጽድቅ ወምጽዋት ያበድር እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ይሁብ ክብረ ወሞገስ። እግዚአብሔር ኢያስተፄንሶሙ እምበረከቱ ለእለ የሐውሩ በየዋሃት"። መዝ 83፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 2፥27-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 18፥23-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ቆሮስ የዕረፍት በዓል፣ የቅድስት ዜና ማርያም የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በተመለከታትም ጊዜ ከመልኳ የተነሳ አደነቀ። ከርሱም ጋራ በመኝታ አንድ እንድትኾን በፈለገና መሻቱን በነገራት ጊዜ "እኔ አንተን ከዚህ ዓለም ምድራዊ እሳት ነጻ አደረግሁህ፣ አንተ ግን በሰማዩ እሳት ትጥለኝ ዘንድ እንዲህ ክፉ ምክንር ትመክረኛለህን?" አለችው። እግዚአብሔርንም እንደምትፈራ ባየ ጊዜ ተዋት። በኋላም በመርከብ የሚኼዱ ብዙ ሰዎችን ተመለከተና "በገንዘቤ ኹሉ የገዛኋት አንዲት አመት(አገልጋይ) አለቺኝ፣ ገንዘቤን መልሳችሁ ከሰጣችሁኝ እርሷን እሸጥላችኋለሁ" አላቸው። ከእነርሱም እጅግ ብዙ ወርቅ የነበረው(ይኸውም ማለት አንድ፡መቶ ዲናር የነበረው) አንድ ሰው ነበር። ያም እናታችን አርዋ ከስቅላት ያዳነችው ሰው ለዚያ ሰው በዚህ ገንዘብ ሸጣት። የገዛትም ሰው መርከብ እንድትሳፈር አደረጋት፣ መልኳንም ባየ ጊዜ ወደዳት ከርሷም ጋር ይተኛ ዘንድ ተመኘና እጇን ያዘ። በዚህም ጊዜ ፀሐይ ጨለመች፣ ነፋሳቱም እጅግ በኃይል ነፈሱ፣ ማዕበላቱም ፈጽመው ተነሱና መርከቡንም ሊያሰጥሙት ደረሱ። በዚያም በመርከቡ የነበሩት ኹሊ ወደ እግዚአብሔር፡ማልቀስና መጮህ ጀመሩ።
ቅድስት አርዋም "እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ እምነቱን በእግዚአብሔር ያደረገ ከቶ አይሞትም፣ በርሱም የሚያምን ከቶም አይጠፋም" በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነች።
❤ ወደ እነዚያም ሰዎች ዘወር አለችና "በማይገ'ባ የገዛችሁኝ እናንተ ሰዎች! እናንተም በማይገ'ባ የሸጣችሁኝ ሰዎች! እኔ ከቶ አመት(አገልጋይ) አይደለሁም፣ ነገር ግን እመቤት ነኝ እንጂ። እኔ የምላችሁንም የምታደርጉ ከኾነ ከዚህ መከራ የምትወጢበትን መንገድ እንዲያፈርግላችሁ እጸልያለሁ"። እነርሱም "እናደርገው ዘንድ የምትነግሪንን ኹሉ እናደርጋለን" አሏት። እርሷም "ይህ ሰው የሸጠኝ ከእኔ ጋር የተኛ ዘንድ ስላላሰናበትሁት ነው፥ ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ከቶ የማይወደው ምግባር ነው" አለቻቸው። ሰዎቹም ኹሉ ገንዘብ አወጡና ዐሥር ሺህ ዲናር እርሷን ለገዛት ሰው ሰጡት። እርሱም ነጻ አደረጋት። አርዋም ጸለየችና ማዕበሉ ጸጥ አለ፣ ነፋሳቱም ቆሙ። ፈጽሞም ጸጥታ ኾነ። በዚያም የነበሩት ኹሉ ወደድዋትና በርሷም ላይ ሊወድቁ ተመኙና "እኔ እኔ" እየተባባሉ ሲገፋፉ ወዲያውኑ ነፋስ መጣና መርከቡን ሰባበረው። እነርሳቸውም ኹላቸው በባሕሩ ላይ ተበተኑና ሰጠሙ። ገንዘባቸውም ኹሉ ከርሷ ጋር ቀረ። የወንድ መታጠቂያ ሱሪም ሰራችና ራስዋንም መልክዋን ልክ እንደወንድ ተቀብታ በልብሷም ፈጽሞ ተመሳሰለችና በመርከብ ኼደች።
❤ ወደ አንድ ትልቅ ወደኾነ ብዙ ሰዎችም፡ወዳሉበት ደሴት ደረሰችና ወደ ንጉሡ ኼደች። ንጉሡም ባያት ጊዜ ገና ጽሕሙ ያላደገ ወጣት ወንድ መስላዋለች። ኋላም ቀርባ "እነሆ ገንዘቤ እጅግ ብዙ ነው፣ በዚያም ሙሉ ኹኖ የተጫነ መርከብ አለ። የዚያም ባለቤቶቹ የነበሩት በባሕር ሰጥመው ሙተው ጠፍተዋልና እንደምታየው እኔ አንዲት ደካማ ቀርቻለሁ። እኔም እንዳልጠፋ እሰጋለሁና ይህን ለአንተ አደራ እሰጣለሁ። ለሞቱትም ሰዎች ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው የድርሻቸውን ትሰጣቸው፡ዘንድ ደብዳቤ እጽፍልሃለሁ"። ንጉሡም ከሰዎቹ ገንዘብ ምንም ምን እንዳልወሰደች ተመልክቶ አደነቀ። ገንዘቡንም ተቀበለ። ቅድስት አርዋም እግዚአብሔርን በመፍራት ሳለች እግዚአብሔር ልመናዋን ሰማት፣ በጸሎትዋም ብዙ ድውያን ተፈወሱ። ከዚያም ተነስታ ወደ ባሕር ዳርቻ ኼደችና በዚያ በዋሻ ገብታ በገድል ተጸምዳ መኖር ጀመረ። የዚያችም ደሴት ንጉስ በጽኑዕ ታመመና ሰዎች ወደርሱ ተሰበዘቡ። ከዚያም በርሱ ፈንታ ሊነግሥ የሚገባውን ቢጠይቁት "በመርከብ እጅግ ብዙ ገንዘብ አምጥቶ የሰጠኝ አንድ ወጣት አለና እርሱ ከኔ በኋላ ንጉሥ ይኾን ዘንድ መርጫለሁ" አላቸው። እነርሱም በዚህ ነገር አደነቁና እጅግ ደስ ተሰኙ፥ "ከአንተ በኋላም፡ሊነግስ ይገባዋል፣ ይደልዎ" አሉ። ከዚህም፡በኋላ ንጉሡ ሞተ። ቅድስት አርዋንም በነርሱ ላይ አሰለጠንዋት፣ እርስዋም ወጣት ወንድ መስላቸው ነበር። እርሷም በልቧ እንዲህ አለች፥ "ይህ ቤተ መንግሥት ከእግዚአብሔር ያርቀኛል"። ከዚያም ይህን በነርሱ ላይ መሰልጠንን እና ንግሥናውን እንደማትፈልግ መናገር ወደደችና ሕዝቡን ኹሉ ሰብስባ እንዲህ አለች።
❤ "ከእናንተ ዘንድ ሴቶች ልጆችና እኅቶች ያሏችሁ ኹሉ በወርቅና በሐር በንጹሕም ልብስ አስጊጣችሁ ወደ እኔ አምጧቸው፥ ለእኔም ሚስት የምትኾነኝን እመርጣለሁ" አለቻቸው። እነርሱም ካመጡላት በኋላ ቅድስት አርዋ ከነዚያ ሴቶች ጋራ ለብቻዋ ከኾነች በኋላ የተሸፈነችበትን መሸፈኛዋን ኹሉ አውልቃ ተመለከቷት። ከመልከ መልካምነቷም የተነሳ እጅግ አደነቁ። እጅግም የተዋበች እንደኾነች ተመለከቱ። ምንም ወንድ ሳታገባ ብትመራቸውም እጅግ ደስ እንደሚሰኙ ነበሩ። እርሷ ግን በዚህ መቆየትን አልወደደችምና ወደ ዋሻዋ ተመልሳ በዚያ በገድል ተጸምዳ መኖርን ቀጠለች። በጸሎት የመትጋትዋና ድንቆችን የማድረጓ ዜና፣ ድውያንንም በጸሎት ኃይል የመፈወሷ ነገር በአገሩ ኹሉ ተሰማ።
❤ የአርዋም ባል(በዚህ ጊዜ ደክሞና አይነ ሥውርና ሽባ ኹኗል) ከብዙ ጊዜ በኋላ ወደ ቤቱ ተመለሰና። ቅድስቷን ባጣት ጊዜ ወንድሙን ሚስቴን አርዋን ምን አደረግህባት አለው። ወንድሙም መለሰና "ከወንድ ጋር አንድ ስትኾን አገኘናት፣ ከዚያም በድንጋይ ወገርናትና ገድለን ቀበርናት" አለው። የአርዋም ባል ዝም አለና ከብዙ ቀናት በኋላ ድውያንን የመፈወሷንና ሌሎችንም ድንቅ ዜናዎቿን ሰማና ወደ ወንድሙ ሄደና"በደሴቱ የምትኖር በጸሎትዋ የምትፈውስ አንዲት ቅድስት አለችና ወደዚያ ውሰደኝ" አለው። ወንድሙም "እዚያ ድረስ የምትኼድበትን አቅም አለህን" አለው። እርሱም "ተነስተን እንሂድ ምናልባት እግዚአብሔር ቢምረን" እያለ ለመነው። ኹለቱም ሰዎች ተያይዘው ወደርሷ ሲኼዱ በመንገድ ላይ አርዋ በመቶ ዲናር ነጻ ያወጣችውን ወጣት (አሁን ግን አይነ ሥውር ኹኖ ሳለ) እና የዚያን ግብጻዊ ጌታውን ሕጻን ልጅ የገደለውንም ዕብራዊ አይነ ሥውርና ድውይ ኾኖ በጌታው እየተመራ ሲወስደው አገኟቸው። አርዋ በመቶ ዲናር ያዳነችው ወጣት በአባቱ እየተመራ፣ የቅድስት አርዋ ባል ወንድም የቅድስት አርዋን ባል እየመራ፣ ያም ዕብራዊ ደግሞ በግብጻዊ ጌታው እየተመራ ኹላቸውም ከቅድስቲቷ ፊት ቀረቡ።
❤ እርስዋም በተመለከተቻቸው ጊዜ ኹሉንም አወቀቻቸው። እነርሱ ግን ከቶ አላወቋትም ነበር። በኋላም ወደ ዋሻዋ ገባችና ተመልሳ ወደ እነርሱ ወጣች። ባልዋም "አድኝ፣ እነሆም ገንዘብ እሰጥሻለሁ" አላት። እርሷም መልሳ "ከድውያን ገንዘብ አልወስድም፣ ከአንተ ግን እወስደዋለሁ፣ ወንድምህም ሊናገረው የሚገባው ሌላም ኃጢአት አለና የሠራውን ኹሉ ከዚህ ይናገረው እናም እንድትድን እንጸልይልሃለሁ" አለችው። እርሱም "ይህች ሴት በሚገ'ባ ተናግራለችና በል ያደረግኸውን ተናገር" አለው። እርሱም "ሚስትህን ጎበኘኋትና ከኔ ጋር እንድትተኛ ጠየቅኋት፣ አይኾንም ባለችም ጊዜ አራት የሐሰት ምስክር አስመስክሬባት ሕዝቡ በድንጋይ ወግረው እንዲገድሏት አደረግሁ" ብሎ ተናዘዘ። የአርዋም ባል "ሚስቴን እንዲህ በግፍ በመግደልህ እጅግ ክፉ አድርገሃል፣ አንድ አባትና አንድ እናት ነው ያለን፣ ላለፈው ነገር እንግዲህ ምን እናደርጋለን? ይቅር ብዬሃለሁ" አለው። አርዋም በባልዋ ዓይን ላይ ጸለየችና ዐይኑ ተከፈተ፣ እግሮቹም ከሽባነታቸው ፈጽመው ተፈቱ፣ መላው አካሉም ፈጽሞ እንደቀድሞው ደህና ኾነ።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ቆሮስ_ለዕረፍት፣ #ተጋዳ_ለሆነች_ፍትወተ_ሥጋን_ድል_ላደረገች በበጎ ሥራዋም እግዚአብሔርን ደስ ላሰነች #ለቅድስት_አርዋ_ለዕረፍት በዓልና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስሳ_ስምንተኛ_ለሆነ ለእስክድርያ ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ሚካኤል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። ተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕት_ዲማዲስ_ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ቆሮስ፦ ይህም ቅዱስ ጌታችን በሚያስተምርበት ወራት ሦስት ዓመት አገልግሎታል ከዕረገቱ በኋላም ሐዋርያትን አገልግሏቸዋል ከእርሳቸውም ጋራ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ።
❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ጋራ በመሆን መልእክቶቹንም ወደ ብዙ አገሮች ተሸክሞ በመውሰድ አገለገለው። ከአይሁድና ከአሕዛብም ብዙዎቹን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትና አጠመቃቸው።
❤ ከዚህም በኋላም በምሥራቅ ወዳሉ አገሮች ሔደ ከምኵራቦችም ብዙ መከራ ደርሶበት ግንቦት 30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቆሮስ ጸሎት ይማረ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ #ተጋዳ_የሆነች_ፍትወተ_ሥጋን_ድል_ያደረገች #ቅድስት_አርዋ፦ ይህችውም ቅድስት እስራኤላዊት ናት። ባልዋም እጅግ ብዙ ሀብት ያለው ባዕለ ጸጋ ነው። እርስዋም በውበትዋ በሥነላህይ በዚያ ከነበሩት ማንም ማን የማይተካከላት ሴት ናት። ባልዋም በንግድ ምክንያት ወደ ሩቅ አገር በኼደ ጊዜ ቤቱንና ንብረቱን ኹሉ ለወንድሙ አደራ ሰጥቶ ኼደ። የሚኼድበትም መንገድ ሩቅ ነበርና ለወንድሙ ኹሉንም ነገር አደራ ብሎ ወጣ። የባልዋም ወንድም ከጊዜ በኋላ ወደ እናታችን ይቀርብና "እኔ ባልሽን፡ስለፈራሁ እንጂ አንቺን ከወደድሁሽ ቆይቻለሁ፥ አሁን ግን እርሱ ርቆ ኼዷልና ስለዚህ ከአንቺ ጋር ላድር እወዳለሁ" በማለት ከእርሱ ጋራ አንድ እንድትኾን ይጠይቃታል። እርሷም "ምን እንኳ ባሌ ርቆ የኼደ ቢኾን እግዚአብሔር ሩቅ ነውን? ባሌ ሊያየኝስ ባይችል እግዚአብሔር ከሰማይ ሊያየኝ አይችልምን?" በማለት ገሠጸችው። እርሱም ተዋትና ወጣ።
❤ ከርሷም ወጥቶ በመንገድ ሲኼድ ግን ሰይጣን ከመንገድ ላይ አገኘውና እንዲህ አለው፣ "ፈጥነህ ወደርሷ ተመለስ፣ እኔም የወደድኸውን ኹሉ አደርግልሃለሁ" አለው። እርሱም ተመለሰና እንዲህ አላት፣ "እንግዲህ አሁን አንዱን ምረጭ፣ ከእኔ ጋራ የበመኝታ አንድ የምትኾኝ ከኾነ በሚገባ እንከባከብሻለሁ፣ ነገር ግን ይህን አይኾንም ብትዪኝ እንድትወገሪ አደርግሻለሁ" አላት። ቅድስት አርዋም መለሰችና "ምን ልታደርገኝ ትችላለህ" አለችው። ያም ሰው "ከእሥራኤል የለበሩ ሰዎች መኻከል ምስክሮችን አስነሳብሻለሁ፣ ባልሽ ወደ ሩቅ አገር ሲኼድ ሌላ ሰው አግብተሻልና"። እርሷም "አንተ የባሌ ወንድም ነህ፣ ከአንተም ጋር ከቶ እንዲህ አላደርግም። የወደድኸውን አድርግ፣ ከአንተም እጆች ቸሩ አምላኬ እግዚአብሔር ያድነኛል" አለችው። እርሱም ፈጥኖ ወጣና ወደ አገረ ገዢውና ወደ ሕዝቡ ኼደ። እነርሱም ኹላቸውም ተሰበሰቡ። እርሱም እንዲህ ሲል ቅድስት አርዋን ከሰሳት፣ "የወንድሜ ሚስት ባልዋ ወደ ሩቅ አገር ሲኼድ ሌላ ሰው አግብታለች" በማለት። እንዲህም ባላቸው ጊዜ ቅድስት አርዋን ይዘው አመጧትና ከአገረ ገዢው ፊት አቁመው የሐሰት ምስክር አቆሙባት። እሊያንም አራት የሐሰት ምስክሮች የባልዋ ወንድም "ከሌላ ወንድ ደርሳለችን?" ሲል ቢጠይቃቸው "አዎን ከሌላ ወንድ ደርሳ አይተናታል" ብለው በሐሰት በማያውቁት መሰከሩባት።
❤ አገረ ገዢውም ነገሩን ስንኳ ገና ሳይመረምር በዚህ ፈረደባትና ከከተማው ወደ ውጭ አውጥተው አገረ ገዥውም አብሮ በድንጋይ ወገሯት። ከፊቷም እጅግ ብዙ ደም እንደ ውሃ ፈሰሰና ሞተች። እርስዋም ጅግ መልከ መልካም ነበረችና (እሥራኤል በልማዳቸው በድንጋይ የወገሩትን ሰው የማይቀብሩት ኹነው ሳለ እርስዋን ግን ስለመልኳ ሲሉ) ቆፍረው በዚያው ቀበሯትና ተመለሱ። በኋላም አንድ ግብጻዊ ነጋዴ ከመንገድ አምስት ግመሎቹን ጭኖ በዚያ ሲያልፍ ከቅድስት አርዋ መቃብር አካባቢ ድምጽ ይሰማና ሲመጣ ቢመለከት ቅድስት አርዋን ልክ እንደፀሐይ ስታበራ አገኛት። እጇንም ሰጠችውና ከዚያ እንዲያወጣት ውኃም እንዲያጠጣት ጠየቀችው። እርሱም አወጣትና ውኃ ከሰጣት በኋላ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ባለ መድኃኒትም አምጥቶላት ከቀድሞ ይልቅ በእጅጉ ደህና ኹና ተነሳች። ከዚያም በኋላ ይህ ግብጻዊ ቅድስት አርዋ እጅህ መልከ መልካም ነበረችና የርሱ እንድትኾን ተመኘ። ኋላም ከርሱ ጋራ እንድትተኛ ቢጠይቃት እርስዋ ግን "እግዚአብሔርን መትፈራም፣ ስለራስህስ አታዝንምን፣ ስለ ፍርድ ቀንና ስለዓለም ፍጻሜስ አታስብምን ከቶ አታስብምን? ከአንተ ጋር ከቶ እንዲህ አላደርግም፣ ስለምንስ ባሌን እበድለዋለሁ?" አለችው። እርሱም ትቷት ወደ ውጭ ወጣ።
❤ ለዚህም ሰው የሚያገለግለው አንድ ዕብራዊ ሰው ነበር፣ ከዚህም በኋላ እርሱ ወደርሷ ገባና "አንድ እንድንሆን እወዳለሁና ፈቃዴን ፈጽሚልኝ" አላት። "እንደውሻ የኾንህ አንተ ከእኔ ዘወር በል!" በማለት ገሠጸችው። ይህም ሰው ፈቃዱን ስላልፈጸመችለት ቂም አደረገና ለዚያ ግብጻዊ ጌታው ምንም ምትክ የሌለው አንድ ሕጻን ልጅ ነበረውና፣ ያንን ሕጻን ልጅ ከእናቱ አጠገብ ተኝቶ ሳለ ሳታውቅ አንስቶ ወስዶ በወቅለምት ከገደለው በኋላ ከቅድስት አርዋ፡አጠገብ አምጥቶ አስቀመጠው። ወቅለምቱንም እጇ ከሚደርስበት ርቀት አቅርቦ አስቀመጠው። እንዲህም ማድረጉ ያ ግብጻዊ ጌታው በዚህ ተቆጥቶ ቅድስት አርዋን ይገድላት ዘንድ ነው። በኋላም የሕጻኑ እናት ተነስታ ልጇን፡ልታጠባ ብትፈልገው አጣችው። ስትመጣም ከቅድስት አርዋ አጠገብ ሙቶ አገኘችው። እናቲቱም ከበር ወጣችና አሰምታ መራራ ልቅሶን አለቀሰች። ሰዉም ኹሉ ተሰበሰበ። ያም ግብጻዌ ነጋዴ መጥቶ እናታችን አርዋን "ስለምን ስለበጎ ፈንታ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር አደረግሽ? ከሞት አዳንሁሽ፣ ከመቃብርስ ያወጣሁሽ አይደለምን?" አላት። እርሷም መልሳ፣ "በሚገ'ባ ጠይቀኸኛል፣ ከመቃብርም ቦታ አውጥተኸኛል። እንግዲህ ታዲያ እንዲህ ስላደረግህልኝ በጎ ነገር ስለምን ብዬ ልጅህን በመግደል በክፉ እመልስልሃለሁ? ከጥቂት ጊዜ በፊት ልታገባኝ ስትጠይቀኝ እኔ በአንተ ላይ የተመኘሁት ምን ክፉ ነገር ከቶ ነበር? እግዚአብሔርን ከመፍራት የተነሳ አይኾንም አልሁ እንጂ። እንግዲህ ከዚህ የሚበልጥ ኃጢአት እሠራ እና ሰው እገድላለሁን? ልጅህን ፈጽሞ አልገደልሁትም" አለችው።
❤ ግብጻዊውም "እንግዲህ ላቆይሽ አልችልምና ከዚህ ኺጂልን"። ለራስዋም እንዲኾናት መቶ ዲናር ሰጣትና "ከዚህ በኋላ ከቶ በዚህ ኹኔታ ልቆይሽ አልችልምና ከዚህ ኺጂ፣ በእኔ ላይ የመጣውን ከቶ አላወቅሁትምና"። እርስዋም ከዚያ ወጥታ በመንገድ ስትኼድ ወደ ከተማው ስትቀርብ አንድን ሰው ከዛፍ ላይ እያሰቃዩ ሲሰቅሉት ተመለከተች። ቀርባም በምን ምክንያት እንደሚሰቅሉት ስትጠይቅ መቶ ዲናር ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እንደሚሰቅሉት ነገሯት። እርሷም ለራስዋ የያዘችውን መቶ ዲናር ከፈለችና ሰውየውን ነጻ አደረገችው። ያም ሰው አባቱን ማን ነጻ እንዳደረገው ሲጠይቅ አባቱ እርሱ ነጻ፡እንዳላወጣው ነጻ ያወጣችው መልከ መልካም የኾነች አንዲት ሴት መኾንዋን ነገረው። ብዙ ሲፈልጋትም ከቆየ በኋላ በመንገድ አገኛት።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ ጌታችን በዕለተ
አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት በማሰብ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት #ደርጣ (አዋህዳ) ትመመገብ ለነበረች ለታላቋ እናት #ለቅድስት_ዜና_ማርያም_ለልደት_በዓል፣ #ለቅድስት_ወለተ_ማርያም_ዘጎንደር_የዕረፍት በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ #ጻድቋ_ቅድስት_ዜና_ማርያም፦ ከአባቷ ከቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ከእናቷ ከቅድስት አመተ ማርያም በ11 መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በምድ ነጋሲ በጎጃም ምድር ግንቦት 30 ቀን የተወለደች ሲሆን ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ በንፅህ ድንግልና በምድረ ሂንፍራንስ ጣራ ገዳም አካባቢ በሚገኘው በአቡነ እንድርያስ ዋሻ ለ25 ዓመት በጾም በፀሎት ምንም አይነት የላመ የጣፈጠ እህል ሳትቀምስ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) በመዘፍዘፍ ከ3 ቀን በኃላ በመመገብ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ላይ የቀመሰውን መራራ ሐሞትን በማሰብ ሙሉ ሕይወቶን እየተመገበች ታላቅ ተጋድሎዋን ፈፅማለች፡፡ ከዚህ የተነሳ ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜ ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ ተብሎ እስከ አሁን ድረስ በስሞ እየተጠራ ይገኛል፡፡
❤ ከአቡነ እድርያስ ዋሻ በመቀጠል ከአዲስ አበባ ተነስተን ስንጓዝ አዲስ ዘመን ከተማ በስተቀኝ በኩል ተገንጥለን 15 ኪሜ ያክል የጥርጊያ መንገድ እንደተጓዝን በስሟ የተሰየመውን ደሪጣ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ገዳም ላይ ቀሪ ሕይወቶን ምንም አይነት ዋሻ ባልነበረበት በከፍተኛ ተራራ ላይ እጅግ አስቸጋሪ ቀዝቃዛ አየር ባለበት ብርዱን፣ ፀሐዩን፣ ቁሩን፣ ረኃቡንና ጥሙን በመቋቋም ራቁቶን በመሆን መራራ ምግቦችን አዋህዳ በመመገብ በጾም በፀሎት በመትጋት አስቸጋሪ የሆነውን ተጋድሎዋን በመፈፀም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን በታላቅ ክብር አርፋለች፡፡
❤ በዚህም ወቅት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አላፋት ቅዱሳ መላዕክት ጋር እንዲሁም ከሐዋርያት ፣ ከሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከደናግል ጋር በመሆን ከሰማይ በመውረድ በታላቅ ክብር ዕረፍቷን አክብሮላታል ታላቅ ኪዳንም ገብቶላታል፡፡
❤ በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ላይ ወይንም በአሁኑ ሰዓት መቃብሯ በሚገኝበት ዋሻ ቤተመቅደስ አካባቢ በተጋድሎዋ ጊዜ ራቁቷን በሆነች ሰዓት መላ ገላዋን የሸፈነላት ፀጉር በእየ ዛፎቹ ላይ እስከ አሁን ድረስ አለ፡፡ ይህም የጸጉር አምሳያ ከገዳሙ በመውሰድ ብዙ ሰዎች በቤታቸው በመታጠን ከአስም እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች እየተፈወሱና እየዳኑ ሲሆን ታላላቅ ታምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡
❤ በዚህ ገዳም ከሌሎች ገዳማት ለየት የሚያደርገው ታሪክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ በመውረድ ራሱ የባረከው ልዩ ታሪክ ያለው ጠበል የሚገኝ ሲሆን ይህም ጠበል በቦታው ላይ ሆኖ የተጠመቀ ፣ የጠጣ ፣ አልያም በአለበት ቦታ ሆኖ የተጠቀመ እስከ አሁን ድረስ መካን የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ልጅ የሚያገኙ ከመሆናቸው ባሻገር ከማንኛውም ከተለያዩ በሽታዎች በመፈወስ ታላላቅ ታምራትን እየሰራ ይገኛል፡፡
❤ በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱስ ላሊበላ በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሰረት ወደዚሁ ታላቅ ስፍራ በመምጣት የጻድቋ ማረፈያ መታሰቢያ ዋሻ ቤተ መቅደስ በመፈልፈል የሰራላት ሲሆን በመቀጠል አፄ ይስሐቅ በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህን ገዳም በስሟ በመገደም በዚሁ ዋሻ ውስጥም የጻድቋ የቅድስት ዜና ማርያም መቃብሯ እንዲሁም የመታሰቢያዋ ፅላት የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር በአካባቢው ያሉት ሕዝበ ክርስትያን ከካህናት ጋር በመሆን ሥርዓተ አምልኮ በመፈፀም እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
❤ ይህ ዋሻም አስቀድሞ ሦስቱ ቅዱሳን ማለትም አቡነ እንድርያስ ዘጣራ ገዳም ፣አቡነ ተክለኃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ፣ ጻድቋ ቅድስት ዜናማርያም ዘደሪጣ ውስጥ ለውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በፀጋ እግዚአብሔር ይገናኙበት የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓትም እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳን ይመላለሱበታል፡፡
❤ ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም የተሰጠ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ መርጦና ፈቅዶ በጻድቋ አማላጅነት ካለበት ስፍራ ተነስቶ የጻድቋ ደጃን የረገጠ ለ3 ግመል ጭነት ጤፍ ወይም የሦስት አህያ ጤፍ ያህል ነፍሳትን እምርልሻለሁ፤ ከሲዖልም እሳት ነፍሳትን አወጣልሻለሁ የሚል ቃል ኪዳን ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ተሰቶታል። ከእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ማኅበረ ዜማ ማርያም ካዘጋጁት በራሪ ወረቀት የተወረደ።
+ + +
❤ #ቅድስት_ወለተ_ማርያም_ዘጎንደር፦ ትውልዷ ጎንደር ሲሆን በዐፄ ወናአግ ሰገድ ዘመን የነበረች ከቤተ መንግሥት ወገን የሆነች ጻድቅ እናት ናት፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሄዳ ከመነኰሰች በኋላ ወደ ጣና ገዳም ገብታ በጣና ባሕር ውስጥ ለ11 ዓመት ቆማ የጸለየች ድንቅ እናት ናት፡፡ ከእናታችን ከቅድስት ወለተ ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን እኛንም በጸሎቷ ይማረን!።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘግንቦት #ሰላሳ (፴)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘግንቦት #ሃያ ዘጠኝ (፳፱)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘግንቦት #ሃያ ስምንት (፳፰)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘግንቦት #ሃያ ስምንት (፳፰)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በትላንትናው ዕለት በደብራችን በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የፃድቁ አባታችን የአቡነ ሐብተማርያም ልደት እና የደብሩ ቅዳሴ ቤት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ አልፋል
ከሚዲያና እቅብተ እምነት የፎቶ ማህደር በትንሹ
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ግንቦት ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን #ጌታችን_ይወደው_ለነበረ ከሞቱ በኋላ #በአራተኛው_ቀን_ላስነሳው_ለማርያምና_ለማርታ #ወንድም_ለጻድቁ_ቅዱስ_አልዓዛር_ለዕረፍት_በዓል መታሰቢያና #ለእስክንድርያ_ሠላሳኛ_ሊቀ_ጳጳስ #ለአባ_ዮሐንስ_ለዕረፍት_በዓል_መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ #ቅዱስ_አልዓዛር፦ ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኀኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ። አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ።
❤ ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ ግንቦት 27 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቅ አባት በቅዱስ አልዓዛር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህም አባት በእስክድርያ ለተሾሙ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ ነው። ደግ የተማረም ነበር። ከልጅነቱም ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ነበር። ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። የትሩፋቱና የዕውቀቱም ዜና በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሹሙት። ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ እግዚአብሔርም በዘመኑ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን አጸና።
❤ ይህ አባት በተሾመበት ወራት ደግ ምዕመን አንስጣዮስ የሚባል ንጉሥ ነበር። በአንጾኪያም የከበረ አባት አባ ሳዊሮስ ነበር እርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ስለ ቀናች ሃይማኖት እንዲህ ብሎ በመልእክቱ ውስጥ ጻፈ "ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋህዶው በኋላ እንደ አባቶቻችን እንደ አባ ድሜጥሮስና እንደ አባ ዲዮስቆሮስ እምነት ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለዋወጥ፣ ያለ መለያየትና ያለ መጨመር አንዲት ባሕርይ አለችው"። አባ ዮሐንስም መልእክቱን ተቀበለው ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ተለያይተው የነበሩ። ሕዋሳትም ተመልሰው አንድ ስለ ሆኑ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰገኑት።
❤ ከዚህም በኋላ ለመልእክቱ መልስ አባ ዮሐንስ ለአባ ሳዊሮስ እንዲህ ብሎ ጻፈለት "ይኸውም ስለ መለኮትና ትስብእት የአንድ ባሕርይ ህልውና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ያለ መለያየት፣ ያለ መቀላቀልና ያለ መለወጥ ሁለት ያይደለ የሰውን ባሕርይ ከመለኮቱ ባሕርይ ጋራ አንድ አድርጎ በመዋሐድ ሰው ስለመሆኑ። ጌታችንንም የሚከፋፍሉትን ወይም ተጨመረበት የሚሉትን ወይም ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ተሰቀሎ የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚሉትን በመለኮት ባሕርይ መከራ ተቀብለ የሚሉትን አወገዘ። "የቀናች ሃይማኖትስ ይቺ ናት እግዚአብሔር ከእኛ በነሣው ሥጋ ስለ እኛ መከራ እንደ ተቀበለ እናውቃለን እኮን። ይቺም የሚጓዝባት የማይሳሳትባትና የማይደናቀፍባት የሕይወት መንገድ ናት" አለ።
❤ አባ ሳዊሮስም ይቺን የአባ ዮሐንስን መልእክት በአነበባት ጊዜ በመልካም አቀባበል ተቀበላት። በአንጾኪያ አገርም ሰበከባት ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመካከላቸው ሰላም ፍቅርና ስምምነት ሆነ። ይህም አባት ሕዝቡን እያስተማረ ዐሥራ አንድ ዓመት ኑሮ ከዚህ በኋላ ግንቦት 27 ቀን በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት27_ስንክሳር።
+ + +
❤ "#ሰላም_ለአልዓዛር_ኤጲስቆጶስ_ዘተሠይመ። ረቡዐ መዋዕለ ድኅረ በመቃብር ተሐትመ። ኢየሱስ ክርስቶሰ ድኅረ አንሥኦቶ ቀደመ። ምስለ ምውታን እስከ ያነሥኦ ዳግመ። በዛቲ ዕለት አዕረፈ ወኖመ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 27።
❤ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ "ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ። ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ። ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ" አላቸው ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋራ ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት_18 ስንክሳር።
+ + +
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ 77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ 24፥1-13።
+ + +
❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ 117፥24-25 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥20-41፣ 1ጴጥ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 2፥22-37። የሚነበው ወንጌል ዮሐ 14፥15-26 ወይም ዮሐ 20፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካች #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ #ለጰራቅሊጦስ_(ለመንፈስ ቅዱስ) #በዓል_እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና ደረሰን።
+ + +
❤ #ጰራቅሊጦስ፦ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኃጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጉምን ይሰጣል መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ፤ ከትንሣኤ በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠርጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
❤ "እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ" አላቸው። ሁለተኛም "ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል" አላቸው።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው "እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናስበውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ"። ይህንንም ሲነግራቸው እንሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደ ርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ። የተከፋፈለ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ። በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ።
❤ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ "በዓለ ኃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ። ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ መላው የተከፋፈለ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀምጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየአገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና። ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ። "እንሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ፣ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን። በሁለት ወንዝ መካከል በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣ በፍርግያም በጽንፍልያም፣ በግብጽም፣ በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እንሆ እንሰማቸዋለን። ሁሉም ደግጠው የሚናገሩትን አጡ። እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው "ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል" አሉ።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው "የይሁዳ ሰዎቼ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደለም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና። ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለውነው፦ "እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴ አሳድራለሁ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁ ሕልምን ያልማሉ። ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ። ደግሞ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሓይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል"።
❤ ዳዊትም እንዲህ አለ "ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ድኅነትህንም ስጠኝ። በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው"። ሁለተኛም "መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ" አለ። ደግሞ "ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ" አለ። ደግሞም "በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"።
❤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ"።
❤ ጌታችንም እንዲህ አለ "ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ። ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። እኔ ሰላም እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣች። እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም። እኔ እሔዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ"።
❤ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ "እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይምሰክራል። እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና። ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሰዋል። ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንዲህም አታዩኝም ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና" አላቸው። "የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ። ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና"።
❤ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁ የሚለን"። ጌታ ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐውቀባቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ። እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል"።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘግንቦት #ሃያ ሰባት (፳፯)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33
#ስንክሳር
ዘግንቦት #ሃያ ስድስት (፳፮)
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
