የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
前往频道在 Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
显示更多4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
4 374
#የቅዱሱ_ኪዳን_ቅርስ_ወይም_ቅዱሱ_ጽዋ
https://telegram.me/EOTC2921
✔✞ አባቶቻችን እንደተናገሩንና በድርሳነ ዑራኤልም እንደተፃፈው ጌታችንና መድኃኒታችን በዕለተ አርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ ከሰውነቱ የፈሰሰውን ደም በብርሃን ጽዋ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ተቀበለው፡፡ ደሙንም በመላው ዓለም ረጨው፡፡ የደሙ ንጣቢ ያረፈበት ቦታ ሁሉ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ማረፊያ፣ የቅዱስ ቁርባን መፈፀሚያ እንዲሁም ታላቅ ቃል ኪዳን ለዓለም ተሰጠ፡፡
✔✞ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ክቡር ደሙን በዐራቱም ማዕዘናት ከረጨ በኃላ ጽዋውን በመድኃኔዓለም ፈቃድ በቅድስ አገር ኢትዮጵያ መንዝ ውስጥ እመጓ ቆላ አምጥቶ ቀበረው፡፡
#መንዝ ማለት ነዝሃ ከሚለው ግእዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ይኸውም መርጨት ማለት ነው፡፡ የክርስቶስ ደሙ የተረጨበት ጽዋ ማረፊያ ስለሆነ ነው፡፡
#እመጓ ማለት እመ እጓል ከሚለው የግእዝ ሐረግ አጥሮ የተገኘ ቃል ነው፡፡ ይህም የልጅ እናት ማለት ነው፡፡
✔✞ የቅዱሱ ኪዳን ቅርስ /የቅዱሱ ጽዋ/ ጠባቂዎች፦ ለዚህ ቃል ኪዳን የታመኑና የተገቡ በመሆናቸው የነፍሳቸውን ጽድቅ ብቻ ሳይሆን እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ የከበረ ስጋቸው እንዳይበሰብስ ዐፅማቸው እንዳይፈርስ በመድኃኔዓለም ቃል የተገባላቸው ናቸው፡፡
✔✞ የአርማትያሱ ዮሴፍ ይህን ክቡር ጽዋ ወደ ቤቱ ወሰደው ከዚያም ወደ አርማትያስ ኬብሮን ሸሸ፡፡
ከዚያም ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ወደ ኬብሮን ተጓዘ ከዛም ዮሴፍ ወደ ሶርያ ተሰዶ ስለነበር ከሶሪያ ከዮሴፍ ተቀብሎ ወደ አክሱም ፅዮን አመጣው፡፡
የዚህ ጃንደረባ ታሪክ በጌምድር እንዳቤት ከግሼና ተክለሃይማኖት ደብር ይገኛል፡፡
✔✞ ቅዱሱን ጽዋ ለመመልከት የታደለ ሰው ታሞም ቢሆና ይድናል፡፡ በዛች ሳምንት አይሞትምና የቻለውን ያክል ዘመን ጽዋዋን ቢመለከታት የፊቱ ጸዳል ሳይቀር እንደልጅነቱ እንደለመለመ ይኖራል፡፡ ድንጋይ የተባለው ቅዱሱ ጽዋ የሰውን ልጅ አጥንትና ሥጋ ከመስበስ ታደጎ ለምለም ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፦ ከእመጓ መጽሐፍ
https://telegram.me/EOTC2921
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
4 374
🌾🕊✞ #ሀይልን_በሚሰጠኝ ✞🕊🌾
ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፣ (2)
መከራ ቢገጥመኝ ለበጎ ነው ብዬ አልፋለሁ፣
ፈተና ቢገጥመኝ ለበጎ ነው ብዬ አልፋለሁ።
t.me/EOTC2921
በሰንሰለት አስረው በወህኒ ቢጥሉን፣
መከራን አብዝተው እጅግ ቢያስጨንቁኝ፣
ለበጎነው ብዬ ተስፋ አድርጌሀለሁ፣
ይሁን አንተ ያልከው እገዛልሀለሁ።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
በመከራው ፅናት ጉልበቴ ደከመ፣
ትካዜ ከቦኛል ተስፋዬም ጨለመ፣
ነገር ቢሆን ባይሆን አንተን እንዳከብር፣
አድለኝ በፀጋ ጌታዬ ያንተን ፍቅር።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ከሀገር ወጥቼ በዱር መሰደዴ፣
ከባዕዳን ሀገር እርቄ መሄዴ፣
ለበጎ ነውና መቼ ይከፋኛል፣
ፈፅሞ እንዳልጠፋ ክንድህ ይይዘኛል።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ትላትናም ዛሬም አንተ ያው አንተ ነህ፣
ፍቅርህ አይቀየር ወረትም የለብህ፣
ስምህን መጥራቴ ሞገስ ሆኖልኛል፣
ጠላቴ ቢፎክር መች ያሸንፈኛል።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ከሀገር ወጥቼ በዱር መሰደዴ፣
ከባዕዳን ሀገር እርቄ መሄዴ፣
ለበጎ ነውና መቼ ይከፋኛል፣
ፈፅሞ እንዳልጠፋ ክንድህ ይይዘኛል።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
4 374
#ስምህ_በሁሉ_ተመሰገነ
ስምህ በሁሉ ተመሰገነ፣
ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ፣
አንተን ማወደስ ያስደስተናል፣
ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል።
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
አምላክ ተመስገን በሰማያት፣
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት፣
ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ፣
አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ፡፡ /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
በምግብ እጦት ብንሰቃይም፣
ማኅሌትህን አናቋርጥም፣
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም፣
እንዘምራለን ለአምላኝችን ስም። /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
ሰማዩ ዝናብ ደመና ሲያጣ፣
ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም፣
ቸርነትህን እንጠብቃለን፣
ከአንተ ደጅ አምላክ የት እንሄዳለን፣
ቸርነትህን እንጠብቃለን፣
ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን። /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
አምላክ ተመስገን በሰማያት፣
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት፣
ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ፣
አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ፡፡ /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
4 374
🌾🕊✞ #እውነተኛው_ሰላም ✞🕊🌾
እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(2)
አርዳኝ አልናወፅ እለምንሃለሁ(2)
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
ሀጢያቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል፣
ካንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል፣
ወዳንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለሁ፣
እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ለቅዳሴው ጸሎት ዘውትር እንዳልተጋሁ፣
ባደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ፣
ተሰነካክዬ ወድቄያለሁና፣
እርዳኝ አማኑኤል በሐይማኖት ልፅና።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
አይኔ እንባን ያፍስ ላልቅስ ስለሀጥያቴ፣
የንስሃ ትሁን ቁሪዋ ህይወቴ፣
በመዳኔ ሰዓት በዛሬዋ ዕለት፣
ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ካንተ ፊት።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ጌታ ሆይ ፀፀቴን እንባዬን ተቀበል፣
አባትሽ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል፣
ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መተህብኝ፣
በርህን በመዝጋት ከደጅ አታስቀረኝ።
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
4 374
#ዝሙት_የስጋና_የነፍስ_በሽታ_ነው!!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
☞አሁን ባለንበት ዘመን በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት ነው። የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው ። ቅዱስ ጳውሎስ" ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን" ( 1ኛ ቆሮ 14፥40) እንዳለው ማንኛው ሰው ተፈጥራዊ ስሜት ይንሮው እንጂ እንደ እንስሳ ሳይሆን በስርዓት መሄድ ይኖርበታል ። አንድ ሰው በሂወቱ
ሃላፊነት ካልወሰደ በስተቀር ማንም ሃላፊነት ሊወስድለት አይችልም።
ወንዱ ይሁን ሴቷ የእግዚአብሔር ሕግ ከማስቀደም ይልቅ ፋሽን እየተባለ ወንዱ
በየቀኑ ሴቶችን እንደ ልብስ እየቀያየረ ፣ ሴቷም በየቀኑ ወንዶች እንደ ልብስ
እየቀያየረች ወደ ሞት ይነዳሉ። ይህ የዝሙት መንፈስ የተጠናወተበት ሰው
በስጋው ይሁን በነፍሱ የረከሰና የድያብሎስ መኖርያ ይሆናል።
አላስተዋልም እንጂ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ሥጋውን ቆርሶ ደሙን
አፍስሶ በዋጋ የገዛን በመሆናችን በራሳችን ላይ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የማድረግ ስልጣን የለንም። ሰለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፡፡(1ቆሮ 3፥16)
☞ታድያ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ ከተባልን የእግዚአብሔር መንፈስ
መኖርያ እንሆን ዘንድ ከዝሙት መራቅ አለብን። አለበለዚያ ንስሐ ሳንገባ
በዝሙት ተጠምደን የምንኖር ከሆንን ግን ነፍሳችን ከእግዚአብሔር ፀጋ ተራቁታ ወደ ሲኦል ትገባለች። ዝሙት የነፍስና የስጋ በሽታ መሆኑን የአምላክ ቃል እንዲህ ብሎ ያስተምረናል፦
☞ " ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን
ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ፡፡ ( 1ኛ ቆሮ 3:17)
#መፅሐፍ_ቅዱስ_ስለ_ዝሙት_እንዲ_ይለናል፦
☞ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል "( ማቴ 5፥32)።
☞ " ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት
መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና" ( ማቴ 15፥19)።
☞ " ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ
ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ
ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና
ይስጣችሁ "( ሐዋ.ሥራ 15፥28-29)።
☞ " በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥
በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ( ሮሜ 13፥13)።
☞ " በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት
ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና (1ኛ ቆሮ 5፥1)።
☞ " መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው " ( 1ኛ ቆሮ 6:13)።
☞ " ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤
ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል" ( 1ኛ ቆሮ 6:18)።
#ታድያ_ምን_እናድርግ????
" እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ " (ራእ.ዮሐ 2፥10)። ይህ የህይወት አክሊል የሚገኘው በፆም ፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ ንስሐ ገብተን በቅዱስ ቁርባን መኖር፣ አስራት በኩራት በማውጣት ስንኖር ነው። ቅዱስ አምላካችን በማቴ 6፥33 ላይ " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" እንዳለው በምግባር በሃይማኖት ፀንተን ስንኖር የፈለግነው እንደሚሰጠን በተስፋው ቃል እንኖራለን።
☞እህቴ ሆይ ከላይ በማቴ 6:33 የተጻፈውን ስትፈፅሚ አምላካችን ሌላው
ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት ለመራቅ፣ ለመተጋገዝና ለመረዳዳት፣ ዘር
ለመተካት በአጠቃላይ ለትዳር የሚሆንሽ ወንድ ልጅ ላንቺ ይሰጥሻል።
☞ወንድሜ ሆይ ከላይ በማቴ 6፥33 ላይ የተጻፈውን ስተፈፅም አምላካችን ሌላው
ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት እንድትርቅ፣ የምትረዳህና ዘር ለመተካት
በአጠቃላይ ለትዳር የምትሆንህ ሴት ልጅ ላንተ ይሰጠሃል።
🙏ንስሐ ገብተን የአምላካችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን እንቀበል ዘንድ
አምላካችን ይፍቀድልን🙏(ዮሐ 6፥53-56)!!!
•✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዘላለሙ አሜን ✞•
4 374
✅ድንግልናን ማጣት የሚያስከትለው ችግር
🔸በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጸው #ከጋብቻ_ውጪ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት #ዝሙት ነውና በነፍሱ ይቀጣበታል፡፡
🔸በባልና ሚስት በኩል ደስታን ፣ #መተማመንን ፣ ፍቅርን ይቀንሳል፡፡
🔸#አለመታመን ፣ #አለመታገስ እና #አለመፅናትን ያስከትላል ፤ መንፈሳዊ ፀጋዎችን ያሳጣል፡፡
🔸#የጋብቻ_መዘግየትን ያመጣል፡፡ ጓጉታችሁ ወደጋብቻ የምትገቡበት ምክንያት አይኖራችሁም፡፡ ከጋብቻ በፊት ስሜቱን መቆጣጠር ያልቻለ ፣ መታቀብም ያልቻለ ከጋብቻም በኋላ አይታቀብም፡፡
🔸ከጋብቻ በፊት ግንኙት መፈፀም እንደአምኖንና ትዕማር ታሪክም ሊፈጠር ይችላል፡፡ አምኖን በትዕማር የዓይን ፍቅር ተማረከ፡፡ ከዛ ክፉ መንገድ ተጠቅሞ አስነወራት፡፡ ልክ ሩካቤ (sex ) ከፈፀሙ በኋላ ግን #ያቺ_በፍቅር_የታመመላት_ትዕማር #ለዓይኑ_አስጠላችው፡፡ “ ይህችን ሴት ዓይኗን ማየት አልፈልግም : አስወጡልኝ::“ አለ፡፡ ተመለከትክ ወንድሜ ከሩካቤ በኋላ እንዲህ መጠላላትም አለ፡፡ #ኃጢአት_የምታስጎመጀው እስክንፈጽማት ነው፣ ከፈጸምናት በኋላ ግን #እንደሬት_ትመረናለች፡፡
🔸ያጡትን ሲያስቡ መፀፀትንና #ሰላም_ማጣትን ይፈጥራል፡፡
🔸ለተለያዩ በሽታዎች ፣ ላልታሰበ እርግዝና እና ውርጃ ያጋልጣል፡፡
🔸ለከፋ #የዝሙት_ተግባር ይገፋፋል፡፡
✅በአጠቃላይ #ስሜታችንን_ለመግለጽ ፣ #ስለምንተማመን_ብናደርግ_ችግር_የለውም ፣ #ፍቅራችን_እንዲፀና ፣ #ለመጠናናት… ወዘተ በሚሉ ምክንያቶች ድንግልናችንን ከትዳር በፊት ማጣት የለብንም፡፡ ስሜት_መግለጫ ሌሎች ብዙ መልካም መንገዶች አሉ፤ ከተማመንንም እሰየው ፣ ከትዳር በኋላ እንደርስበታለን፡፡ ሩካቤ የፍቅር ስሜታችንን ቢቀንስ እንጂ አይጨምርም፡፡ ለመጠናናትም የሚያስፈልገው ሩካቤ ሳይሆን የእጮኝነት ግዜ ማሳለፍ ነው፡፡
✅ወንድሞቼና እኅቶቼ #ፍቅራችሁ_እንዲበረታ ፣ #ትዳራችሁ_እንዲሰምር ፣ በዘመናችን እንደምናየው 80ቸውን በወሩ እንደሚቀዱት እንዳትሆኑ ፣ ከትዳር አጋራችሁም #እምነትና #እርካታ እንድታገኙ በድንግልና ኑሩ፡፡ ከእጮኛችሁም ጋር ከትዳራችሁ በፊት ሩካቤ ከማድረግ ተከልከሉ፡፡ “ መልካሙን የድንግልና ሥጦታዬን በጋብቻ ግዜ እሰጥሀለሁ/ሻለሁ/” ተባባሉ፡፡ ስለዚህ ድንግልናችንን እስከጋብቻ መጠበቅ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለምና እንጠብቅ ፤ እንታገስ፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች #ድንግልናችንን_ያጣን ደግሞ ያለፈው አልፏል ፤ መመለስ አንችልም፡፡ ከአሁን በኋላ ላለው ግን #ታቅቦ መኖር ይገባል፡፡ “አንዴ አጥቼዋለሁና…” ብለን ካሰብን ግን ከማጣት የከፉ ዓዘቅቶች ውስጥ ያስገባናል፡፡ ድንግል ለሆናችሁ #ለተክሊል_ጋብቻ ፣ ድንግል ላልሆናችሁ #ለቁርባን_ጋብቻ ያብቃችሁ ፤ አሜን፡፡
🌾✞ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ✞🌾
4 374
#ምስጢሬን_ላካፍላችሁ!!!
#ጥያቄ፡- በቤተ-ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለጋብቻ የሚፈቀደው አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ነው፡፡ እና አንድ ልጅና አንዲት ልጅ ከልብ ተዋድደው ሊጋቡ ነው፡፡ ከመዋደዳቸው የተነሳ ሳይተያዩ ካደሩ ምግብ አይቀምሱም፡፡ ሥራ መሥራት አይችሉም፡፡ ብቻ ስሜት የሚባለው ነገር በጣም ገኖባቸዋል፡፡ በቤተ-ክርስቲያችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል? ነው ወይስ የራሱ እስከሆነች የራሷ እስከሆነ ድረስ ምንም ቢያደርጉ ኃጢአት አይሆንም? ከትዳር በፊት #መሣሣም ( የከንፈር ወዳጅ / kiss ) ወይም ሌሎች የስሜት መግለጫዎችን መፈፀም ይቻላል? ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚዋደዱ ከትዳር በፊት #ሩካቤ ( #sex ) መፈፀምስ ምን ችግር አለው?
#መልስ፡- ውድ ጠያቂያችን ከሁሉም አስቀድመን የድንግልናን እና የጋብቻን ትርጉም መረዳት ያስፈልገናል፡፡ ድንግልና የሚለው ቃል ተደንገለ፣ ተጠበቀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ሰው ድንግል ሲባል ወንድ የማታውቅ (sex ፈጽማ የማታውቅ) ልጃገረድ ወይም ሴት የማያውቅ (sex ፈጽሞ የማያውቅ ) ወንድ ማለት ነው፡፡ ሰው ከሩካቤ ሥጋ ( sex ) የሚጠበቀው እስከጋብቻው ወይም እስከሕይወቱ ፍፃሜ ነው፡፡ እግዚአብሔር ጋብቻ ክቡር መሆኑን ያስተማረን ድንግልናን ሰጥቶን ነው፡፡ ስለዚህ #ድንግልና ማለት እስከጋብቻ ድረስ በጥንቃቄ የሚያዝ #የክብር_ዕቃ ፤ #በዕለተ_ጋብቻ ለትዳር አጋራችን የምናበረክተው #ውድ_ሥጦታ ማለት ነው፡፡
በመሰረቱ #የሩካቤ_ስሜት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ አብዛኛው ሰው በዚህ ስሜት ይፈተናል፣ ለምን ይህ ስሜት ተሰማህ ተብሎም አይወቀስም፤ ነገር ግን የሩካቤ አፈፃፀም #በሥርዓት እንዲሆን #ክርስትናችን ያስገድደናል፡፡ ይህም ማለት እስከጋብቻ ድረስ በድንግልና ቆይተው ከዚያ ከጋብቻ በኋላ ሩካቤ እንዲፈጽሙ ነው፡፡ በዚህ ግዜ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል ይፈጸማል፡፡ “ #ጋብቻ_ክቡር ነው ፤ #መኝታውም_ንጹህ ነው፡፡” ዕብ 13፣4፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ጋብቻን የሰራበት አንዱ ምክንያት የሩካቤ ስሜት ስላለ እና ይህም ይፈፀምበት ዘንድ ነው፡፡
✝️✝️✝️
✅ከጋብቻ_በፊት የሚደረግ #መሳሳም እና #መተሻሸት ወይም ሌላ የስሜት መግለጫ
🔸ከጋብቻ በፊት የሚፈፀም መሳሳምና መተሻሸት ለግብረ ሥጋ ግንኙነት መንገድ ይከፍታል፡፡ ውድ ጠያቂያችን:- #እጅግ_ርቦህ እያለ #እጅግ_የጣፈጠ ምግብ ከፊት ለፊትህ ቢቀመጥ ከዚያ #የምግቡ_መዓዛ መጥቶ አፍንጫህን ጎብኘት ቢያደርገው ሆድህ እየጮኸ ዝም ትላለህ? መሳሳምም እንዲሁ ነው፡፡ ውስጥህ #የወጣትነት_ስሜት እየታገለህ ፣ ከፊት ለፊት ደግሞ #የፍቅረኛህ_መዓዛ እያወደህ ፣ #ከንፈርህን_ከከንፈሯ አጋጥመህ ከዚያ ምን የሚቀጥል ይመስልሃል? “ ለዛሬ ይበቃናል:: ” ትላላችሁ? “ ከጋብቻ በፊት sex አንፈጽምም አይደል!? መሳሳምና መተሻሸት ብቻ፡፡” ትላላችሁ? በፍጹም፡፡ ወደመሳሳምና ወደመተሻሸት ያደረሳችሁ የወጣትነት ስሜት ወደሩካቤ ይመራችኋል ፤ ምክንያቱም ያንን ጣፋጭ ምግብ አስብና ምራቅህን ላለመዋጥ ሞክር፡፡
🔸የተከበርክ ወንድማችን ፍቅራችሁን በመሳሳም ልትገልጹ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን #መሳሳም_እሳት_ላይ_ጋዝ_እንደማርከፍከፍ ነውና “ እውነት ይሄ መሳሳም ፍቅራችሁን ብቻ ገልጻችሁበት ታቆማላችሁ?” የሚለው ይታሰብበት፡፡ ዕለቱኑ ወደ sex ባያመራም መሳሳምን ከለመዳችሁ በኋላ ደግሞ ሰው ለውጥን ይፈልጋልና " የተሻለ የፍቅር መግለጫ" በማለት ወደሩካቤ ( sex ) ታመራላችሁ፡፡ መሳሳምን መቋቋም አቅቷችሁ እንደፈጸማችሁት ሁሉ sexንም የማትፈጽሙበት ምንም ዋስትና የላችሁም፡፡
🔸መዘንጋት የሌለብህ ግን የፍቅር መግለጫም ይሁን የአክብሮት መግለጫ #ሰላምታችን_ክብር_ያለው እንዲሆን #ቅዱስ_ጳውሎስ በመልእክቱ ይመክረናል:- “ ክብር ባላት ሰላምታ እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ፡፡” 2ኛ ቆሮ 13 ፤ 12፡፡ መሳሳም ዓለም ነገሩን አስረስቶ እጅግ ወደሚያስጠላ ፣ #ክብርም_ወደጎደለው_ድርጊት ያመራልና ይህ ይታሰብበት፡፡
🔸ለፍቅረኛ ፍቅርን ወይም ስሜትን ለመግለጽ ያለው #የተሻለ_አማራጭስ መሳሳም ወይም መተሻሸት ነው እንዴ? ፍቅረኛህን ስታገኛት #ሥጦታ ይዘህላት መሄድ ፣ ሁሌም #እንደምትወዳት መንገር ፣ በጨነቃት ወይም ባዘነች ግዜ #ከአጠገቧ_መሆን… እና የመሳሰሉት የፍቅር መግለጫዎች አሉ፡፡
#ታድያ በሰላም አገር ይሄን ሁሉ ፈተና በፈቃዳችሁ ከምትስቡ መሳሳሙ ቢቀርባችሁ አይሻልም! ደግሞስ የምትተማመኑ ከሆነ መሳሳሙ የት ይሄድባችኋል!
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ከትዳር በፊት “ሩካቤ መፈፀም በቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ እንዴት ይታያል?” የሚለውን እንመልከት፡፡ ለድንግልናችን ክብር የማንሰጠውና ድንግልናችንንም የማንጠብቅበት አንደኛው ምክንያት #የድንግልናን_ጥቅም_በአግባቡ_አለመረዳት ነውና የድንግልናን የነፍስና የሥጋ ጠቀሜታዎቹን በአጭሩ እንመልከታቸው፡፡
🔸ከእግዚአብሔር ዘንድ #የድንግላችንን_ዋጋ እናገኛለን፡፡
🔸በአግባብ_ለመኖር - በድንግልና መኖር ሕግና ሥርዓት እየፈፀሙ በአግባቡ ለመኖር ይጠቅማል፤ ድንግልናን ጠብቆ መኖር #ሕጋዊ_ሰው ሆኖ መኖርን ያለማምዳል፤
🔸ሳይባክኑ መኖር - በድንግልና የሚኖር ሰው አይባክንም፡፡ ወዲህና ወዲያ አይልም፤ ወንዱ የሴት ገላ ፍለጋ ጊዜውን አያባክንም፡፡ ሴቷም ያማረ ቁመና ያለው ወንድ ፍለጋ ጊዜዋን አታባክንም፡፡ #ሁሉም_በጊዜው እንደሚሆን አምነው መደረግ ያለበትን በትክክለኛው ጊዜ እየሰሩ ይኖራሉ እንጂ፡፡
🔸ድንግልናን መጠበቅ #በሃይማኖት_ያጸናል - ድንግልናን ለመጠበቅ የቆረጠ ሰው #ሃይማኖቱን_በመጠበቅና #ለፈጣሪው_ባለው_ፍቅር ፀንቶ ይኖራል፡፡ ድንግልናን መጠበቅ በራሱ ፅናትንና ትዕግስትን ይጠይቃል፡፡
🔸ድንግልናን ጠብቆ መኖር #ታማኝነትን_ያረጋግጣል - ምክንያቱም ድንግልና በሥርዓት ጠብቀን እንድንይዘው #በአደራ_እንደተሰጠን_የከበረ_ንብረት ነው፡፤ ባለአደራው ፈጣሪያችን በሚያስፈልግ ግዜና ሰዓት ለትዳር አጋራችን እንድንሰጠው ይጠበቅብናል፡፡
🔸ድንግልናን መጠበቅ #መጠንቀቅ ነው - በድንግልና የኖረ ከበሽታ ፣ ካልተፈለገ እርግዝና፣ ከፀፀት እና በአጠቃላይ ለወደፊት መንፈሳዊ ሆነ ስጋዊ ችግር ከሚፈጥሩ የኑሮ ጠንቆች ይጠበቃል፡፡
🔸ባል የሚስቱን ማኅተመ ድንግልና ሲያገኝ ደስ ይለዋል፤ ሚስትም ባሏ እሷ የመጀመርያው እንደሆነች ስታውቅ ትደሰታለች፡፡
- ድንግልናን ካጠፉ በኋላ የሚደረግ ጋብቻ አግብቶ የፈታ ሰው እንደሚፈፅመው እንደ ሁለተኛ ጋብቻ ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም የተጋቡ ሰዎች ብቻ ሊፈፅሙት የሚገባውን ሩካቤ-ሥጋ ከጋብቻ በፊት ፈፅሞ በመገኘቱ ነው፡፡
🔸ድንግልናን ጠብቆ መኖር #ጋብቻ_ሳይዘገይ በጊዜው እንዲፈፀም ይገፋፋል፡፡
- ማንኛውም ጤናማ ሰው የተቃራኒ ፆታ አቻውን የመሻት ዝንባሌ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ዝንባሌውን እና ድንግልናውን ጠብቆ መኖር የሚታረቅለት ሲያገባ ነው፡፡ እናም ድንግልናውን ጠብቆ እስከጋብቻ ለመቆየት ዓላማ ያለው ሰው በውስጡ ያለውን የፍትወት ግፊት ለማብረድ ሲል ሊያገባ ይችላል፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤ የጋብቻን ቀነ ቀጠሮ እንዲራዘም ከማድረጉም በላይ ለመለያየትም በር ከፋች ነው፡፡
••• #ይቀጥላል •••
4 374
🌾 ✞ #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ ✞ 🌾
#የካቲት_፪_ሰኞ_ይጀምራል ።
✔‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ
ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ
ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ
ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ
ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
✔በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው (ሉቃ.፲፩፥፴)፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናገረ (፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩)፡፡
✔ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ሆነ የቤተ
ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (፩ኛነገ.፲፯፥፲፱)፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል (ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪)፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ
‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ
እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡
እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡
ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ
መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ
እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም
ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ
ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት
ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን
ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና
በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ
መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል››
በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን
አስረድቶታል፡፡
✔ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ
አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል (ትንቢተ ዮናስ)፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
✔ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ
የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣
ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች
(አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ
ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ
በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡
✔ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡
ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ
እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር
በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው
ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡
የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ
ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን
‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ
ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች
ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም
የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም
ጾመን፣ ጸልየን ከኃጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል
እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡ ስለሆነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
✔ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
✍በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል
🌿🌾 ✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞ 🌾🌿
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌻✞ #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተክርስቲያን_ቴሌቭዥን ✞🌻
Channel Name: EOTC
Frequency: 12519 MHz
Symbol rate: 27500 KS/s
Polarity: Vertical(V)
Satellite: Eutelsat 8WB
FEC: 7/8
🌻✞ #የማህበረ_ቅዱሳን_ቴሌቭዥን ✞🌻
"የምናውቀውን እንናገራለን የአየነውን እንመሰክራለን"
Channel Name: EOTCMK
Frequency: 11555 MHz
Symbol rate: 27500 KS/s
Polarity: Vertical(V)
Satellite: Nilesat
FEC: 7/8
ይህ መረጃ ለሌሎች ክርስቲያን እህት ወንድሞቻችን እንዲዳረስ👉 #Share ያድርጉ፡፡
4 374
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•
•••✞•••✞•••✞•••
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)
•••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ
#አዝ•••
