ch
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

显示更多
4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Ethio_Orthodox1 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

በኾነ መልኩ ሱባኤውን ይፈጽሙታል፤ በመኾኑም ትውልድ ኹሉ ብፅዕት የሚላት አጋንንትን መናፍቃንን የምታሸብራቸው የአምላካችን እናትም በቀንም ኾነ በሌሊት ከእኛ በረድኤት ባለመለየት ረድኤቷን በረከቷን ልታትረፈርፍልን የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ ደርሷልና የእውነተኛዪቷ ሐይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በእጅጉ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ!!!፡፡ 🙏🌻የምእመናን ወዳጅ የመስቀል ሥር ሥጦታችን በዚኽ የፍልሰታ ሱባኤ ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን!!! መልካም የበረከት ሱባኤ!!!🌻🙏 ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ☞ @EOTC2921 Channel ☞ @Ethio_Orthodox1 Group

#የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_በዚኽ_የፍልሰታ_ሱባኤ_ለምእመናን_መገለጥ!🌾🌿 ✞❖ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝ ፵፬፥፲፪ ላይ “ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር” (የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ኹሉ በፊትሽ ይማለላሉ) በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት ብዙዎች ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ብዙዎቹም ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው እጅግ አስደናቂ ውበቷን አይተዋል፡፡ ከነዚኽ አባቶች ውስጥ ቅዱስ ኤፍሬም፣ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ይሥሐቅ፣ አባ ቴዎፍሎስ እና በደብረ ምጥማቅ የነበሩ ምእመናን ሌሎችም ብዙዎች ንጹሓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል፡፡ ✞❖ የመልክአ ማርያም ደራሲም የአምላኩን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ በናፍቆት ኾኖ፡- “ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ ዘያበርህ ወትረ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ” (ኹልጊዜ (ዘወትር) የሚያበራ ፀሓይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ ፍቅረኛዬ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡ ✞❖ ቅዱስ ያሬድ አባታችንም በማይ ኪራሕ ሳለ እመቤታችን ተገልጻለት ፊቷን ለማየት ታድሏልና ይኽነን በዐይኑ ያየውን ውበቷን በድጓው ላይ እንዲኽ ሲል ጽፎታል፡- “አይ ይእቲ ዛቲ እንተ ትወርድ እምሰማይ፤ ብርህት ከመ ፀሓይ፤ አዳም ቆማ ወክሣዳ ከመ አርማስቆስ፤ መዐዛ አፉሃ ከመ ኮል” (ከሰማይ የምትወርደው እንደ ፀሐይም የምታበራው ርሷ ማን ናት! አንገቷ እንደ ግንብ ቀጥ ያለ ነው፤ የአፏም መዐዛ እንደ እንኮይ ነው) በማለት በተመስጦ የተመለከተውን ውበቷን ተናገረ፡፡ ✞❖ ይኽ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ቅዱስ ያሬድ በዚኽ ሳያበቃ በመላእክት እየተመሰገነች ስለተገለጸችለት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ያየውን የውበቷን ነገር ሲናገር “እምኀበ መላእክት ትሴባሕ አዳም ሥና፤ መዐርዒር ቃላ ወኲሉ ነገራ በሰላም … እምወርኅ ወእምፀሓይ ይሤኒ ላሕያ …ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ወከመ ኮል መዐዛ አፉሃ ወከመ ሮማን ቂሐተ መላትሒሃ … (በመላእክት ትመሰገናለች፤ ደም ግባቷ ያማረ ነው፤ ቃሏ እንደ ማር የጣፈጠ፤ ነገሯ ኹሉ በሰላም የተመላ ነው … ውበቷ ደም ግባቷ ከጨረቃና ከፀሓይ ይልቅ ያምራል፤ ከንፈሮቿ ፍሕሶ እንደሚባል አበባ ቀይ ናቸው፤ የጒንጯ ቅላትም እንደ ሮማን ቅርፍት ነው) እያለ ሊቁ ማሕሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ ይመሰክርላታል፤ አይ መታደል! አይ መባረክ! ✞❖ ውዳሴዋ በእጅጉ የበዛለት ስለ ርሷ ኆኅተ ብርሃን፣ እንዚራ ስብሐት፣ መዐዛ ቅዳሴ፣ አርጋኖን፣ ሰላምታ፣ መዝሙረ ድንግል እና ሌሎችም ብዙ ብዙ ለመሰከረላት ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ብዙ ጊዜ እየተገለጸችለት በዐይኑ ተመልክቷታልና የመልኳን ውበት በአርጋኖን ዘቀዳሚት ላይም፡- “አልቦ ዘይሤንዮ ለላሕይኪ ኢ ጎሕ ወኢበርህ ኢ ፀሓይ ወኢወርኅ ኢ ዋካ ወኢጸዳል አልቦ ዘይበርህ እምጸዳለ ዐይንኪ ኢ ቤዝ ዘያንበለብል በገጸ ሰማይ ወኢባሕርይ ዘያንጸበርቅ ዲበ ርእሰ ነገሥት ወአልቦ ዘይምዕዝ እምጼና አንፍኪ ወእምጼና አልባስኪ ኢከልበኔ ወኢሐንክሶ ወኢአስጰዳቶስ ወኢናርዱ ቅድው ዘዕጹብ ሤጡ ወመዐድም ኲለንታኪ ወክሉል በጸጋ መንፈስ ቅዱስ” (ደም ግባትሽን የሚያምረው (የሚበልጠው) የለም፤ የንጋት ውጋገንም ቢኾን! ብርሃንም ቢኾን! ፀሓይም ቢኾን! ጨረቃም ቢኾን! ወዝሽን ለዛሽን የሚመስለው የለም፤ ከዐይንሽ ብርሃን ይልቅ የሚበራ የለም፤ በሰማይ ፊት የሚንቦገቦግ ኮከብም ቢኾን! በነገሥታት ራስ ላይ የሚያንጸባርቅ ዕንቊም ቢኾን! ከአፍንጫሽም መዐዛ ከልብሶችሽም ሽታ የበለጠ የሚሸት የለም፤ ከልበኔም ቢኾን! ሐንክሶም ቢኾን! አስጰዳቶስም ቢኾን! ዋጋው ውድ የኾነ ናርዱ የሚባል ሽቱም ቢኾን! ኹለንተናሽ ያማረ ነው በመንፈስ ቅዱስ ጸጋም የተጋረደ ነው) ብሏታል፡፡ ✞❖ ልክ እንደ ርሱ የአምላክን እናት ፊቷን ለማየት የተመኙ ብዙዎች ቅዱሳን ነበሩ፤ ለምሳሌም ያኽል ከቅዱሳን አበው መኻከል አባ ይሥሐቅ እመቤታችንን በፍጹም ልቡናው ከመውደዱ የተነሣ ከሠርክ ጸሎት በኋላ ሌሎች መነኮሳት ለመኝታ ወደ የበኣታቸው ሲኼዱ ርሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመኼድ በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቆሞ በፊቷ እየተማለለ ሦስት መቶ ስግደትን እየሰገደ፤ በእያንዳንዱ ስግደቱ ላይ “ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ” (ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትኽን አሳየኝ) እያለ በመጸለይ ለሰባት ዓመት ከቈየ በኋላ፤ በሰባተኛው ዓመት በታላቅ ግርማ ተገልጻለት የአምላክን እናት ፊት ለማየት በቅቷል፤ ርሷም ምን እንደሚሻ ብትጠይቀው በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በመኾን የንግሥተ ሰማይ ወምድር የርሷን ገጽ ያዩ ዐይኖቹ ሌላ ነገርን ማየት እንደማይፈልጉና ከልጇ እንድታማልደው ብቻ እንደሚፈልግ ነግሯት፤ ርሷም ከሦስት ቀን በኋላ እንደሚያርፍ ክፍሉም ከርሷ ጋር መኾኑን ገልጻለት ባርካው ዐርጋ፤ መልኳን አይቶ በሦስተኛው ቀን ይኽ ቅዱስ አባት ዐርፏል፡፡ ✞❖ የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛለት አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ተገልጻ ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት ለርሱም ትገለጽለት ዘንድ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፉ ላይ፡- “አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሑ መዓልተ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ” (የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለዐምስት ቀናት ያኽል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያኽል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው) በማለት ተማፅኗታል፡፡ ✞❖ የእመቤታችን ታማኝ ወዳጅ አባ ጽጌ ድንግል በተመስጦ በመኾን እጅግ ድንቅ የኾነችውን የአምላክን እናት ሥዕል ካየ በኋላ ይኽነን የምስጋና ቃላት ለርሷ ያቀርባል፡- “ሥዕልኪ ጽግይተ ላሕይ ዘከመዝ ትኤድም በዓለም እፎ ይሤኒ በሰማይ ላሕየ ገጽኪ ማርያም ሐሤተ ትእምርትኪ እጽገብ አስተርእዪኒ በሕልም እስመ አውዐየኒ ነደ ፍቅርኪ ፍሕም አጥፍኦቶ ዘኢይክል ዝናም” (ማርያም ሥዕልሽ በዓለም እንዲኽ የምታበራ ከኾነ በሰማይ የፊትሽ መልክ ምን ያምር! አንቺን ከማየት የሚገኘውን ደስታ እጠግብ ዘንድ በሕልም ተገለጪልኝ፤ ዝናብ ሊያጠፋው የማይቻለው የፍቅርሽ እሳት አንድዶኛልና) ብሏል፡፡ ✞❖ በመኾኑም በዚኽ ሱባኤ ሐዋርያት የአምላክን እናት አይተው እንደተደሰቱ፤ ዛሬም ለእኛ ለልጆቿ በረድኤት ትገለጽልን ዘንድ አበው ካህናት ሌሊቱን በሰዓታት ምስጋና “ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ” (ድንግል ሆይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ወደ እኔ ነዪ እኛን ትባርኪ ዘንድ (በእኛ ላይ በረከትን እንድታሳድሪ) በማለት ይማፀኗታል፤ እኛም የማይጠገበው ውዳሴዋን ቅዳሴዋን በመተርጐም የቅዱስ ኤፍሬም የአባ ሕርያቆስ እመቤት ትባርከን ዘንድ እንለምናታለን፡፡ ✞❖ በገዳም በበረሓ ያሉት አበውም ምስጋናዋን በማድረስ ፍጹም በረከቷን ሽተው በፊቷ ይማለላሉ፤ ርሷም ለሱባኤዋ በወደቁበት በረሐ እየተገለጸች በረከቷን ታድላቸዋለች፤ ክቡራን ምእመናንም ከልጅ እስከ ዐዋቂ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሰብሰብ ቅዳሴ ማርያምን በማስቀደስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በመቀበል፤ እጅግ ድንቅ

🌿🌾 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ🌾🌿 ✔እውነተኛ ፈተና አንድና አንድ ብቻ ነው ፣ እርሱም ኃጢአት ነው፡፡ ✔አንተ የራስን ድርሻ ተወጥተ ስትጨርስ እግዚአብሔር የራሱን ድርሻ ይወጣል፡፡ ✔መውደቅ አዳማዊ ነው ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያብሎሳዊ ነው፡፡ ✔ከውኃ እንዴት እንወለዳለን የሚል ሰው ካለ እንዴት ከአፈር ተወለድን ብዬ እጠይቀዋለው፡፡" ✔ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡” ✔ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፋ ደዌ ነው፡፡ ✔ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ ፤ ከዚያም ሰማይና ምድር ከአንተ ጋር ይታረቃሉ ✔ዕውቀት የሚባለው የገዛ ራስን ሲያውቁ ነው፡፡ ራስን አለማወቅ ከለየለት ዕብደት እጅግ የከፋ ነውና፡፡ ምክንያቱም የለየለት ዕብደት የሚባለው ሳይወዱና ሳይፈቅዱ የሚመጣ በሽታ ሲኾን ራስን አለማወቅ ግን ወደውና ፈቅደው የሚያብዱት ዕብደት ነው፡፡ ✔ሰዎች ከፍቅር በላይ በየትኛውም ዓይነት መንገድ ከክፋታቸው ልንመልሳቸው አንችልም፡፡ ፍቅር ሰዎች ከአውሬነታቸው መልሳ ሰዎች እንድሆኑ የምታደርግ ታላቅ መምህርት ናት፡፡ ✔የበለስ ቅጠል ሰፊና ደስ የምታሰኝ ናት፤ ወደ ጥፋት የምትወስደው የኃጢአት መንገድም ሰፊ በር ናት፡፡ የበለስ ፍሬ ሲበሏትና ሲያላምጧት ጣፋጭ ናት፤ ኃጢአትም ሲሠሯት ደስ ታሰኛለች፡፡ ከሠሯት በኋላ ግን (እንደ በለሲቱ) መከራን ታመጣለች፡፡ በሚሠሯት ጊዜ ጣፋጭ ከሠሯት በኋላ ግን መራር ናትና እርሷን ከመሥራት ሽሽ፡፡ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ☞ @EOTC2921 Channel ☞ @Ethio_Orthodox1 Group

🌿🌾 #ጌታዬ_ሆይ! 🌾🌿 ✔በሕይወቴ አንተ ያደረክልኝን ላስተውለው የሚገባኝ ነገር ግን ያላስተዋልኩት ብዙ ነገር እንዳለ ይሰማኛል። ለዛም ነው ካለማስተዋሌ ላመሠግንህ ሲገባ የማማርርህ። ✔ውሎዬን አሠብኩት አልሞትኩም ፣ በቸርነትህ አለሁ!! ☞አልራበኝም በልቻለሁ። ☞አልጠማኝም ጠጥቻለሁ፣ ☞አልተራቆትኩም ለብሻለሁ፣ ✔የንጉሥ ልጅ ሆኜ ተፈጥሮን ባሪያ አድርገህልኝ በፀጋህ ሥጦታ እመላለሳለው ። #ግን_ጌታዬ_ሆይ! ✔ዛሬ ስንቴ አመሰገንኩህ??ስላደረክልኝ፣ ስለምታደርግልኝ ነገር ሁሉ በረከቶቼን ቆጥሬ ምን ምስጋና አቀረብኩልህ?! አልዋሽህም ምንም አላመሠገንኩህም። ከሠጠኸኝ ይልቅ አጣሁ ባልኩት ሳማርርህ ነበር!! ካለኝ ይልቅ በጎደለኝ ሳጉረመርም ነበር። ታዲያ እኔ ማስተዋል አልጎደለኝም?? አዎ ጎሎኛል!! ✔አምላኬ ሆይ ካጣሁት ይልቅ ባለኝ እንዳመሠግንህ ማስተዋልንና ጥበቡን ስጠኝ። አንተ የማውቅበት፣ አውቄም የማመሰግንበት የእውቀት አይኖቼንም አብራልኝ! አሜን ጌታ ሆይ ሁላችንንም ለንስሐ ሞት አብቃን፡፡ 🌻💐🌹 #Join...🌹💐🌻 #Share #Share #Share 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇 @EOTC2921 👇 👇 @Ethio_Orthodox1 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

✞ #_ቅዱስ_ኡራኤል_መልአክ_ብርሃን✞ ☞✞ኡራኤል የሚለው ስም 'ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሰረተ ስም ነው ። ☞✞ኡራኤል ማለት ትርጉሙ "የብርሃን ጌታ" የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው ። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ አለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነው ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መፅ ሄኖክ {6፤2} ☞✞ሚስጢር ሰማይና እዉቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለፀለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል ። መፅ ሄኖክ {28 ፤13} ☞✞ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ፤ እዉቀት ለተሰወረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብን ያጠጣ መለአክ ነው ። 🙏በረከቱ በሁላችንም ላይ ባለንበት ቦታ ይደርብን፡፡🙏

ነይ ነይ እምዬ ማርያም @EOTC2921.m4a1.10 MB

መመኪያዬ_እርስቴ_የሆነች.m4a9.71 KB

ሰባቱ መብራቶች.m4a1.06 MB

ሰላም ለኪ እንዘንሰግድ.m4a9.29 KB

#ጽምዕት_ምድር_ዘኢሳይያስ [ #የኢሳይያስ_የተጠማች_ምድር ] #የአምላክ_እናት_ቅድስት_ድንግል_ማርያም 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ❖ ነቢዩ ኢሳይያስ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በምዕ ፵፬፥፫ ላይ የሕይወት ፍሬ፣ የሕይወት ውሃ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ፀንሳ የተገኘችውን ቅድስት ድንግል ማርያምን፤ በተጠማች ምድር በመመሰል ልዩና አስደናቂ ትንቢትን ተናግሯል፡፡ ❖ ነቢዩ ኢሳይያስም አስቀድሞ ተገልጾለት በምዕ ፵፬፥፫ ላይ "በተጠማ ላይ ውሃን፤ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለኹና፤ መንፈሴን በዘርኽ ላይ በረከቴንም በልጆችኽ ላይ አፈስሳለኹና" በማለት ውሃን ስለምታስገኘው ነገር ግን ዘር ባልተዘራባት ይብስትና የተጠማች ስለኾነቺው ምድር በትንቢቱ ላይ ተናግሯል፡፡ ❖ በቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት በእጅጉ የተራቀቁ ሊቃውንትም በመንፈስ ቅዱስ ምስጢር ገላጭነት ዘርዐ ብእሲ ሳይወድቅባት፤ ሩካቤ ብእሲ ሳይደርስባት፤ በግብረ መንፈስ ቅዱስ የሕይወት ውሃ ክርስቶስን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያምን በኢሳይያስ የተጠማች ምድር በመመሰል በስፋት አስተምረዋል፡፡ ❖ ከእነዚኽ ሊቃውንት መኻከል ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዱስ ያሬድና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይገኙበታል፡፡ የእመቤታችን ጣዕመ ውዳሴዋ ከበዛላቸው ከነዚኽ አበው አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነቢዩ አሳይያስ በምዕ ፯፥፲፬ላይ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች" በማለት በድንግልና እንደምትወልድ የተናገረውን በምዕ ፵፬፥፫ ላይ "በተጠማ ላይ ውሃን፤ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለኹና" ሲል ያለ ወንድ ዘር የሕይወት ውሃ ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና እንደምትወልድ የተናገረውን ትንቢታዊ ኀይለ ቃልን በማስተባበር፦ በልደት ድርሳኑ ሲገልጽ፡- "Come, Isaiah, see the Immanuel in the cave..." (ኢሳይያስ ሆይ ና፤ ዐማኑኤልንም በዋሻው ውስጥ ተመልከት፤ እውነት በትንቢትኽ ውስጥ ጸንቷልና ነገሩን አትመው፤ ከዚያች ከተጠማችው ምድር ከድንግል ማርያም ተክል በቀለ፤ አንተ በትንቢትኽ እንዳሳወቅኸው ርሷ አልተዘራባትም አልተተከለባትም፤ እንሆ ድንቁ፤ ተነሥ እና ከብዙ ሕዝቦች ጋር ተደነቅ፤ ምከንያቱም በድንቅ የተመላችው የርሷ ማኅተመ ድንግልናና ወተት በአንድ አካሏ ተስተባብረው አሉና። ድንግል እናቱ ናት፤ ከዚኽ የተነሣም ርሱ ስሙ "ድንቅ" ነው፤ በፊቱ የሰው ፍጥረት እና የሰው ልጆች ኹሉ ንግግር ኀይል የሌላቸው ናቸው፤ በድንግልናዋ የወለደቺው ብላቴናዪቱ ልጅ ጸሓፊውን አፉን አስያዘቺው፤ ቃሎቹም ደግሞ ለአንዳች ትርጉምም ይኹን ለአንዳች ገለጻ ዐቅም አልነበረውም፤ ጠቢቡ እና የረዘሙ ንግግሮቹ (ኑፋቄዎቹ) ተረትተዋል፤ ምከንያቱም ድንግልናና ወሊድ ተስተባብረው ለተመለከተ ኹሉ መናገር እጅግ የሚከብድ ነውና። ታላቁ የጽድቅ ፀሓይ ነጸብራቁ ወደ ውስጥ አሰባሰበ፤ አንዲት ብላቴና ልጅም ብቻዋን በቅድስና በማሕፀኗ ተሸከመቺው፤ ርሷ ብርሃናት የሚኾኑ ኹሉ የሚፈሩትን አማናዊ ብርሃን ወለደቺው፤ ምክንያቱም በልደቱ አማካይነት ርሱ ጨለማን ከኹሉም ስፍራዎች ላይ አንሥቷልና) በማለት ያለ ዘር ያለ ሩካቤ የሕይወት ተክል፣ የሕይወት ፍሬ፣ የሕይወት ውሃ ጌታን የፀነሰች፤ ድንግል ስትኾን ከጡቶቿ ወተት የተገኙባት በመኾኗ ነቢዩ ኢሳይያስ "በተጠማ ላይ ውሃን፤ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈሳለኹና" በማለት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን ማግኘቱንና፤ ይኽም አዋቂዎች ነን ከሚሉ ኹሉ የረቀቀ ሰማያዊ ምስጢር መኾኑን አስተምሯል፡፡ ❖ ከእመቤታችን በረከትን የተቀበለው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በተጠማች ምድር መስሎ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የተናገረውን ትንቢት እያራቀቀ ስለ ክርስቶስ ልደት በጻፈው ድርሳኑ ላይ ሲገልጽ:- ❖ "Mary acquired by you..." (ድንግል ማርያም ባንተ ያገቡ ሴቶችን መለያን የራሷ አደረገች፤ ይኸውም ያለ ተራክቦ ፅንስ በርሷ አለና፤ ከተለመደው ኹናቴ ውጪ ድንግል ስትኾን ነገር ግን ወተት በጡቶቿ አለ፤ አንተ ሳይታሰብ (በድንገት) የተጠማቺውን መሬት የወተት ምንጭ አደረግኻት) በማለት ድንግልናና ወተትን አስተባብራ በመገኘቷ የኢሳይያስ የትንቢት ቃል የተፈጸመባት መኾኑን ገልጾታል፡፡ ❖ ሊቁ ኤፍሬምም ይኽነን ሲያጐላ "From the thirsty earth…" (የተጠማችው ምድር ምንጭን በሚበቃ መጠን አመነጨች የመሬትንም ጥም ስትቈርጥ ዘንድ (ልትቈርጥ) በማለት የተጠማች ምድር ከተባለች ከቅድስት ድንግል ማርያም፤ የሕይወት ውሃ ዐማኑኤል ተወልዶ፤ ከመሬታውያን ከእኛ የነፍሳችን ጥም የቈረጠልን መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡ ❖ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ካፈራቻቸው በቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት ከተራቀቁት ሊቃውንት መኻከል ሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ "ጽምዕት ምድር ዘኢሳይያስ" (የኢሳይያስ የተጠማች ምድር) በማለት ገልጿል። ❖ ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስም በአርጋኖን መጽሐፉ ላይ፦ "ተፈሥሒ ኦ ምድር ጽምዕት ዘኢሳይያስ ዘኢሰቀያ ዝናመ ደመናት" (ከደመናት የሚገኝ ዝናብ ያላጠጣት (የኢሳይያስ የተጠማች ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ) በማለት የትንቢተ ኢሳይያስ አማናዊ ትርጓሜን እንደ ወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡ 🌻🌾🌻🌾🌻🌾🌻🌾🌻🌾🌻 [የአምላካችን የክርስቶስ እናቱ የኢሳይያስ የተጠማች ምድር ድንግል ሆይ ጸሎትሽ ልመናሽ ጋሻ መከታ ይኹነን አሜን] ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

#ኦሪት_ዘፍጥረት፡፲፰፥፩-፲፮ 🌿🌿🌿 ✞✞✞ 🌿🌿🌿 1፤በቀትርም፡ጊዜ፡ርሱ፡በድንኳኑ፡ደጃፍ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡እግዚአብሔር፡በመምሬ፡የአድባር፡ዛፍ፡ ተገለጠለት። 2፤ዐይኑንም፡አነሣና፥እንሆ፥ሦስት፡ሰዎች፡በፊቱ፡ቆመው፡አየ፤ባያቸውም፡ጊዜ፡ሊቀበላቸው፡ከድ ንኳኑ፡ደጃፍ፡ተነሥቶ፡ሮጠ፥ወደ፡ምድርም፡ሰገደ፥እንዲህም፡አለ፦ 3፤አቤቱ፥በፊትኽስ፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፡ባሪያኽን፡አትለፈኝ፡ብዬ፡እለምናለኹ፤ 4፤ጥቂት፡ውሃ፡ይምጣላችኹ፥እግራችኹን፡ታጠቡ፥ከዚችም፡ዛፍ፡በታች፡ዕረፉ፤ 5፤ቍራሽ፡እንጀራም፡ላምጣላችኹ፥ልባችኹንም፡ደግፋ፡ከዚያም፡በዃላ፡ትኼዳላችኹ፤ስለዚህ፥ወደ፡ ባሪያችኹ፡መጥታችዃልና።እነርሱም፦እንዳልኽ፡አድርግ፡አሉት። 6፤አብርሃምም፡ወደ፡ድንኳን፡ወደ፡ሳራ፡ዘንድ፡ፈጥኖ፡ገባና፦ሦስት፡መስፈሪያ፡የተሰለቀ፡ዱቄት ፡ፈጥነሽ፡አዘጋጂ፥ለውሺውም፥ዕንጐቻም፡አድርጊ፡አላት። 7፤አብርሃምም፡ወደ፡ላሞቹ፡ሮጠ፥እጅግ፡የሰባም፡ታናሽ፡ጥጃ፡ያዘና፡ለብላቴናው፡ሰጠው፥ያዘጋጅ ም፡ዘንድ፡ተቻኰለ። 8፤ርጎና፡ወተትም፡ያዘጋጀውንም፡ጥጃ፡አመጣ፥በፊታቸውም፡አቀረበው፤ርሱም፡ከዛፉ፡በታች፡በፊታ ቸው፡ቆሞ፡ነበር፥እነርሱም፡በሉ። 9፤እነርሱም፦ሚስትኽ፡ሳራ፡ወዴት፡ናት፧አሉት።ርሱም፦በድንኳኑ፡ውስጥ፡ናት፡አላቸው። 10፤ርሱም፦የዛሬ፡ዓመት፡እንደ፡ዛሬው፡ጊዜ፡ወዳንተ፡በእውነት፡እመለሳለኹ፤ሚስትኽ፡ሳራም፡ልጅ ን፡ታገኛለች፡አለ።ሳራም፡በድንኳን፡ደጃፍ፡በስተዃላው፡ሳለች፡ይህንን፡ሰማች። 11፤አብርሃምና፡ሳራም፡በዕድሜያቸው፡ሸምግለው፡ፈጽመው፡አርጅተው፡ነበር፤በሴቶች፡የሚኾነውም፡ ልማድ፡ከሳራ፡ተቋርጦ፡ነበር። 12፤ሳራም፡በልቧ፡እንዲህ፡ስትል፡ሣቀች፦ካረጀኹ፡በዃላ፡በእውኑ፡ፍትወት፡ይኾንልኛልን፧ጌታዬም ፡ፈጽሞ፡ሸምግሏል። 13፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡አለው፦ካረጀኹ፡በዃላ፡በእውኑ፡እወልዳለኹን፧ስትል፡ሳራ፡ለምን ፡ሣቀች፧ 14፤በእውኑ፡ለእግዚአብሔር፡የሚሳነው፡ነገር፡አለን፧የዛሬ፡ዓመት፡እንደ፡ዛሬው፡ጊዜ፡ወዳንተ፡ እመለሳለኹ፤ሳራም፡ልጅን፡ታገኛለች። 15፤ሳራም፡ስለ፡ፈራች፦አልሣቅኹም፡ስትል፡ካደች።ርሱም፦አይደለም፥ሣቅሽ፡እንጂ፡አላት። 16፤ሰዎቹም፡ከዚያ፡ተነሥተው፡ወደ፡ሰዶም፡አቀኑ፤አብርሃምም፡ሊሸኛቸው፡ዐብሯቸው፡ኼደ። የአብርሃምና የሳራን ቤትና ህይወት የባረኩ አጋይዝት አለም ስላሴ የኛንም ጓዳና ህይወት ይባርኩልን፤ ይቀድስልን አሜን።

✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✞ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• 🌿🌿✞ #ምስጢረ_ስላሴን ✞🌿🌿 ✞ #ለህፃናት_እንዲህ_እናስተምር ✞ #ማን_ፈጠረን? ☞✞ ስላሴ #ስላሴ_ስንት_ናቸው? ☞✞ አንድም ሶስትም #ሶስትነታቸው_በምን_በምን_ነው? ☞✞ በስም፣ በአካል፣ በግብር #አንድነታቸውስ_በምን_ነው? ☞✞ በባህሪ፣በህልውና፣ በመለኮት፣ በፍቃድ፣ በስም፣ በአካል፣ በግብር ይህችን፣ አለም በመፍጠርና በማሳለፍ #የስም_ሦስትነታቸው_እንዴት_ነው? ☞✞ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ #የአካል_ሶስትነታቸው_እንዴት_ነው? ☞✞ #አብ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው። ☞✞ #ወልድ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው። ☞✞ #መንፈስቅዱስ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገፅ አለው። #የግብር_ሶስትነታቸው_እንዴት_ነው? ☞✞ አብ=ወላዲ፤ ወልድ=ተወላዲ፤ መንፈስ ቅዱስ=ሰራፂ #አብ_ምን_ማለት_ነው? ☞✞ አባት፦ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ፤ ያለእናት ወልድን የወለደ #ወልድ_ምን_ማለት_ነው? ☞✞ ልጅ፦ የሚወለድ፤ ያለእናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ #መንፈስ_ቅዱስ_ምን_ማለት_ነው? ☞✞ ሰራፂ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ሁኖ ከአብ የሰረፀ ✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞ የእግዚአብሔር አብ በረከት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞

🌿🌿✞ #መርሳት ✞🌿🌿 ☞✞ በአንድ ወቅት የግብጹ ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እያስተማሩ ባሉበት ወቅት በዙ ጥያቄዎች በጹሑፍ ይደርሳቸው ነበር። ☞✞ ታዲያ ከነዛ ጹሑፎች መካከል አንዱ እንዲ ይላል፦ ☞✞... አባቴ እኔ ታላቅ የመርሳት ችግር አለብኝ ያደረኩትን የሰማሁትን ነገሮች በሙሉ እረሳቸዋለው እናም አባቴ ምን እንደማደርግ ይምከሩኝ ነበር የሚለው። ☞✞ ብጹእነታቸውም ልጄ መምከሩንስ እመክርሃለሁ ምን ማድርግ እንዳለብህ እነግርሃለሁ ነገር ግን እንዳትረሳው እፈራለሁ አሉት ይባላል። ☞✞ ቃለ እግዚአብሔር ስንሰማ በማስተዋል ልቦናችንንም ሰብስበን ሊሆን ይገባል። በነገሮችም ሁሉ አስተዋዮች ልንሆን ይገባል። ስለዚህ ማስተዋልና ጥበብን ወደሚሰጥ አምላክ አጥብቀን ልንጸልይ ይገባናል!!!

•✞ #ድንግል_ማርያምና_የዕንቁ_ወፍ_በሊቃውንት ✞• 🌿✝✝✝🌿✝✝✝🌿✝✝✝🌿 ✞ዕንቆ ባሕርይ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደችውን ቅድስት ድንግል ማርያምን ቀደምት ሊቃውንት ዕንቁ በምታስገኘው በብርጋና (በከርከቤዴል) ወፍ መስለዋት አስተምረዋል፤ ከሊቃውንቱ ውስጥ የአራቱን ትምህርት ከምሳሌው ጋር "በመጽሐፈ ፊስአልጎስ በግእዝና በዐማርኛ" በሚል ተርጉሜ ካሳተምኩት ጥቂቱን እነሆ ብያለሁ፨ ❖ የአምላክ ከ፲፫፻፶፯- ፲፬፻፲፯ (1357-1417) ዓ.ም. የነበረው ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በሰባቱ ጊዜያት የጸሎት መጽሐፉ (መልክአ ሕማማት) ላይ በመጽሐፈ ፊሳአልጎስ ክፍል ፶፫ ላይ ዕንቊን የምትወልደው የእመቤታችን ምሳሌ የኾነችው የብርጋና ወፍን በምሳሌነት ሲጠቅስ፡- “ማርያም ባሕርይ ጽድልተ ንጻሬ ወዜና እምጸዳል ዕንቈ በማሕፀና ዘትወልድ ዖፈ ብርጋና” (ከብርሃን ዕንቊን በማሕፀኗ የምትወልድ የብርጋና ዎፍ በመባል የታወቅሽ ታሪኳና ፊቷ የሚያበራ (ስመ ጥርና ብርኅተ ገጽ) የተባልሽ ባሕርይ (ዕንቊ) ማርያም ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል) ይላታል፡፡ ❖ ይኽቺ በመጽሐፈ ፊስአልጎስና በአክሲማሮስ የተጠቀሰችው ብርጋና የተባለችው ዎፍ የምትፀንሰው በመዠመሪያው ወር፣ በሦስተኛው ወር፣ በስድስተኛው ወር ነው፤ ይኽቺም ዎፍ ከወንዱ በዘር አትፀንስም፤ ከባሕር ወጥታ ሦስት መዓርግ ከፍ ብላ ወደ ሰማይ ወጥታ ወደ ፀሓይ ተጠግታ መላ አካሏን ከተመታች በኋላ ገላዋ ሲተኩስ ረባ ወርዳ ወደ ጥልቅ ባሕር ትገባለች፤ ያን ጊዜ ረባ ወርዳ ወደ ጥልቅ ባሕር ስትጠልቅ ከጸዳለ ፀሓይ ከውሃ ጠል ተከፍሎ በማሕፀኗ ይፀነሳል ይላሉ፡፡ ❖ ይኽቺም “ንጽሕት እምአዕዋፍ” (ከአዕዋፍ የነጻች) ስትባል ስትፀንስም በግራ ማሕፀኗ አዕዋፍን በቀኝ ማሕፀኗ የተለያዩ አዕናቁ ካስገኘች በኋላ በመጨረሻው ክቡር ዕንቊን ታስገኛለች፤ ይኽነንም ዕንቊ ዓሣ ተቀብሎ ይውጠዋል፤ በዋጠውም ጊዜ የዚኽ ዕንቊ ብርሃን የዓሣውን አካልና የባሕሩን ጥልቀት ሠንጥቆ ከባሕር ዳርቻ ላሉት ሰዎች ይታያቸዋል። ❖ ከዚኽ በኋላ ጠቢባኑ ብርሃን የማይከለክል ውሃ የማያስገባ ልብስ ተጐናጽፈው ገብተው ዓሣውን በቀስት ነድፈው በመግደል ዕንቁዉን አውጥተው ለነጋዴ ይሸጡታል፤ አንድም ዓሣው ምግቡን ለመፈለግ ወደ ዳር ይወጣል፤ ሰዎችም በግራና በቀኝ ጎጆ ሠርተው ይጠብቁታል፤ ዓሣውም ምግቡን ሲፈልግ በቀስት ገድለው ዕንቁዉን አውጥተው ለነጋዴ ይሸጡታል፨ ❖ ይኽም ነጋዴ ለነጋዴ ሲወዳጅ ወደ ቤተ መንግሥት ይደርሳል ይላሉ፡፡ ❖ ዖፈ ብርጋና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ምሳሌነቷም እንደምንድነው? ቢሉ ይኽቺ ብርጋና “ንጽሕት እምአዕዋፍ” (ከአዕዋፍ የነጻች) እንደኾነች እመቤታችንም “ንጽሕት እምልማደ አንስት” (ከሴቶች ልማደ ተፈጥሮ ኹሉ የነጻች) ናትና (መሓ ፬፥፯፤ ሉቃ ፩፥፳፰)፨ ❖ ዖፈ ብርጋና ያለ ዘር እንደፀነሰች እመቤታችንም ያለ ዘርዐ ብእሲ አምላክን ፀንሳለች (ማቴ ፩፥፲፰)። ❖ ዳግመኛም ዖፈ ብርጋና ሦስት መዓርጋት ከፍ ብላ ወጥታ ከፀሓይ ተመትታ ዕንቊን እንዳስገኘች እመቤታችንም ሦስት መዓርጋተ ትውልድ ዐልፋ በአራተኛው ክፍለ ዘመን በዘመነ ካህናት በአራተኛው መዓርገ ትውልድ ከነገደ ይሁዳ ተወልዳ ዕንቈ ባሕርይ አምላክን በድንግልና ወልዳ አስገኝታልናለችና (ራእ ፭፥፭) ይላል፡፡ ❖ በርካቶች ሊቃውንት ይኽቺን ዎፍ ለምሳሌነት ሲጠቀሙባት የመልክአ ኢየሱስ ደራሲ አባ ዐምደ ሐዋርያት በዚኽች ወፍ አንጻር በመመሰል ሲያስተምር፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ በላዕለ ቅዱሳን ዕሩፍ ይፀነስ ውስተ ከርሥየ ዘርዐ ቃልከ መጽሐፍ ጸዳለ እምጸዳል ከመ ትፀንስ ዖፍ” (በቅዱሳን ላይ ዐድረኽ የምትኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የቃልኽ ዘር መጽሐፍ በማሕፀነ አእምሮዬ ይፀነስ፤ ዎፍ ጸዳልን ከጸዳል እንድትፀንስ) በማለት የወንጌል ትምህርት በአእምሮው እንዲቀረጽበት ተማፅኗል፡፡ ❖ ዳግመኛም የማሕሌተ ጽጌ ደራስያን አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በመጽሐፋቸው ላይ ከዚኽ ምስጢር በመነሣት የብርጋና ወፍ የወለደችውን ዕንቊ ስለሚውጠው ዓሣ ሲያስተምሩ ፦ ❖ “ዓሣ ባሕርኒ እንዘ ይጸውር ወርቀ ይጸብት ቀላያተ ወየዐርግ ሐይቀ” (የባሕር ዓሣም ወርቅን ተሸክሞ በባሕር ላይ ዋኝቶ ከጥልቁ ይወጣል) በማለት አስቀምጠውታል፡፡ ❖ የረቀቀ የሥነ ፍጥረት ዕውቀት የነበረው ሊቁም በመጽሐፈ ፊስአልጎስ ክፍል ፶፫ ላይ ስለ ብርጋና ዎፍ ምሳሌነት ይኽን ይላል፦ “በእንተ አክሊጦስ ወመርጋሊጦስ ዘውእቱ ብርጋና ሶበ ይፈቅድ ኖትያዊ ኬንያ ከመ ይርከብ ባሕርየ፤ የኀሥሥ መሥገርተ ወያወርድ ውስተ ባሕር እንዘ የአስር መቃጥነ በጽኑዕ ሀብል..." (ይኽ ክፍል ስለ አክሊጦስና መርጋሊጦስ የሚናገር ነው፤ ያም ብርጋና ነው፤ ጠቢብ ዋናተኛ ዕንቊን ሊያገኝ በወደደ ጊዜ ወጥመድን ፈልጎ በጠንካራ ገመድ መንጠቆን በማሰር ወደ ባሕር ውስጥ ያወርዳል፤ ያን ጊዜ መንጠቆውን ከቦታው ያንቀሳቅሰውና ያነቃንቀው እንደኾነ ለማየት ወደ ባሕሩ ዳርቻ ቀርቦ ይቆማል፤ ባንቀሳቀሰው ጊዜ ዕንቁዉን እስኪያገኙት ድረስ መንጠቆውን ወደ ኼደበት ይከተሉታል። ተናጋሪ እንዲኽ አለ ዕንቊ ከምን ይገኛል፤ ምላሽ ያውም ብርጋና ነው፤ ስሙ ኮንኮስ ከሚባል ዎፍ፤ ርሱ ግን የፀሓይ ሙቀትን ከመቀበል ጋራ የውሃ ቅዝቃዜንና የሰማያትን ጠልን በመሳብ አፉን ከፍቶ ሳለ ወደ ምሥራቅ ዳርቻ ይወጣል፤ የከዋክብትንና የጨረቃን ድምቀት ከማየት የተነሣ ዕንቊ ከብርጋና ማሕፀን ይወለዳል፤ ዕንቊ ከርሷ የሚገኝ ብርጋና ኹለት ክንፎች አሏት። ዕንቊም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው ነው፤ ዮሐንስ ስለ ርሱ “እነሆ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በጉ ነው” አለ (ዮሐ ፩፥፳፱)፤ ብርጋናም ያለ ሩካቤ የወለደችው በኾነች በማርያም ትመሰላለች፤ ኹለቱ ክንፎችም በድንግልናዋ ይነገራሉ (በድንግልናዋ ይተረጐማሉ)፤ ጨረቃና ከዋክብት በመንፈስ ቅዱስ፤ ፀሓይም የፍጥረት ኹሉ መብራት በኾነ በአብ አምሳል ነው፤ ሰው ሆይ አንተም ሀብትኽን ኹሉ ሽጠኽ ለነዳያን ስጥ፤ የሰማያት ድልብን ሰብስብ፤ ያውም ዋጋው እጅግ የበዛ የኾነ የሕይወት ዕንቊ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ዳግመኛም ብዙውን እንድታገኝ በትንሹ ተወጃጅ (ማቴ ፲፱፥፳፩))፡፡ በማለት ድንቁን ምስጢር ያስቀምጠዋል፨ [የአምላክ እናት ሆይ ዕንቆ ባሕርይ ከሚባል ልጅሽ ከአእምሯችን ድንቁርናን አርቆ ከርሱ በሚገኘው ዕውቀት ብሩህ ያደርገው ዘንድ ዘወትር ለምኚልን፤ እንወድሻለን ] [መጽሐፈ ፊስአልጎስ በግእዝና በዐማርኛ ከሚለው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ከግእዝ ተተርጉሞ ከታተመ መጽሐፍ የተወሰደ]

ውድ የተዋህዶ ልጆች እጅግ ጠቃሚ የሆነ ምክር እነሆ፤ ሁሉም ልብ ብሎ ሊሰማውና ሊተገብረው የሚገባ መንፈሳዊ ስንቅ፦ የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ፫ኛው የግብፅና የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳሳት መንፈሳዊ ስብከት፤ በእውነቱ በረከታቸውና ጸሎታቸው አይለየን አሜን፡፡

10 track 10 - 10 track 10.mp42.27 MB

09 track 9 - 09 track 9.mp42.53 MB

08 Track 8 - 08 Track 8.mp41.55 MB