ch
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

显示更多
4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
🕊✞ #ኅዳር_ሚካኤል ✞🕊 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ኅዳር 12 እንኳን ለታላቁ መልአክ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሰን፦ ✉ለምንድን ነው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ወር በገባ በ12 የሚከበረው የሚታሰበው? ✉ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት እንየሆነ እንመለከታለን። #ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡ ✔ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡- + ዮሐንስ አፈወርቅ + ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ + ቅዱስ መቃርዮስ + ቅዱስ ያሬድ + አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ + የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡ ✔እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር 12 ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡ ❖የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ለምን ወር በ12 ይከበራል? ✔በእስክንድርያ ሀገር ውስጥ ‹‹ሳተርን›› (ዙሐል) የተባለ ቤተ ጣዖት ነበራቸው። ይህን የንግስት ክሌዎፓትራ በእስክንድርያ (በግብፅ ) ‹‹ሳተርን›› (ዙሐል) ለሚባለው ጣዖት ቤተ ጣዖት ያሰራችለት እርሷ እንደሆነቸ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ ፡፡ ✔ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312- 326/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ 18 ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው በ12 ነው። እስክንድሮስም ስአስተምሮ የሳተርን አጠፋው። ሕዝብ በ12 በገባ ሳተርን›› (ዙሐል) እናከብር ነበር አንተ እርሱን አጠፋህብን ሰለዚህ የለመድነው እንዳይቀር አንድ ነገር አድርግልን አሉት እስክንድሮስም በ12 የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ሚካኤልም ስም አብያተ ክርስቲያናት መታነጽ ጀመሩ በዓሉ በዚህ ቀን እንዲከበር ተወስኗል፡፡ ✔ይህ ወደ እኛ የመጣው እስክንድሮስ ካረፈ በኋላ ቅዱስ አትናቴዎስ በተሾመ ጊዜ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ከኢትዮጵያ ሀገር ተልከው በእስክንድርያ ሀገር ጵጵስና ይዘው ሲመጡ ቅዱስ አትናቴዎስ ወር በገባ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዲያከብሩ አስተምሯቸው አንድ ሕዝብ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን በአል ሲያከብሩ እግዚአብሔር ሲያመሰግኑ ተመልክተው ይህ ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መተዋል አባቶቻችንም ወር በገባ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዲ ዘከር እንዲከበር እንዲቀደስ በፍትሐ ነገስ ሥርዓት ሰርተውልናል። ❖ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት ነው? ✔ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት እንየሆነ እንመለከታለን፡፡ ➊ቅዱስ ዱራታዎስ ቴዋብለት (ቴውብስታ) ቤት የተገለጠበት ቤታቸውን የባረከበት ዕለት ነው። እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡ መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ✔ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡ በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡›› ብሎ ባርኳቸው ከእንርሱ ተሰወረ። •••••• #ይቀጥላል•••••

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 👉💟እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ፤ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽሸ💟👈 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ✍ልጄ ጸጉርህ ወጣት ሳለህ ጥቁር፣ ጐልማሳ ስትሆን ገብስማ፣ ስትሸመግል ነጭ ይሆንልሃል። በወጣትነት ማስተዋል ያጥርሀልና ፀጉርሕ ጥቁር፣ በጎልማሳነትህ ጉልበትና ጥበብ ተዋህደውሃልና ገብስማ በሽምግልናህ እውቀትህ በዝቷልና ነጭ ይሆንልሃል። 👉ጉልበት ያለው ወጣት ማስተዋል ያጥረዋል። ማስተዋል ያለው ሽማግሌ ጉልበቱ ይከዳዋል። ጉልበትና ጥበብ የተዋሃዱት ጎልማሳ ስትሆን ግን ብዙ መስራት ይጠበቅብሃል። 👉ሀኪም ታማሚ ታካሚውን አስቀምጦ ወይም አስተኝቶ እንጂ በቁሙ እንደማያክመው ሁሉ እግዚአብሔርም አሳምሞ ወይም ጥሎ ያስተምርሃል። ደግሞም ያክምሃል። ሲያስተኛሕና ሲጥልህ "ጌታ ሆይ የምታስተምረኝ ምንድን ነው?" በለው እንጂ አትዘን አትማረር። ለሰው በቁሙ መማርና መለወጥ ብዙ ጊዜ ጭንቅ ነውና እግዚአብሔር ጥሎ ያስተምርሃል። ያነሣሃል። 👉ልጄ ሽምግልናን እንድታያት ወጣትነትህ ሽምግልናን ታክብራት። የናቅኸውን ነገር እግዚአብሔር አይሰጥህምና ሽማግሌ እንድትሆን ሽምግልናን አክብራት። 👉ልጄ አምስት አይነት ዘውዶች አሉ። አምስተኛው ግን ከሁሉም ይበልጣል። ✟ የመጀመሪያው የንግስና ዘውድ፣ ✟ ሁለተኛው የትምህርት ዘውድ፣ ✟ ሦስተኛው የተክሊል ዘውድ፣ ✟ አራተኛው የክህነት ዘውድ ሲሆኑ ✟ አምስተኛው ግን የሽበት ዘውድ ናቸው። አራቱም ዘውዶች ሲመሽ ይወልቃሉ። የማይወልቀው የተፈጥሮ ዘውድ ሽበት ግን ከሁሉም ይበልጣል መብለጡም በኑሮ ማስተዋልን መውለዱ ነው። 👉ልጄ የክብር ኑሮ አድካሚ ነውና አትመኘው ሀብትም ርካታ የለሽ ያደርጋልና ፍቅርን ምረጥ። አፈር ሥጋዬን ካላከበሩልኝ ብለህ ጠብ አታብዛ የምትረግጣት መሬት አንድ ቀን ትረግጥሃለችና አረማመድህ በዝግታ ይሁን። ገንዘብ ካለኝ ወዳጅ ይኖረኛል ብለሕ አታስብ። ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም። ፍቅር በፍቅር እንጂ በገንዘብ አይገዛምና በገንዘብሕ ሀሰተኛ ወዳጅና እውነተኛ ጠላት እንደምታተርፍ እወቅ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ለአውሮፕላን እንጂ ለፅድቅ አይደለምና ገንዘብሕን ተማምነህ የድንግልን አማላጅነት የክርስቶስን ቤዛነት አትርሳ። 👉ልጄ እኔ ብቻ በችግር እኖራለሁ ብለህ ሌላው ባለመቸገሩ አትቅና። ሁሉም ለማኝ ሲሆን ደግ (ጥሩ) አይደለምና። ዛሬ ዓለም የተጨነቀው ሁሉም ሀገር በመቸገሩ ነው። ሁሉም ሲቸገር ደግ አይደለምና ይሕን አትመኝ። 👉ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ። መከራህን ለጌታ ደስታህን ለዓለም አታድርግ። እምነት ብታጣ ይሉኝታ አትጣ።ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ። ሕፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም (ኃጢያትህ ሲበዛ) ወደ እናት ቤተክርስቲያንህ ሽሽና ንስሀ ግባ። ንስሃ ደግሞ ያጣኸውን ለማግኘት የብልጠት መንገድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ስጦታ በትዕቢት ስለመያዝህ የምትፀፀትበት ሊሆን ይገባዋል። 👉ልጄ የወጣህበት ሰረገላ በመሬት ላይ ቆሟል! መሬት ደግሞ በእግዚአብሔር እጅ ላይ ተቀምጣለች። የተሸከመንን የተሸከመ እርሱ እግዚአብሔር ነው። የኮራንባቸው ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው። ከእርሱ በቀር የሚችለን ማንም የለም። ብዙ ዘመን ግን ያለ እግዚአብሔር በራሳችን ለመኖር እቅድ አውጥተናል፤ ያለ እግዚአብሔር መኖር ግን አይቻልም። ያለ እርሱ መኖር ፍፃሜው ሞት ነውና። 👉ልጄ ሆይ ከእግዚአብሔር ተለይተሕ መኖር አይቻልም። እርሱ በነፍስም በሥጋም ገዢሕ ነውና ከእርሱ ጋር ተጣበቅ። መንግስት ችግር ሳይመጣ ወታደሩን በችግር ያሰለጥናል፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን መቆም እንድንችል በትግል ውስጥ ያሰለጥንሃልና አትመረር። 👉ልጄ አንተ የሠማይ ኮኮብ ነህ። የተደበቅህ ቢመስልህም ሁሉ ያይሃል። የክዋክብት ሕልውናቸው ብርሃናቸው ነው። የአንተም ክርስትና ሕልውናው የተለወጠ ሕይወት መሆኑን አስተውል። አዎ የሰማይ ኮኮብ ነህ አገርህም በሰማይ እንደሆነ እወቅ። ስምህ ክርስቲያን አገርህ በሰማይ ዘርህ ክርስትና እናትህ ድንግል ማርያም ንጉስህ ክርስቶስ ነው። 👉ልጄ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል። ብዙዎች ስለጠሉህም ይጠላሃል። አንተ ግን የብዙሃን እውነት ነው ሳይሆን እግዚአብሔር እውነት ነው በሚል መመሪያ ተመራ። ለመልካምነትህ ክፉ ምላሽ ለወሮታህ ከሳሽ ቢነሳብህ የመልካም ነገር ደሞዝ ሰጪ እግዚአብሔር መሆኑን አምነህ ሥራህን ሥራ። 👉ልጄ መልካም ነገርህ ነገ ሊረሳ ይችል ይሆናል መልካም መሆንህንም ሰዎች ላይረዱልህ ይችላሉ እውነተኛ መልካምነት ግን ምስጋናን ሳያደምጡ የሚፈፀም መሆኑን እወቅ። 👉ልጄ ታማኝ ስትሆን ያለፈብሕ ትመስል ይሆናል፤ ግልፅ ስትሆን በቀላሉ ልትጠቃ ትችላለህ፤ ታማኝና ግልፅ መሆንህን ግን እግዚአብሔር ስለሚወደው ብቻ አጥብቀህ ያዘው። 👉ልጄ ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት ያዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናሕም የምታጭደው የወጣትነትሕን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ። "ምክር ከእማሆይ ፅጌ አሌልቱ ደብረ ሰዋሰው አደሬ ኪዳነ ምሕረት የሴቶች ገዳም 🌻💐🌹 #Join us...🌹💐🌻 #Share #Share #Share #Share 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ድንቅ_ተአምር_በኪዳነ_ምሕረት ዕለቱ ታህሳሥ 3 ቀን 2003 ዓ/ም ነበር፡፡ አንድ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረች እህት በእርኩስ መንፈስ ተጠምዳ ነበር፡፡ እናም የያዛት መንፈስ እጅግ ከባድ ነበር፤ መንፈሱ እርሷን ብቻ ሳይሆን በቤተሰቧም የተሰራጨ ነበር፤ ታዲያ ልጅቷ በዚህ ቀን ያ መንፈስ ተነሳባትና ከአለችበት ዩኒቨርሲቲ ዶርም አንስቶ በእግሯ ወደ አዲስ አበባ መስመር እስከ ባኮ ድረስ ይወስዳታል፡፡ ልጅቷ ታዲያ ስልክና መታወቂያዋን በእጇ አንቃ እንደያዘች ነበር ያ እርኩስ መንፈስ አብሮ የማይታመነውን ሩቅ መንገድ የወሰዳት፡፡ ጓደኞቿ በጣም ተጨንቀው የሚያረጉት ግራ ገባቸው ስልክ ይደውላሉ፤ አንስቶም ያስፈራራቸዋል፣ ይዝትባቸዋል ይባስ ብሎ አሁን አታገኟትም ገደል ልከታት ነው፡ አንዴ ባህር ልከታት ነው ይላቸዋል፡፡ ታዲያ የተረበሹት ልጆች ወደ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አገልጋይ ወደነበሩት ቀሲስ ሙሴ ይደውላሉ፡፡ እርሳቸውም በመገረም ስልክ ተቀብለው ሲደውሉ አያነሳም ነበር፡፡ ከዚያም እዛው ባኮ አካባቢ ጠመዝማዛ ቦታ ላይ አንድ መኪና ከነቀምቴ ወደ አዲስ አበባ ይጓዛል፡፡ ልክ ከማዞሪያው ሲደርስ የመኪናው ባውዛ/የፊት መብራት/ ተሻግሮ የሆነ ቦታ ላይ ያርፋል፡፡ ከውስጥ ያሉት ሹፌርና ጓደኞቹ የሆነ የሚረብሽ ነገር ያያሉ••• ከመሀል ነጭ ለባሽ በዙሪያዋ ጥቋቁር ነገር ከበዋት ያያሉ፤ ለማመን የሚከብድ ነገር እየተባባሉ፡ ወረዱ ከዚያም ቀስ ብለው መጠጋት ጀመሩ፡ የእጅ መብራት አብርተው በደንብ ሲያዩ በዙሪያዋ የከበቧት ጅቦች ነበሩ፡፡ እነሱም በመጨነቅ ስሜት ማነው የሆነ የተገደለ ሰው፡ ወይም የተመታ ሰው መሆን አለበት፡ ብለው ጅቦችን አባረው መጠጋት ጀመሩ፡፡ ጠጋ ብለው ሲያዩ አይኖቿን ሳታርገበግብ እንዳፈጠጠች፡ በእጆቿ የግቢ መታወቂያ እና ስልክ የጨበጠች ልጃገረድ ነበረች፡፡ ከዚያም ለሦስት አንስተው ጋቢና አስገቧት፡፡ ጠጋ ብሎ ልብ ትርታዋን አዳመጠ አልሞተችም ልጅቷ መተንፈስ ጀመረች፡፡ ከዚያም ስልኳ ጠራ፡ ቀሲስ ነበሩ የደወሉት፡ አነሱና ያዩትን ሁሉ ነገሯቸው ይዘዋት ሊመጡ ሲሉ፡ የጓደኛቸው መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምቴ እየከነፈ መጣ እነሱም የሆነውን ነግረዋቸው እንዲወስዷት አዝዘው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ከዚያም ቀሲስ ግቢው ድረስ ለመቀበል ሄዱ ልጆችም እንዲሁ አብረው ተቀበሏት፡፡ ጊዜውም ጨልሞ ነበር ከዚያም ልጅቷ ካህኑን ባየች ጊዜ ባሰባት ጭራሹን በድንጋይ ልጆችን ልትፈጃቸው ነበር፡፡ በስንት ትግል ይዘዋት ያ መንፈስ አልሄድ ብሎ ስለነበር በቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤ በስላሴ ስም ገዝተው እጇን በነጠላ አስረው ወደ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ወሰዷት፡፡ ከቤተ ክርስቲያን አጥር ሲደርሱ አልሄድም አለች፡፡ ቢገፋ ሂድ ቢሉ እቢ አልሄድም ከፊት ሰው ይቅደምልኝ አለች ከዚያም አንድ ሰው ቀድሞ የእጅ መብራት ሲያበራ የአንድ ጅብ አይኖች ከርቀት መብራት ጀመሩ ያን ጅብ አባረው ወደ ውስት አስገብተው ቀሲስ ሙሴም የተለመደ ጸሎታቸውን እያረጉ ማስለፍለፍ ጀመሩ፡፡ ከዚያም ልጅቷ እንዴት እንደሄደች ሁሉን አንድ በአንድ ተናገረች፦ ከዚያ ድረስ የወሰዷትም በኪዳነ ምሕረት ጠበቃ ነበር፡፡ አንዴ ከባህር ሊከቷት ሲሉ ኪዳነ ምሕረት በጨረሯ እየወጋች ታስቀራታለች አንዴም በገደሉ፣ አንዴም በመኪና ጎማ ከተው ሊገድሏት ነበር፤ ብቻ በቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጨጨር እየተወጉ ማድረግ ሳይችሉ ከዚያ ቦታ በጅብ ተከባም ተቀመጠች ጅቦችም እንዳይበሏት ተገዝተው ዙሪያዋን ከበው ጠበቋት እንጂ መብላት እንኳ አልተፈቀደላቸውም ነበር፡፡ ከዚያም አልወጣም ያለው እርኩስ መንፈስ ይባስ ብሎ ቤተሰቦቿ ካልተጠመቁ ንስሃ ካልገቡ አለቅም አለ፡፡ ለጊዜው ከልጅቷ አስለቀቁትና ወደ ማንነቷ ተመለሰች፡፡ ከዚያም ልጅቷ ዊዝድራው ሞልታ/ትምህርት ለጊዜው አቁማ ጸበል መከታተል ጀመረች፡፡ ያ እርኩስ መንፈስም በቁጥር 328 ነበር፡፡ ያ መንፈስ በሌላ ጊዜ ስልክ ለንስሐ አባቷ እንዳትደውል እንዳትገናኝ በአንድ ወንድ ልጅ አድሮ ያውም ሴቶች ዶርም ገብቶ ከፖርሳዋ ነበር ሰርቆ የወሰደው፡፡ ያ መንፈስም በኪዳነ ምሕረት ስም ስለተገዘተ ይዞት እንዲመጣ ታዘዘ እንደተባለውም ልጁ ስልኳን ይዞ መሰስ ብሎ ቤተ ክርስቲያን መጣና ሰጣት፡፡ ሁሉም ቤተሰቦቿ ተነግረው ስለነበር ሁሉም በያሉበት ተጠመቁ ንስሃ ገቡ፡፡ ከብዙ ውጣ ውረዶች በኃላ ልጅቷ ለመመረቅ የቀራትን አንድ አመት ከመንፈቅ ጨርሳ በሰላም ተመረቀች፡፡ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጣዕምና ፍቅሯ፣ ምልጃና ጸሎቷ፣ ረድኤትና በረከቷ ከሁላችንም ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን፡፡ ከቀሲስ ሙሴ የኪዳነ ምሕረት አገልጋይ ካህን የሰመሁት አስደናቂ ነገር በጥቂቱ ነበር ✍ተፃፈ፡ በገ/ስላሴ መንግስቴ ኅዳር 8/2012 ዓ/ም 🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

የሚጠብቀኝ አይተኛም.m4a8.93 KB

ትንሳኤሽን ያሳየን.m4a8.16 KB

✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✞ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• 🌿🌿✞ #ምስጢረ_ስላሴን ✞🌿🌿 ✞ #ለህፃናት_እንዲህ_እናስተምር ✞ #ማን_ፈጠረን? ☞✞ ስላሴ #ስላሴ_ስንት_ናቸው? ☞✞ አንድም ሶስትም #ሶስትነታቸው_በምን_በምን_ነው? ☞✞ በስም፣ በአካል፣ በግብር #አንድነታቸውስ_በምን_ነው? ☞✞ በባህሪ፣በህልውና፣ በመለኮት፣ በፍቃድ፣ በስም፣ በአካል፣ በግብር ይህችን፣ አለም በመፍጠርና በማሳለፍ #የስም_ሦስትነታቸው_እንዴት_ነው? ☞✞ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ #የአካል_ሶስትነታቸው_እንዴት_ነው? ☞✞ #አብ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው። ☞✞ #ወልድ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው። ☞✞ #መንፈስቅዱስ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው። #የግብር_ሶስትነታቸው_እንዴት_ነው? ☞✞ አብ=ወላዲ፤ ወልድ=ተወላዲ፤ መንፈስ ቅዱስ=ሰራፂ #አብ_ምን_ማለት_ነው? ☞✞ አባት፦ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ፤ ያለእናት ወልድን የወለደ #ወልድ_ምን_ማለት_ነው? ☞✞ ልጅ፦ የሚወለድ፤ ያለእናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ #መንፈስ_ቅዱስ_ምን_ማለት_ነው? ☞✞ ሰራፂ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ሁኖ ከአብ የሰረፀ ✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞ የእግዚአብሔር አብ በረከት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞

❖ “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ” (በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ይደርብን፤ በቃል ኪዳኗ ትጠብቀን፡፡ 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏 https://telegram.me/EOTC2921

#ሰማዕቷ_ቅድስት_አርሴማ https://telegram.me/EOTC2921 ✔✞ መስከረም 29 ቀን ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ያረፈችበት እለት ነው፤ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የቅድስት አርሴማ እናት አትኖስያ ትባላለች። ልጂ በማጣት ለረዥም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር። በኃላም እግዚአብሔር ልመናዋን ሰማት። ይህቺን ክብርት ቅድስት ልጅም ሰጣት። ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፣ 15 አመት ሲሆናት ሊያጋቧት አሰቡ፣ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም በድንግልና ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚያም በኃላ እንዲህ ሆነ፤ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጢያኖስ ሊያገባት ወደደ። ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማኒያ ሄደች። በዚያም በበረሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች። በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበረሃ እንደሚኖሩ ሰማ፤ ወታደሮቹንም ልኮ አስመጣቸው። የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ፤ የፊቷ ውበት እፁብ ድንቅ ግርማዋ የሚያስደንቅ ልብ የሚያርድ ነበረና ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም። በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት። ሌሎቹን ግን ለጣኦት እንዲሰግዱ ገፋፋቸው። ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃየኝ እያለች አምርራ ታለቅስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ወደደ፤ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦቱንም ትረግም ነበር። እርሷ ፀንታ ደናግሉን ታፀና ነበር፤ ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር። ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጣው ባወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ። https://telegram.me/EOTC2921 ✔✞ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በሗላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆርጧት ከእርሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል። በአገራችን በስሟ ሰሜን ወሎ ውስጥ ሲሪንቃ ቅድስት አርሴማ የሚያስገርም ገዳም አላት። በዚህ ገዳም 7 ቀን ብቻ ሱባኤ የሚገባ የልቡን መሻት ትፈፅምለታለች። በመዲናችን አድስ አበባም የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያኖች አሉ። እንዲሁም አስኮ ቃሎ ተራራ ላይ የሚያስገርም ቤተ ክርስቲያን አላት። ይህንን የቃሎ ተራራ ሲወጡ ዝቋላ ትዝ ይላል። መስከረም 29 በደማቅ ተቦተ ህጉ ወጥቶ ተከብሮ ይውላል። ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ነው። #የቅድስት_አርሴማ_ተጋድሎ_በቀደምት_የኢትዮጵያ_ሊቃውንት፦ https://telegram.me/EOTC2921 ❖ ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕላቷን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ ገድሏን አጽፈዋል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች፤ ሊቁ እንደጠቀሰው እጅግ መልከ መልካም ነበረች ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር፤ በጊዜው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡ ❖ እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡ ❖ ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡ ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡ ❖ የመልኳን ደም ግባትም በማየት ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው ብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡ ❖ ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በክድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡ ❖ ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው። ❖ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ፤ ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን ተገልጾ ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም ፳፱ በ፪፻፺ ዓ.ም አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለችና፤ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ ፮ ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡ ❖ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ በረከቷን ለመሳተፍ በባሕር ማዶ የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ፣ በአውሮፓ በስዊድን በማልታና ስኮትላንድ ግላስኮ ይገኛሉ፨ ❖ ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦ ❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡- “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ” (በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡ (ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨ ❖ እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨

#የቅዱሱ_ኪዳን_ቅርስ_ወይም_ቅዱሱ_ጽዋ https://telegram.me/EOTC2921 ✔✞ አባቶቻችን እንደተናገሩንና በድርሳነ ዑራኤልም እንደተፃፈው ጌታችንና መድኃኒታችን በዕለተ አርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ ከሰውነቱ የፈሰሰውን ደም በብርሃን ጽዋ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ተቀበለው፡፡ ደሙንም በመላው ዓለም ረጨው፡፡ የደሙ ንጣቢ ያረፈበት ቦታ ሁሉ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ማረፊያ፣ የቅዱስ ቁርባን መፈፀሚያ እንዲሁም ታላቅ ቃል ኪዳን ለዓለም ተሰጠ፡፡ ✔✞ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ክቡር ደሙን በዐራቱም ማዕዘናት ከረጨ በኃላ ጽዋውን በመድኃኔዓለም ፈቃድ በቅድስ አገር ኢትዮጵያ መንዝ ውስጥ እመጓ ቆላ አምጥቶ ቀበረው፡፡ #መንዝ ማለት ነዝሃ ከሚለው ግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ይኸውም መርጨት ማለት ነው፡፡ የክርስቶስ ደሙ የተረጨበት ጽዋ ማረፊያ ስለሆነ ነው፡፡ #እመጓ ማለት እመ እጓል ከሚለው የግእዝ ሐረግ አጥሮ የተገኘ ቃል ነው፡፡ ይህም የልጅ እናት ማለት ነው፡፡ ✔✞ የቅዱሱ ኪዳን ቅርስ /የቅዱሱ ጽዋ/ ጠባቂዎች፦ ለዚህ ቃል ኪዳን የታመኑና የተገቡ በመሆናቸው የነፍሳቸውን ጽድቅ ብቻ ሳይሆን እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ የከበረ ስጋቸው እንዳይበሰብስ ዐፅማቸው እንዳይፈርስ በመድኃኔዓለም ቃል የተገባላቸው ናቸው፡፡ ✔✞ የአርማትያሱ ዮሴፍ ይህን ክቡር ጽዋ ወደ ቤቱ ወሰደው ከዚያም ወደ አርማትያስ ኬብሮን ሸሸ፡፡ ከዚያም ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ወደ ኬብሮን ተጓዘ ከዛም ዮሴፍ ወደ ሶርያ ተሰዶ ስለነበር ከሶሪያ ከዮሴፍ ተቀብሎ ወደ አክሱም ፅዮን አመጣው፡፡ የዚህ ጃንደረባ ታሪክ በጌምድር እንዳቤት ከግሼና ተክለሃይማኖት ደብር ይገኛል፡፡ ✔✞ ቅዱሱን ጽዋ ለመመልከት የታደለ ሰው ታሞም ቢሆና ይድናል፡፡ በዛች ሳምንት አይሞትምና የቻለውን ያክል ዘመን ጽዋዋን ቢመለከታት የፊቱ ጸዳል ሳይቀር እንደልጅነቱ እንደለመለመ ይኖራል፡፡ ድንጋይ የተባለው ቅዱሱ ጽዋ የሰውን ልጅ አጥንትና ሥጋ ከመስበስ ታደጎ ለምለም ያደርገዋል፡፡ ምንጭ፦ ከእመጓ መጽሐፍ https://telegram.me/EOTC2921 🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏

#የኢትዮጲያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_14ቱ_ቅዳሴያት (The 14 anaphoras) #1) ቅዳሴ ሐዋርያት (anaphora of the Apostles) #2) ቅዳሴ እግዚእ (anaphora if the lord) #3) ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (anaphora of st.John the son of thunder) #4) ቅዳሴ ማርያም (anaphora of st.mary) #5) ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት (anaphora of the 318 orthodox fathers) #6) ቅዳሴ አትናቴዎስ (anaphora of Athanasius) #7) ቅዳሴ ባስልዮስ (anaphora of Basil) #8) ቅዳሴ ጎርጎርዮስ (Anaphora of Gregory of Nyssa) #9) ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ (Anaphora of Epiphanius) #10) ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ (Anaphora of John Chrysostom) #11) ቅዳሴ ቄርሎስ (Anaphora of Cyril) #12) ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Anaphora of Jacob of sarug) #13) ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ (Anaphora of Dioscoros) #14) ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ (Anaphora of Gregory of Nazianzus)

#ወዳጄ_ሆይ (ምክረ አበው) ✔ወዳጄ ሆይ ኃጢአት ለመስራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ፅድቅ ለመስራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ። ✔ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ የንስሐ አባትህ ለማግኘት ጊዜ የለህም። ✔ስጋህ ሲራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢሆን) ትበላለህ፤ ነፍስህ ግን የክርስቶስን ስጋ ከራባት ዘመናት ተቆጥረዋል። #ወዳጄ_ሆይ እባብ አሳተኝ ያለችውና ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋንን ታስታውሳታለህ? እንግዲያውስ አንተም እንደ እሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፤ ይህም ሲነገርህ በተግባር እንጂ በአፍህ ለመመለስ አትጣር።

☞= "ፍፁም ፍቅር" = ባልንጀራውን የሚወድ በባልንጀራው ላይ ክፉ ሥራ አይሠራም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።[ ሮሜ 13፥10] ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ☞"ይቅር ባይነት" በምትጸልዩበትም ጊዜ በሰማያት ያለው አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲላችሁ በወንድማችሁ ያለውን በደል ይቅር በሉ። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይላችሁም።" (ማር. 11፥25-26) ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ☞"በጎነት (ቸርነት)" ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚበድሉአችሁና ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ። ||ማቴ 5፥44|| ክፉ ላደረገባችሁ ክፉ አትመልሱ፤ የሰደባችሁንም አትስደቡ፤ጠላታችሁንም መርቁ፤ በረከትን ትወርሱ ዘንድ ለዚህ ተጠርታችኃልና።[ 1ኛ ጴጥ.3፥9] ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ☞"ትህትና" ለትዕቢተኞች ጥፋት ፈውስ የላትም፤ ክፉ ተክል በውስጣቸው ሥር ሰድዶአልና። (መ.ሲራክ 3፥26) ራሱን ከሁሉ ዝቅ የምያደርግ እርሱ ታላቅ ይሆናል።{ሉቃስ 9፥48} እግዚአብሔርን በመፍራት ለባልንጀራችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።// ኤፌሶን 5፥21// ትህትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩእንጅ አትታበዩ። ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም፤ ዐመፃን የሚናገር በፊቴ አይጸናም። መዝ 100 ፥ 7 ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና። [[ማቴ7፥12]] ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ "ለራስህ የምትጠላውን ለማንም አታድርግ።" (መ.ጦቢት 4፥15) አቤቱ አባታችን ሆይ! ማስተዋሉን አድለን፤ እኛ ደካሞች ነንና አንተ አጋዥ ሁነን። ከሁሉ አስቀድመን እንለምንሃለንና ሁሉን እንወድ ዘንድ ንፁህ ልብን ስጠንን፤ የይቅርታ ልብንም ስጠን፤ ነፍሳችን ትህትናን ትላበስ ፤ በጎ ምግባርን ይዘን 30,60,100 ያማረ የሕይወት ፍሬ አፍርተን የመንግሥትህ ወራሾች እንድንሆን ፍቀድልን ሁሉ ይቻልሃልና። ክብር ምስጋና ለስምህ ይሁን አሜን። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#ፍቅር ከእግዚአብሔር ቤት መራቅ ስትጀምር ፍቅር ካንተ ትርቃለች። ከምታየው ነገር ጋር ሁሉ ትጣላለህ። የምትጣላውም ከሰዎች ጋ ብቻ አይደለም። ካገኘከው ነገር ጋ እና ከራስህም ጋ ጭምር እንጂ። ከራስህ ጋ ተከራክረህ እራስህን መርታት ከማትችልበት ጭንቀት ውስጥ ትወድቃለህና የምትሞትበትን ጊዜ ታመቻቻለህ። እንደ ይሁዳ ታንቆ ለመሞት አልያም እንደ ሌሎቹ በሌላ ምክንያት እራስህን እስከማጥፋት ድረስ ማንነትህን ትጥላለህ። እራስህን እንደ ሰው መቁጠር ከማትችልበት ከባድ ሙግት ውስጥ ትወድቃለህ። በዚህም ከአምላክህ ጋ እና ከሰዎች በፍቅርና በሰላም መኖር አልችል ትላለህ። ሁልጊዜ ከሰዎች ጋ ክርክርና ጥላቻ ይሆንብሀል። ጠላትን የምታጠፋበት ትልቁ መሳሪያ ፍቅር ብቻ መሆኑን ትዘነጋለህ። ይህን የከበሩ እንቁዎች የማይተካከሉትን ልዩ ፀጋ ማጣት ማለት ሰው ሁኖ ተፈጥሮ ሰው ሁኖ አለመገኘት ነው። የሰውነት መመዘኛው ትልቁ ሚዛን ፍቅር ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ንሀስ ወይንም እንደሚንሿሿ ፅናፅል ሁኛለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ፣ ሚስጥርንም ሁሉና፣ እውቀትንም ሁሉ ባውቅ፣ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፣ ስጋዬን ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሳል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋ ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሳል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይፀናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም። እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ። ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛ ቆሮ 13፥1-13 ፍቅር በሰዎችና በመላእክት ልሳን ከመናገር በላይ ነው። ድሆችንም ከመመገብና ስጋችንም ለእሳት አሳልፈን ከመስጠት የላቀ ነው። እውነተኛ ፈቅር የሚታገስ፣ ሁሉን የሚያምን፣ ከእውነት ጋ ደስ የሚለው፣ የማይቀና፣ ቸርነት የሚያደርግ የማይመካ፣ በደልን የማይቆጥር፣ ሁሉን ተስፋ የሚያደርግ ነው። ይህንን ፍቅር የምናገኘው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋ በመሆን ብቻ ነው። ምክንያቱ ፍቅር ከእግዚአብሔር ነው እራሱ እግዚአብሔርም ደግሞ ፍቅር ነውና። ሐዋርያው ዮሃንስ በመልእክቱ እንዲህ ይላል:-ወዳጆቼ ሆይ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ የሚወደው ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለተወለደ እግዚአብሔርም ስለሚያውቅ እርስ በራሳችን እንዋደድ።1ኛ ዮ 4፥7 ለዚህም ነው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሔርን ስትርቅ ፍቅር ደግሞ ከአንተ የምትርቀው። ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ በመሆኗ ትልቁ ገንዘብ ናት። ፍቅርን የምንገልፀው ሰውን እግዚአብሔርን እንዲሁም ሀገርን በመውደድ ነው። እኛም እንደታማኙ አገልጋይ ጌታ የሰጠንን መክሊት ልናተርፍበት ይገባል። በመክሊታችን ትርፋማ ለመሆን ደግም ፍቅር ትልቁን ሚና ይጫወታል። ስለዚህ ፍቅርን ለብሰን ትህትናን ተጫምተን በማስተዋል መጓዝ አለብን። የፍቅር አምላክ ፍቅርን ያድለን! የአብ_ፀጋ_የወልድ_ፍቅር_የመንፈስ_ቅዱስ_አንድነት አይለየን አሜን። ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንንበየቀኑ አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክEOTC2921 #በመንፈሳዊ ሕይወትህ ለውጥ እንዲኖርህ #1ኛ የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣ #2ኛ ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ #3ኛ ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣ #4ኛ የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን መፃህፍት፥የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣ #5ኛ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣ #6ኛ ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም አትደገፍ፣ #7ኛ አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ' አትበል ውዳሴ ከንቱንም አትፈልግ፣ #8ኛ ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣ #9ኛ ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣ #10ኛ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም ፀንተህ ተገኝ፣ #11ኛ የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን ለመምሰል ትጋ፣ #12ኛ ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው #13ኛ ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣ #14ኛ ነገርን ሁሉ ለበጎነው ብለህ ተቀበል። ጌታ ሆይ ይህን እንድናደርግ እርዳን አሜን!!! ☞@EOTC2921