ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
603
订阅者
-324 小时
-87 天
-1730 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መጋቢት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ የሚወደው ጻድቅ ሰው #ቅዱስ_አልዓዛርን ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነስቶት ነበርና ስለዚች ምልክት ገናናነት ብዙዎች በጌታችን ላመኑበት በዓል፣ ለተጋዳይም በተአምራቷ ከ5,685 በላይ ሰዎችን በጌታችን እንዲያም ላደረገ #ለቅድስት_አስጠራጦኒቃ  ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓልና ለእስክንድርያ ሃምሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ሚካኤል ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከተጋዳይዋ #ከቅድስት_ጽጌ_ሥላሴ ከመታሰቢያዋና #ከቅዱስ_አስቃራን ቤተ ክርስቲያኑ ከከበረችበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ጻድቅ_ሰው_አልዓዛርን ከሞተ በኋላ በአራተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነስቶት ነበርና ስለዚህ ምልክት ገናናነት ብዙዎች አመኑበት። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱና ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ጋር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_አስጠራጦኒቃ፦ የዚች ቅድስት አባቷ ጣዖት አምላኪ ነው እርሷ ግን በክብር ባለቤት በክርስቶስ የምታምን ናት ሥጋዋም እስቲከሣና እስቲደርቅ መልኳም እስቲለወጥ ድረስ በሥውር ትጾማለች ትጸልያለችም። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #መጋቢት (፲፱) 19 ቀን። ❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ደቀ መዝሙር #ለቅዱስ_አርስጥቦ
+2
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #መጋቢት (፲፱) 19 ቀን። ❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ደቀ መዝሙር #ለቅዱስ_አርስጥቦሎስ ለዕረፍት በዓል፣ #ለቅዱስ_አሰከናፍርና_ለሚስቱ ማርታ፣ ለልጆቹ #አርቃድዮስና_ዮሐንስ ለዕረፍታቸው በዓልና #ለሰባቱ_ሰማዕታት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_አርስጥቦሎስ፦ እርሱም ጌታችን ከመረጣቸውና ከመከራው በፊት ወንጌልን እንዲሰብኩ ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቈጠረ ነው። ❤ በሃምሳኛው ቀን በዓልም መንፈስ ቅዱስ በላዩ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሕይወት በሚገኝበት በወንጌል ትምህርት ሐዋርያትን ተከትሎ በመሔድ አገለገላቸው። ብዙዎችንም ወደ ድኅነት መንገድ መልሶ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጥቆ የአምላክን ሕግና ትዕዛዝ ከማስጠበቁ የተነሣ ነፍሳቸውን አዳነ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨                      

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤           ❤ #መጋቢት፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን #ለሰማዕት_ቅዱስ_ፃና ጓደኛው የበግ ጸጒር ልብሶችን በመስራት የሚያገኘው ገንዘብ ለድኆች ይመጸውት ለነበረው ለከበረ #ለቅዱስ_ኤስድሮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ ቅዱሳን ፃናና ኤስድሮስ፦ ፃና ግን ፈርማ በሚባል አገር ለአገረ ገዥው ከጦር ሠራዊቱ ውስጥ ወታደር ነበር እርሱም ከደቅስያ ሰዎች ወገን ነው ከበግ ጸጒር ልብሶችን ለሚሠራ ለኤስድሮስ ወዳጁ ነው። ሁለቱም ሠርተው ከሚያገኙት ለድኆችና ለችግረኞች ይመጸውታሉ። ❤ በአንዲት ሌሊትም ከእርሷ ጋር አክሊሎች ያሉ ድንግል ሴት በራሳቸው ላይ ስታኖረው ሁለቱም ራእይን አዩ። ከእንቅልፋቸውም በነቁ ጊዜ ያዩትን እንዴት እንዳዩ ተነጋገሩ። ምስክሮቹ ሊሆኑ የጠራቸው እግዚአብሔር እንደሆነ አውቀው እጅግ ደስ አላቸው። ❤ ከዚያም ተነሥተው ሒደው ወደ መኰንኑ ደረሱ ቅዱስ ፃናም ትጥቁን ፈትቶ በመኰንኑ ፊት ጣለው ሁለቱም በጌታችን በክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውን ገለጡ። መኰንኑም ነገራቸውን ሰምቶ አሥረው ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አዳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ እስክንድርያ ቅዱስ ፃናን ላከው ቅዱስ ኤስድሮስን ግን በዚያው ተወው ከጥቂት ቀኖችም በኋላ የእስክንድርያው መኰንን ቅዱስ ፃናን ወደ ፈርማ ከተማ መለሰው። ሁለቱ ቅዱሳንም ተገናኙ በመገናኘታቸው ደስ ብሏቸው በላያቸው በየአንዳንዳቸው የደረሰውን መከራ ተነጋገሩ። ❤ ዳግመኛም ለቅዱስ ኤስድሮስ ዐዘቅትን ይቆፍሩለት ዘንድ በዐዘቅቱም ውሰጥ እሳትን አንድደው ቅዱስ ኤስድሮስን እንጨምሩት መኰንኑ አዘዘ። ቅዱሱም ጥቂት እስቲጸልይ ይታገሡት ዘንድ ወታደሮቹን ለመናቸው ወደ ጌታችንም ነፍሱን ይቀበል ዘንድ ለሥጋውም ያስብ ዘንድ ጸለየ። ከዚያም ወደ እሳት ጒድጓድ ቀረበ ወደ እሳቱም ውስጥ ጨመሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ በሥጋውም ላይ ምንም ጒዳት አልደረሰም መልኩም አልተለወጠም። ❤ የቅዱስ ፃና እናትም ከሚወደው ጓደኛው ስለመለየቱ ታላቅስለት ነበር። ከዚያም ሥጋውን ተሸክመው ወሰዱ የስደቱም ወራት እስቲፈጸው በመልካም ቦታ አኖሩት። ❤ ቅዱስ ኤስድሮስ ምስክር ሁኖ በሞተ ጊዜ የቅዱስ ፃና እናት ብዙ መላእክት የቅዱስ ኤስድሮስን ነፍስ ይዘው በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ሲያሳርጓት አየች። እግዚአብሔር ሁላችንን የክርስቲያን ወገኖችን በቅዱሳን ፃናና ኤስድሮስበጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት18 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለኤስድሮስ_እምነ_ሤመ_ፀምር_ግብረ እዱ። ዘይሁብ ምጽዋተ ለእለ ፈቀዱ። ምንዳቤያተ ፈጺሞ ወኵነኔያተ ለለ፩ዱ። በዕለተ ውዕየ ለዐዘቅት እሳት በነዱ። መላእክት ነፍሶ በስብሐት ወሰዱ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት_18።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦"ብፁዓን እለ ንጹሐን በፍኖቶሙ።ወእለ የሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር። ብፁዓን እለ የኃሡ ስምዖ"። መዝ 118፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 16፥1-12፣ 1ኛ ጴጥ 2፥1-11። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 18፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።  √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤         ❤  መጋቢት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊ_ጻድቅ ከመቃብራቸው እስከ አሁን ድረስ ለበሽተኞች የሚሆን #ፈዋሽ_ቅባ_ቅዱስ_ለሚያፈልቁት ኤርትራ አገር የሚገኙ አምስት ታላላቅ ገዳማትን ለመሰረቱ #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ዮናስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ዮናስ፦ ከአባታቸው ንዋየ እግዚእ ከእናቻው ሂሩተ ማርያም ሕዳር 17 በ1357ዓ.ም በጉናጉና ቤተ መስቀል ተወለዱ ስመ ክርስትናቸው ሀብተ እግዚእ ተባሉ። ሀብተ እግዚእ ገና ልጅ እያሉ የበጎች እረኛ ሆነው እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ መልአኩን ልኮ 70 መዝሙረ ዳዊት አስተማራቸው ፍላጎታቸውም ወደ መንፈሳዊ ትምህርት እና ምናኔ ነበር። ከዛም ከተወለዱበት ቦታ ተነስተው ወደ ደብረ ሲና የምትባል ገዳም ሄዱ ከዛ የእናታቸው የሥጋ ወንድም አጎታቸውን አገኙ። አቡነ ዲያምኖስ የሚባሉ በጣም ትልቅ ባለጸጋ አባት አገኙ ከዛም በኋላ የመጡበትን ምንክንያት ለምናኔ መሆኑን ካወቁ በኋላ ሐዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን እና ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩዋቸው በኋላ በ14 ዓመታቸው በ371ዓ.ም ስርዓተ ምንኲስናን ተቀበሉ የምንኲስናቸውም ስም አቡነ ዮናስ ተባሉ። ዮናስ ማለት የዋህ ልክ እንደ ርግብ ማለት ነው። ባሕር ውስጥ ገብተው እየጸለዩ በቀን 5 የዛፍ ፍሬ ዋርካ ወይም 5 ፍሬ  እየተመገቡ በከባድ ጾምና በጸሎት በመንፈስዊ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር። ❤ አቡነ ዮናስ ያደረጉት ተአምር። 1. ሶስት ሙታን አስነስትዋል። 2. ከኤርትራ በደመና ተጭነው ወደ ኢሩሳሌም ሄደው ቀድሰው ወደ ደብረ ጽጌ ገዳም ተመልሰው መክፈልት ይቀምሱ ነበር። 3. ዕረፍታቸው ቀን ሲደርስ በ5ቱ ገዳም የሚገኙ ልጆቻቸው ሰብስበው እኔ የዕረፍቴ ቀን እየደረሰ ነው ከእኔ በኋላ ልክ እንደእኔ አባት የሚኖናችሁ አባ ጳውሎስ ናቸው። እና ለእርሳቸው ልክ እንደ እኔ ታዘዙ አሏቸው። ልጆቻቸውም ይህን ሲሰሙ በጣም አዘኑ መጋቢት 17 ቀን 1452 በ92 ዓመታቸው በዐቢይ ጾም ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የዕረፍት በዓላቸው የሚከበረው ግን ጥር21 ቀን ነው። ልጆቻቸውም ከሀዘን ብዛት የተነሳ በትንሣኤ ቀን ምንም ሳያደርጉ ዝም አሉ። ከዚያም አቡነ ዮናስ ተገልጸው "ልጆቼ ከእኔ ሀዘን የጌታዬ ትንሣኤ ይበልጣል። እና አሁን ትንሣኤውን አድርጉ" አሏቸው ልጆቻቸውም ደግሞ "እኛ ምንም ነገር የለንም እና እንዴት እናደርግ" አሉ ጻድቁ አቡነ ዮናስ "ሦስት አጋዘኖች ወደ እናንተ ይመጣሉ እና እነርሱን አርዳችሁ በዓሉን አሳልፉ እንቢ ቢሏችሁ እንኳን በአቡነ ዮናስ ስም ገዝቷቸው" አሉ። ከዛ ጻድቂ እንዳሉ ሦስት አጋዘኖች መጡ ሁለቱ ታረዱ አንዱ ደግሞ ሊሮጥ ብሎ "በጻድቁ አቡነ ዮናስ ስም ቁም" ብለው ሲገስጹት ቆመ። 4 ጻድቁ አቡነ ዮናስ ካረፉ በኋላ በአምስቱም ገዳማት ዘይት ፈልቋል። በአሁን ጊዜ ግን በመቃብራቸው ብቻ ነው የሚገኘው። 5 ጻድቁ አቡነ ዮናስ የአምስቱ ገዳማት አባት ናቸው። 1.ደብረ ጽጌ 2.ደብረ ድሁሃን 3.ደብረ ሳህል 4.ደብረ ጽዮን 5.ደብረ ጸሪቅ በኢትዮጵያና በኤርትራ አገር ውስጥ ይገኛል። 6. ጻድቁ ባህር ውስጥ ገብተው ሲጸልይ እጃቸውም ልክ እንደ ጸሐይ ያበራ ነበር። ❤ #ቃል_ኪዳናቸው፦ በዚህ ከባድ መንፈሳዊ ተጋድሎአቸው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ወርደው ለአባታችን አቡነ ዮናስ እንደዚህ የሚል ትልቅ ቃልኪዳን ገባላቸው "ወዳጄ ዮናስ ሆይ ጾምህንና ጸሎትህን ተቀብዬልሀለው ከአሁን በኋላ ገድልህን የሰማ፣ ያሰማ፣ ያነበበ አስኬማህንና ቆብህን በስምህ የተቀበለ የ135 ሺ ከእናንተ ጋር የሚነግሱ ዓስራት አድርጌ ሰጥቼሀለው፤ በስምህ እና በጸሎትህ የተማጸነ ያለ ቁጥር እንደ ክረምት ዝናብ ምሬልሀለሁ ዝክርህን የዘከረ መጽሐፍ ገድልህን የጻፈ ያጻፈ፣ ለገዳሙ ዘቢብ፣ ዕጣን ፣ ስንዴ፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ ንዋየ ቅድሳት የሰጠ፣ ገዳሙን ያነፀ፣ በስምህ የተማጸነ፣ ገዳምህን የረገጠ፣ እንደነጭ ሀር አነጻዋለሁ። ኃጢያቱ ልክ እንደ ቁራ ቢጠቁርም እንደነጭ በረዶ አነጸዋለሁ ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው። ከአባታች አቡነ ዮናስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ገዳሙ ካሳተመው ከአቡነ ዮናስ ስዕል ጀርባ የተወሰደ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #መጋቢት፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_አርባ_ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት በተሾሙ ጊዜ ለሦስት ቀናት ስለ ቅድስናቸው እግዚ
+1
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #መጋቢት፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_አርባ_ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት በተሾሙ ጊዜ ለሦስት ቀናት ስለ ቅድስናቸው እግዚአብሔር ዝናብን ላዘነበላቸው፤ በግብፅ አገር አሕዛብ በእሥራትና በስደት ብዙ ላሠቃዩአቸውና #የኢትዮጵያው_ንጉሥ_ሦስት_መቶ_ሺህ_ሠራዊት አዝምቶ ከዚህ ሥቃያቸው ታድጎ ነፃ ላወጣቸው ለከበሩ አባት #ለአባ_ሚካኤል ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ሚካኤል፦ ይህም አባት በእስክንድርያ ከተሾሙ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሰባተኛ ነው፡፡ በአስቄጥስ በአባ መቃርስ ገዳም መንኰሶ ኖረ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎድሮስ በዐረፈ ጊዜ በላዩ የትንቢት መንፈስ ያደረበት አንድ ጻድቅ ሰው እስከ ሚያስረዳቸው ድረስ ለዚች ሹመት ስለሚሻል ሲመክሩና ሲመረምሩ ብዙ ቀኖች ኖሩ። ❤ ከዚህም በኋላ ያ ሰው እኔ በአባ መቃርስ ገዳም በነበርኩ ጊዜ ስጸልይ "የሊቀ ጵጵስና ሹመት ለሚካኤል ይገባዋል ለዚች ሹመት የሚሻል እሱ ነውና የሚል ቃልን ከሰማይ ሰማሁ" አላቸው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

​​​​ምኩራብ (የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት) #ምኩራብ ማለት፦ ቤተ-ጸሎት ሲሆን፤ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ከአይሁድ ምኩራብ ገብቶ ምኩራቡን ገበያ አድርገው ሲገበያዩበት አገኛቸው። ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ያለውን አላነበባችሁምን? ትዕንቢተ ኢሳይያስ ፭፮፥፯ እናንተ ግን ገበያ አደረጋችሁት በማለት በተናቸው እቃውንም ገለባበጠባቸው በሮቹንም፤በጎቹንም በገመድ አየገረፈ አባረራቸው። የዮሐንስ ወንጌል ም. ፪፥፩፯ (ማቴዮስ ፪፩፣፩፫) ደቀ መዛሙርቱም የቤትሕ ቅንዓት በላኝ ተብሎ የተጻፈው ለካ ኣሁን ተፈጸመ ብለው አስተዋሉ። መዝ. ዳዊት ፮፰፤፱ ✙ የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡ ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው) ፤ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ። ✙ ምንባባት መልዕክታት (ቆላ. 2÷16-ፍጻ.) እንግዲህ በመብልም ቢሆን÷ በመጠጥም ቢሆን÷ በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን÷ በመባቻም ቢሆን÷ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡ (ያዕ.5÷14) ወንድሞቻችን ሆይ÷ እምነት አለኝ፤ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር÷ ምን ይጠቅመዋል? በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን? ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ ....... ግብረ ሐዋርያት (የሐዋ.10÷1-8.) በቂሳርያም ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራም የመቶ አለቃ ነበር፡፡ እርሱም ጻድቅና ከነቤተሰቡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነበር፤ ለሕዝቡም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወትርም ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፡፡ ✙ ምስባክ:- መዝ 68፡9 እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡ ትርጉም፦ የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡ ✙ ወንጌል • ዮሐ. 2÷12-ፍጻ. ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ÷ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ፡፡ ........ ✙ ቅዳሴ: - ቅዳሴ ዘእግዚእ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤       ❤ #መጋቢት ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን #ለሐዋያው_ለቅዱስ_ቶማስ ሰባት ዓመት ያህል የጋኔን ግንኑኙነት በአስቸገራት በአንዲት ሴት ላይ ተአምራትን ላደረገበት በዓል፣ ለአረጋውያን ፍጹማን መነኰስ አመንዝራ ሴቶች ብር እየሰጠ በጥበብ ለትዳርና ምንኵስና ላበቃ #ለአባ_ባጥል ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ሲኖዳ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍት በዓል፣ ለእስክድርያ ሰባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ቆርሎስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ #ቅዱሳን_አጋንዮስ_ለአውንድርያኖስና_ለብንድዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ ሰባት ዓመት ያህል የጋኔን ግንኑኙነት በአስቸገራት በአንዲት ሴት ላይ ያደረው ተአምራትን ይህ ነው፦ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስንም በአየችው ጊዜ "የክርስቶስ ሐዋርያው ሆይ እጅግ ከሚያሠቃየኝ ጠላት አድነኝ" ብላ ወደርሱ ጮኸች። እርሱም "በምን ምክንያት አገኘሽ" አላት። እርሷም "ከመታጠቢያ ከውሽባ ቤት ስወጣ እንደ ሰው ድው ድው እያደረገ በመታወክ መጣ ድምጡም ሰላላና ቀጭን ነው በሴትና በወንድ ሥራ ሁሉ ነይ እርስበርሳችን አንድ እንሁን አለኝ በተኛሁም ጊዜ በሌሊት መጥቶ ከእኔ ጋር አንድ ሆነ ብሸሽም አይተወኝም መጥቶ ያሠቃየኛል እንጂ እኔም ከጸሎትህ የተነሣ አጋንንት እንደሚንቀጠቀጡ አውቃለሁና ጸልይልኝ አድነኝም" አለችው። ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ሰምቶ ጸለየ ጋኔኑንም ከእርሷ እንዲወጣ አዘዘው ያንጊዜም በእሳትና በጢስ አምሳል ከሴቲቱ ላይ ወጥቶ ተበተነ ከዚህ በኋላ በክርስቶስ መስቀል በላይዋ አማተበ ሥጋውንና ደሙንም አቀበላት ወደ ዘመዶቿም አሰናበታት። የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ልዩ የሆነች በረከቱም በሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ላይ ትደር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ባጥል፦ ይህም ቅዱስ ሰው ከአባ ዮሐኒ የተባለ አበ ምኔት በመነኰሳት ላይ ነገረ ሠሪን እንደሚቀበል በሰማ ጊዜ በዓቱን ትቶ ወደ እስክንድርያ መጥቶ የሴት አዳሪዎችንና የአመንዝራዎችን ሁሉ ስማቸውን ጻፈ። ከኪራይ ሠራተኞችም ጋራ ሲሠራ ይውላል። ደመወዙን በተቀበለ ጊዜ የሽንብራ ቂጣ ገዝቶ ይበላል የቀረውንም ገንዘብ ይዞ ወደ አንዲቱ ሒዶ ይሰጣታል "በዚች ቀን ከአንቺ ጋራ አድራለሁና ራስሽን ለእኔ አዘጋጂ" ይላታል። ከኀጢአትም ሊጠብቃት ከእርስዋ ዘንድ ያድራል ሌሊቱን ሁሉ ተነሥቶ ሲጸልይና ሲሰግድ እግዚአብሔር ሲለምን ያድራል ሲነጋም ሥራውን ለማንም እንዳትገልጥ አምሏት ወደ ተግባሩ ይሔዳል። ❤ በየዕለቱም ወደ የአመንዝራዎቹ እየሔደ እንዲህ ያደርግ ነበር አንዲቱም ሴት ምሥጢሩን ገለጠች ጋኔንም ይዞ አሳበዳት። ሰዎችም ስለዚህ ክፉ ሽማግሌ ክፉ ሥራ የለበትም ብላ ወሽታለችና እግዚአብሔር መልካም አደረገባት ተባባሉ። እርሷም "እንዳናመነዝር ገንዘብ በመስጠት ከኃጢአት ይጠብቀናል እንጂማ ነውር የለበትም" ብላ ነበርና። የቀሩት አመንዝራዎች በእርሷ ላይ የሆነውን በአዩ ጊዜ ደነገጡ እንደርሷም እንዳያብዱ እውነቷን ነው ማለትን ፈሩ። እርሱም "ይችስ በእገሌ ዕለት ትጠብቀኛለች" ይል ጀመረ ሰዎችም ሁሉ ያሙት ጀመር እርሱም "እንደ ሰው ሁሉ ሥጋ የለኝምን ወይስ እግዚአብሔር መነኰሳትን ተቆጥቶ በፍትወት ተቃጥለው እንዲሞቱ ትቷቸዋልን" አላቸው። እነርሱም "ልብስህን ለውጠህ ሚስት አግባ ይህ ይሻልሃልና" አሉት። እርሱም "አዎን ብወድ በሚስቴ እጠነቀቃለሁ በዚህም በክፉ አኗኗር እኖራለሁ እናንተ ግን ከእኔ ዘንድ ሒዱ ምን ትሻላችሁ በእኔ ላይ እግዚአብሔር ፈራጆች አድርጓችኋልን ይልቁንስ እናንተ እንዳይፈረድባችሁ ለራሳችሁ አስቡ ፈራጅ አንድ ነውና ዕለቲቱም አንዲት ናትና" አላቸው። ❤ ይህም ቅዱስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አገኘ በሰው ዘንድ ግን የተናቀ ሁኖ ኖረ። ከእርሱ ጥቅም የአገኙ አመንዝራዎችም ዝሙታቸውን ተዉ። ከእርሳቸውም ሕጋዊ ጋብቻ ተጋብቶ የኖረ አሉ ወደ ገዳምም ገብቶ መንኵሶ በጾም በጸሎት ተወስኖ የኖሩ አሉ። ❤ በአንዲት ዕለትም ከአንዲት አመንዝራ ቤት ሲወጣ ያቺን ሴት አስቀድሞ የለመዳት አንድ ሰው አገኘውና "ይህ ሽማግሌ እስከ መቼ ድረስ በዚህ በክፉ ሥራ ይኖራል" ብሎ ፊቱን በጥፊ መታው። ❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን በበዓቱ ውስጥ ሰግዶ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጥቶ በቤቱም መድረክ "የዚች አገር ሰዎች ጊዜው ሳይደርስ በማንም ላይ አትፍረዱ እንዳይፈረድባችሁ" የሚልም ጽሑፍ ተጽፎ ተገኘ። ከአባ ባጥል በጸሎቱ የሚገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ሲኖዳ፦ እርሱም በግብጽ አገር ከብሕንሳ ነው። ወደ መክስምያኖስም ክርስቲያናዊ ሲኖዳ "አማልክትን የሚያመልክ ነው" ብለው ነገር ሠሩበት። እርሱም አስቀርቦ ስለ ሃይማኖቱ ጠየቀው በንጉሡም ፊት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ እርሱም ዕውነተኛ አምላክ እንደ ሆነም መሰከረ። ❤ መክስምያኖስም ይህን የከበረ አባ ሲኖዳን በምድር ላይ ዘርግተው በበትሮች እንዲደበድብት አዘዘ። ዐጥንቶቹ እስቲሠነጠቁ ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ እስቲፈስ እንዲሁ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ እግሩን ይዘው ጐትተው ወስደው ሽታው በሚከረፋ በጨለማ ወህኒ ቤት ጣሉት የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለት። ቊስሎቹንም አድኖ ጤነኛ አደረገው አበረታውም "በርታ አትፍራ ስለ መከራህም የክብር አክሊል ተዘጋጅቶልሃልና ደግሞም በጽኑዕ ሥቃይ ትሠቃይ ዘንድ አለህ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እኔም ከአንተ ጋራ እኖራለሁ" አለው። ከዚያም ከእርሱ ተሠወረ። ❤ በነጋ ጊዜም "የነገሥታትን ትዕዛዝ የሚተላለፍ ያንን ዓመፀኛ ሒዳችሁ እዩት ሙቶም ከሆነ ለውሾች ጣሉት" ብሎ መክስምያኖስ ወታደሮቹን አዘዘ። ወደርሱም በደረሱ ጊዜ ቁሞ ሲጸልይ አግኝተውት "ያለምንም ጥፋት ጤነኛ እንደሆነና በሥጋውም ውስጥ የሕማም ምልክት እንደሌለ እርሱም ከቶ ምንም ሥቃይ እንዳላገኘው ጤነኛና ደስ እንዳለው ሰው ተግቶ እንደሚጸልይ" ስለርሱ ለንጉሡ ነገሩት። ንጉሡም ወደርሱ አስመጣው ከሕይወቱም የተነሣ አደነቀ ልብሶቹንም አስወልቆ ያለጉዳት ጤነኛ እንደሆነ ሥጋውን አየ ደግጦም "ይህ ያየሁት ሥራይ ታላቅ ነው" አለ። ከዚያም ዘቅዝቀው ሰቅለው ከታቹ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ። ይህንንም አደረጉበት ደግሞ በመንኰራኵር አሠቃዩት በአለንጋዎችም አብዝተው ገረፉት ደበደቡትም። ❤ ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው ለውሾች እንዲጥሉት አዘዘ ውሾች ግን ፈጽሞ አልቀረቡትም ሌሊትም ሲሆን ምዕመናን መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በአዳዲሶች ልብሶችና በጣፋጭ ሽቶዎች ገነዙት በሣጥንም አድርገው ቀበሩት። ከሥጋው ብዙዎች አስደናቂዎች ተአምራቶች ተደረጉ። የአባ ሲኖዳ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨✨ምክረ አበው✨✨✨ የዕለቱ መርሐግብራት -መዝሙር -ወንጌል -ምክረ አበው እንዲሁም የተለያዩ ኪናዊ ዝግጅቶች የአዳጊና ወጣት መርሐግብር አንድ ላይ ስለሆነ ከ08:00 ሰዓት ጀምሮ እንድንገኝ በእግዚ
✨✨✨ምክረ አበው✨✨✨ የዕለቱ መርሐግብራት -መዝሙር -ወንጌል -ምክረ አበው እንዲሁም የተለያዩ ኪናዊ ዝግጅቶች የአዳጊና ወጣት መርሐግብር አንድ ላይ ስለሆነ ከ08:00 ሰዓት ጀምሮ እንድንገኝ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።     ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፲፪ (12 ) ቀን። ❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ወደ ፈላስፋው በለዓም ለተላከበት ወራዊ መታሰቢያ በዓልና
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ መጋቢት ፲፪ (12 ) ቀን። ❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ወደ ፈላስፋው  በለዓም ለተላከበት ወራዊ መታሰቢያ በዓልና ለከበረና ለተመሰገነ ለእስክንድርያ ዐሥራ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ድሜጥሮስ ለልደቱና ድንግልናውን ለገለተለጠበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከፍልስጥዔም አገር ከሆነ ከቅዱስ መላዚ በሰማዕትነት ከዐረፈ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                 + + + ❤ ቅዱስ ሚካኤል ወደ በለዓም መላክ፦ በለዓምን እስራኤልንም ይረግማቸው ዘንድ ባላቅ በጠራው  ጊዜ። በጐዳናም በፊቱ ቅዱስ ሚካኤል ቆሞ ስለተገለጠ አስደንግጠው አህያው በሰው አንደበት እስተናገረች ድረስ። መርገሙንም ወደ በረከት መለሰው። በቅዱስ ሚካኤል በአማላጅነቱ ለዘላለሙ ይጠብቀን አሜን።                                               + + + √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #መጋቢት ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ከተሰዓቱ_ቅዱስ ለአንዱ ኤርትራ ጠረፍ አካባቢ የሚገኘው ደብረ ብኅዛን (አኅሰአ) ለመሰረ
+1
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #መጋቢት ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ከተሰዓቱ_ቅዱስ ለአንዱ ኤርትራ ጠረፍ አካባቢ የሚገኘው ደብረ ብኅዛን (አኅሰአ) ለመሰረቱት #ለአቡነ_አሌፍ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                      ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_አሌፍ፦ ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት። አባ አሌፍ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው። ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው። ❤ ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው። በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:- 1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ። 2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና 3.ገዳማዊ ሕይወት ነው። ❤ አባ አሌፍን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው። እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #መጋቢት ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ ታላቁን ዲማ ጊዮርጊስን ለመሠረቱ #አቡነ_ተከስተ_ብርሃን_ዘደብረ_ድማኅ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                ❤ #መጋቢት ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ ታላቁን ዲማ ጊዮርጊስን ለመሠረቱ #አቡነ_ተከስተ_ብርሃን_ዘደብረ_ድማኅ ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ተከስተ_ብርሃን፦ ትውልድ ቦታቸው መንዝ ከሚባለው አገር ነው። ይህች መንዝ የምትባለው አገር የምትገኘው በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለየች በደብረ ብርሃን አውራጃ ውስጥ ነው። መንዝ ማለትም ነዝሀ ከሚለው ከግእዝ ቃል የተገኘ ነው። መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል እግዚአብሔር በሰጠው (በፈቀደለት) ስልጣን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም በሰጠው ተስፋ በተወለደ በ33 ዓመት ከ3 ወር ወንጌልን አስተምሮ ለድኅነተ ዓለም መጋቢት 27 ቀን በዕለተ አርብ በተሰቀለ ጊዜ የፈሰሰ ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን መነሳንስ ዓለምን ሲረጭ አስቀድሞ ይችን መንዝ የምትባልን አገር ከሁሉ አስቀድሞ ስለረጫት ደመ መለኮቱን እንደ አውድማ ስለለቀለቀው በዚህ ምክንያት መንዝ ተብላለች። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨ቅድስት✨ ሁለተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት:- ቅድስት ይባላል:: ቅድስት ማለት :- የተቀደሰች የተለየች ማለት ነው፡፡ ይህ ሳምንት "ሰንበትየ ቅድስት" የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘ
✨ቅድስት✨ ሁለተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት:- ቅድስት ይባላል:: ቅድስት ማለት :- የተቀደሰች የተለየች  ማለት ነው፡፡ ይህ ሳምንት "ሰንበትየ ቅድስት" የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ፵ ቀን ጌታችን የጾመበት ሳምንት ስለሆነ፤ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡ "የሰንበት ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።" ዘዳ፣ 20÷8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ "ዕረፍባት" ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ ሰናይ ሰንበት ✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤           ❤ #መጋቢት ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ሰማዕትነት ሲቀበል በጨርቅ ዐይኑን ሊሸፍኑ ሲል "ይህ ሞትን ለሚፈሩ ነው እኔ ግን #በክብር_ባለቤት_በጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ሞትን አልፈራም" ብሎ አንገቱ በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_ቴዎዶጦስ ለዕረፍቱ በዓልና ለከበሩ #ለቅዱሳን_ፊልሞን_አብላንዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከጻድቅ ንጉሥ #ከቅዱስ 9_ቴዎድሮስ ከዕረፍቱ መታሰቢያ  ረደኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_ቴዎዶጦስ፦ እርሱም ከገላትያ አገር የሆነ በምክርና በተግሣጽ አምልኮተ እግዚአብሔርንም በማጽናት ያደገ ነው። ወደ ከሀዲ መኰንንም ሒደው የክርስቲያን ወገን እንደሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም አሥረው እንዲያመጡት አዘዘ። ቅዱስም ይህን በሰማ ጊዜ ሳይዙት ወደ መኰንኑ ሔዶ መኰንኑንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ ዘለፋቸውም መኰንኑ እሱን በማስፈራራት ሁኖ የሥቃይ መሣሪያዎችን ሁሉ አሳየው ለጣዖት እንዲሠዋ በመሸንገል አስገደደው ቅዱሱም ስለ ድንቁርናው ረገመው ዘለፈውም። ከዚህ በኋላ የውስጥ ዕቃው እስከሚታይ ሰቅለው ጐኖቹን ይሠነጣጥቁ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ። ❤ ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ይጨምሩት ዘንድ ደግሞ አውጥተው በዕንጨት እንዲሰቅሉት ቊስሎቹንም እንዲአድሱ ጐኖቹንም እንዲሠነጣጥቁ አዘዘ። እርሱ ግን መኰንኑ የሚያመጣውን ሥቃይ እንደ ኢምንት አደረገው በክብር ባለቤት በጌታችን ክርሰቶስ በፍቅሩ ፍላጻነት ልቡ ተነጽፏልና ዓይኖቹም ወደላይ ይመለከቱ ነበር። መኰንኑም ብርታቱን በአየ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ❤ ቅዱስ ቴዎዶጦስ የራሱን መቆረጥ ሰምቶ እጅግ ደስ እያለው ወጣ። ወደ እግዚአብሔርም ሲጸልይና ሲማልድ እንዲህ አለ "የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርሰቶስ ሆይ አመሰግናለሁ ከተከታተለኝ ክፉ ነገር ሁሉ አድነኸኛልና በጠላትነት የተነሡብኝም ወደ ገሃነም አወረድካቸው እኔንም ከሞት በር ከፍ ከፍ አደረግኸኝ"። ይህንንም ብሎ በሰገደ ጊዜ ወታደሩም የቅዱሱን ዐይን ይሸፍን ዘንድ መሸፈኛ አመጣ። ቅዱሱም  "ይህ ሞትን ለሚፈሩ ነው እኔ ግን በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሞትን አልፈራም" አለ። ወታደሩም ሰይፍን መዝዞ የከበረች ራሱን መጋቢት 7 ቆረጠ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። የቅዱስ ቴዎዶጦስ በረከቱም በላያችን ትደር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ለቅዱሳን_ፊልሞንና_አብላንዮስ፦ ይህ ፊልሞንም በእንዴናው ገዥ በሆነ በአርያኖስ ፊት በአዝማሪነት ይጫወት ነበር። ከአዝማሪው አብላንዮስ ጋራ እርስበርሳቸው ወዳጆች ሆኑ ለክብር ባለቤት ክርስቶስም ስለ ስሙ ምስክሮች ሊሆኑ ተስማሙ። ❤ አዝማሪው ፊልሞንም ልብሱን ወስዶ ለአብላንዮስ ሰጠው እርሱም የአብላንዮስን ልብስ ለብሶ ወደ መኰንኑ ወደ አርያኖስ ገብቶ በፊቱ ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም ተመልክቶ አዝማሪው አብላንዮስ እንደሆነ አሰበ በፍላጻም እንዲነድፋት አዘዘ ያንጊዜም አዝማሪው ፊልሞን መሆኑን አውቆ እጅግ ተቆጣ። ደግሞ አብላንዮስን እንዲነድፉት አዘዘ ሁለቱንም ነድፉቸው አንዲት ፍላጻም ወደ መኰንኑ ተመልሳ ዓይኑን አወጣቻት እጅግም አሠቃየችው። ❤ የከበሩ ፊልሞንና አብላንዮስ ግን ገድላቸውን መጋቢት7 ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ። የቅዱሳን ፊልሞንና አብላንዮስ በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 7 ስንክሳር።