ch
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

显示更多
4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
📖📻 #ዝጎራ 📻📖 @EOTC2921 ✍ ደራሲ፦ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ 🎙 ተራኪ፦ አያልቅበት ተሾመ ክፍል_፫_3 t.me/EOTC2921

📖📻 #ዝጎራ 📻📖 @EOTC2921 ✍ ደራሲ፦ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ 🎙 ተራኪ፦ አያልቅበት ተሾመ ክፍል_፪_2 t.me/EOTC2921

📖📻 #ዝጎራ 📻📖 @EOTC2921 ✍ ደራሲ፦ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ 🎙 ተራኪ፦ አያልቅበት ተሾመ ✈ #ሥውር_ትዕዛዝ ክፍል_፩_1 t.me/EOTC2921

🌾✞ #ያከብርዋ_ለሰንበት ✞🌾 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት ||፪ ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያዕረፋ ባቲ እስመባቲ አዕረፈ እምኩሉ ገብሩ |||፪ 🌾✞¤¤¤~~~✞~~~¤¤¤✞🌾 ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃንም በገነት ||፪ ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ |||፪ ➤➤➤➤➤➤✞➤➤➤➤➤➤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

https://t.me/EOTC2921 🌾✞ #ማርያም_አርጋለች ✞🌾 ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪) የሰማይ መላእክት እያረጋጒዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = = ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = ✞✞✞ = = =

☞❀በ69 ዓ.ም. ያረፈው ከ72ቱ አርድዕት የኾነው የአንጾኪያ የመጀመሪያው ጳጳስ ቅዱስ ኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር ፳፩ የኾነ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና በነሐሴ ፲፮ የተከናወነ በዓለ ዕርገቷን በዐይኖቹ የተመለከተውን “ድርሳን ዘደረሰ አባ ኢቮዲየስ ሊቀ ጳጳሳት ዘአንጾኪያ በእንተ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” (Evodius of Rome, Homily on the Dormition The falling asleep of Mary) በሚል ርዕስ ሲጽፍ የዚኽ መጽሐፍ ቅጂ በታችኛው ግብጽ ይነገር በነበረው በቦሃይሪክ ቅጅ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጻፈው ተገኝቷል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፍ ላይ ያንብቡ፨ ☞❀ቅዱስ ሚሊቶ በምዕራብ አናቶሊያ በሲሚርና አጠገብ በሳርዴስ ጳጳስ የነበረ ሲኾን በግሪክ (Μελίτων Σάρδεων Melíton Sárdeon) ሲባል ዕረፍቱም በ፻፹ (180) ዓ.ም ነው፤ ሊቁ ጀሮም የብሉይ ኪዳን ቀኖናን ሚሊቶ ሠርቶ እንደነበር መስክሮለታል፡፡ የጻፋቸውም መጻሕፍት ዝርዝር አውሳብዮስና ጀሮም ጽፈውት እናገኛለን፡፡ ብዙ መጻሕፍት ሲኖሩት በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ኅልፈተ ሕይወትና አካላዊ ዕርገት አስመልክቶ "የሳርዲሱ ቅዱስ ሚሊቶ የቡርክት ማርያም ኅልፈተ ሕይወት ትምህርት" The Passing of Blessed Mary) በሚል ርዕስ ርሱም እንደ ሐዋርያትና ሰባ አርድእት ጽፏል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ ዐማርኛ ቋንቋ በነገረ ማርያም በሊቃውንት ተተርጉሟል። ☞❀በ380 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ጳጳስ የነበረው ጢሞቴዎስ (Timothy of Jerusalem) ሲገልጽ “Wherefore the Virgin is immortal…” (ድንግል እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው) በማለት ሞት በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሳረጋት መኾኑን መስክሯል፡፡ ☞❀በተጨማሪም ከ70 ዓ.ም. ጀምሮ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ በነበረው ስደት በክርስቲያኖች ዘንድ ዐፅመ ቅዱሳን ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ሲኾን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ እንደሚያስረዱን በዚያ የስደት ዘመን ክርስቲያኖች በድፍረትና ሐላፊነትን ተሸክመው በቈራጥነት የሰማዕታትን ሰውነት ከመግደያው ስፍራ በመውሰድ ዐፅማቸውን በክብር ይጠብቁ የነበረ ሲኾን ይኽነንም አጥብቀው በመጠበቃቸውና ለትውልድ በማስተላለፋቸው የከበረ ዐፅማቸው ባረፈበት ቦታ ላይ ዛሬ አብያተ ክርስቲያን ታንጸውበት እጅግ በርካቶች ጐብኚዎች እየጐበኙት ሲገኙ ለምሳሌ ያኽል የነቅዱስ ጴጥሮስ፣ የነቅዱስ ጳውሎስ፣ የነቅዱስ ቶማስ፣ የነያዕቆብ ወ.ዘ.ተ የከበረ ዐፅማቸው ስፍር ቊጥር በሌላቸው ሰዎች ከጥንት ዠምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲጐበኝና ሲታይ የቅድስት ድንግል ማርያምን አንድ የራሷን ጠጒርና የእጇን ጥፍር አገኘኊ የምትል ምንም ሀገርና ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ፈጽማ የለችም ምክንያቱም አምላካችን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ያደረባት የአምላክ ታቦት ክቡር ዳዊት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” ብሎ ትንቢት እንደተናገረላት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በዕረፍቱ ስፍራ አለችና ነው፡፡ ☞❀ይኸውም ሊታወቅ የዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን በ400 ዓ.ም አካባቢ ነግሦ የነበረው ንጉሡ ማርሲያን የኢየሩሳሌሙን ፓትሪያርክ የቅድስት ድንግል ማርያም ዐፅም ካለ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲያመጣለት ቢጠይቀው ርሱ ግን እመቤታችን እንዳረገችና ምንም ዐይነት የርሷ ቅሪት እንደሌለ አስረድቶ ስለ ዕርገቷ ጽፎለታል። ☞❀የሚገርመው ቅሪቶች ከፍተኛ ዋጋ ስላላቸው ብዙ ሰዎች ወደ ከተማቸው ጐብኚዎችን ለመሳብ ሲሉ አስመስለው ለመሥራት በመሞከራቸው ብዙዎች ተከሰው የነበረ ሲኾን ለምሳሌ አክሊለ ሦኩን መስቀሉን አስመስለው ለመሥራት ከበፊት ዠምሮ ቢሞክሩም ኾኖም ግን የቅድስት ድንግል ማርያም አካል አለን የሚልና የሚሞክር ከጥንት ዠምሮ እስከ ዛሬ በዓለም ላይ ለምን ጠፋ? ቢባል ማንም ሰው ይኽነን ሐሰት ስለማያምንና ከሐዋርያት ጊዜ ዠምሮ እስከ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እስከ አኹንም ድረስ የቅድስት ድንግል ማርያም አካል ፈጽሞ በምድር ላይ እንደሌለና ወደ ሰማይ በአካል እንዳረገች ስለሚታወቅ ነው፡፡ ☞❀በተጨማሪም ከመዠመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን-16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስም የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በቤተ ክርስቲያን፣ በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ኹሉ ሙሉ በሙሉ የታወቀ በመኾኑ በዕርገቷ ዙሪያ ምንም ዐይነት የጥርጥር ጥያቄን ያቀረበ ማንም የለም፡፡ ☞❀ዛሬ በጭፍኑ አንዳንዶች ከዕውቀት የራቁ መናፍቃን የካዱትን ይኽነን እውነታ የእምነቶቻቸው መሥራቾች እንኳን ደፍረው አልተናገሩትም ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሪፎርመር የኾነው ሄንሪች ቡሊነግር በ፲፭፻፴፱ (1539 ዓ.ም) ላይ ጣዖታትን ተቃውሞ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስለማረጓ ሲገልጽ፦ "Elijah was transported body and soul in a chariot of fire; ...he was not buried in any Church bearing his name,…It is for this reason, we believe, that the pure and immaculate embodiment of the Mother of God, the Virgin Mary, the Temple of the Holy Spirit, that is to say her saintly body, was carried up to heaven by the angel." (ኤልያስ በሥጋና በነፍስ ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ወጣ፤ በርሱ ስም በተሠየሙ ባንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን አልተቀበረም፤ ይኽም ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ለሚያምኑበት ለነቢያቱ ድንቅና ለማይነጻጸሩ ፍጡራኑ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀ ያሳውቀናል … በዚኽ ምክንያት የአምላክ እናት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ፣ አካሏ ንጹሕና ኀጢአት አልባ የኾነው የድንግል ማርያም ንጹሕ የተቀደሰ ሰውነቷ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንዳረገ እናምናለን) በማለት ጽፏል (Heinrich Bullinger, cited in Thurian, page 89, 197, 198) ☞❀ዛሬ ደግሞ ጥቂቶች ይኽነን እውነት መቃወማቸው የእምነት መሪዎቻቸው እንኳን ያስተማሩትን ትምህርትና የጻፏቸውን መጻሕፍት እንዳላነበቡ ያጋልጥባቸዋል፡፡ ☞❀ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ከሚታሰብባቸው ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣ ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን፣ ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ኮትዲቭዋር፣ ማዳጋስካር እና ሌሎች በርካቶች የዓለም ሀገራት ይገኛሉ (Columbus World Travel Guide, 25th Edition) 🙏እመቤታችን ሆይ ከልጅሽ መንግሥት ለይቶ ሳጥናኤል ከሰራዊቱ ጋር ወደ ሚገባበት ዘላለማዊ እሳት ውስጥ ከሚያስጥል የሃይማኖት ክሕደት እኛ ልጆችሽን በምልጃሽ ጠብቂ አሜን🙏 [ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]

#የቅድስት_ድንግል_ማርያምን_እውነተኛ_ዕርገት_ክደው_ለሚያስክዱ_በዘመናችን_ለተነሡ_ሐሰተኞች_የተሰጠ_ምላሽ ☞❀ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ሥር በአደራ የተቀበለ ፲፭ ዓመት ከርሷ ጋር የኖረ በ፷፬ ዓመቷ የኾነ ዕረፍቷን፣ ፍልሰቷን፣ ትንሣኤዋን፣ ዕርገቷን በዐይኑ ያየው ቅዱስ ዮሐንስ አምላክን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ለመሸከም የበቃች የአምላክ ታቦት ካረገች በኋላም በሰማያት ያላትን ታላቅና ፍጹም ክብር በራእ ፲፩፥፲፱ ላይ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ከተናገረ በኋላ በተከታይነት አሕዛብንም ኹሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ የወለደች ርሷ በሰማይ ፀሓይን ተጐናጽፋ፣ ጨረቃን ተጫምታ፣ ከዋክብትን ደፍታ እንዳያት ጽፏል፡፡ ☞❀ዮሐንስ የአምላክ ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያምን በዕርገቷ በሰማያት ያላትን ክብር በዐይኑ ዐይቶ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ሲጽፍልን፤ ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ዳዊት ደግሞ አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” በማለት ክብር ይግባውና ልጇ በሥልጣኑ አስቀድሞ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ለዐይን ቅጽበት እንኳን ወዳልተለየው ወደ ጌትነቱ ዙፋን ወደ ሰማይ እንዳረገ ኹሉ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችው ታቦቱ ቅድስት ድንግልም በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ እንደምታርግ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ ☞❀በዚኽ አማናዊ ምስክርነት በሰማይ ዮሐንስ ያያት ታቦት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ያረገችው የአምላክ ታቦት ንግሥተ ሰማያት ወምድር ቅድስት ድንግል ናትና ኢትዮጵያዊዉ ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት የተባለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ “ወታቦተ ራእየ ምስጢረ ኅቡአቲሁ ለዮሐንስ አቡቀለምሲስ ረኣዬ ኅቡአት” (የተሰወረ ነገርን የሚያይ የራእይ አባት የዮሐንስ የምስጢራቱ ምስጢር ራእይ ታቦት አንቺ ነሽ) በማለት በትክክል ገልጾታል፡፡ ☞❀ጌታችን እንኳን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን በዠርባዋ ያዘለችውን በክንዶቿ የታቀፈችውን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የኾነው ታቦቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ትቅርና ያገለገሉት ወዳጆቹን እንኳን ሞትን ሳያዩ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብብ፤ ለምሳሌ ሔኖክ ሞትን ሳያይ በሕይወቱ ሳለ እግዚአብሔር እንደወሰደው በዘፍ ፭፥፳፬ እና በዕብ ፲፩፥፭ ላይ ተጠቅሷል። ☞❀ነቢዩ ኤልያስም ሞትን ሳያይ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማይ እንደወጣ (፪ነገ ፪፥፲፩‐፲፪) ተጽፎልናል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከእግረ መስቀሉ ሥር በጌታ ሥልጣን ስለተነሡ ቅዱሳን ማቴዎስ ሲጽፍ “መቃብሮችም ተከፈቱ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” ይለናል (ማቴ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡ ☞❀ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ናትና በመቃብር ፈርሶ መቅረት አይስማማትም። ☞❀አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፤ ርሱን በመፅነስና በመውለድ ዕድፍ ጉድፍ ያላገኘው ያልተለወጠ ድንግልናዋ፤ የተሸከመው ማሕፀኗ፤ የታቀፉት ክንዶቿና፣ የዳሰሱት እጆቿ፤ የሳሙት ከንፈሮቿ ያሳደጉት ጡቶቿ፤ ከርሱ ጋር የተመላለሱ እግሮቿና፤ ያዘለው ጀርባዋ፤ ብሩሃት የሚኾኑ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ያላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች የሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ብሥራትን የሰሙ ዦሮቿ ፈጽመው በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት የለባቸውም፤ ከርሷ ሥሮችንና ጸጒርን፣ ደምንና ዐፅምን ነፍስንና ሥጋን ነሥቶ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡ ☞❀የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የነበረ አስተምህሮ ሲኾን ይኽን ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈው በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ነው ብሎ መጻፍ የመጨረሻው የአለማወቅ ጥግ ነው ቢባል አያስከፋም፨ ☞❀ዮሐንስም የዕረፍቷንና የዕርገቷን ነገር በዐይኑ በማየቱ ስለአምላክ እናት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምስክርነት (The Account of St. John the Theologian of the Dormition of the Holy Mother of God) በሚል ርዕስ የጻፈው ሲኾን፤ ይኽም ጽሑፉ በእኛ በብራና በሚገኘው በነገረ ማርያም መጽሐፍ ላይና በመጽሐፈ ፍልሰታ ላይ በቀደምት መተርጒማኖቻችን የተተረጐመልን በመኾኑ ይኽነን የተቀደሰ ታሪክ ቀደምት የኾነችው ቤተ ክርስቲያናችን አስቀድማ አግኝታዋች፤ ይኽ በግሪክ ቋንቋ ተጽፎ የሚገኘው የዮሐንስ ምስክርነት አስቀድሞ በሱርስትና በዐረብኛ ቋንቋ የተተረጐመ ሲኾን በኋላም ወደ ተለያዩ የዓለም ቀደምት ቋንቋዎች ጽሑፉ ተተርጒሟል፤ በዚኹ ምዕራፍ በክፍል ኹለት ላይ ከጽርዕ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ተጽፎ ያለውን ሙሉውን ምስክርነት ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ ተርጉሜዋለኹና ያንብቡ። ☞❀የአርማትያሱ ዮሴፍም ከጌታ ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ያልተለየና ዐብሯቸው የነበረ በመኾኑ የቅድስት ድንግል ማርያምና ዕረፍትና ዕርገት በዐይኖቹ በማየቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገትን ርሱም እንደ ዮሐንስ “ዮሴፍ ዘአርማትያስ የጻፈው የቡርክት ድንግል ማርያም ኅልፈት” (Joseph of Arimathea, The Passing of the Blessed Virgin Mary) በሚል ርዕስ ከእመቤታችን ዕርገት በኋላ የጻፈላት ሲኾን ይኽም አስቀድሞ በላቲንና በሱርስት ቋንቋዎች ተተርጒሞ ይገኛል፤ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ያለውን የአርማትያሱ ዮሴፍን ሙሉውን ምስክርነት በነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ በአማርኛ ቋንቋ አስፍሬዋለኊ፡፡

☞✞ አንድ ንጉሥ መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፦ ✔አስር መዝሙር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ከሰኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ1–10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ30–40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡ ፪. #ውዳሴ_ማርያም ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው። የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡ ✔በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡ ✔በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎችእና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡ ✔እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡ ፫. #ወንጌል_ዘዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡ ✔አባቶች ይህንንጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል። ፬. #ሌሎች_ጸሎታት ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣ እንዲሁም ገድላት፣ ተአምራትን፣ እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡✔አጭር ጸሎት በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል። አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ ሃይማኖት፣ ሰላም ለኪ /ስለውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣ አቡነ ዘበሰማያት፣ አንድ ከመዝሙረ ዳዊት(መዝሙር 150) /በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/ በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው። ✔ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምሆኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል። ✔አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡፡ ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣ አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ። ✔አጭር ጸሎትን እነደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ✔አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው። ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል። ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል። እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው። ሁልጊዜ ወተት መመኘት ሁልጊዜ አልበረታውም እያሉ አጭር ጸሎት እያደረሱ መተኛት ተገቢ አይደለም። ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው። ✔ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል። የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ መዘምራን ወዘተ እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል። አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል። ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል። ✔አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡ ✔በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡ በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን። ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡ ✔የማህበር ጸሎት በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆኗ በእርሷ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው። በካህናት እየተመራ፣ በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው። እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል። "አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፣ ጆሮቼም ያደምጣሉ። ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።"/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው። በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት። በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል። ከዚህ ጋር በሰዓታት፣ በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል፡፡ ✔የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሐይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው። አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል። የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል። ✔ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምክ፣ የጸሎት ዓይነቶችንም በምትችለው መልኩ እያደረስህ፣ በቤተ መቅደስ እየተገኘህ ኪዳን እያደረስህ፣ ቅዳሴ እያስቀደስህ ከፈጣሪህ ጋራ እለት እለት ተነጋገር ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆንይ መጣል፡፡ ስለዚህ በርታና ጸልይ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡ አሜን፡፡ 🙏✞ የእግዚአብሔር አብ በረከት፤ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፤ የጻድቃን የሰማዓታት ፀሎት፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖታችን ይጠብቅልን፡፡ አሜን ለዘላለሙ፡፡ ✞🙏

❀♣✞ #ጸሎት ✞♣❀ #ምን_ዓይነት_ጸሎት_ልጸልይ? #ሊነበብ_የሚገባው_ድንቅ_አስተምሮ ☞✞ ጸሎት በክርስትና ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በጥያቄዎቻችሁ መሠረት የምንጸልይባቸውን ጊዜያት፣ የምንጸልየውን የጸሎት ዓይነት፣ ምን መምሰል እንዳለበት ለማየት እንሞክራለን፡፡ #1. የጸሎት ጊዜያት ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ፣ ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡ ➊. #ጸሎተ_ነግህ ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡ ✔ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን። ✔የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ ✔የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡ ✔የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ✔ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን። ➋ #ጸሎተ_ሠለስት ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ ይህ የጸሎት ጊዜም የምናስበው፦ ✔ሔዋን የተፈጠረችበት ✔እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት ✔ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ✔ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት/ ሰዓት ነው፡፡ ➌. #ጸሎተ_ቀትር በእለቱ እኩሌታ(6 ሰዓት) ላይ የምናገኘው ይህ የጸሎት ጊዜ ነው፡፡ ይህንም ጊዜ የምናስበው፦ ✔ሰይጣን አዳምን ያሳተበት ✔በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የዋለበት ✔የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው። ✔ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የዳግማዊ አዳም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣ እያሰብን የቀን እኩሌታ በመሆኑ መዳከማችንን ተገን አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡ ➍. #ጸሎተ_ተሰዓተ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን። በዚህ ጊዜ የምናስበው፦ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው። ✔ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው፡፡ ✔ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ሰዓት ነው፡፡(ሐዋ 10÷9) ✔በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡ ➎. #ጸሎተ_ሰርክ አምስተኛው የጸሎት ጊዜ(11 ሰዓት) የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ ✔ስለዚህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡ "ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን" (መዝ 140÷2) ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡(ማቴ. 27÷57) ➏. #ጸሎተ_ንዋም ይህ የመኝታ ጊዜ ጸሎት ዕለቱን በሰላም ስላሳለፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት ነው፡፡ እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል። ስለዚህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን። በዚህ ጊዜም የምናስበው፦ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡ ✔ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ ✔ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡ ➐. #ጸሎተ_መንፈቀ_ሌሊት ይህ እኩለ ሌሊት እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ” “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”/መዝ 118-62/ በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው። ✔ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው። ✔ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት ነው። ከዚህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደነሳልንም አስበን በማመስገን ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡ ☞✞ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠብቀን መጸለይ ካልተቻለንስ? በሰባቱ የጸሎ ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡ እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ ይጸልዩባቸዋልም፡፡ በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል። ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡ ☞✞ ምን ዓይነት ጸሎት እንጸልይ? በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት /በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው፡፡ ፩. #መዝሙረ_ዳዊት መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው። አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣ እየጸለዩበት ይኖራሉ። ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም። መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው። ቀጥለን እንመልከት፦ ሰኞ (ከ1–30)፣ ማክሰኞ (ከ31–60)፣ ረቡዕ(ከ61–80)፣ ሐሙስ (ከ81– 110)፣ አርብ (ከ111–130)፣ ቅዳሜ (ከ131–150)፣ እሁድ (ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) ይጸለያል፡፡

🌿🌾✞ #ንጹም_ጾመ ✞🌾🌿 ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ/፪/ ወንትቅፋቀር/፬/ ንትፋቀር በበይናቲነ//፪// | | |...፫ #ትርጉም፦ ጾምን እንጹም ወንድሞቻችንን እንውደድ እርስ በእርሳችን እንዋደድ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

​ነሐሴ 13/12/2010 ዓ.ም #ደብረ_ታቦር ✞ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ዲያቆን፦ ዕብ 11÷23-30 ንፍቅ ዲያቆን፦ 2 ጴጥ 1÷15-ፍ.ም ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-51 #ምስባክ፦ መዝ 88፥12-14 ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኀይል #ትርጉም፦ ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል ስምህንም ይመሰግናሉ ክንድክ ከኃይልክ ጋር ነው #ወንጌል፦ ሉቃ 9÷28-38 #ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ

🌾✞ #ስለ_በዐለ_ደብረ_ታቦር ✞🌾 በብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገሪማ (ዶክተር) የተሠጠ የሚያስደንቅ አስተምሮ ማንም ሳያነብ እንዳይቀር፤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

~~~✞ #ግጥም ✞~~~ https://t.me/EOTC2921 🌾✞ #ደብረ_ታቦር ✞🌾 መለኮት ተገለጦ ብርሃንን አበራ፣ በተቀደሰችው የታቦር ተራራ። የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት፣ በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት። ዮሐንስ ጴጥሮስ ያዕቆብን ጠርቶ ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አሥነስቶ ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ በሕያው መለኮት በብርሃናት ደምቆ አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና፣ የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና። እርሱን ብቻ ስሙት እስከ ዘለዓለም፣ ሕይወትን በእርሱ እንጂ ያለርሱ አትድኑም። ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ፣ አምላክነቱንም በተግባር ነገረ። "...ታቦርና አርሞንዔም በስምኽ ደስ ይላቸዋል፤ ክንድኽ ከኀይልኽ ጋራ ነው፤ እጅኽ በረታች ቀኝኽም ከፍ ከፍ አለች።" መዝ ፹፰፥፲፪ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

  🍀✞ #ቡሄ_በሉ ✞🍀 ቡሄ በሉ (2) ሆ ልጆች ሁሉ ሆ የኛማ ጌታ ሆ    የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባ ረቀው ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን (2) ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ       #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ       #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) በተዋህዶ ልጆች ሆ ወልድ የከበረው ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደ ማርያም ነው ሆ ቡሄ በሉ (2) የአዳም ልጆች ሆ ብረሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ #ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን ለኛ_መጣልን(2) አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ አጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ አክስቴም አለኝ ለከት ሆ ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ   #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ  ያላችሁ ሆ ባህላችሁን ሆ ያዙ ሆ አጥብቃችሁ ሆ ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ    #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)   አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ #ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)     ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)  ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችን ይድረስ ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)   ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና #በጋሽዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት  ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና #በእማምዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና       #እንዲሁ_እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ #ለዓመቱ_በሰላም በፍቅርያ ድርሳችሁ #ክርስቶስ_በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ #የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ #እንዲሁ_እንዳለን በፍቅር አይለየን #ለዓመቱ_በሰላም በፍቅር ያድርሰን #አማኑኤል_በቀኙ በፍቅር ያቁመን  #የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርገን የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት #በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት #በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት እንቁም በሃይማኖት ፀንተንበትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት #ባህላችንን_የአባቶች_ትውፊት (3) ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን #ለደብረ_ታቦር በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!!! እነሆ በዓሉን የሚመለከት ድንቅ ዝማሬ፦ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ☞ @EOTC2921 Channel ☞ @Orthodox2921 Group

🌾✞ #ደብረ_ታቦር ✞🌾 ❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ክብር ይግባውና ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አሥነስቶ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን ብርሃኑ የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9) ❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው። ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡ ❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት፦ መጀመሪያ አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡ ❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡ ❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ሲኾን ሙሴና ኤልያስም ጌታቸው ፈጣሪያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በተራራው ላይ መስክረዋል፡፡ ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡ ❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው። ❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡ ❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡ ❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦ 1⃣ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት 2⃣ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመን የነቢያትንና የሐዋርያትን ክብርና ምልጃ እንደምታስተምር ለማሳየት ነው፡፡ 3⃣ ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ 4⃣ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት 5⃣ ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡ 6⃣ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ 7⃣ ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨ 8⃣ ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨ 9⃣ ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡ ❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡ ❖ ሌላው “ብሑዕ” ማለት የቦካ ማለትን ሲያመላክት በዚኽ ቀን የሚጋገረውን ሙሉሙል ዳቦ የሚያመለከክት ነው፡፡ ❖ በዚህ በዓል የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ነሐሴ 12 ማታ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡ ❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡ [በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው] ✍መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ t.me/EOTC2921

🍀✞ #ደብረ_ታቦር_የታሪክ_ተራራ ✞🍀 ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ✅✞ ደብረ ታቦር ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁለቱ ነቢያትና ለሶስቱ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ታሪካዊ ተራራ ነው። ጌታችንን መለኮታዊ ታሪክ የሰራባቸው ብዙ ታሪካዊ ተራራዎች አሉ። እነርሱም፦ #ደብረ_ሲና፦ ምሥጢረ ሥጋዌን የገለጠበት የምሥጢር ተራራ ነው #ደብረ_ቁስቋም፦ በስደቱ ጊዜ መላእክቱ ክንፋቸውን ዘርግተው ያመሰገኑበት የምስጋና ተራራ ነው። #ደብረ_ገዳመ_ቆሮንቶስ፦ ሶስቱ ፈተናዎችን እስከፈታኙ ድል ነስቶ አምላክነቱን የገለጠበት የድል ተራራ ነው። #ደብረ_ዘይት፦ ለሐዋርያቱ ወደሰማይ ሲያርግ ባርኳቸው ያረገበት የወይራ ተራራ ነው። #ደብረ_ታቦር፦ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት የለመለመ ተራራ ነው። ወደዚህ ተራራ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን ከሐዋርያት ዮሐንስን ያእቆብን እና ጴጥሮስን ይዞቸው ወጥቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦላቸዋል። #ለምን_ከነቢያት_ሙሴና_ኤልያስን_መረጠ_ቢሉ? ነቢዩ ሙሴ በደብረ ሲና መልክህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ጠይቆት ነበረና ዛሬ መልኬን አታይም በሇላ ጀርባየን ታያለህ ብሎት ነበረና ጥያቄውን ለመመለስ ነው፤ በተራራ የተጠየቀውን በተራራ ለመመለስ ወደተራራው ወስዶታል። ኤልያስም ተአምር አድራጊ ነቢይ ስለሆነ ጌታችን ታምራቱን አይተው ኤልያስ ነው ብለውት ነበርና ኤልያስ እንዳልሆነ እና የኤልያስ አምላክ መሆንን ለማስመስከር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን አመጣ። ከሐዋርያት ዮሐንስ ያእቆብ ጴጥሮስ ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ? ጌታችን ወደተራራው ወጥቼ እነግሣለው ባለ ጊዜ የዮሐንስና የያእቆብ እናት ማርያም ልጆቼን በቀኝና በግራ አንግሥልኝ ብለው ነበረና የጠየቀችውን ጥያቄ ለመመለስ ያእቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወጥቷል ጴጥሮስን፤ #ለምን_ይዞ_ወጣ_ቢሉ? ጌታችን ሰዎች ማን ይሉኛል ባለ ጊዜ? ጴጥሮስ አንተ የአብ የባህርይ ልጁ ኢየሱስ ነህ ብሎት ነበረና ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ አምላክነቱን ሊያስረደው ወደተራራው ወስዶታል። #ሌሎችን_ሐዋርያት_ለምን_ተዋቸው_ቢሉ? "የሐትትዎ ለኀጥእ ከመ ኢይርዓይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል ኀጢአተኛውን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዳያይ ይከለክሉታል የተባለው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ይሁዳ ብረሃነ መለኮቱን እንዳያይ ነው። በሱ ምክንያት ስምንቱም በእግረ ደብር ቀርተዋል ለሶስቱ ሐዋርያት የተገለጠው ምሥጢር ለስምንቱ ሐዋርያት ተገልጦላቸዋል ። ይሁዳን ትቶ ሁሉን ይዞ እንዳይወጣ ከምሥጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት እንዳይል ነው። ከነቢያት ካገቡትም ካላገቡትም ከሐዋርያትም ካገቡትም ካላገቡትም ይዞ ወጥቷል። ✅✞ ከነቢያት ያገባው ሙሴ፤ ያላገባው ኤልያስ ነው። ከሐዋርያት ያገባው ጴጥሮስ ያላገቡት ያእቆብና ዮሐንስ ናቸው። የደናግል የሕጋዉያንም አምላክ እንደሆነ ለመግለፅ ህጋውያንን ደናግላንን ይዞ ወጥቷል፡፡ አንድም ደብረ ታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት መንግስተ ሰማያት የህጋውያንም የደናግልም እንደሆነች ለመግለጽ። ✅✞ አምስት መሆናቸው ስለምን ነው ቢሉ? ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት በቤተ ክርስቲያን የሚቀድሱ ካህናት አምስት እንዲሆኑ ስርዓት ለመስራት ነው አንድም በአምስቱ አእማደ ምሥጢር ምሳሌ ነው። ከሞቱት አንስቶ ካሉት ጠርቶ ለህያዋንም ለሙታንም ብርሃነ መለኮቱን የገለፀው የሙታንም የህያዋንም አምላክ መሆኑን ለመግለፅ ነው። ደብረ ታቦር ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን በዓላት አንዱ ነው፤ ይህ በአል መለኮታዊ አምላካዊ ላእላዊ ሰማያዊ በአል ነው። ✅✞ ደብረ ታቦር በእስራኤል ውስጥ የሚገኝ የለመለመ ተራራ ሲሆን በአሉ በተራረው ተሰይሞ ይከበራል። ከሌሎቹ ነቢያት ሙሴና ኤልያስን መርጦ ገልጦላቸዋል ምክንያቱም ሙሴ ፊትህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ሲጠይቀዉ "ገፅየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድህረሰ ትሬኢ ገፅየ" ዛሬ ፊቴን አታይም ኋላ ታያለህ ብሎት ነበርና ቃሉን ለመፈፀም ከመቃብር አምጥቶ ደብረ ታቦር ላይ ገለጠለት። ✅✞ ሙሴ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢባል? በልጅነቱ ሙሴ በቤተ ፈርዖን ሲያድግ የፈርኦንን ግፍ አይቶ ንጉሡ ፈርዖንን በጥፊ ተማቶ የሞት ፍርድ ቢፈርድበት የንጉሡ አማካሪዎቹ ልጅ ነው ምን ያውቃል ብለው እሳት እና ፍትፍት ይቅረብለት እና እሳቱን ትቶ ፍትፍቱን ከበላ ይገደል ክፉና በጎን ያውቃል ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን ከጎረሰ ገና ስላላወቀ አይፈረድበት ብለው ፍትፍትና እሳት አቀረቡለት ፈትፍቱን ትቶ እሳቱን ጎርሶ ነበርና አፉ ተብታባ ነበር በዚህ ታውቋል አንድም ሙሴ ገና ሲወለድ ከፊቱ ላይ ብርሃን ተስሎበት ተወልዶ ነበርና በዚህ ታውቋል። ✅✞ ኤልያስ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ? በጠጉሩ ኤልያስን ዘፀጓር ብእሲሁ ይለዋልና አንድም ኤልያስ ሲወለድ በእሳት ሰፋድል ተጠቅልሎ ነበር በዚህ ታውቃል ኤልያስን የመረጠበት ምክንያት ኤልያስ ሲያርግ ከኤልሳዕ በቀር ያየው አልነበረመና በህይወት ማረጉን ለመግለፅ ነው፡፡ ማቴ፡17፥1 ከመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞🙏 ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾✞ #ለእኔስ_ልዩ_ነሽ ✞🌾 ለእኔስ ልዩ ነሽ ድንግል ማርያም ለእኔስ ልዩ ነሽ እመብርሃን ፈልጌ ፈልጌ(፪) ለአንቺ ምሥጋና አላገኘሁም ልቤ ሲያበቅል የኃጢአት አረም ውስጤ ሲሸፍት አልተወችኝም ከቤተ መቅደስ እጇን ዘርግታ ትጠራኛለች የኔ መከታ #አዝ---✞---✞---✞--- የሆዴን ሀዘን የልቤን ሚሥጢር እነግርሻለሁ አንድም ሳይቀር የምትሸሽጊ የህዝብን ኃጢአት ለእኔስ ልዩ ነሽ ድንግል አዛኝት #አዝ---✞---✞---✞--- ጣዕሙ ልዩ ነው ከአንቺ ጋር መኖር ድንግልን ይዤ መቼም አላፍር ወደ ጽድቅ ሕይወት ትወስደኛለች ድንግል ማርያም ለእኔ እናቴ እኮ ነች #አዝ---✞---✞---✞--- በሐዘን ስሰበር ማንን ጠራለሁ ውሥጤ ሲደማ ለማን ነግራለሁ ከኃጢአት እድፍ ንጹህ መሆኛዬ አንቺ ነሽ ለኔ ለእኔስ መጽናኛዬ #አዝ---✞---✞---✞--- የኃጢአት ቁስል ያለአንቺ አይጠግም ልጅሽ ሣይፈቅድ በሕይወት አልኖርም ከልጅሽ ሌላ መድኅን የለኝም ከጸሎት በቀር ፍጹም አልድንም መዝሙር ይልማ ኃይሉ "...ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።" ሉቃ ፩፥፳፰