የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
前往频道在 Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
显示更多4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
4 374
ማቸዋል፡፡
♥️ ❖ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ስለሚደርስባቸው ዘላለማዊ ምክነት በመዝ 128፥5-8 ላይ፦ "ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ፤ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ፤ በሰገነት ላይ እንደበቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ ለሚያጭደው እጁን፤ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይመላ ይኹኑ፤ በመንገድም የሚያልፉ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም" በማለት እንደተናገረ ጽዮን የተባለች የድንግል ማርያም አማላጅነት የሚቀዋወሙ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መናፍቃን እንደ ሜልኮል ከእግዚአብሔር ጸጋ የራቁ ናቸው፡፡
♥️❖ ከሊቃውንትም አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው:-
"እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦት ሕግ ከመ ዘፈነ
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቊርባነ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ"
✍️ (አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት ሜልኮል እስከናቀችው ድረስ በእግዚአብሔር የሕግ ታቦት ፊት እንዳመሰገነ፤ ድንግል ሆይ እኔም በሥዕልሽ ፊት እዘምራለኍ፤ ድንቅ ታምርሽንና የቀረበ መንፈሳዊ ምስጋናሽን የሚንቅ በመላእክትና በሰው አንደበት የተረገመ ይኹን) በማለት አስተምረዋል፡፡
🙏የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፡፡🙏
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#የኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_ምስጢርና_የአምላክ_እናት
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
✍️በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
♥️❖ ፈጣሪያችን ክርስቶስን የወለደችልን ቅድስት ድንግል ማርያም በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ጥበብና ማስተዋልን በተቀበለ በባስልኤል እጅ በተሠራችው በቃል ኪዳን ታቦት ትመሰላለች (ዘጸ ፳፭፥፱-፳፤ ፴፯፥፩-፲፭)፡፡
♥️❖ በመጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፪ ቊጥር ፲፪ትን እንደምናነበው፤ ታቦተ ጽዮንን ያገለግሉ የነበሩት የካህኑ የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በሠሩት ታላቅ ኀጢአት ምክንያት እግዚአብሔር አዝኖባቸው የክብሩ መገለጫ የኾነችው ታቦት በፍልስጤማውያን እጅ እንድትማረክ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቤንኤዘር ወደ አዛጦን በመውሰድ በድፍረት ከዳጎን አጠገብ አኖሯት፡፡
❖♥️ ነገር ግን ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ወድቆ ተገኘ፤ እነሱም እንደገና ዳጎንን ወደ ስፍራው መልሰው ኼዱ፤ በነጋታው ለማየት ሲመጡ የዳጎን እጅ እግሩ ተቆራርጠው ደረቱ ለብቻው ወድቆ ተገኘ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይኽነን ታሪክ ይዞ "የእግዚአብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው?" (፪ቆሮ ፮፥፲፮) በማለት የታቦትን ክብር አስተምሮበታል፡፡
♥️❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅም በሰቈቃወ ድንግል መጽሐፉ ላይ የአምላክ ማደሪያ የኾነችው ታቦት ወደ ፍልስጤም ሀገር ኼዳ ዳጎንን ሰባብራ እንዳጠፋች ኹሉ፤ አማናዊት የጌታ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን ይዛ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ የግብጽ ጣዖታት ኹሉ እየተሰባበሩ መውደቃቸውን እንዲኽ በማለት ገልጿል፤-
"ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ
ወድቁ አማልክተ ግብጽ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ
ወተኀፍሩ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ"
(ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የኼደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦት ታቦተ ጽዮን፤ የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፤ በዚች ታቦት የተመሰለች ድንግል ማርያምም ኹሉን ማድረግ ከሚችል ከልጇ ጋር ግብጽ ወደሚባል አገር በኼደች ጊዜ፤የሐሰተኛ ሰይጣን ዘፋኖች የኾኑ የግብጽ ጣዖታት ፈረሱ፤ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ኹሉ ዐፈሩ) በማለት አነጻጽሯል፡፡
♥️❖ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ስለሠሩት ታላቅ የድፍረት ኀጢአት እግዚአብሔር ቀጣቸው ብዙዎቹ ሞቱ፤ ያልሞቱትም በእባጭ ተመቱ፤ የአይጥ መንጋም ምድራቸውን አጠፋባቸው፤ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራው በምን እንስደደው? ብለው በመማከር፤ የሚያጠቡ ቀንበር ያልተጫነባቸው ኹለት ላሞችን በመውሰድ፤ በዐዲስ ሠረገላ ጠምደው እንቦሶቻቸውን (ጥጆቻቸውን) ከቤት ዘግተው በማስቀረት፤ ታቦተ ጽዮንን እጅ መንሻውን በሠረገላው ላይ ጫኑ፤ ያን ጊዜ እነዚኽ ላሞች ጥጆቻቸውን ሳይናፍቁ ወደቀኝ ወደግራ ሳይሉ እምቧ እያሉ ወደ ቤተ ሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ገሠገሡ::
♥️❖ የመልክአ ማርያም ደራሲ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችውን የኻያ መንፈቅ ማለት ዐሥሩ ቃላት የተጻፉባቸው ጽላት የተቀመጡባትን የእግዚአብሔርን ታቦት ጊደሮቹ ከልጆቻቸው ይልቅ በማስበለጥና በመውደድ ይዘዋት ወደፊት እንደነጎዱ፤ እሱም የልዑል ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር በድርሰቱ ላይ:-
"ማርያም ጽዮን ታቦት ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ
ዕጐላት እምዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ"
(የኻያ እኩሌታ የሚኾን የእውነት ቃል ማደሪያ ጽዮን ማርያም ሆይ፤ ጊደሮች ከጥጆቻቸው ይልቅ አንቺን እንደአፈቀሩ፤ ወድጄሻለኹና ከዛሬ ዠምሮ ፈጽሞ ውደጅኝ) በማለት ገልጦታል፡፡
♥️❖ ይኽቺም የእግዚአብሔር ታቦት በቤተ ዐሚናዳብ ኻያ ዓመት ተቀምጣለች፤ ከዚያም የሳኦል ዘመን ዐልፎ የእግዚአብሔር ወዳጅ ዳዊት በነገሠ ጊዜ በዐዲስ ሠረገላ አድርገው ከቤተ ዐሚናዳብ አውጥተው በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በነጋሪት፣ በጸናጽል እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይዘዋት ሲመጡ፤ የእግዚአብሔርን ታቦት ኦዛ በድፍረት በመያዙ እግዚአብሔር ቀሥፎት ወዲያውኑ በታቦቷ አጠገብ ሕይወቱ አልፏል።
♥️❖ ያን ጊዜ ነቢዩ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ያደረገችውን ተአምራት ተመልክቶ፤ እግዚአብሔር በእርሷ እንዳደረ በማመን በፍርሃት ተውጦ "የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?" በማለት ለታቦቷ ያለውን ታላቅ ክብር ገልጧል (፪ ሳሙ ፮፥፮-፲)።
♥️❖ በዘመነ ሐዲስም በተመሳሳይ መልኩ ጌታን በማሕፀኗ የተሸከመች የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ አማናዊት ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ኤልሳቤጥ ልክ እንደ ዳዊት መንፈስ ቅዱስ መልቶባት፤ የጌታ ታቦት (ማደሪያው) መኾኗን ተረድታ፤ ድምፅዋን አሰምታ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል?" በማለት ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላትን ታላቅ አክብሮት እንደ ዳዊት ገልጣለች (ሉቃ ፩፥፵፫-፵፮)፡፡
♥️❖ ከዚያም ዳዊት ይኽነን ታላቅ ቃል ከተናገረ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት በአቢዳራ ቤት ለሦስት ወር ያኽል እንደተቀመጠች (፪ ሳሙ ፮፥፲)፤ በተመሳሳይ መልኩ የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያምም በካህኑ በዘካርያስ ቤት ለሦስት ወር ተቀምጣለች (ሉቃ ፩፥፶፮)፡፡
♥️❖ ኦዛ ተቀሥፎ ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቢዳራ ቤት ገብታ ቤቱ ለሦስት ወር በበረከት እንደተመላ ኹሉ፤ በተመሳሳይ መልኩ ዘካርያስም የመልአኩን ቃል ባለመቀበሉ ከተረገመ በኋላ (ሉቃ ፩፥፳)፤ እውነተኛዪቱ የአምላክ ታቦት ድንግል ማርያም ቤቱ ለሦስት ወር ተቀምጣለች፡፡
♥️❖ እግዚአብሔር በታቦቷ ምክንያት የአቢዳራን ቤት እንደባረከ ኹሉ የዘካርያስንም ቤት በእመቤታችን ምክንያት የባረከው መኾኑን ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ በመጽሐፉ ሲገልጽ ‹‹ድንግል በምስጢር የተመላ ታቦትን ኾና ትኖራለች፣ የካህናት ወገኖችም ደስ ይላቸዋል፣ ያከብሯታልም›› በማለት ታቦትነቷን አጒልቶ አስተምሯል፡፡
♥️❖ በተጨማሪም የእግዚአብሔር ታቦት ከቤተ አቢዳራ ወደ ዳዊት ከተማ ስትገባ፤ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ከደስታው ብዛት የተነሣ የጌታ የክብሩ መገለጫ በኾነችው በታቦቷ ፊት እየዘለለ እንዳመሰገነ ኹሉ (፪ሳሙ ፭፥፲፪-፲፭)፤ አካላዊ ቃልን በማሕፀኗ የተሸከመች የአምላክ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኤልሳቤጥ ቤት በኼደች ጊዜ፤ ታላቁ ነቢይ መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማሕፀን ኾኖ ከደስታው ብዛት የተነሣ እየዘለለ አመስግኗል (ሉቃ ፩፥፵፩-፵፭)፡፡
♥️❖ ዳግመኛም ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በደስታ ሲያመሰግን አይታ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ብትንቀው እግዚአብሔር ተቈጥቷት በሕይወቷ ዘመን ኹሉ የልጅ ጸጋ እንዳታገኝ በምክነት ቀጥቷታል (፪ሳሙ ፮፥፳-፳፫)፡፡
♥️❖ ይኸውም ማደሪያው የኾነች ታቦቷን በድፍረት ሊነካት የሞከረውን ኦዛን የቀሠፈ፤ ዳግመኛ የጌትነቱ መገለጫ በኾነች በታቦቷ ፊት ያመሰገነ ዳዊትን የናቀች ሜልኮልን በምክነት የቀጣ አምላክ፤ ዛሬም ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን፤ የድንግልና ጡቶቿን የመገበችውን፤ በጀርባዋ ያዘለችውና በደረቷ የታቀፈችውን ቅድስት እናቱን በድፍረት የሚነቅፉ፤ ለዚኽ ድፍረታቸው ንስሓ ድፍረታቸው ንስሓ ካልገቡ የዘላለም ቅጣትና፤ በዚኽ ዓለምም ከድንግል ማርያም አማላጅነት የሚገኘውን ታላቅ በረከት በማጣት እንደ ሜልኮል የበረከትና የጸጋ ምክነት ያጋጥ
4 374
ለማሰብ
2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገ
ደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
4. ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
5. ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
6. ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
7. አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት
8. በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት
በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡ ይኽ ሲባል ግን በዓሉ የሚከበረው በአክሱም ጽዮን ማርያም ብቻ ነው ማለት ሳይሆን፤ ታቦተ እግዝእትነ ማርያም ባለችበት ቦታ ሁሉ መከበሩን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋርም የመመኪያችን ዘውድ፣ የመዳናችን ምክንያት፣ የንጽሕናችን መሠረት ስለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያልተነበየ ነቢይ፣ ያልሰበከ ሐዋርያ፣ ያልተቀኘ ባለቅኔ ከቶ የለም፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በቤዛነቱ ዓለምን አዳነ፣ ዳግመኛም በክበበ ትስብእት፣ በግርማ መለኮት ለፍርድ ይመለሳል ብንል ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በመሆኑ ያለ ወላዲተ አምላክ ምስጢረ ሥጋዌን፣ ነገረ ድኅነትን፣ ነገረ ምጽአትን ማሰብ ከቶ የማይቻል ነው፡፡
«ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን ክበቧት» እንዳለ ነቢዩ፤ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባትን የእስራኤል አምባና መጠጊያ የሆነችውን ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡
በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምስጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህቺ የቃል ኪዳን ታቦት በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች፣ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያ. 3÷14-17/፤ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያ 6÷1-21/፤ ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን ጣዖት የቆራረጠች /1ሳሙ 5÷1-5/፤ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ሳሙ 6÷6/፤ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/፣ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት/1ነገ 8÷1/፤ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለውን ረቂቅ እና ድንቅ ምስጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ ሦርያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም፤ «ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሔ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤ ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በው ስጥ በአፍአ በወርቅ የተለበጠ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኃጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም፤ «አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኃጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» /መኃ 4÷7/ ሲል ተናግሯል፡፡
ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡
ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ሆናለች፡፡ ይኽንንም ቅዱስ ኤፍሬም ሲያስረዳ፤ «ኮንኪ ታቦቶ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ ተሰዓተ አውርኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር፤ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» ብሎ ተቀኝቶላታል፡፡ ስለሆነም ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን የቸርነት በዓል እግዚአብሔርበፈቀደልን ቦታ ሆነን ስናከብር ከእኛ የሚጠበቀውን በጎ ነገር እያሰብን በተግባርም እየገለጥን ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ተሳታፊ እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡
የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እና ምልጃ አክሊልና ጉልላት በሆነው በእናታችን በወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ሁላችንንም ይማረን፡፡ አሜን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#ህዳር_፳፩__ታቦተ_ጽዮን
_ወደ_ኢትዮጵያ_የገባችበት
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
ኅዳር ፳፩ ለምን በድምቀት ይከበራል?
👉ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡ከአራት ሺሕ ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ዓመተ ዓለም (4327 ዓ.ዓ.) ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያህል እስራኤላውያንን በክህነት ያገለግል የነበረው ካህኑ ዔሊ ዕድሜው ሲገፋ ሁለት ልጆቹን ጠርቶ ምሉዕና ዱግ /ዋናና ምክትል/ አድርጎ ሾማቸው፡፡
በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ የተሾሙት ሁለቱ ወጣት ካህናት /አፍኒን እና ፊንሐስ/ ፈቃደ እግዚአብሔርን ተላልፈው ሦስት ታላላቅ በደሎችን ፈጸሙ፡፡ የመጀመሪያው በደል፤ በሙሴ ሥርዓት በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርታ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የምትጠፋ መብራት እንድትቀመጥ የተሠራ ሥርዓት ነበር፡፡ ሆኖም አገልግሎት ከሌለ ሲበራ ማደሩ ለምን ? ብለው መቅረዙን አነሡ፤ መብራቱንም አጠፉ፡፡ ሁለተኛ፣ ለራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ለመሥዋዕት እንዲሆን ከመጣው እንስሳ ታርዶ ስቡ ሳይጤስ፣ደሙ ሳይፈስ ሥጋውን እየመረጡ ተመገቡ፡፡ሦስተኛ ጸሎት እናደርሳለን ሥርዓተ አምልኮ፣ እንፈጽማለን ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጡ ከነበሩት እስራኤላውያን ቆነጃጅት ጋራ በዝሙት ወደቁ፡፡ አባታቸው ካህኑ ዔሊም የልጆቹን በደል እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ቸል በማለቱ እግዚአብሔርአዘነ፡፡ በዚህም ምክንያት ፍልስጥኤማውያንን አስነሥቶ በጦርነት ቀጣቸው፡፡
ዕብራውያን በጦርነት ውሎ ያለልማዳቸው በአሕዛብ ተሸነፉ፡፡ ሕዝበ እስራኤልም ግራ ቢገባቸው «ድል የተነሣነው ታቦተ ጽዮንን ይዘን ባለመዝመታችን ነው» ብለው አፍኒን እና ፊንሐስ ጽላቱን እንዲሸከሙ አድርገው ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ምሽግ ገሠገሡ፡፡ ሆኖም ያሰቡት ሳይሳካ ታቦተ ጽዮን ተማረከች፣ አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፤ ዕብራውያንም በጦርነቱ ድል ተደረጉ፡፡ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ዳጎን ከተባለው ጣዖታቸው ላይ አስቀመጧት፡፡ በማግስቱ ሲመለሱ ዳጎን ተገልብጦ ታቦተ ጽዮን በላይ ተቀምጣ አገኟት፡፡ በማግስቱም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሞ ዳጎን ወድቆና ተሰባብሮ አገኙት፡፡ 1ሳሙ 5÷4 ይኽን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ሰቆቃወ ድንግል በተባለው ድርሰቱ፤
«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፤
አመ ነገደት ቁስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፡፡
ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ. . .፤
ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» በማለት በንጽጽር አስቀምጦታል፡፡ ኢሳ 19÷1 ኃይል እና ድል ማድረጉን በዳጎን የጀመረችው ታቦተ ጽዮን የፍልስጥኤማውያንን መንደር በአባርና በቸነፈር በእባጭም መታች፡፡ ሕዝበ ፍልስጥኤምም ታቦተ ጽዮን ወደ እስራኤል ምድር እንድትመለስ አደረጉ፡፡
በእንደዚህ ዓይነት ታላቅ ክብር በሀገረ እስራኤል ትኖር የነበረችው ታቦተ ጽዮን ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ ሐሴት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
ከአርባ ሁለት ጊዜ በላይ ስሟ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ በእግዚአብሔርየተወደደች ለመሆኗ ነቢያቱ መስክረዋል፡፡ ከነቢያት አንዱ አሞፅም፤ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን ?» ብሎ እግዚአብሔር መናገሩን ጽፏል /9÷7/፡፡ ከሁሉም ከፍ ባለመልኩ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት፤ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» ብሎ ሕዝበ ኢትዮጵያ እደ ሕሊናውን እና እደ ልቡናውን ዘወትር በአምልኮተ እግዚአብሔር፣ በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትና በትሩፋት፣ ዘርግቶ በሃይማኖት ጸንቶ፣ በምግባር ቀንቶ የሚኖር በመሆኑ፤ ሕዝቡ ሕዝበ እግዚአብሔር ምድሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ተብለዋል፤ /መዝ.68÷31/፡፡
ለታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ዋናው ምክንያት በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው የሠመረ ግንኙነት ነው፡፡ ይኽም በመሆኑ የንግሥት ሳባ እና የንጉሥ ሰሎሞን ግንኙነት ሰፊውን ታሪክ ይዞ ይገኛል፡፡የንግሥተ ሳባ ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረው ታምሪን ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ንጉሥ ሰሎሞን ያሠራውን ቤተ መቅደስ ዓይቶ፣ የሰሎሞንን ጥበባዊ ዝና ሰምቶ በፍጹም መደነቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ ያየውንና የሰማውን ለንግሥቲቱ አጫወታት፡፡ እሷም የሰማችውን ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ የሰሎሞንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ ተመልክታ እግዚብሔርን አመስግና ተመለሰች፡
ከንጉሥ ሰሎሞን ምኒልክን ፀንሳ ከኢየሩሳሌም ተነሥታ ባሕረ ኤርትራን ተሻግራ፣ ሐማሴን አውራጃ ስትደርስ አሥመራ ከተማ በሚገኘው ማይበላ ከተባለው ቦታ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ የሕፃኑንም ስም የንጉሥ ልጅ ስትል «እብነ መለክ» አለችው፡፡ ይኽ ስም በዘመን ሒደት ምኒልክ ተብሎ ተለወጠ፡፡
ምኒልክ ተወልዶ በአእምሮ እያደገ ሲሔድ አባቴ ማን ነው ? አድራሻውስ ወዴት ነው ? እያለ ጥያቄ ቢያበዛባት በሃያ ሁለት ዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ላከችው፡፡ ምኒልክም አባቱ ንጉሥ ሰሎሞንን አግኝቶ ሕገ ኦሪትንና የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያጠና ከቆየ በኋላ፤ ዐሥራ ሁለት ሺሕ እስራኤላውያንን አስከትሎ ከምድረ እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን አቀና፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ለጉዞ የተነሡ ዕብራውያን ከቤተሰቦቻቸው መለየታቸው ሳያሳዝናቸው ከታቦተ ጽዮን መለየታቸው እጅግ ከበዳቸው፡፡ ወዲያው በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንን ከመንበሯ አንሥተው በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ እና እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ይዘው አክሱም የደረሱት ኅዳር ፳፩ ቀን ነበር፡፡ ንግሥተ ሳባም የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በጣም ስላስደሰታት በክብር ተቀበለቻቸው፡፡ «ወአንበርዋ ውስተ ሕፅነ ደብረ ሀገረ ማክዳ» እንዲል በአክሱም ከተማ መካከል ደብረ ማክዳ /ዛሬ ቤተ ጊዮርጊስ ከሚባለው/ ላይ ደብተራ ኦሪት ሠርተው አስቀመጧት፡፡
አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ዐቅድ የታነፀው የአክሱም ጽዮን ገዳም ቅዳሴ ቤቱ ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ /የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት/ እና ልዑል ፊልፕ ከክብር ባለሟሎቻቸው ጋር በተገኙበት ተከብሯል፡፡
ኅዳር ጽዮን በአክሱም
አክሱም ማርያም ጽዮን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ከተማዋም የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻ ናት፡፡ አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣ በሕገ ወንጌል ያመነች ናት፡፡ ለዚህም ነው «ሕግ ይወጽእ እምጽዮን፤ ከጽዮን ሕግ ይወጣል» የሚለው ጥቅስ የሚነገረው፡፡
በዓለ ልደትን በላሊበላ፣ ጥምቀትን በጎንደር፣ ኅዳር ጽዮንን በአክሱም ጽዮን ሲያከብሩት ልዩ የሆነ ሥርዓት ስለሚቀርብባቸው ምእመናን መንፈሳዊ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡
ኅዳር ፳፩ ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት
ምክንያት፡-
1. በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን
4 374
🌾✞ #ኪዳነ_ምሕረት_እመቤት ✞🌾
ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት/፪/
ነይልን ነይልን ከአለንበት/፪/
#አዝ---
ከሠማያት በላይ ከአለው ከማደሪያሽ/፪/
ዝማሬ ከሞላው ከዘለዓለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ /፪/
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሠረገላሽ /፪/
#አዝ---
ከጸጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ /፪/
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ
ሰአሊ ለነ ቅድስት ውዳሴ ሲሠማ /፪/
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ /፪/
#አዝ---
ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሠማያት/፪/
ዕንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት
በጽዮን ዝማሬ ተሞላ ነፍሳችን /፪/
ንዒ ንዒ ንዒ እንበል እንደ አባቶቻችን/፪/
#አዝ--
ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ /፪/
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይኽን አምኖ ብጽዕት ይልሻል/፪/
እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል /፪/
#አዝ---
የልብን ሲያዋዩሽ ሠምተሽ ዝም አትይም/፪/
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም
ከዓይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሽለታለሽ /፪/
ከሐዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ /፪/
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✞ #ኪዳነ_ምሕረት_የእረፍቴ_እናት ✞
ኪድነ ምሕረት የእረፍቴ እናት
ሠላም ሆነ በአንቺ አማላጅነት
ንጽሕት ድንኳን በዕምነት የአጌጥሁብሽ
ሠላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ/፪/|//፪//
#አዝ---
የብርሐን ዝናር በአይኖረኝም
በንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በምልጃሽ ነው ሥሜ መቀየሩ
በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አዎ ሥሜ ተጠርቷል በልጅሽ
ከታች በምድር እስከ ሠማያት ድረስ
ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ/፪/
#አዝ---
የከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለክብርሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሠማይ ጸሐይ
ሥለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሠሠ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሠ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ጽናቱ/፪/
#አዝ---
ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለ አንቺ እናቴ
ተዋብሁብሽ ነፍሴ በአንቺ አበራ
አንደበቴ ሥምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫዬ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲኽማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ/፪/
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✞✞✞ #ጾመ_ነቢያት_የገና_ጾም ✞✞✞
🌾✞ ኅዳር 15 ይጀምራል ✞🌾
✔ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡
✔ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡
✔ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡
✔ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
✔ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡
ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡
✔በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡
✔በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡
#ምንጭ፦ ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፤ ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
