የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
前往频道在 Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
显示更多4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
4 374
ዓለመ፡፡
✍ቸር እረኛ እስራኤልን የሚጠብቃቸው
ታዛዥ የሆነ ክርስቶስ ለአሕዛብ የመጣ፡፡ እሺ ብሎ ታዛዥ ሆኖ ዓለምን ይቤዥና ያድን ዘንድ ከሰማይ ወረደ፤
መጣ፡፡›› (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ገጽ)፡፡ በማለት ሁሉን
የሚገዛ አምላክ ዓለሙን ሊቤዥና ሊያድን እሺ ብሎ በፈቃዱ መምጣቱን መሰከረ፡፡
ሁሉን የሚመግብ፣ የሕይወት እንጀራንና የሕይወት መጠጥን የሚሰጥ ጌታ ወደ ሰርግ ተጠራ፡፡ ለፍጥረቱ ማዕድን የሚያዘጋጅ ጌታ በፈሪሳዊው ስምዖን ቤት
ለግብዣ ተጠራ፡፡ ዮሐ 2፤2፣ ሉቃ ፤36-37፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በፈሪሳዊው ማዕድ ላይ የቀረበው የጌታ ማዕድ በሚለው ስብከቱ ‹‹ ንስሓ ስለምትገባው ስለዚያች ኃጢአተኛ ሴት ሲል ከግብዣው ቤት ተገኘ፤ ጌታ ርሀቡ ሥጋዊው ምግብ ሳይሆን የዚያች ኃጢአተኛ እንባ እንጂ… ወደ ፈሪሳዊው ስምዖን ቤት የሄደው በምግብና በመጠጥ ለመዝናናት አልነበረም ሕይወት መድኃኒት የሆነውን ትምህርቱን በማዕዱ ለማቅረብ በመሻቱ ነበር እንጂ፡፡ … ክፉ የተባለው ሰይጣን በመብል ምክንያት አዳምና ሔዋንን ሞትን የሚያመጣ ምክርን እንደመከራቸው እንዲሁ ቸሩ ጌታችን ደግሞ በማዕድ ቦታ ተገኝቶ ሕይወት ሰጪ የሆነ ትምህርቱን ለአዳም ልጆች በማዕዱ አቀረበ፡፡ እርሱ ጌታችን የጠፉትን ነፍሳት ለማጥመድ አሳ አስጋሪ ነበር፡፡ ቀራጮችና አመንዝሮች ወደ ስካርና ሥርዐት አልበኝነት ሲፋጠኑ ተመለከታቸው፤ ሥጋንም ከሚያወፍር የማዕድ ቦታ እነርሱን በማስገር ነፍስን ወደሚያወፍር ጾም ሊያሻግራቸው የቃሉን መረብ በማዕዱ ውቅያኖስ ላይ ጣለው፡፡››በማለት ገለጸው፡፡"ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም"
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#JOIN #JOIN #JOIN #JOIN
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
4 374
✍☞⛪️ ነገረ ክርስቶስ ⛪️☜✍
🌼💓 @EOTC2921 💓🌼
✍ብርህት፣ ንጽህት፣ ጽድልት፣ የሆነች ቤተክርስቲያናችን
ከምታስተምራቸው ትምህርቶች አንዱና ዋነኛው ነገረ
ክርስቶስ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ሲሆን
ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ ሲሆን በኋላኛ
ዘመን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን
ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆነ፡፡
እንዲህ እናምናለን፤ እንዲህም እናስተምራለን፡፡(ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ)፡፡
✍ነገረ ክርስቶስ ማለት ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የምናምነውን እምነት የምናስተምረውን
ትምህርት የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ስለ ጌታችን
መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የሚታመነው፣ የሚነገረው፣ የምንመራበት ምንድነው
የሚለውን በሚገባ ለመረዳት በቅዱሳት መጻሕፍት፣
በሊቃውንት፣ በትውፊት የተላለፈውን አስተምህሮ
የምናቀርብበት ነው፡፡
አግዚአብሔር አምላካችን የሚታየውን ዓለም
ከማስገኘቱ በፊት እስከ ዘላለም ድረስ በአንድነቱና
በሦስትነቱ፣ በመለኮቱ፣ በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና
ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት
ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ፣
የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከሚንቀሳቀስ እንስሳ
በፊት ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት፣ እግዚአብሔር በመንግስቱ ነበረ፡፡ አዳምን በእርሱ
አምሳልና አርአያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዙንም ሳያፈርስ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ
ማርያም ሥግው ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን
የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ የተገኘ ባሕርይ፣ ከሕይወት
የተገኘ አዳኝ ከመድኃኒት የተገኘ መድኅን፣ ከገዥ የተገኘ
ገዢ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ህላዌ እንደሆነ
እናምናለን (መዝገበ ሃይማኖት)፡፡
ከአብ መወለዱም በዚህ ዘመን፣ በዚህ ወቅት፣ በዚህ
ሰዓት ተብሎ ዘመን አይቆጠርለትም፤ በሰውና በመላእክት
አእምሮም ሊመረመር አይችልም፡፡ ሰውንም ስለማዳን
በአባቱ ፈቃድ በእርሱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ
ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በድንግልና
ተወለደ፡፡ ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ
አልተለወጠም፡፡ በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ሆነ፤
በሚያስደንቅ ዙፋኑ ለደቀመዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት
ጊዜ አገልጋዮች መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት
ፍቅር የአሕዛብን እግረ ልቡና ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት
በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ መላእክት ደነገጡ
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘስሩግ)፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ
ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግብ ጌታቸው
በብብቷ (በክንዷ) ተቀምጦ ጡቷን ሲጠባ ባዩ ጊዜ
በአርያም ፈለጉና በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞው ከአባቱና
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት፡፡ የጌታን ትሕትና ባዩ ጊዜም
ዓይኖቻቸውን ወደ ላይ ወደ አርያም ከፍ ከፍ አደረጉ
ክንፋቸውንም ዘርግተው ለሁሉ ጌታ ለአንተ ምስጋና
ይገባሃል እያሉ ጌታቸውን አመሰገኑ፡፡ (አንቀጸ ብርሃን)
አዳምን ካልታረሰች መሬት የፈጠረው ሔዋንንም ከአዳም
ያለእናት የፈጠራት እርሱ ከንጽሕት ድንግል ያለ ወንድ
ዘር ተወለደ፡፡ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና ስለዚህ
የአዳምን ብድራት ትከፍለው ዘንድ አዳም ያለ እናት
ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት
ክርስቶስን ወለደች ይህም ድንቅ በሚሆን አንድነት
የፍጥረት ሁሉ እኩልነት ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ (ሃይማኖተ
አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡
ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ከአዳም አጥንት
ጎድን ሲነሳ ምንም አካል እንዳልጎደለው እንዲሁ
ከድንግል የምትናገር ነፍስን ሲነሳ ማኅተመ ድንግልናዋ
አልተለወጠም፡፡ አዳም የጎድን አጥንት ከእርሱ ከተነሳ
በኋላ አካል ሳይጎድለው ፍጹም ሆኖ እንደኖረ እንዲሁ
ድንግልም ሕጻን ክርስቶስ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ
በድንግልና ጸንታ ኖረች›› አለ፡፡ ሕዝ 44፤1-3፣ መኃ 4፤12
ነቢያት ስለእርሱ ሰው መሆን ተነበዩ፡፡ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም
አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር
ሆነ ማለት ነው›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም
በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና
በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ
የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።›› በማለት ትንቢት ተናገረ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃኑ አባቱንና
እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን
ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ›› አለ፡፡ (ኢሳ
14 ፣ 9፤6፣ 8፤4)፡፡ ጌታችን በመወለዱ በዲያብሎስ የተያዙትን ማርኳል፣ ሲኦልን በዝብዟልና ስሙ ‹‹ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ›› ተብሎ ተጠራ፡፡
የማይደፈር ግሩም ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን ትሑት ነው፡፡ የማይደረስበት ልዑል ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን የባርያውን
መልክ ነሳ፡፡ የማይዳሰስ እሳት ነው፡፡ እኛ ግን አየነው፣ ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋር በላን ጠጣንም (ቅዳሴ
ማርያም)፡፡ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረና ሁሉን ሚመግብ
ሁሉ በእጁ የተያዘ መላእክት የሚታዘዙለትና የሚያገለግሉት፣ እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል
ነኝ አለ (ሉቃ 22፤27)፡፡
በአዳም ምክንያት የጨለመውን ልቡናችንን ለማብራትና በእርሱ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኖ የመጣ (ዮሐ 12፤16)፡፡ ጨለማን ያስወገደ ብርሃን
የሃይማኖትና የጽድቅ ጣሪያዋ (ጠፈሯ)፣ ሃይማኖትም ወንጌልም፣ በብዙ ድካም እርሱን ደስ ያሰኙት የሚወርሱት፣ የሃይማኖት ገንዘብን ይዘው በሠርክ
የሚገቡበት መንግስተ ሰማያት እርሱ ነው (ሉቃ 17፤21፣ መልክአ ኢየሱስ)፡፡
ክብርና ምስጋና ይግባውና የእኛን ሞት ሞቶ የእርሱን ሕይወት የሰጠን፡፡ ድዳ ለነበሩት ቃል፣ ለተሰበሩት ምርጉዝ፣ ለዕውራን ብርሃን፣ለሐንካሶች መሄጃ፣
ለለምጻሞች የሚያነጻቸው ሆነ፡፡ በዴዌ የተያዙትን አዳነ፣ ደንቆሮዎችን ፈወሰ፣ ሞትን ዘለፈው ጨለማንም
አሰቃየው፡፡ ብርሃን ኅልፈት የሌለበት፣ ፀሐይ፣ የማይጠፋ
ፋኖስ፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ፣ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ሁሉን የፈጠረ፣ ሰውን
ለማዳን ለሁሉ የተገለጠ፣ ነፍሳችንን የመለሳት እርሱ ነው
(ኪዳን ዘነግህ)፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ምንስ እላለሁ ምንስ እናገራለሁ ከዘመን በፊት የነበረ እርሱ ትንሽ ሕጻን ሆኗልና ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ
የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ›› በማለት የጌታን ትሕትና አደነቀ፡፡ ነፋሳት
የሚታዘዙለት፣ መላእክት የሚላላኩት እርሱ ለእናቱና ለዘመዶቹ እየታዘዘ አደገ፡፡ ሁሉን አዋቂ ሲሆን አልአዓዛርን የት ቀበራችሁት ብሎ ጠየቀ፤ እርሱ የሕይወት ውሃ ሲሆን ከሳምራዊት ሴት ውሃ ለመነ፡፡ ምራቅ ከጭቃ ጋር ለውሶ እውር ያበራ እርሱን አይሁድ ምራቅ ተፉበት፡፡ ጠባቂ አጥተው ለባዘኑት መልካም እረኛ ሆኖ መጣ ስለበጎቹም ነፍሱን ሰጠ፡፡ (ዮሐ 1፤11) ቅዱስ ያሬድ ‹‹ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ዘመጽአ ውስተ ዓለም ተአዛዚ ከዊኖ ክርስቶስ ለአሕዛብ፡፡ ኦሆ ብሂሎ ተአዛዚ ከዊኖ ወረደ ወመጽአ ለአድኅኖ… ከመ ይቤዙ ወያድኅን
4 374
#መድኃኔዓለም_አዳነን
መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
ደስ ይበለን /2/ እልል በሉ /2/
አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
4 374
✍✞ኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ሀብተ ማርያም ታሪክ ባጭሩ,,,✞
አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃዲቁ አቡነ
ሀብተማርያም የነበረበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ
ነው። አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ። ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ
እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ
ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ
አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡-
1/ መብረቅ፣
2/ ቸነፈር፣
3/ ረሃብ፣
4/ ወረርሽኝ፣
5/ የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣
ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ
ታዩት።
እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን
ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ
ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ
አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው
ጊዜው አልደረሰም አለው።
የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡
23 ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር
ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ
ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ
አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ አለው።
1/ ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2/ አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3/ ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4/ ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5/ ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6/ በጾም ስለተጋደልክ፣
7/ ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ
ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን
ሰጠው፡፡
በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን
ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣
ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ
በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ
ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡
የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ
ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው
በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር
የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች። # መዝ [115*6] በሰማያዊ መልአክት
በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ # ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡
ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ
ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
አሜን የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከተ ረድኤት ምልጃቸው ከሁላችን
ጋር ይሁን።
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
✍ @EOTC2921 ✍
4 374
✞📖 #ማንም_ሳያነብ_እንዳያልፍ 📖✞
እስኪ ስንቶቻችን ነን ስልካችን ላይ ያለው #መጽሐፍ_ቅዱስ ትክክለኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እንዳልሆነ የምናውቀው❓❓❓
እስኪ ለምሳሌ ያክል በመዝሙረ ዳዊት የመጨረሻው ምዕራፍ (መዝ፡150፥1-መጨረሻው) ያለውን ብቻ እንመልከት እንዴት እንደተቀየረ እና እንደተቆራረጠ!?!?
#ቃል_በቃል_እንይ(ስህተተኛውን መጽሐፍ ቅዱስ)
1 #ሃሌ_ሉያ_እግዚአብሔርን_በመቅደሱ_አመስግኑት_በኀይሉ_ጠፈር_አመስግኑት።
2 #በችሎቱ_አመስግኑት_በታላቅነቱ_ብዛት_አመስግኑት።
3 #በመለከት_ድምፅ_አመስግኑት_በበገናና_በመሰንቆ_አመስግኑት።
4 #በከበሮና_በዘፈን_አመስግኑት_በአውታርና_በእንቢልታ_አመስግኑት።
5 #ድምፁ_መልካም_በኾነ_ጸናጽል_አመስግኑት_እልልታ_ባለው_ጸናጽል_አመስግኑት።
6 #እስትንፋስ_ያለው_ዅሉ_እግዚአብሔርን_ያመስግን_ሃሌ_ሉያ፨
#ቃል_በቃል_እንይ(ትክክለኛውን መጽሐፍ ቅዱስ)
#ሃሌ_ሉያ
1 #እግዚአብሔርን_በተቀደሱ_ቦታዎች_አመስግኑት_በኀይሉ_ጽናት_አመስግኑት።
2 #በከሃሊነቱ_አመስግኑት_እንደ_ታላቅነቱ_ብዛት_አመስግኑት።
3 #በመለከት_ድምፅ_አመስግኑት_በበገናና_በመሰንቆ_አመስግኑት።
4 #በከበሮና_በሽብሸባ_አመስግኑት_አውታር_በአለው_መሳሪያና_በእንዚራ_አመስግኑት።
5 #ድምፁ_መልካም_በኾነ_ጸናጽል_አመስግኑት_በጸናጽልና_በእልልታ_አመስግኑት።
6 #እስትንፋስ_ያለው_ዅሉ_እግዚአብሔርን_ያመስግን፡፡
#ሃሌ_ሉያ፡፡
☞እስኪ በእግዚአብሔር ስም ልጠይቃችሁ ምንድነው የሚያመሳስለው??? አለም ወደተዘፈቀበት የሀጢያት ስር ወደሆነው ዘፈን(ጭፈራ) የእግዚአብሔር መቅደስ በምንባለው በሰው ልጆች ላይ ይህ ሁሉ ሴራ ለምን? በዚህ ጽሁፍ ስንቶቻችን ተሳስተን ይሆን? በአንድ በኩል መናፍቃን በዘፈን አምላክን ማመስገን እንችላለን፡፡ እያሉ ቆርጠው የተነሱበት ጊዜ ላይ ነን፡፡
☞ኦ•ኦ•ኦ•• ወዮልን ወዮልን ለመልካምም ይሁን ለመጥፎ ብለን፣ በማወቅም፣ ባለማወቅም፣ ለዓላማ ማስፈፀሚያም፣ እንዲሁም ለገንዘብም ተገዝተን ይሁን አይሁን፤ ብቻ ምንም ይሁን ምን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳችስ ቃል እንኳ ብንጨምር ወይንም ብንቀንስ፡ ያለብንን ሀጢያት፣ ኩነኔና ፍዳ እራሱ እራሱ አምላካችን ፈጣሪያችንና መድኃኒታችን መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ እንዲህ ብሎንናል፡፡
የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 22፡11-መጨረሻው
11፤ዐመፀኛው፡ወደ፡ፊት፡ያምፅ፥ርኩሱም፡ወደ፡ፊት፡ይርከስ፥ጻድቁም፡ወደ፡ፊት፡ጽድቅ፡
ያድርግ፥ቅዱሱም፡ወደ፡ፊት፡ይቀደስ፡አለ።
12፤እንሆ፥በቶሎ፡እመጣለኹ፥ለያንዳንዱም፡እንደ፡ሥራው፡መጠን፡እከፍል፡ዘንድ፡ዋጋዬ፡ከእኔ፡ጋራ፡
አለ።
13፤አልፋና፡ዖሜጋ፥ፊተኛውና፡ዃለኛው፥መዠመሪያውና፡መጨረሻው፡እኔ፡ነኝ።
14፤ወደሕይወት፡ዛፍ፡ለመድረስ፡ሥልጣን፡እንዲኖራቸው፡በደጆቿም፡ወደ፡ከተማዪቱም፡እንዲገቡ፡
ልብሳቸውን፡የሚያጥቡ፡ብፁዓን፡ናቸው።
15፤ውሻዎችና፡አስማተኛዎች፡ሴሰኛዎችም፡ነፍሰ፡ገዳዮችም፡ጣዖትንም፡የሚያመልኩት፡ውሸትንም፡የሚወዱና፡
የሚያደርጉ፡ዅሉ፡በውጭ፡አሉ።
16፤እኔ፡ኢየሱስ፡በአብያተ፡ክርስቲያናት፡ዘንድ፡ይህን፡እንዲመሰክርላችኹ፡መልአኬን፡ላክኹ።እኔ፡የዳዊት፡
ሥርና፡ዘር፡ነኝ፥የሚያበራም፡የንጋት፡ኮከብ፡ነኝ።
17፤መንፈሱና፡ሙሽራዪቱም፦ና፡ይላሉ።የሚሰማም፦ና፡ይበል።የተጠማም፡ይምጣ፥የወደደም፡
የሕይወትን፡ውሃ፡እንዲያው፡ይውሰድ።
18፤በዚህ፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡የትንቢት፡ቃል፡ለሚሰማ፡ዅሉ፡እኔ፡እመሰክራለኹ፤ማንም፡በዚህ፡ላይ፡
አንዳች፡ቢጨምር፡እግዚአብሔር፡በዚህ፡መጽሐፍ፡የተጻፉትን፡መቅሠፍቶች፡ይጨምርበታል፤
19፤ማንምም፡በዚህ፡በትንቢት፡መጽሐፍ፡ከተጻፉት፡ቃሎች፡አንዳች፡ቢያጐድል፥በዚህ፡መጽሐፍ፡ከተጻፉት፡
ከሕይወት፡ዛፍና፡ከቅድስቲቱ፡ከተማ፡እግዚአብሔር፡ዕድሉን፡ያጐድልበታል።
20፤ይህን፡የሚመሰክር፦አዎን፥በቶሎ፡እመጣለኹ፡ይላል።አሜን፥ጌታ፡ኢየሱስ፡ሆይ፥ና።
21፤የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡ከዅላችን፡ጋራ፡ይኹን፤አሜን፨
በእውነቱ በእግዚአብሔር ስም ያለምንም ሊንክ ለበጎ ፈቃድ ብቻ #ሼር እናድርግ፡፡
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
✞✞#መንፈሳችን_በፀሎት_እንዲበረታ_አበው_እንዲህ_ይመክሩናል✞✞
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
☘ 1. ‹‹ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ፣ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከሆነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል….ህይወትም የለውም›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
☘ 2. ‹‹ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ
☘ 3. ‹‹ጸሎት አእምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው ›› የሶሪያው ማር ይስሐቅ
☘ 4. ‹‹ጸሎት ጸጋን ይጠብቃል፣ቁጣንም ያሸንፋል…ትዕቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል››
የሶሪያው ማር ኤፍሬም
☘ 5. ‹‹የመንፈስ ፍሬዎችን ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
☘ 6. ‹‹ጸሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግበት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
☘ 7. ‹‹በጸሎት ግዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርክ አይደለምን??እንዴት ያለ መብት ነው!!!››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
☘ 8. ‹‹ጸሎትን ለማድረግ አታቅማማ፣ሥጋ ከመብል(ከምግብ) በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች››
አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ
☘ 9. ‹‹ያለ ጸሎት የምናደርገው ወይም የምንናገረው ነገር መጨረሻው ውደቀት ነው፡፡ፍጻሜው ኃጢአት ወይም ጉዳት ነው፡፡በማናውቀው ምስጢራዊ በሆነ መልኩ ሲጎዳን እንመለከተዋለን››
አባ አጋቶን
☘ 10. ‹‹ሰው እራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካልጸለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም›› አባ አጋቶን
4 374
#በከንቱ_እንዳንደክም_መጾም_እንደሚገባን_እንጹም
https://telegram.me/EOTC2921
✔በመጾም እየደከምን ሳለ የጾም አክሊልን ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበርና፤ ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የኼደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነውና (ሉቃ.18፡12)፡፡ ቀራጩ ደግሞ በአንጻሩ አልጾመም ነበር፤ ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው፡፡ ይህም የኾነበት ምክንያት [ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ በመፃዒ ሕይወቱም ጾም አላሻውም ለማለት ሳይኾን ከተአምኖ ኃጣውእ ጋር] ሌሎች ግብራት ካልተከተሏት በቀር ጾም ረብ ጥቅም እንደሌላት [እና ትሕትና የጾም አጣማጅ መኾኑን/ የምትሠምረው ከትሕትና ጋር መኾኑን] እንድታውቅ ነው፡፡
✔የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል (ዮና.3፡10)፡፡ እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም (ኢሳ.58፡3-7፣ 1ኛ ቆሮ.9፡26)፡፡ ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለባቸው ለማያውቁ ሰዎች የጾም ጉዳቱ ትልቅ ነውና በጥርጣሬ እንዳንኼድ፣ እንዲሁ አየርን እንዳንደልቅ፣ እንዲሁ ከጨለማ ጋር እንዳንጋደል፥ ይህን የምናከናውንባቸውን ሕጎች ልንማር ያስፈልገናል፡፡
✔ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
4 374
ማቸዋል፡፡
♥️ ❖ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ስለሚደርስባቸው ዘላለማዊ ምክነት በመዝ 128፥5-8 ላይ፦ "ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ፤ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ፤ በሰገነት ላይ እንደበቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ ለሚያጭደው እጁን፤ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይመላ ይኹኑ፤ በመንገድም የሚያልፉ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም" በማለት እንደተናገረ ጽዮን የተባለች የድንግል ማርያም አማላጅነት የሚቀዋወሙ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መናፍቃን እንደ ሜልኮል ከእግዚአብሔር ጸጋ የራቁ ናቸው፡፡
♥️❖ ከሊቃውንትም አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው:-
"እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦት ሕግ ከመ ዘፈነ
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቊርባነ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ"
✍️ (አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት ሜልኮል እስከናቀችው ድረስ በእግዚአብሔር የሕግ ታቦት ፊት እንዳመሰገነ፤ ድንግል ሆይ እኔም በሥዕልሽ ፊት እዘምራለኍ፤ ድንቅ ታምርሽንና የቀረበ መንፈሳዊ ምስጋናሽን የሚንቅ በመላእክትና በሰው አንደበት የተረገመ ይኹን) በማለት አስተምረዋል፡፡
🙏የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፡፡🙏
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#የኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_ምስጢርና_የአምላክ_እናት
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
✍️በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
♥️❖ ፈጣሪያችን ክርስቶስን የወለደችልን ቅድስት ድንግል ማርያም በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ጥበብና ማስተዋልን በተቀበለ በባስልኤል እጅ በተሠራችው በቃል ኪዳን ታቦት ትመሰላለች (ዘጸ ፳፭፥፱-፳፤ ፴፯፥፩-፲፭)፡፡
♥️❖ በመጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፪ ቊጥር ፲፪ትን እንደምናነበው፤ ታቦተ ጽዮንን ያገለግሉ የነበሩት የካህኑ የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በሠሩት ታላቅ ኀጢአት ምክንያት እግዚአብሔር አዝኖባቸው የክብሩ መገለጫ የኾነችው ታቦት በፍልስጤማውያን እጅ እንድትማረክ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቤንኤዘር ወደ አዛጦን በመውሰድ በድፍረት ከዳጎን አጠገብ አኖሯት፡፡
❖♥️ ነገር ግን ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ወድቆ ተገኘ፤ እነሱም እንደገና ዳጎንን ወደ ስፍራው መልሰው ኼዱ፤ በነጋታው ለማየት ሲመጡ የዳጎን እጅ እግሩ ተቆራርጠው ደረቱ ለብቻው ወድቆ ተገኘ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይኽነን ታሪክ ይዞ "የእግዚአብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው?" (፪ቆሮ ፮፥፲፮) በማለት የታቦትን ክብር አስተምሮበታል፡፡
♥️❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅም በሰቈቃወ ድንግል መጽሐፉ ላይ የአምላክ ማደሪያ የኾነችው ታቦት ወደ ፍልስጤም ሀገር ኼዳ ዳጎንን ሰባብራ እንዳጠፋች ኹሉ፤ አማናዊት የጌታ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን ይዛ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ኹሉ እየተሰባበሩ መውደቃቸውን እንዲኽ በማለት ገልጿል፤-
"ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ
ወድቁ አማልክተ ግብጽ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ
ወተኀፍሩ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ"
(ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የኼደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦት ታቦተ ጽዮን፤ የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፤ በዚች ታቦት የተመሰለች ድንግል ማርያምም ኹሉን ማድረግ ከሚችል ከልጇ ጋር ግብጽ ወደሚባል አገር በኼደች ጊዜ፤የሐሰተኛ ሰይጣን ዘፋኖች የኾኑ የግብጽ ጣዖታት ፈረሱ፤ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ኹሉ ዐፈሩ) በማለት አነጻጽሯል፡፡
♥️❖ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ስለሠሩት ታላቅ የድፍረት ኀጢአት እግዚአብሔር ቀጣቸው ብዙዎቹ ሞቱ፤ ያልሞቱትም በእባጭ ተመቱ፤ የአይጥ መንጋም ምድራቸውን አጠፋባቸው፤ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራው በምን እንስደደው? ብለው በመማከር፤ የሚያጠቡ ቀንበር ያልተጫነባቸው ኹለት ላሞችን በመውሰድ፤ በዐዲስ ሠረገላ ጠምደው እንቦሶቻቸውን (ጥጆቻቸውን) ከቤት ዘግተው በማስቀረት፤ ታቦተ ጽዮንን እጅ መንሻውን በሠረገላው ላይ ጫኑ፤ ያን ጊዜ እነዚኽ ላሞች ጥጆቻቸውን ሳይናፍቁ ወደቀኝ ወደግራ ሳይሉ እምቧ እያሉ ወደ ቤተ ሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ገሠገሡ::
♥️❖ የመልክአ ማርያም ደራሲ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችውን የኻያ መንፈቅ ማለት ዐሥሩ ቃላት የተጻፉባቸው ጽላት የተቀመጡባትን የእግዚአብሔርን ታቦት ጊደሮቹ ከልጆቻቸው ይልቅ በማስበለጥና በመውደድ ይዘዋት ወደፊት እንደነጎዱ፤ እሱም የልዑል ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር በድርሰቱ ላይ:-
"ማርያም ጽዮን ታቦት ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ
ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ"
(የኻያ እኩሌታ የሚኾን የእውነት ቃል ማደሪያ ጽዮን ማርያም ሆይ፤ ጊደሮች ከጥጆቻቸው ይልቅ አንቺን እንደአፈቀሩ፤ ወድጄሻለኹና ከዛሬ ዠምሮ ፈጽሞ ውደጅኝ) በማለት ገልጦታል፡፡
♥️❖ ይኽቺም የእግዚአብሔር ታቦት በቤተ ዐሚናዳብ ኻያ ዓመት ተቀምጣለች፤ ከዚያም የሳኦል ዘመን ዐልፎ የእግዚአብሔር ወዳጅ ዳዊት በነገሠ ጊዜ በዐዲስ ሠረገላ አድርገው ከቤተ ዐሚናዳብ አውጥተው በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በነጋሪት፣ በጸናጽል እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይዘዋት ሲመጡ፤ የእግዚአብሔርን ታቦት ኦዛ በድፍረት በመያዙ እግዚአብሔር ቀሥፎት ወዲያውኑ በታቦቷ አጠገብ ሕይወቱ አልፏል።
♥️❖ ያን ጊዜ ነቢዩ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ያደረገችውን ተአምራት ተመልክቶ፤ እግዚአብሔር በእርሷ እንዳደረ በማመን በፍርሃት ተውጦ "የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?" በማለት ለታቦቷ ያለውን ታላቅ ክብር ገልጧል (፪ ሳሙ ፮፥፮-፲)።
♥️❖ በዘመነ ሐዲስም በተመሳሳይ መልኩ ጌታን በማሕፀኗ የተሸከመች የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ አማናዊት ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ኤልሳቤጥ ልክ እንደ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ መልቶባት፤ የጌታ ታቦት (ማደሪያው) መኾኗን ተረድታ፤ ድምፅዋን አሰምታ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል?" በማለት ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላትን ታላቅ አክብሮት እንደ ዳዊት ገልጣለች (ሉቃ ፩፥፵፫-፵፮)፡፡
♥️❖ ከዚያም ዳዊት ይኽነን ታላቅ ቃል ከተናገረ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት በአቢዳራ ቤት ለሦስት ወር ያኽል እንደተቀመጠች (፪ ሳሙ ፮፥፲)፤ በተመሳሳይ መልኩ የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያምም በካህኑ በዘካርያስ ቤት ለሦስት ወር ተቀምጣለች (ሉቃ ፩፥፶፮)፡፡
♥️❖ ኦዛ ተቀሥፎ ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቢዳራ ቤት ገብታ ቤቱ ለሦስት ወር በበረከት እንደተመላ ኹሉ፤ በተመሳሳይ መልኩ ዘካርያስም የመልአኩን ቃል ባለመቀበሉ ከተረገመ በኋላ (ሉቃ ፩፥፳)፤ እውነተኛዪቱ የአምላክ ታቦት ድንግል ማርያም ቤቱ ለሦስት ወር ተቀምጣለች፡፡
♥️❖ እግዚአብሔር በታቦቷ ምክንያት የአቢዳራን ቤት እንደባረከ ኹሉ የዘካርያስንም ቤት በእመቤታችን ምክንያት የባረከው መኾኑን ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ በመጽሐፉ ሲገልጽ ‹‹ድንግል በምስጢር የተመላ ታቦትን ኾና ትኖራለች፣ የካህናት ወገኖችም ደስ ይላቸዋል፣ ያከብሯታልም›› በማለት ታቦትነቷን አጒልቶ አስተምሯል፡፡
♥️❖ በተጨማሪም የእግዚአብሔር ታቦት ከቤተ አቢዳራ ወደ ዳዊት ከተማ ስትገባ፤ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ከደስታው ብዛት የተነሣ የጌታ የክብሩ መገለጫ በኾነችው በታቦቷ ፊት እየዘለለ እንዳመሰገነ ኹሉ (፪ሳሙ ፭፥፲፪-፲፭)፤ አካላዊ ቃልን በማሕፀኗ የተሸከመች የአምላክ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ታላቁ ነቢይ መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማሕፀን ኾኖ ከደስታው ብዛት የተነሣ እየዘለለ አመስግኗል (ሉቃ ፩፥፵፩-፵፭)፡፡
♥️❖ ዳግመኛም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በደስታ ሲያመሰግን አይታ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ብትንቀው እግዚአብሔር ተቈጥቷት በሕይወቷ ዘመን ኹሉ የልጅ ጸጋ እንዳታገኝ በምክነት ቀጥቷታል (፪ሳሙ ፮፥፳-፳፫)፡፡
♥️❖ ይኸውም ማደሪያው የኾነች ታቦቷን በድፍረት ሊነካት የሞከረውን ኦዛን የቀሠፈ፤ ዳግመኛ የጌትነቱ መገለጫ በኾነች በታቦቷ ፊት ያመሰገነ ዳዊትን የናቀች ሜልኮልን በምክነት የቀጣ አምላክ፤ ዛሬም ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን፤ የድንግልና ጡቶቿን የመገበችውን፤ በጀርባዋ ያዘለችውና በደረቷ የታቀፈችውን ቅድስት እናቱን በድፍረት የሚነቅፉ፤ ለዚኽ ድፍረታቸው ንስሓ ድፍረታቸው ንስሓ ካልገቡ የዘላለም ቅጣትና፤ በዚኽ ዓለምም ከድንግል ማርያም አማላጅነት የሚገኘውን ታላቅ በረከት በማጣት እንደ ሜልኮል የበረከትና የጸጋ ምክነት ያጋጥ
