ch
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

显示更多
4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞• •••✞•••✞•••✞••• አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2) በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2) •••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ #አዝ••• ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ #አዝ••• በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ #አዝ••• ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ #አዝ••• የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ #አዝ•••

አልፋ እና ኦሜጋ.mp32.71 MB

✞✞✞ #ጌታ_ሆይ ✞✞✞ ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/ የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል የሄዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ/2/ ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለሙ ጌታ የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/ በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል ሃሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ/2/ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••

ጌታ ሆይ.mp36.96 MB

#ድንግል_ሆይ_ስላንቺ •••✞•••✞•••✞••• ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሀሪ አማልጅኝ ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ ፊቱንም እንዳላይ ስራዬ አስቸገረኝ #አዝ••••••• ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ ትዛዙን እንደሻርሁ ህጉን እንደጣስኩኝ #አዝ••••••• በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ እለምንሃለሁ ከአሁኑ ይቅርታ #አዝ••••••• አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ #አዝ••••••• ፃድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ #አዝ•••••••

ድንግል ሆይ ስላንቺ @EOTC2921 .mp31.67 MB

✤፨✤ #አቡነ_መብዓ_ጽዮን ✤፨✤ እንኳን ለመድኃኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ✔አቡነ መብዓ ጽዮን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል (ጥቅምት 27 ቀን) ጋር አብረው የሚታሰቡ ታላቅ የተጋድሎ አባት ናቸው፡፡ የጻድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያቸው ከመድኃኔዓለም በዓል ጋር ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር ታሪካቸውን ይዘን ቀርበናል፡፡ ✔አቡነ መብዓ ጽዮን የተገኙት እግዚአብሔርን እያስደሰቱ ያለነቀፋ ከሚኖሩ ቅዱሳን ነው፡፡ በክህነታቱ፣ በየዋህነቱ ከሰዎች የተስማማው አባታቸው ሀብተጽዮን፣ በደግነቷና በቸርነቷ የምትታወቀው እናታቸው ጽዮንትኩና በሕግ በንፅህና በጋብቻ ተወስነው ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይለምኑ ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ክርስቶስም መብዓ ጽዮን የተባለ ደግ ልጅ ሰጣቸው፡፡ ✔መብዓ ጽዮን ከልጅነቱ ጀምሮ ማስተዋል እና የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረበት ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ ይኸውም በአንዲት ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄድ የነበረ ሰው እግሩን እንቅፋት ተመቶ ደሙ ከመሬት ሲፈስስ በአየ ጊዜ እውቀት በልጅነቱ የሞላ መብዓ ጽዮን የደማው ጣቱ እስኪደርቅ ድረስ ጠባው፡፡ በመሬት የፈሰሰ ደሙን ከአፈሩ ጋር በላ፡፡ ይህ ሥራው ከልጅነቱ የመስቀሉ ፍቅር በልቡ የቸነከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ያገባ ሰው ሚስቱን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል፡፡ ያላገባ ግን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሥራ ያስባል$ የሚለው የመጽሀፍ ቃል ያፀናው ወጣቱ መብዓ ጽዮን ከቤተሰቡ የመጣለትን የጋብቻ ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ኃጢአትን ከመጨመር ውጭ ምን እጠቀማለሁ እያለ የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቃት፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ተውት፣ እርሱም ራሱን ይበልጥ ለእግዚአብሔር አስገዛ፡፡ ✔የምንኩስና እና ተጋድሎ ሕይወቱ የምንኩስ እና የተጋድሎ ሕይወት የጣመ የላመ የሌለበት ፍፁም ራስን ለእግዚአብሔር ማሳለፍ ነው፡፡ ይህንን የማይወድ ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ፍፁም ፈተናን ያበዛል፡፡ ቅድሳንም በረድኤተ እግዚአብሔር እና በተጋድሏቸው ያልፉታል፡፡ ሠይጣንን ድል ይነሡታል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንም የምንኩስና ቀንበር ከተሸከመ ጊዜ ጀምሮ ከፈረስ፣ ከበቅሎ፣ ከአልጋ፣ ከምንጣፍ ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ መኖሩን ገድሉ ይነግረናል፡፡ ለዚህም ተጋድሎ ሕይወቱ ያግዘው እና ይረዳው ዘንድ ክህነትን አባ ገብርኤል ከተባለ ጳጳስ ተቀብሏል፡፡ ቄስም ሆኖ የመድኃኔዓለምን ሥጋው እና ደሙን እያቀበለ ብዙ ዘመን ኖሯል፡፡ የምንኩስና ሕይወቱና ትጋቱም ታላቅ አባት እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ትልቅ ድንጋይ በደረቱ ተሸክሞ ከምድር ከአመድ በተቀመጠም ጊዜ በራሱ ተሸክሞ፣ በሚሰግድም ጊዜ በጀርባው አዝሎ ስለ ክርስቶስ መከራ ያስባል፡፡ ራሱን ይበድላል፣ ስጋውን ያደክማል፡፡ ይኸውም ያለሰንበት እና ያለበዓላት በቀር በዚህ ተጋድሎ የምንኩስና ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከዛም ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ከአቡነ ተክለሃይማኖት መቃብር በረከትን እንደተቀበለ ገድለ መብዓ ጽዮን ይነግረናል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱን ለእግዚአብሔር በሰጠ ቁጥር መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋወደሙ እየተገለፀ፤ እመቤታችንም እየታየች ትመክረው ታስተምረው ነበር፡፡ ✔ቅዱሳንን ማክበር በዓላቸውን መዘከር እንዲገባ ከምንማርባቸው ታሪኮች አንድ የአቡነ መብዓ ጽዮን ታሪክ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን እና የእናቱን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል አብዝቶ ያከብር ነበር፡፡ በዚህም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከቅድሳን ጋር መጥቶ ባርኮታል፡፡ የመለኮት ምሥጢርም ሥርዓትም በአካባቢው ላሉ ሠዎችም ተሠጥቷቸዋል፡፡ መናፍቃን በዓል ማክበር አይገባም ቢሉ የበዓል ማክበር ውጤቱ እዚህ ድረስ መሆኑን እናያለን፡፡ ✔በፀሎቱም #ኦ እግዚኦ አንተ ትብለኒ ሰአል ኩሎ ዘፈቀድከ ወአነ እሁበከ፣ ጌታ ሆይ አንተ የወደድከውን ሁሉ ለምን እኔ እሠጥሃለሁ አልከኝ፡፡ አሁንም የለመንኩን ግለጽልኝ በማለት የቀራንዮን መስቀል መከራውን ያሳየው ዘንድ ሁልጊዜ ይለምን ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን የሆኑ እጆቹን በመስቀሉ እንዲዘረጋ፣ እግሮቹም እንዲቸነከሩ፣ የሾህ አክሊልም በራሱ ተሸክሞ የጥቅምት 27 ቀን ታየው፡፡ ለሙሴ ሊታያቸው እንዳልቻለ አባ መብዓ ጽዮን ከመሬት ወደቀ፡፡ እንደ ሞተም ሆነ፡፡ ማንም የመስቀሉን መከራ ሕማሙን ማየት እንደማይችል ነገረው፣ በቸርነቱም አነሳው፡፡ የሞቱ ገናንነት የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ መሆኑን አሳውቀው፡፡ መከራው ታላቅ በሰው አእምሮ አይታሰብምና ነው፡፡ ✔ኃጢአትን ያልሠራ ሐሰትም በአፉ ያልተገኘበት ስለሠው ኃጢአት ስለሞተው ስለመድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ በምትሆን በዕለተዓርብ ታላቅ ተጋድሎን በማድረጉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል በሚታሰብበት በ27 በመድኃኔዓለም ዕለት የአቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያ ተደረገ፡፡ ይኸውም ጥቅምት 27 ነው፡፡ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/ የጻድቁ የአባታችን የአቡነ መብዓ ጽዮን በረከት ከእኛ ጋር ትሁን!!! የመስቀሉ ፍቅር በልባችን ይኑር አሜን!!!

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት https://telegram.me/EOTC2921

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት

#የነገ_የመድኃኔዓለም_ስርዓተ_ማሕሌት https://telegram.me/EOTC2921

#የፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_መታሰቢያ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን 📖ጥቅምት 24 #ደብረ_ሊባኖስ ይኽ ሐዲስ ሐዋርያ በኢትዮጲያ የወንጌል ብርሃን ያበራ: በአምልኮ ጣዖት የተያዙትን ወደ ሚደንቅ ብርሃን ያመጣ:: በቃሉም በተአምሩም በክብርና በጸጋ ያጌጠ:: የቃል ኪዳኑን በረከትን እያጎናጸፈ ሞገስ የሚሰጠን አባት ነው:: የቃሉን ትምህርት የሰሙ: የገድሉን ጽናት ያደነቁ: በተአምሩ የተማረኩ: በጸሎቱ የዳኑ ዓለምን ትተው ተከተሉት:: ቃል ኪዳኑ የጎበኛቸው አምላከ ተክለ ሃይማኖት ክበር ተመስገን አሉ:: ፃድቁ አባታችን በተሰጣቸው ጸጋና ቃል ኪዳን መሠረት በደብረ ሊባኖስ ገዳም ድንቅ የተባለ መለኮታዊ ተአምራቶች እስከ አሁን ድረስ ታላላቅና በሰው አእምሮ ሊታመን ሊታሰብ የማይችሉ ግን የተደረጉና የታዩ ተአምራቶች እየተፈፀሙበት ይገኛል:: ክብር ይግባውና አምላከ ተክለሃይማኖት:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ደንቆሮዎች ይሰማሉ:: በአልጋ ሸንኮርና "በዊልቸር" ተይዘው የመጡ ሕሙማኖች ገና ገዳሙን ሲረግጡ ይድናሉ:: ገዳሙ ውስጥ በሚደረገው ጸሎትና ለፃድቁ በተሰጣቸው ቃል ኪዳን መሰራት አፈፍ ብለው ተነስተው ይሔዳሉ:: ዘመኑ ዘመነ ጽጌ የያዝነውም ወር ከፃድቁ ቀን ጋር ገጥሟልና:: በዚህ ቀንና ሰዓት በዚሁ ወራት የዛሬ 2012 ዓመት በጌታ ልደት ዓለም ከጨለማ ወደ ብርሃን ለመውጣት ጎህ በሚቀድበት ሰዓት ጥንት ጠላታችን ዲያብሎስ በሄሮድስ አድሮ ጌታን ለመግደል ባሰበ ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ ለእመቤታችን ጠባቂ ለዮሴፍ ሕፃኑን ከእናቱ ጋር ይዞ ወደ ግብፅ እንዲሰደድ ይነግረዋል:: ወደ ግብፅ ይዞ በተሰደደ ሰዓት በጥበበ እግዚአብሔር ወደ ኢትዮጵያም መጥቶ በደብረ አስቦ ገዳም ለተወሰነ ጊዜ ተቀምጠዋል :: በዚህም ገዳም ወደፊት ለሚደረገው ተአምራት የመጀመሪያ የሆነው ተአምር በዚህ ገዳም በስደቷ ጊዜ ተፈጽሟል:: በደብረ አስቦ በቆዩበት ሰዓት ቦታው ገደላማ ወጥተው ወርደው ምግብ አዘጋጅተው ለመብላት የማይቻል ስለሆነ ተራቡ:: በዚህ ሰዓት በስደቷ ወራት ወደ ገዳሙ እየመራ ያመጣቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በገዳሙ ዙሪያ ላሉት አሕዋፋት እነ ድንግል ማርያም መራባቸውን ነገራቸው:: አእዋፋትም በአፋቸው ለቃቅመው እያመጡ የተቀመጡበት ዋሻ የተለያዩ ፍራፍሬ በሞምላት እስከሚሔዱም ድረስ መገቧቸው:: ሲሔዱም ቦታውን፥ አፈሩን፥ ውኃውንም ለሰው ልጆች በረከት ሕይወት መድኃኒት ያድጋችሁ ብለው ባረኩት:: ጌታም ወደፊት በዚህ ገዳም ንጽሕናው ቅድስናው እንደ ኤልያስ የሆነ ፃድቅ ሰው ይኖርበታል:: በመንፈስ የወለዳቸውም ልጆቹም አንቺን የሚወዱ ስምሽን በምስጋና የሚጠሩ ይሆናሉ:: መሥዋዕታቸው ጸሎታቸው በእኔ ዘንድ ተቀባይነት አለው:: በማለት የቦታውን ክብር የተክለ ሃይማኖት መነሳት ለድንግል ማርያም ነገራት:: በዚህም ምክንያት ዛሬ እንደሚታየው በገዳሙ ጸሎታት የታጎሉበት መስዋዕት የቀረበት ጊዜ የለም:: ብዙ አባቶችም በገዳሙ የሚደረገው ጸሎትና ሌላም መንፈሳዊ አገልግሎት በማየት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታጎለውን ጸሎት የሚሞላ ይህ ቦታ ደብረ ሊባኖስ በማለት የቦታውን ክብር ይመሰክራሉ:: በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባ ሊባኖስ የተባለ ጻድቅ ከትግራይ ወደዚህ ገዳም በመምጣት የደብረ አስቦን ዋሻ አበጅተው ለአርባ ዓመት ከቆዩ በኋላ በቅዱስ ገብርኤል ትእዛዝ ይህ ቦታ የሌላ ሰው ነው አንተ ወደ መጣህበት ተመለስ ቦታው ግን በስምህ ደብረ ሊባኖስ ተብሎ ይጠራል ብሎ ነገራቸው:: በቦታው የነበሩ የአባ ሊባኖስ የመንፈስ ልጆቻቸው አባ ሊባኖስ የገደሙትን ገዳም እያስፋፉ እስከ አስረኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ይገለገሉበት ነበር:: በመቀጠልም ኮራ የሚባል ሽፍታ ተነስቶ በገዳሙ የሚኖሩ ገዳማውያንን በመግደል ንዋያተ ቅድሳትን በመዝረፍ ቦታውን ከተቆጣጠረ በኋላ ሞቷል:: በመቀጠልም ጠላት ሰይጣን የቦታውን ክብር ያውቃልና ቦታውን ለማጥፋት ቃልቻ እንዲመለክበት አድርጎ ለሁለት መቶ ዓመት ያህል ቆይቶ ነበር:: ከዚህ በኋላ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሸዋ ክፍለ አገር በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሙ ኤቲሳ በተባለ ቦታ ከአባታቸው ጸጋ ዘአብ ከእናታቸው እግዚእ ኃርያ ተወለዱ:: የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በአጭር ጊዜ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ ከሃያ ሁለት ዓመታቸው ጀምረው ወንጌልን በማስተማር ሐዋርያዊ ሥራቸውን በማከናወን ኢትዮጵያን በወንጌል ብርሃን አበራት:: በገዳማት እየዞረ በገዳማት የሚኖሩ አባቶችን እያገለገሉ መንፈሳዊ አገልግሎትን ይፈጽሙ ነበር:: በ1267 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመምጣት ገዳሙን ለ29 ዓመታት በደብረ አስቦ ዋሻ ከጸለየ በኋላ በ1296 ዓ.ም አረፉ:: ጌታችንም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ባረፉ በ57 ዓመታቸው በ1353 ዓ.ም አጽማቸው ፈልሶ ወደ ኤላም መጣ:: በኤላምም 40 ዓመት ከቆየ በኋላ አሁን ቤተ ክርስቲያን ወዳለበት ቦታ ፈልሶ በላዩ ላይ ተሰርቶበታል:: ይኽ ጻድቅ ይኽ ቅዱስ ይኽ ሐዲስ ሐዋርያ ተክለ ሃይማኖት የጸለዩበት፣ ቃል ኪዳን የተቀበሉበትና ያረፉበት የተቀደሰ ሥፍራ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ተአምራት ያደርጋል፥ ይፈውሳል: ዕውቀትን ይገልጻል፥ ይኽ ቦታ በረከት አለው፥ ፀጋ አለው፥ በክብር በቃል ኪዳን የከበረ የጻድቁን ሥጋ የያዘ ነውና:: አሁን ያለውን ሕንፃ ጨምሮ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ታሪክ ውስጥ 10 አብያተ ክርስቲያናት በተከታታይ ተሠርተዋል፡፡ የመጀመሪያው የገዳሙ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው ዔላም በተባለውና ከደብረ አስቦ ወረድ ብሎ በሚገኘው ሜዳማ ሥፍራ ላይ ሲሆን ዘመኑም በ1362 ዓም ነው፡፡ ያሳነጹትም አራተኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ናቸው፡፡ አሁን ያለውን ቤተ ክርስቲያን ያሠሩት ደግሞ በ1955 ዓ.ም. በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ አማካኝነት ነው፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያን ሊሰራ ግንቦት 12 ቀን 1929 ዓም. የአባታችንን የፍልሰተ ዐጽም በዓል ለማክበር የተሰበሰቡትን ካህናትና ምእመናንን የግራዝያኒ ጦር ጨፍጭፎ፣ ቤተ ክርስቲያኑን አቃጥሎ፣ ቅርሱን ዘርፎ በመሄዱ የተነሣ ገዳሙ በመዳከሙ ምክንያት እንደገና እንዲሠራ ጻድቁ የላኳቸው መናንያን ለንጉሡ በመናገራቸው ነው፡፡ የብርሃን ዓለም ተክለ ሃይማኖት ገድላቸው በ1399 ዓ.ም ተጽፏል:: በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ትእዛዝም በ1426 ዓ.ም ገዳሙ ደብረ ሊባኖስ ተባለ:: በ1523 ዓ.ም ሐምሌ 23 ቀን በግራኝ ወረራ ገዳሙና ቤተ ክሬስቲያኑ ሲቃጠል መነኰሳቱ በሃይማኖታዊ ስሜት ከእሳቱ ውስጥ እየገቡ ተቃጥለዋል:: ብዙዎችም ቅርሶችን ይዘው ተሰደዋል:: የደብረ ሊባኖስ ገዳም ክልል ከ30 በላይ እጨጌዎች የተቀበሩበት፣ የብዙ ቅዱሳን ዐጽም ያረፈበት፣ ታላላቅ ጉባኤያት የተደረጉበት፣ ከዕብራይስጥና በዐረብኛ ሳይቀር ትርጓሜ መጻሕፍት ሲሰጡ የኖሩበት፣ አያሌ ቅዱሳት መጻሕፍት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ የተተረጎሙበት ቅዱስና ታሪካዊ ገዳም ነው፡፡ የዚህችን ቦታ ጥፋት የማይወድ እግዚአብሔርም ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት በሰጠው ቃል ኪዳን መሰረት ልጆቻቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ እያበዛ እስከ ዛሬ ድረስ ገዳሙን በማክበርና በማስከበር እየጠበቁና ለመላው ዓለም ልጆቻቸው ብርሃን በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ:: ይቆየን:: የአባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቃል ኪዳን ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።