ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多609
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-1130 天
帖子存档
Repost from የግ/ደ/ቅ/አርሴማ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ቤት መዝሙር ክፍል
+9
🔴✨🔴✨🔴✨🔴✨🔴✨🔴✨🔴
በዕለተ ሰንበት የጠዋጥ ጉባዔ በደብራችን ስብከተ ወንጌል ክፍል ሀላፊ እና በተጋባዥ ዘማሪ ወንድማችን በዚህ ሁኔታ በዓለ ደብረዘይትን አክብረናል እግዚአብሔር አምላክ ለትንሳኤው ብርሃን ያድርሰን።🙏🙏🙏
ከፍኖተ ብርሃን ሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል
✨✨✨ ሰናይ ዕለተ ሰንበት ✨✨✨
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ቄርሎስ፦ ይህም አባት የእስክንድርያ ሰባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ነው። እርሱም በምግባሩ ፍጹም ዐዋቂ ሆነ በአገሩ ፍዩም ይባላል በእርሷም ቅስና ተሹሞባት ነበር። ከዚያም ለቆ ወደ አባ ፊቅጦር ገዳም ደረሰ እርሱም ከምስር ከተማ ውጭ የኢትዮጵያውያን ዐዘቅት የዐባይ ግድብ በአለበት ነው። በዚም ታላቅ ገድልን እየተጋደለ ብዙ ዘመናትን ኖረ። ብዙ መጻሕፍትንም ተምሮ ትርጓሜያቸውንና ምሥጢራቸውን ጠንቅቆ ዐወቀ። አሸናፊ ወደሚባለውም ንጉሥ አደባባይ ቀርቦ የእስላሞች ታላላቅ ሊቃውንቶቻቸውና ከምሁራኖቻቸው ውስጥ መምህሮታቸውን ተከራከሩት። ጠቃሚ የሆነ ዕውቀት የተመላበትን መልስ አገኙ የሚጠይቁትንም ሁሉ በመልካም አመላለስ ነገራቸው ከዚህ በኋላ የዕውቀቱና የቅድስናው ዜና በተሰማ ጊዜ ያለ ፈቃዱ ይዘው በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት መንጋውንም ጠበቀ በጸሎትና በቅዳሴ ያገለግሉ ዘንድ ለካህናት ሥርዓትንና መመሪያን ሠራ።
❤ ይህም አባት በሊቀ ጵጵስናው ሰባት ዓመታት ከዘጠኝ ወር ከዐሥር ቀኖች ኖረ። ከቀኑም በሦስት ሰዓት መጋቢት14 ቀን ዐረፈ። በምስክርነት አደባባይም ተቀበረ። ከአባ ቄርሎስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ የከበሩ #ቅዱሳን_አጋንዮስ_አውንድርያኖስና_ብንድዮስ፦ እሊህም ቅዱሳን ከአባቶቻቸው ጀምሮ ክርስቲያኖች ናቸው። አምላካዊ ትምህርትንም ሁሉ የተማሩ ናቸው።
❤ በእግዚአብሔርም ሕግ ጸንተው ሲኖሩ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አርሞስ መርጦ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ ሾማቸው ግን በታወቁ ቦታዎች ላይ አይደለም በብዙዎች አገሮች ውስጥ እንዲሰብኩ ላካቸው እንጂ። በአገሮችም ያሉ ከሀድያን ያዟቸው ያለርህራሄም አብዝተው ገረፏቸው በደንጊያም ወገራቸው መጋቢት 14 ቀን ነፍሳቸውንም በጌታች እጅ ሰጡ። የከበሩ ቅዱሳን አጋንዮስ፣ አውንድርያኖስና ብንድዮስ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት14 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለቶማስ_እንዘ_ይገብር_መድምመ። እምነ ብእሲት አግኂሦ ትድምርተ ጋኔን ኅሡመ። መንጽሔ ኃጢአት መጠዋ ሥጋ ወደመ። በጊዜ ትቤሎ ሀበኒ ማሕተመ። ከመ ላዕሌየ ኢይግባእ ዳግመ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት14።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን #ለሐዋያው_ለቅዱስ_ቶማስ ሰባት ዓመት ያህል የጋኔን ግንኑኙነት በአስቸገራት በአንዲት ሴት ላይ ተአምራትን ላደረገበት በዓል፣ ለአረጋውያን ፍጹማን መነኰስ አመንዝራ ሴቶች ብር እየሰጠ በጥበብ ለትዳርና ምንኵስና ላበቃ #ለአባ_ባጥል ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ሲኖዳ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍት በዓል፣ ለእስክድርያ ሰባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ቆርሎስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ #ቅዱሳን_አጋንዮስ_ለአውንድርያኖስና_ለብንድዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ ሰባት ዓመት ያህል የጋኔን ግንኑኙነት በአስቸገራት በአንዲት ሴት ላይ ያደረው ተአምራትን ይህ ነው፦ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስንም በአየችው ጊዜ "የክርስቶስ ሐዋርያው ሆይ እጅግ ከሚያሠቃየኝ ጠላት አድነኝ" ብላ ወደርሱ ጮኸች። እርሱም "በምን ምክንያት አገኘሽ" አላት። እርሷም "ከመታጠቢያ ከውሽባ ቤት ስወጣ እንደ ሰው ድው ድው እያደረገ በመታወክ መጣ ድምጡም ሰላላና ቀጭን ነው በሴትና በወንድ ሥራ ሁሉ ነይ እርስበርሳችን አንድ እንሁን አለኝ በተኛሁም ጊዜ በሌሊት መጥቶ ከእኔ ጋር አንድ ሆነ ብሸሽም አይተወኝም መጥቶ ያሠቃየኛል እንጂ እኔም ከጸሎትህ የተነሣ አጋንንት እንደሚንቀጠቀጡ አውቃለሁና ጸልይልኝ አድነኝም" አለችው።
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ሰምቶ ጸለየ ጋኔኑንም ከእርሷ እንዲወጣ አዘዘው ያንጊዜም በእሳትና በጢስ አምሳል ከሴቲቱ ላይ ወጥቶ ተበተነ ከዚህ በኋላ በክርስቶስ መስቀል በላይዋ አማተበ ሥጋውንና ደሙንም አቀበላት ወደ ዘመዶቿም አሰናበታት። የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ልዩ የሆነች በረከቱም በሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ላይ ትደር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ባጥል፦ ይህም ቅዱስ ሰው ከአባ ዮሐኒ የተባለ አበ ምኔት በመነኰሳት ላይ ነገረ ሠሪን እንደሚቀበል በሰማ ጊዜ በዓቱን ትቶ ወደ እስክንድርያ መጥቶ የሴት አዳሪዎችንና የአመንዝራዎችን ሁሉ ስማቸውን ጻፈ። ከኪራይ ሠራተኞችም ጋራ ሲሠራ ይውላል። ደመወዙን በተቀበለ ጊዜ የሽንብራ ቂጣ ገዝቶ ይበላል የቀረውንም ገንዘብ ይዞ ወደ አንዲቱ ሒዶ ይሰጣታል "በዚች ቀን ከአንቺ ጋራ አድራለሁና ራስሽን ለእኔ አዘጋጂ" ይላታል። ከኀጢአትም ሊጠብቃት ከእርስዋ ዘንድ ያድራል ሌሊቱን ሁሉ ተነሥቶ ሲጸልይና ሲሰግድ እግዚአብሔር ሲለምን ያድራል ሲነጋም ሥራውን ለማንም እንዳትገልጥ አምሏት ወደ ተግባሩ ይሔዳል።
❤ በየዕለቱም ወደ የአመንዝራዎቹ እየሔደ እንዲህ ያደርግ ነበር አንዲቱም ሴት ምሥጢሩን ገለጠች ጋኔንም ይዞ አሳበዳት። ሰዎችም ስለዚህ ክፉ ሽማግሌ ክፉ ሥራ የለበትም ብላ ወሽታለችና እግዚአብሔር መልካም አደረገባት ተባባሉ። እርሷም "እንዳናመነዝር ገንዘብ በመስጠት ከኃጢአት ይጠብቀናል እንጂማ ነውር የለበትም" ብላ ነበርና። የቀሩት አመንዝራዎች በእርሷ ላይ የሆነውን በአዩ ጊዜ ደነገጡ እንደርሷም እንዳያብዱ እውነቷን ነው ማለትን ፈሩ። እርሱም "ይችስ በእገሌ ዕለት ትጠብቀኛለች" ይል ጀመረ ሰዎችም ሁሉ ያሙት ጀመር እርሱም "እንደ ሰው ሁሉ ሥጋ የለኝምን ወይስ እግዚአብሔር መነኰሳትን ተቆጥቶ በፍትወት ተቃጥለው እንዲሞቱ ትቷቸዋልን" አላቸው። እነርሱም "ልብስህን ለውጠህ ሚስት አግባ ይህ ይሻልሃልና" አሉት። እርሱም "አዎን ብወድ በሚስቴ እጠነቀቃለሁ በዚህም በክፉ አኗኗር እኖራለሁ እናንተ ግን ከእኔ ዘንድ ሒዱ ምን ትሻላችሁ በእኔ ላይ እግዚአብሔር ፈራጆች አድርጓችኋልን ይልቁንስ እናንተ እንዳይፈረድባችሁ ለራሳችሁ አስቡ ፈራጅ አንድ ነውና ዕለቲቱም አንዲት ናትና" አላቸው።
❤ ይህም ቅዱስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አገኘ በሰው ዘንድ ግን የተናቀ ሁኖ ኖረ። ከእርሱ ጥቅም የአገኙ አመንዝራዎችም ዝሙታቸውን ተዉ። ከእርሳቸውም ሕጋዊ ጋብቻ ተጋብቶ የኖረ አሉ ወደ ገዳምም ገብቶ መንኵሶ በጾም በጸሎት ተወስኖ የኖሩ አሉ።
❤ በአንዲት ዕለትም ከአንዲት አመንዝራ ቤት ሲወጣ ያቺን ሴት አስቀድሞ የለመዳት አንድ ሰው አገኘውና "ይህ ሽማግሌ እስከ መቼ ድረስ በዚህ በክፉ ሥራ ይኖራል" ብሎ ፊቱን በጥፊ መታው።
❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን በበዓቱ ውስጥ ሰግዶ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጥቶ በቤቱም መድረክ "የዚች አገር ሰዎች ጊዜው ሳይደርስ በማንም ላይ አትፍረዱ እንዳይፈረድባችሁ" የሚልም ጽሑፍ ተጽፎ ተገኘ። ከአባ ባጥል በጸሎቱ የሚገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሲኖዳ፦ እርሱም በግብጽ አገር ከብሕንሳ ነው። ወደ መክስምያኖስም ክርስቲያናዊ ሲኖዳ "አማልክትን የሚያመልክ ነው" ብለው ነገር ሠሩበት። እርሱም አስቀርቦ ስለ ሃይማኖቱ ጠየቀው በንጉሡም ፊት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ እርሱም ዕውነተኛ አምላክ እንደ ሆነም መሰከረ።
❤ መክስምያኖስም ይህን የከበረ አባ ሲኖዳን በምድር ላይ ዘርግተው በበትሮች እንዲደበድብት አዘዘ። ዐጥንቶቹ እስቲሠነጠቁ ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ እስቲፈስ እንዲሁ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ እግሩን ይዘው ጐትተው ወስደው ሽታው በሚከረፋ በጨለማ ወህኒ ቤት ጣሉት የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለት። ቊስሎቹንም አድኖ ጤነኛ አደረገው አበረታውም "በርታ አትፍራ ስለ መከራህም የክብር አክሊል ተዘጋጅቶልሃልና ደግሞም በጽኑዕ ሥቃይ ትሠቃይ ዘንድ አለህ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እኔም ከአንተ ጋራ እኖራለሁ" አለው። ከዚያም ከእርሱ ተሠወረ።
❤ በነጋ ጊዜም "የነገሥታትን ትዕዛዝ የሚተላለፍ ያንን ዓመፀኛ ሒዳችሁ እዩት ሙቶም ከሆነ ለውሾች ጣሉት" ብሎ መክስምያኖስ ወታደሮቹን አዘዘ። ወደርሱም በደረሱ ጊዜ ቁሞ ሲጸልይ አግኝተውት "ያለምንም ጥፋት ጤነኛ እንደሆነና በሥጋውም ውስጥ የሕማም ምልክት እንደሌለ እርሱም ከቶ ምንም ሥቃይ እንዳላገኘው ጤነኛና ደስ እንዳለው ሰው ተግቶ እንደሚጸልይ" ስለርሱ ለንጉሡ ነገሩት። ንጉሡም ወደርሱ አስመጣው ከሕይወቱም የተነሣ አደነቀ ልብሶቹንም አስወልቆ ያለጉዳት ጤነኛ እንደሆነ ሥጋውን አየ ደግጦም "ይህ ያየሁት ሥራይ ታላቅ ነው" አለ። ከዚያም ዘቅዝቀው ሰቅለው ከታቹ እሳትን እንዲያነዱ አዘዘ። ይህንንም አደረጉበት ደግሞ በመንኰራኵር አሠቃዩት በአለንጋዎችም አብዝተው ገረፉት ደበደቡትም።
❤ ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው ለውሾች እንዲጥሉት አዘዘ ውሾች ግን ፈጽሞ አልቀረቡትም ሌሊትም ሲሆን ምዕመናን መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በአዳዲሶች ልብሶችና በጣፋጭ ሽቶዎች ገነዙት በሣጥንም አድርገው ቀበሩት። ከሥጋው ብዙዎች አስደናቂዎች ተአምራቶች ተደረጉ። የአባ ሲኖዳ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከዘጠኙ ንዑስ በዐላት አንዱ ለሆነው ለዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት #ለደብረ_ዘይት እግዚአብሔር በሰላም በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የደብረ_ዘይት_መዝሙር፦ "እንዘ ይነብር #እግዚእነ_ውስተ_ደብረ_ዘይት ወይቤሎሙ #ለአርዲኢሁ_ዑቁኬ_ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ #አነ_ውእቱ_ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን #ወአመ_ምጽአቱሰ_ለወልደ_እጓለ_እመሕያው ይትከወስ ኵሉ ኀይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኵሎሙ ኀጥአነ ምድር። #ወይወርድ_እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ #ወበአዕላፍ_መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን #ዘእምኀበ_እግዚአብሔር_ይምሐረነ_አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ #እግዚአ_ለሰንበት። ትርጉም፦ #ጌታችን_በደብረ_ዘይት_ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ #ለደቀ_መዛሙርቱ_ማንም_እንዳያስታችሁ_ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ #ብዙዎች_እኔ_ክርስቶስ_ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል። የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ። ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው። #ጌታችንም_ከባሕርይ_አባቱ_ከእግዚአብሔር_አብ ዘንድ በመለከት ድምጽ #ከአእላፍ_መላእክት ጋር #በግርማ_መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል። በዚች ዕለት ሞትን ከሚያስከትል ኃጢአት #አብ_ይማረን_የሕይወት_ባለቤት_የሰንበትም_ጌታ_ነውና። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
❤ "#ደብረ_ዘይት"
❤ ትርጉሙ፦ ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም "ደብር" ማለት "ተራራ" ማለት ሲሆን "ዘይት" ማለት ደግሞ "ወይራ" ማለት ነው። በተገናኝ "ደብረ ዘይት" ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ይሆናል።
❤ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው ያለው። ከግርጌው ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ይገኛል። የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ያረፈበት ወይም የድንግል መካነ መቃብር በዚህ ተራራ ግርጌ ይገኛል። ቤተ ፋጌ እና ቢታንያ በኮረብታው ጫፍ እና በምስራቅ ዳገታ ላይ ይገኛሉ።
❤ ይህ ተራራ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ብዙ ድርጊቶች የተደረጉበት ቦታ ነው። ጌታችን ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ፣ ስለ ዓለም ፍጻሜና ስለ ዳግም ምጽአት በዚህ ተራራ ላይ በትንቢት መልክ ተናገረ (ማቴ 24፥3)። በዚሁ ተራራ ላይ ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ 24፥50)። በዚሁ ተራራ ላይ ቀን በከታማና በገጠር ሲያስተምር ውሎ ሌሊት የሚያድርበት የኤሌዎን ዋሻ ይገኛል።
በኋለኛው ምጽአቱ በዚሁ ቦታ እንደሚገለጥ ትንቢት ተነግሯል።(ዘካ 14፥3-5)።
❤ ስያሜው፦ የዐቢይ ጾም እኩሌታ ላይ ያለው ሰንበት በዚህ ተራራ ተጠርቷል። ይህንን ዕለት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዳግም ምጽአት አድርጎ መዝሙሩን ጽፏል። በዚህ ተራራ ላይ «እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት» (ማቴ.24፥3)። ተብሎ እንደተጻፈው
ለደቀ መዛሙርቱ የደግም ምጻቱን፣ የዓለምን ፈጻሜ፣ የትንሣኤ ሙታንን፣ ትምህርት በሰፊው ስላስተማረ በዓሉ በተራራው ስም ተሰይሟል።
❤ አመጣጡስ እንዴት ነው?
❤ ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበበ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርኃ መጋቢት ዕለተ እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡
ምነው "የሚያውቀው የለም ይል የለምን" ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን ብዙ የመጋቢት ወር ብዙ የእሑድ ዕለት የበዙ ሌሊቶች አሉና ለይቶ የሚያውቅ የለም ለማለት ነው፡፡
❤ ሞት ለማንም አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ 3፥19 በዕለተ ምጽአትም ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፍን ነቅለው ድንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ነጋሪቱን ይመታል 1ኛ መቃብ 9፥8 ነጋሪት የተባለው በቁሙ ነጋሪት የሚመታ ሆኖ ሳይሆን አዋጁን የምትክ ንቃ የሚል አዋጅ የሚናገር ይታወጃልና ነጋሪት ይመታል አለ።
❤ ስለዚህ ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ "ዘያነቅሖሙ ለሙታን" ሲል በዱር በገደል በባህር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም እንደ ዕለት በድን ይሆናሉ፡፡
ሦስተኛው ነጋሪቱን መትቶ "ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት" "ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም" ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደግነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡
❤ ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ 13፥43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያብሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የኣባቴ ብሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥኣንን ስለክፋ ሥራቸው /ከኔ ሂዱ/ ብሎ ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ ዋይ ዋይ እያሉ ደረት ይደቃሉ እንባቸውን ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ልቅሶ የማይረባ ኃዘን ነው ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን 0ይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡
❤ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን አሜን። 🤲 ምንጭ፦ አምኃ ሥላሴ (መኩሪያ ተስፋዬ) ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ። ወአምላክነሂ ኢያረምም"። እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። መዝ 49፥3። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ተሰ 4፥13-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 3፥7-15 እና የሐዋ ሥራ 24፥1-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥1-36። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ አትናቴዎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የደብረ ዘይት በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።
መጋቢት ፲፫ /13/
በዚች ቀን ልብጥያ በሚባል አገር የከበሩ አርባ ሐራ ሰማይ በሰማዕትነት አረፉ።
እሊህ ቅዱሳንም በአልፊያኖስ ዘመን ተጋደሉ። በሌሊትም እሊህ አርባ ጭፍሮች ወደ መኰንኑ ደርሰው በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ምስክር ይሆኑ ዘንድ እርስ በርሳቸው ተስማሙ።
በሌሊትም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ አበረታቸው። በጥዋትም ተነሥተው የጭፍራ አለቃ በሆነ በአግሪጎላዎስ ፊት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመኑ።በድንጋይ እንዲወግሯቸውና ቀዝቃዛ በሆነ የጉድጓድ ውሀ ውስጥ ይጥሏቸው ዘንድ መኰንኑ አዘዘ።
በውስጥዋም በጣሉአቸው ጊዜ ከውርጭ ጽናት የተነሣ ሕዋሳታቸው ተቆራረጠ ከእርሳቸውም አንዱ ፈራ ከዐዘቅቱም አውጡኝ ብሎ ወጣ ወደ ወሽባው ቤትም ገባ ፈጥኖም ሞተ ዋጋውንም አጠፋ የፈለገውንም አላገኘም።
አርባ አክሊላትም ከሰማይ ሲወርዱ በሠላሳ ዘጠኙ ሰማዕታት ላይም ሲቀመጡ አንዱ አክሊልም በመልአኩ እጅ ተንጠልጥሎ ሲቀር ከወታደሮች ይህን ያየ ከዚያ ተነሥቶ በጌታ አምኖ ልብሶቹንም አውልቆ ቅዱሳን ወደአሉበት ወደ ዐዘቅቱ ወረደ በመልአኩ እጅ ተንጠልጥሎ የቀረውንም አክሊል ወሰደ ።ከዚህ በኋላም በእሳት አቃጥለው ስጋቸውን ኸደ ባሕር ጣሏቸው።
ከዚህም በኋላ በሦስተኛ ቀን ለስብስጥያ አገር ኤጲስቆጶስ ተገለጡለትና። ስጋቸውን ከወንዝ እንዲያወጣ ነገሩት ኤጲስቆጶሱሕ አስወጥቶ ቤተክርስቲያን አሰራላቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፲፪ (12 ) ቀን።
❤ እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ #ፈላስፋው_በለዓም ለተላከበት ወራዊ መታሰቢያ በዓልና ለከበረና ለተመሰገነ ለእስክንድርያ ዐሥራ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ድሜጥሮስ ለልደቱና ድንግልናውን ለገለተለጠበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከፍልስጥዔም አገር ከሆነ #ከቅዱስ_መላዚ በሰማዕትነት ከዐረፈ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ቅዱስ_ሚካኤል_ወደ_በለዓም_መላክ፦ በለዓምን እስራኤልንም ይረግማቸው ዘንድ ባላቅ በጠራው ጊዜ። በጐዳናም በፊቱ ቅዱስ ሚካኤል ቆሞ ስለተገለጠ አስደንግጠው አህያው በሰው አንደበት እስተናገረች ድረስ። መርገሙንም ወደ በረከት መለሰው። በቅዱስ ሚካኤል በአማላጅነቱ ለዘላለሙ ይጠብቀን አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ቅዱስ_ድሜጥሮስ፦ ድንግልናው የመገለጡ ምክንያት እንዲህ ነው ከእርሱ በፊት ሊቀ ጳጳሳት ለነበረው ለቅዱስ ዮልያኖስ መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት "አንተ ወደ ክብር ባለቤት ወደ ክርስቶስ ትሔዳለህ የወይን ዘለላ ይዞ ነገ ወደ አንተ የሚገባ ሰው ከአንተ በኋላ ሊቀ ጳጳስ ሊሆን የሚገባው እርሱ ነው" አለው።
❤ ማግስት በሆነ ጊዜም የከበረና የተመሰገነ ድሜጥሮስ የወይን ዘለላ ይዞ ወደ ከበረ ዮልያኖስ ዘንድ ገባ ቅዱስ ዮልያኖስም ያዘው "ከእኔ በኋላ ሊቀ ጳጳሳታችሁ እንሆ" ብሎ ለሕዝብ አስረከባቸው ስለእርሱም የእግዚአብሔር መልአክ እንደተገለጠለት ነገራቸው።
❤ አባ ዮልያኖስም በዐረፈ ጊዜ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ከእርሱ በቀር ሚስት ኑራው የተሾመ የለም።
❤ ሰይጣንም በሰዎች ልቡና አደረ። በእርሱ ላይም በመናገር የሚያሙት ሆኑ። ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለቅዱስ ድሜጥሮስ ተገልጦ እንዲህ አለው "ከሕዝቡ የሚያሙህ አሉና ከልባቸው ጥርጥርን ልታርቅ ይገባሃል። ከሚስትህም ጋር ያለውን የገድልህን ምሥጢር ልትገልጥላቸው ይገባሃል አንተ ራስህን አድነህ በአንተ ምክንያት ሌሎች ይጠፉ ዘንድ አይገባህም ቸር ከሆንክስ ወገኖችህን ለማዳን ትጋ" አለው።
❤ ማግስት በሆነ ጊዜም ይህም መጋቢት ዐሥራ ሁለት ቀን ነው የቁርባንን ቅዳሴ ቀደሰ። ሕዝቡንም እንዲጠብቁ እንጂ ከቤተ ክርስቲያን እንዳይወጡ አዘዛቸው። ደግሞ እሳትን እንዲያነዱ አዘዛቸው ወደ ሴቶች መቆሚያም ልኮ ሚስቱን አስመጣት ከሥራው የተነሣ ሕዝቡ ያደንቁ ነበር ምን ሊሠራ እንደፈለገ ሕዝቡ አላወቁምና።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ ተነሥቶ ተንቀሳቀሰ ከእሳቱ መካከል ገብቶ በመቆም በእሳቱ እየነደደ በውስጡ ጸለየ ከእሳቱም ፍም በእጁ ዘግኖ በልብሰ ተክህኖው ላይ አኖረ በእሳቱ ውስጥም ቁሞ ለረጅም ጊዜ ጸለየ በልብሰ ተክህኖው ውስጥ ያለ እሳቱንም አይቀጣጠልም። ከዚህም በኋላ ሚስቱን ጠርቶ ያንን እሳት በመጐናጸፊዋ ውስጥ ጨመረ ረጅም ጸሎትም ጸለየ ከልብሶቻቸው ምንም ምን አላቃጠለም። ሕዝቡም አድንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
❤ ሕዝቡም ይህን ሥራ በምን ምክንያት እንደሠራ ያስረዳቸው ዘንድ የከበረ ቅዱስ ድሜጥሮስን ለመኑት። እርሱም ከሚስቱ ጋራ ያለውን ገድሉን ገለጠላቸው "ያለውዴታው እርሷም ጋብቻ ሳትሻ እንዳጋቡት እንዲህም አለ እነሆ በአንድነት እኛ አርባ ስምንት ዓመት ስንኖር በጋብቻ ሥርዓት ከተገናኘንበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ አልጋ አንድ ልብስን እንተኛለን ግን ወንዶች ሴቶችን በግብር እንደሚአውቋቸው ሴት እንደሆነች አላውቃትም። በዚህ ሁሉ ዘመን በየሌሊቱ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ እየወረደ በክንፎቹ ይሸፍነናል። ይህንንም በዚህ ሁሉ ዘመን ከሰው ወገን ለማንም ከቶ አልገለጥኩም። ልገልጠውም ከቶ አልሻምና ግን እናንተ ከበደል ትድኑ ዘንድ እርሱ እግዚአብሔር አዘዘኝ እንጂ" አላቸው።
❤ ከአዩትና ከሰሙት የተነሣ ሕዝቡ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔር አመሰገኑት እርሱን ስለማማታቸው የበደሉትን በደል ይቅር ይላቸው ዘንድ እያለቀሱ ቅዱስ ድሜጥሮስን ለመኑት። እርሱም ስሕተቻቸውን ይቅር ብሎ "በጎ ሥራን ከሚጠላ ከሰይጣን እንጂ ከእናንተ አይደለምና አትዘኑ" አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ባረካቸው ወደ ቤታቸውም ይገቡ ዘንድ በሰላም በፍቅር አሰናበታቸው ከሊቀ ጳጳሳቱ ከቅዱስ ድሜጥሮስ ከአዩት ተአምራት የተነሣ እግዚአብሔር እያመሰገኑ ወደ ቤታቸው ገቡ። ከቅዱስ ድሜጥሮስ በጸሎቱ የምትገኝ በረከት ከእኛ ጋር ለዘላለም ትኑር። ምንጭ፦ የመጋቢት12 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለድሜጥሮስ እንተ በእዴሁ ተጽሕፋ። ሐሳበ አዝማን ዘድኅር ወእለ ኀለፋ። አርአየ ዮም ኃይለ ድንጋሌሁ በሥምረተ አምላክ አልፋ። ዐቊሮ እሳት በኵፋሩ ወለብእሲቱ በዓጽፋ። ለእለ ናፈቁ ሕዝብ ከመ ይኩን ተስፋ"።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለከ_ሰማዕት_መላዚ። ዘምድረ ፍልስጥዔም ወልደ አግአዚ። ምሕረተ ነድያን እለቡ እንዘ ኢይሴዚ። ከመ ታምክረኒ ነዓ ናዛዚ። ቅድመ ይዳደቀኒ ሊተ እደ ሞት አኀዚ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢ_12።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አእይንትየሰ ኀበ መሃይምናን ምድር። ከመ አንብሮሙ ምስሌየ። ዘየሐውር በፍኖት ንጹሕ ውእቱ ይትለአከኒ። መዝ 100፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-17።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ_ምሰባክ፦" ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታምእሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ33፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥10-21። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥1-8፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-ፍ.ም እና የሐዋ 27፥1-11። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል ወራዊ በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን #ለቅዱስ_ቴዎቄጤኖስ፣ ለብፅዕት #ቅድስት_እስክንድራ በንጉሥ መክስምኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና #ለተጋዳይ_ለሆኑ_ለኤጲስቆጶስ በመኰንኑ ልጅ መቃብር ላይ ጸሎት አድርገው ልጁን ከሞት ላስነሱና ሕዝቡን አሳምነው ላጠመቁ #ለአባ_ባስሊዖስ ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከአውሳብዮስ_ከኤፍሬም_ከአርቃድዩና ከሰማዕቱ ኤልያስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ቴዎቄጤኖስ፦ ይህ ቅዱስ አስቀድሞ ወታደር ነበር። ትጥቁን በንጉሡ ፊት ጥሎ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ታመነ ከርሱም ጋር ብፅዕት እስክንድራ አለች።
❤ ንጉሡም ሰምቶ ተቆጣ ልብሱን አስወልቀው የሴቶች ልብስ አልብሰው ከሚፈትሉ ሴቶች ጋር እንዲጨምሩት ከዚያም የጋለ የብረት መንኰራኵር በላዩ አድርገው ዘቅዝቀው ቊልቊል እንዲሰቅሉት አዘዘ። ሁለተኛም እንዲህ ብሎ አዘዘ "የፈላ ቅጥራን የተመላ ወጭት አምጥታችሁ ወደ ጆሮው እስቲደርስ በራሱ ላይ ድፉበት ደግሞ ከተሰቀለበት አውርደው ከእሥረኛዋ እስክንድራ ጋር በፊቱ እንዲያቆሙት" አዘዘ። ከዚህም በኋላ ምላሱን እንዲቆርጡ አዘዘ በእሊህ ቅዱሳን በአንገቶቻቸው የሚካበዱተጋድሎአቸውንና ድንጊያዎችን አሥረው በኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ እንዲጥሉአቸው አዘዘ። በዚያም ምስክርነታቸውን መጋቢት11 ፈጸሙ ሥጋቸውንም ምእመናን አግኝተው በሥውር ቦታ ቀበሩት። የቅዱስ ቴዎቄጤኖስ በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ባስሊዖስ፦ ይህንንም ቅዱስ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት አባ አርሞን ከሌሎች ኤጲስቆጶሳት ጋር ሾመው። በታወቀና በተወሰኑ ቦታ ላይ አይደለም። በእምነት በሌላቸው በአረማውያን አገር ይሰብክ ዘንድ ላከው እንጂ።
❤ ይህም ቅዱስ ወደ ከሀድያን አገር ገብቶ የከበረ ወንጌልን ሰበከ። እነርሱም እየደበደቡ በአገራቸው ሁሉ አዞሩት። ደግሞ ወደ ሠርዑና አገርሮች ገብቶ የከበረ የወንጌል ትምህርትን አስተማረ። እኩሌቶቹ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ያላመኑት እኩሌቶቹ ከሀዲያን አስደዱት ከከተማው ውጭ ወጥቶ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። የዚያች አገር ስዎች እግዚአብሔር ወደ ማወቅ ይመለሱ ዘንድ በአንድ ልጁም ያምኑ ዘንድ ስለዚያች አገር ሰዎች አዘወትሮ እግዚአብሔር ማለደ።
❤ በዚያንም ሰሞን ለእርሱ ለአባቱ አንድ ብቻውን የሆነ የመኰንኑ ልጅ ሞተ። አባቱም ታላቅ ኀዘንን አዘነ መኰንኑ አባቱም በሕልምሙ ልጁን አየው። እርሱም በፊቱ ቁሞ "አባቴ ሆይ እንሆ እኔ በታላቅ ጨለማ ውስጥ ነኝና ወደ ክርሰቶስ ስለ እኔ ይጸልይ ዘንድ ኤጲስቆጶሱ አባ ባስሊዖስን ጠርተህ ለምነው ሲለው ነበር"። ከእንቅልፋም በነቃ ጊዜ ደንግጦ ተነሣ ከእርሱም ጋር የአገር ታላላቆችን ይዞ ወደ ቅዱስ ባስሊዖስ በዓት ሔዶ። ከእርሱ ጋራም ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ልጁ እንዲጸልይ ለመነው። እርሱም ልመናውን ተቀብሎ። ወደ ከተማ ገባ በመኰንኑ ልጁ መቃብር ላይም ጸለየ ያንጊዜም የመኰንኑ ልጅ ድኖ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተነሣ መኰንኑ ሕዝቡም ሁሉ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ከአገርም ሰዎች ብዙዎች አምነው የክርስትና ጥምቀትን በቅዱስ ባስሊዖስ እጅ ተጠመቁ በዚያቺም አገር ታላቅ የክርስቲያኖች ጉባኤ ሆነ።
❤ ክፉዎች ሰዎችም ባስሊዖስን ቀንተውበት በጠላትነት ተነሡበት በክርስቶስ ከማያምኑ ጋር ተሰባስበው ወደ ሸንጓቸውም አደረሱት ይህን ቅዱስ ታላቅ ግርፋትን ገረፉት ነፍሱንም በጌታችን እጅ እስከሰጠ ድረስ እያሠቃዩ በዚያች አገር አዋሉት። የቅዱስ ባስሊዖስ በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላሙ ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት11 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለቴዎቄጤኖስ_ዘአድኀኖ°አምተኃጒሎ። ተመትሮ ልሳኑ ኢክህለ ለነቢበ ቃሉ ያብጥሎ። ለእስክንድራ ብፅዕት እንተ ተሳተፈት ገድሎ። ዕብንኒ ዘመኰንን ሰቀሎ። ከመ ልጥረ ፀምር ለክሣዱ ቀሎ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት_10።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ፍታሕ ሊተ እግዚኦ እስመ አንሰ በየዋሃትየ (በየውሃትየ) አሐውር። ወተወከልኩ በእግዚአብሔር ከመ ኢይድክም። ፍትነኒ እግዚኦ ወአመክረኒ"። መዝ 25፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥1-6፣ ያዕ 214-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 27፥22-27። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ አሌፍ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን #ከተሰዓቱ_ቅዱስ ለአንዱ ኤርትራ ጠረፍ አካባቢ የሚገኘው ደብረ ብኅዛን (አኅሰአ) ለመሰረቱት #ለአቡነ_አሌፍ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_አሌፍ፦ ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት። አባ አሌፍ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው። ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው።
❤ ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው። በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ።
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው።
❤ አባ አሌፍን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው። እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል። አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል።
❤ በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ። ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ።
❤ በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም። ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ.ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ።
❤ ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው። ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው። ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች። አባ አሌፍና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር።
❤ ልሳነ ግእዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ። በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ አሌፍ እንደ ገና አቀጣጠሉት።
❤ ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት። የካደውን እየመለሱ፤ የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ። ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::
❤ ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው። በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ አሌፍ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር። በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር። ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::
❤ የነ አባ አሌፍ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ። ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው። እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ።
*ዸንጠሌዎን በጾማዕት::
*ገሪማ በመደራ::
*ሊቃኖስ በቆናጽል::
*አረጋዊ በዳሞ::
*ጽሕማ በጸድያ::
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ።
*አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ (እዛው ትግራይ) ሆነ።
❤ አባ አሌፍ የተወለዱት አውሎግሶንና አትናስያ ከተባሉ ደጋግ ወላጆች ቂሳርያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው። ጻድቁ በሕጻንነታቸው ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ገብተው ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ከ8ቱ ጉዋደኞቻቸው ጋር ወደ ኢትዮዽያ የመጡ ሲሆን ከተስዓቱ /9ኙ/ ቅዱሳን አንዱ ናቸው።
❤ በዐፄ አልዓሜዳ ዘመን አክሱም አካባቢ (ቤተ ቀጢን) የሃገራችንን ቋንቋ አጥንተው ቅዱሳት መጻሕፍትን ተርጉመዋል። ለሕዝቡም የወንጌልን የምሥራች ሠብከዋል።
❤ ከዚያም ገዳም መሥርተው፤ 500 መነኰሳትን ሰብስበው ለ70 ዓመታት በቅድስና ኑረዋል። ለዘጠኙ ቅዱሳን ሁሉ ስም ያወጡት የዘመኑ ሰዎች ቀድመው ወደ አክሱም ስለ ገቡ ጻድቁን "አሌፍ" ብለዋቸዋል። በዕብራይስጥኛ "አንደኛ" ማለት ነው። ጻድቁ ከፈጣሪያቸው የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብለው በዚሕች ቀን አርፈዋል። ከአባታችን ከአቡነ አሌፍ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ዝክረ ቅዱሳን ዘተዋሕዶ ከዲያቆን ዮርዳኖስ መጽሐፍ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ ታላቁን ዲማ ጊዮርጊስን ለመሠረቱ #አቡነ_ተከስተ_ብርሃን_ዘደብረ_ድማኅ ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ተከስተ_ብርሃን፦ ትውልድ ቦታቸው መንዝ ከሚባለው አገር ነው። ይህች መንዝ የምትባለው አገር የምትገኘው በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለየች በደብረ ብርሃን አውራጃ ውስጥ ነው። መንዝ ማለትም ነዝሀ ከሚለው ከግእዝ ቃል የተገኘ ነው። መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል እግዚአብሔር በሰጠው (በፈቀደለት) ስልጣን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም በሰጠው ተስፋ በተወለደ በ33 ዓመት ከ3 ወር ወንጌልን አስተምሮ ለድኅነተ ዓለም መጋቢት 27 ቀን በዕለተ አርብ በተሰቀለ ጊዜ የፈሰሰ ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን መነሳንስ ዓለምን ሲረጭ አስቀድሞ ይችን መንዝ የምትባልን አገር ከሁሉ አስቀድሞ ስለረጫት ደመ መለኮቱን እንደ አውድማ ስለለቀለቀው በዚህ ምክንያት መንዝ ተብላለች።
❤ በዚች ቦታ ብዙ ቅዱሳን ተፀንሰው ተወልደውባታል። ከነዚህም ቅዱሳን በአካባቢውና በዚች ቦታ የተወለዱ እነ ቅዱስ ፊልጶስ፣ እነ ቅዱስ አኖሬዎስ፣ እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ እነ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እርሷ የመሰሉ ብዙዎች ቅዱሳን ተፀንሰው ተወልደው አድገውበታል። ይህች ቦታም የተባረከች የተቀደሰች መሆኗ ቅዱስ አባታች ተፀንሰው እዲወለዱ አድርጋለች።
❤ እኚህ አባታችን አቡነ ተከስተ ብርሃን የመጀመርያ ስማቸው አባ በኪሞስ ይባላል። እኚህ አባ በኪሞስ ከመንዝ መንኖ ደብረ ሊባኖስ ሲረዱ ቆይቶ ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር በ12ኛው ክፍለ ዘመን በአምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት እንደ መጡ ገድላቸው ይናገራል። መጥተውም የተቀመጡበት ቦታ ቢቸና አውራጃ ድማ ጊዮርጊስ ነው። ከዚያም አባታቸው አቡነ ፊልጶስ ወደ ትግራይ ሲሰደዱ እሳቸውም ተሰደው ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ መምህራቸው አቡነ ፊልጶስ "ወደጎጃም ክፍለ አገር ሂደህ አስተምር" አሉት።
❤ ከዚያ ተነስተው በግሸና አድርገው የዐባይ ባሕር ተከፍሎላቸው ወደ ጎጃም ክፍለ አገር ተሻግረው አስተምረው በአንድ ቀን ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ (9999) ምዕመናንን ሲያጠምቁ አምደ ብርሃን ተተክሎ እያበራ ከዚያች ቦታ ስለታየ በኪሞስ ይባል የነበረ ስማቸው ተከስተ ብርሃን ተባሉ። ወንዚቱም እሳት ዙሪያዋን ስለከበባት ነድ ሐጸረ ተብላ ዛሬም ነድ አጥራ እየተባለች ትጠራለች። ከዚህ ተነስተው ወደ ቢቸና አውራጃ እነማይ ወረዳ ውስጥ አንድ ጫካ አገኘ። ከዚያም የያዙትን ታቦት በአንድ ዋሻ አኑረው። ስሟንም ዲማ ማርያም አሏት።
❤ ከዚህ በኋላ ተነስተው ገድ ወንዝ ላይ የነበረችቱን ብዙ ሕዝቦች ይሰግዱላት ያመልኳት የነበረችቱን ሙላድን ከዚያ አባረው ሰኔ 21 ቀን አገው ምድር እንጁባራ ላይ አድርሰዋት ተመልሰው ሲመጡ ዐባይን ተሻግረው ጉታ ሲደርሱ ከዚህ ናዳ ማርያም ገዳም ዐርፈው እንደሄዱ ገድላቸው ይናገራል። ከዚያ ተነስተውም ወደ ዲማ ሂደዋል። ከዚያም ድማ ማርያም የምትባል ተክለዋል። ድማ ማለት በኦሮምኛ ቋንቋ ቀይቱ ማርያም ማለት ነው።
❤ ከዚያም የወንዶችና የሴቶች ገዳም አቋቁመው ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ መጋቢት 9 ቀን ታመው ብዙ ቃል ኪዳን ተቀብለው ስምህን የጠራ፣ በዓልህን ያከበረ፣ ዝክር የዘከረ እስከ 22 ኛው ትውልድ እምርልህለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኋላ መጋቢት 10 ቀን ዐርፈዋል። በዚያው ባቋቋሙት በድማ ማርያም ተቀብረዋል። ከአባታች አቡነ ተከስተ ብሃርሃን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ ከገድለ አቡነ ተከስተ ብርሃን መቅድም።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርሰቶስ_ለመስቀሉ_በንግሥት_ዕሌኒ አማካኝነት ተቆፋሮ ለተገኘበት፣ በድጋሚ በፋርሶች ከኢየሩሳሌም ተወስዶ እንደገና #በሮሜው_ንጉሥ_ሕርቃል ለተገኘበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የቅዱስ_መስቀሉ_መገኘት_ታሪክ፦ የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሁኖአል። መጀመርሪያ የጻድቁ ንጉሥ የቈስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግሥት ዕሌኒ እጅ ነው። እርሷ ለእግዚአብሔር ተስላ ነበርና ልጅዋ ቈስጠንጢኖስ ወደ ክርሰቲያን ሃይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልገው በኢየሩሳሌምም ያሉ ቅዱሳን መካናትንና አብያተ ክርስያናትን ልታንፃቸው ነው።
❤ ከዚህ በኋላ ልጅዋ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠመቀ ጊዜ ዕሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች ከእስዋ ጋራም ብዙ ሠራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች ቦታውንም የሚአስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ ሽማግሌ ሰው አሥራ በረኃብና በጥማት አስጨነቀችው። በተጨነቀም ጊዜ ለንግሥት ዕለኒ የጎልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው። ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግሥት ዕሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ ዓመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ።
❤ አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሦስት መስቀሎች ተገለጡ የክቡር ባለቤት ክርሰቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ። አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሣም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሣም ከዚህም በኋላ ሦስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሣ ዕሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት። ለልጅዋ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል መጽሐፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋር ወደ ልጅዋ የላከችው ነው።
❤ ከዚህም በኋላ ሥርዓታቸውና የሕንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት ተጽፎ የሚገኝ አብያተ ክርስያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች።
✝ ✝ ✝
❤ #ሁለተኛው_በሮሜ_ንጉሥ_በሕርቃል_ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብጽ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዩ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሃን ሲበራ አይቶ ሊያነሣው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።
❤ ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው። ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።
❤ የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እንደማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወሰዱ የሮም ንጉሥ ሕርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲጾሙ ምእመናንን አዝዞ ወደ ፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ ዕፀ መስቀልንም እየፈለገ በአገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።
❤ ያ ዲያቆናቱንና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አንጻር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው። ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷ የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉሥ ሕርቃልም ሒዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው። ይህንም ንጉሥ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋር ብዙ ሠራዊት ሁኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ። ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቆፍረውም የከበረ ዕፀ መስቀልን አገኙ ከዐዘቅቱም አወጡት ንጉሡና ሠራዊቱም ሰገዱለት። በልብስ መንግሥቱም አጐናጸፈው ታላቅ ክብርንም አከበረው እጅግም ደስ አለው ከሠራዊቱ ጋር።
❤ የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት ዐሥር ነው። ከዚህ በኋላ ንጉሡ የከበረ ዕፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው። የመድኃኒታችን የመስቀሉ በረከት ከሁላችን የክርስቲያን ወገንኖች ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 10 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-17።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 6፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 4፥1-11 እና የሐዋ ሥራ 24፥1-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የመስቀለ ኢየሱስ በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
+4
ቀን 09/07/17 የማክሰኞ የወጣት እና የአዳጊ መርሀ ግብር በዚ መልክ አሳልፈናል
በዕለቱ የንስሀ መዝሙራት : በስፋት አስተምረውናል በትምህርቱ ሠላሳ ስልሳ መቶ ያማረ ፍሬ እናፈራ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን
ለቀጣይ ሳምንት በሰላም በጤና ያገናኘን
