የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
前往频道在 Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
显示更多4 374
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
4 374
🌺በስመአብ🌺
🌺 ወወልድ 🌺
🌺ወመንፈስ ቅዱስ🌺
🌺
🌺
🌺አሃዱ🌺
🌺አምላክ🌺
🌺አሜን🌺
✍✞“#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)
✍✞“#በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን)
✍✞“#ዐሠሮ_ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው)
✍✞“#አግአዞ_ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው)
✍✞“#ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ)
✍✞“#እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ)
✍✞“#ኮነ” (ሆነ)
✍✞“#ፍሥሐ_ወሰላም” (ደስታ ሰላም)
✝አሜን እንኳን አደረሳችሁ✝
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ሕያውን_ከሙታን_መካከል_ስለ_ምን_ትፈልጋላችሁ_ተነሥቶአል_እንጂ_በዚኽ_የለም፡፡ሉቃ 24፡5
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #በመስቀሉ_ደም_ሰላምን_አደረገ_በሰማያትም_ላሉት_እርቅን_ሰላምን_አደረገላቸው፡፡ ቆላ፡1÷19
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ለኃጢአት_ሞትን_ለፅድቅ_እንድንኖር_እርሱ_ራሱ_በሥጋዉ_ኃጢያታችንን_በእንጨት_ላይ_ተሸከመ_በመገረፉ_ቁስል_ተፈወሳችሁ_እንደ_በጎች_ትቅበዘበዙ_ነበረና_አሁን_ግን_ወደ_ነፍሳችሁ_እረኛና_ጠባቂ_ተመልሳችሃል። 2ኛ ጴጥ 2÷24 •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#የመሰቀሉ_ቃል_ለምጠፉት_ሞኝነት_ለእኛ_ለምድን_ግን_የእግዚአብሔር_ኃይል_ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ፡1÷18
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ከጌታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል_በቀር_ሌላ_ትምክህት_ከእኔ_ይራቅ፡፡ገላ፡6÷14
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
💐ሰላም💐
💐ለአንተ💐
💐ይሁን💐
💐ውድ የተዋህዶ ልጆች💐
🌹እንኳን🌹
🌹ለብርሃነ🌹
🌹
🌹
🌹
🌹ትንሳኤው🌹
🌹
🌹
🌹በፍቅር🌹
🌹በሰላምና🌹
🌹በጤና🌹
🌹
🌹
🌹አደረሳችሁ🌹
🌹 አደረሰን🌹
🌹
🌹
🌹መልካም🌹
🌹የትንሳኤ🌹
🌹 በአል🌹
🌹ይሁንላችሁ🌹
✞
🌹አ🌹
✞አሜን✞🌹ሜ🌹✞አሜን✞
🌹ን🌹
✞
4 374
#ሕያውን_ከሙታን_መካከል_ስለ_ምን_ትፈልጋላችሁ__ተነሥቶአል_እንጂ_በዚኽ_የለም (ሉቃ 24፡5)"
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
♥ ይህ የትንሣኤ በዓል ሞት የተሸነፈበት፣ መቃብር የተረታበት፣ ሕይወት ያገኘንበት ታላቅ በዓል ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ በሞቱ ሞትን ድል መንሣቱን፣ ሙስና መቃብር መጥፋቱን፣ ዓለም በብርሃን መመላቱን ትመሰክራለች፡፡
♥ ክብር ይግባውና ለአዳም በሰጠው ተስፋ መሠረት ወልደ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ተወልዶ በሚያስተምርበትም ጊዜ 3 ቀንና 3 ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ እንደሚነሣ ያስተምር ነበር፡፡ ጥቅሶቹም፦ (ማቴ 12:40፤ ሉቃ 9:21፤ ዮሐ 2:19)
♥ የዚኽም አቈጣጠር ሁለት ዐይነት ነው የመጀመሪያው “መዓልት ይስሕቦ ለሌሊት ወሌሊት ይስሕቦ ለመዓልት” (ቀን ሌሊትን ሌሊት ቀንና ይስባል) በሚለው የአቈጣጠር ዘዴ ጌታ ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ዐርብ በሠርክ ወደ መቃብር ስለወረደ ዐርብ እንደ አንድ ቀን ሲቈጠር፤ ቅዳሜ ያው አንድ ቀን፣ እሑድ ደግሞ መንፈቀ ሌሊት ስለተነሣ እሑድ እንደ አንድ ቀን ይቈጠራል።
♥ ሌላው አቈጣጠር ደግሞ ዕለት የሚለው ፍቺ አንድ እጅ ብርሃን አንድ እጅ ጨለማን ያካተተ ነው፤ ሰለዚህ በዚህ ተመርጒዘን ካየነው
► የስቅለት ዕለት ዐርብ ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ብርሃን ስለሆነ አንድ እጅ ብርሃን
► ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ስለኾነ አንድ እጅ ጨለማ
► በሠርክ ደግሞ ብርሃን ሆኗል አንድ እጅ ብርሃን
► ቅዳሜ ደግሞ ሙሉ ቀን ሙሉ ሌሊት ስለሆነ አንድ እጅ ብርሃን አንድ እጅ ጨለማ
► ጌታ የተነሣው እሑድ ሌሊት ስለሆነ አንድ እጅ ጨለማ ነበር፡፡
ስለዚህ ሦስት እጅ ብርሃን ሦስት እጅ ጨለማ 3 መዓልት 3 ሌሊት ተብሏል፡፡
♥ ጌታችን ለምን ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐደረ ቢሉ?
ሀ) 1) አዳምን 2) ሔዋንን 3) ሕፃናቱን እንዳደነ ለማስረዳት 3 ዕለት ዐደረ
ለ) 1) ለሥጋችን 2) ለነፍሳችን 3) ለደመ ነፍሳችን እንደካሰልን ለማስረዳት
ሐ) የሰው 3 ጠላቶች ይኸውም 1) ሞት 2) ፍዳ 3) ኀጢአትን እንዳጠፋ ለማጠየቅ ነው
♥ ክብር ይግባውና ትንሣኤና ሕይወት የኾነው አምላካችን ክርስቶስ ሞትን ድል ነሥቶ በድንቅ ምስጢር መቃብሩ እንደተዘጋ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ያን ጊዜ ዓለም በብርሃን ተዋጠ፡፡
♥ የፅንሰቱና የልደቱ ምስጢር ከትንሣኤው ምስጢር ጋር ይስማማል፤ ይኸውም በፅንሰቱና በልደቱ የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ማኅተመ ድንግልና ሳይከፍት እንደተፀነሰና ሳይከፍት እንደተወለደ ሁሉ አሁንም በተዘጋ በተገጠመ መቃብር በድንክ አምላካዊ ጥበብ ረቂቅ ዘእምረቂቅ የሆነው አምላክ ተነሣ፡፡
♥ ለዚህ ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ ቅዳሴዋ ላይ “ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪን” (ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሣልፎ የሚኖረውን በድንቅ አምላካዊ ሥራ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ጌታችንን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በበፍታ ገነዙት) በማለት ለልጆቿ የትንሣኤውን ታላቅነት እየመሠከረች “ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ” (ትንሣኤህን ለምናምን ለእኛ ብርሃንህን ላክልን ወደኛ) እያለች በፍጹም ደስታ ትዘምራለች፡፡
♥ዕለተ እሑድ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ የተነሣባት ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት እናከብራታለን፤ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ የዕለተ ዐርቡን የመከራ እና የዕለተ እሑድን የደስታ ቀን እንዲኽ ያነጻጸረውን እነሆ ብያችለኊ፡-
✍ ከትላንትና ወዲያ አይሁድ እየተዘባበቱበት “ራስኽን አድን” ይሉት ነበር (ማቴ ፳፯፥፵)፤ ዛሬ ግን ርሱ ጥሎት የተነሣበትን መቃብር መላእክት እየሳሙት ነው፤ ትናንት ሞቶ በመቃብር በተቀበረ ሰው ልማድ በታተመ መቃብር በዝምታ ነበር፤ ዛሬ ግን ሕያው ኾኖ ለሙታንም ሕይወትን በመስጠት ኹሉንም ወደ ሕይወት አስነሣቸው።
♥ ከትናንትና ወዲያ ጦር፣ ኾምጣጤ እና ኀሞት እሾኽ እንዲኹም ስቅለት ነበር፤ ዛሬ ግን መላእክት በክብር እና በደስታ ዘመሩለት፤ ከትናንትና ወዲያ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር ልጅ ነፍሱን በአባቱ እጅ አደራ ሰጠ (ሉቃ ፳፫፥፵፮)፤ ዛሬ ግን ኹሉንም የማዘዝ ሥልጣን ያለው ርሱ ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋሐዳት።
♥ ትላንት የመሰቀያውን መስቀል አቆመ፤ ዛሬ ግን ጥንካሬ፣ የሙታን ትንሣኤና ኀይል ኾነ፤ ከትናንት ወዲያ ስምዖን አላውቀውም በማለት በተደጋጋሚ ካደው (ማቴ ፳፯፥፸)፤ ዛሬ ግን ሞትን ድል ነሥቶ በመነሣቱ መቃብሩን ለማየት ሲሮጥ ኼደ (ዮሐ ፳፥፬)፤ የዕለተ ዐርብ መከራው ለሐዋርያት ጉባኤ መሸመቂያ አዘጋጀ፤ እሑድ ግን ዐዲስ ራእይና ደስታ ኾነ።
♥ ትናንት ንጉሡ በመቃብር ተኝቶ ነበር፤ ዛሬ ግን ወይኑ እንደተወው ኀያል ተነሣ (መዝ ፸፯፥፷፭)፤ ባላፈው ቀን ቅዱሳት አንስት በመከራ እና በለቅሶ ውስጥ ነበሩ (ሉቃ ፳፫፥፳፯)፤ ዛሬ ግን ርሱን እንደ አትክልተኛ አይተውት ታላቅ ደስታ ሐሴትን አደረጉ፤ በዐሳዛኙ ሰንበት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ርሱ በኩረ ሙታን ከሙታን መኻከል ነበር፤ እሑድ ግን በመላእክት ጉባኤ ታጀበ (ማር ፲፮፥፭)።
♥ በዕለተ ዐርብ የሐዋርያት ጉባኤ በሐዘን ተበተነ፤ ዛሬ ግን ትንሣኤውን በመደነቅ ለማየት የደቀ መዛሙርት ጉባኤ ወጥተው ነበር፤ በሌላኛው ቀን ሽሽት፣ በመበታተንና ራሳቸውን መደበቅ ነበረባቸው፤ ዛሬ ግን ለመሮጥ፣ በአንድ ላይ ለመሰብሰብ እና የምሥራቹን ለማምጣት ቻሉ፡፡
♥ ትናንት እረኛው ተመትቶ የርሱም ጠቦቶች ተበታትነው ነበር (ዘካ ፲፫፥፯፤ ማቴ ፳፮፥፴፩)፤ ዛሬ ደግሞ ተኲላዎቹ ፈረጠጡ፤ መንጋዎቹ በደስታ ተመሉ፤ ትናንት ይሁዳ ገንዘብ ተቀበለ፤ ቀያፋ ምክር ሲሰጥ ሃናም ሲያወግዝ ተሰማ፤ ጸሓፍት በሁካታ ውስጥ ነበሩ፤ ጲላጦስ ተቀምጧል፤ ጌታችንም ምሰሶውን ይዞ ቆሟል፤ ስምዖን ክዷል፤ እንድርያስ ሸሽቷል፤ ዮሐንስ ርቀቱን ጠብቋል፤ ፊሊጶስ አይታይም፤ ማቴዎስ ተደብቋል፤ በርተሎሜዎስ ጸጒረ ልውጥ ኾኗል፤ ቀነናዊው ተርበትብቷል፤ ኹሉም በያለበት ተበትኗል (ማቴ ፳፯፥፭-፵፭)።
♥ ዛሬ ግን ቀያፋ ኀፍረት ተከናንቧል፤ ሃና ግራ መጋባት ውስጥ ገብቷል፤ ይሁዳም ብሩን በትኖ ራሱን ዐንቋል (ማቴ ፳፯፥፭)፤ ጸሓፍትም መናገር ተስኗቸዋል፤ የምኲራብ አለቆች በኀፍረት ራሳቸውን ሸፍነዋል፤ ሌዋውያን ርስ በርሳቸው እየተወቃቀሱ ነው፤ ጲላጦስ ተደንቋል፤ የዚኽ ኹሉ ጠንሳሾች ከነጭራሹ በቦታው የሉም፤ የተኲላ መንጋዎች ተበትነዋል።
♥ እረኛው ከበጉ ጋር ይነጋገራል፤ መንጋዎቹን ሲሰበስባቸው መዐዛውን ሳቡት፤ ማርያም ተደስታለች (ማር ፲፮፥፩)፤ ሰሎሜም በኀሤት ተመልታለች፤ ማርታ መልካም ዜና ይዛለች፤ ዮሐና የሰላም ዜና ታመጣለች (ሉቃ ፳፬፥፲)፤ ደቀ መዛሙርት ራሳቸውን ገልጠዋል፤ ሐዋርያት ከተደበቁባቸው ቦታዎች ወጥተዋል፤ ስምዖንና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሮጠዋል፤ ማቴዎስና በርቶሎሜዎስ ጭንቀታቸውን ረስተዋል፤ እንድርያስና ያዕቆብ በደስታ ውስጥ ናቸው፤ ቶማስ ተናዝዟል፤ ፊሊጶስ ምስጋናን አቅርቧል። "ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ"
♥ በመኾኑም የጌታ ትንሣኤ ለእኛ ለክርስቲያኖች የድል፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የሕይወት፣ የማሸነፍ በዓል ነውና ይኽ ሰላምታ ይደረሳል፡፡
4 374
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል_7ቱ_የመስቀሉ_ቃላት_7ቱ_ተዐምራት_5ቱ_ችንካሮች_6ቱ_ሰሙነ_ሕማማት_ቀናቶች___5ቱ_ኃዘናት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል
1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሰባቱ_ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተቸነከረባቸው_አምስቱ_ችንካሮች
1. #ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. #አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. #ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. #አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. #ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#የሰሙነ_ሕማማት_ትርጓሜ
#ሰኞ ፡
ይህ ዕለት አንጽ ሆ ተ ቤተመቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ማክሰኞ፡
የምክር ቀን ይባላል
ይኸውም የሆነበት ምክንያት ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ ሰጠ።
ጌታችን ፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሐተ ቤተመቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ
ሥልጣኑ በጻሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል ነው፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ረቡዕ፡
ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሕፋት
ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን
ስለሆነ ነው፡፡
መልካም መዓዛ ያለው ቀን ይባላል
የእንባ ቀንም ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሐሙስ፡
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል
ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል
የምስጢር ቀን ይባላል
የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
የነፃነት ሐሙስ ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ዓርብ፡
ስቅለት ዓርብ ይባላል
መልካሙ ዓርብ (GOOD FRIDAY) ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ቅዳሜ
ቅዳምሥዑር
ለምለም ቅዳሜ ይባላል
ቅዱስ ቅዳሜም ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#አምስቱ_ኃዘናት
ልመናዋ ክብሯዋ በእኛ ለዘለዓለም በእውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች
በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን ያደረገችው
ተዓምር ይህ ነው።
በዕለታት ባንድ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኃዘኖች ማናቸው ኃዘን ይበልጣል አላት፡፡ እመቤታችንም
ፈጣሪዬ ጌታዬ ሆይ በእኔ ዘንድ እኒህ አምስቱ ኃዘኖች ይበልጣሉ አለቸው
፳፩
1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት
በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35
2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ
2:41-48
3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን
ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1
4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች
መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡ ዮሐ 19:17-22
5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ
ነው፡ ዮሐ 19:38-42
፳፩ ጌታችንም እናቱን ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ያገኙሽን እኒህን ኃዘኖችና
መከራዎች በሰላመ ገብርኤልና አቡነ ዘበሰማያትን እየደገመ ያሰበውን
ኃጢአቱን እኔ አስተሰርይለታለሁ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ አላት፡፡ እናቴ ሆይ ከሞቱ አስቀድሞ በሦስተኛው ቀን ካንቺ ጋር መጥቼ እገለጽለታለሁ፡፡ ይህን ሲናገር ቅዱስ ደቅስዮስ ሰምቶ ምእመናን ያነቧት ዘንድ በእመቤታችን ተዓምር መጽሐፍ ውስጥ ጻፈው፡፡
† ልመናዋ ክብሯዋ የልጅዋ ቸርነት በእኛ ለዘለዓም በእውነት ይደርብን †
ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ
ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤
ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት
የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ።
ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች ዕድፍን
የምታውቂ አይደለሽም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ።
ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም የሰማይ መላእክት
ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ። ( ሊቁ አባ ሕርያቆስ) (ምንጭ:ታምረ ማርያም 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
4 374
#ስርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት
(ከሰኞ - እሮብ)
ከሁሉም በፊት የሰዓቱ ተረኛ አገልጋይ ቃጭል እየመታ ሦስት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ይዞራል። የሰባት ቀን ውዳሴ ማርያም ፣ አንቀጸ ብርሃንና መዝሙረ ዳዊት በሙሉ ይጸለያል። የእለቱ ተረኛ መምህር (መሪጌታ) የእለቱን ድጓ ይቃኛል: ድጓው ከአራቱ ወንጌላት ምንባብ ጋር እንዲስማማ ሆኖ የተሰራ ነው። የተቀኘው ድጓ እየተቀባበለ እየተዜመ ይሰገዳል: ሶስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል።
የወንጌላቱ ድጓ እንደሚከተለው ነው:-
በማቴዎስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኲልክሙ አብያተ ከርስቲያናት ከመ ዘአክበሮሙ ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት በወንጌለ መንግሥት እንዘ ይብል ክርስቶስ ወልደ ዳዊት አማን አማን እብለክሙ: እስከ አመ የኃልፍ ሰማይ ወምድር የውጣ እንተ አሐቲ ኅርመታ ወአሐቲ ቅርጸታ ኢተኃልፍ እምኦሪት ወእምነቢያት: እስከ ሶበ ኲሉ ይትገበር ወይከውን ይቤ እግዚእ ዘበዕብራይስጢ ልሳን በወንጌለ ማቴዎስ ብርሃን ዘእምብርሃን።
በማርቆስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኲልክሙ አብያተ ከርስቲያናት ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት በወንጌለ መንግሥት እንዘ ይብል ክርስቶስ ወልደ ዳዊት ኢይምሰልክሙ ዘመጻዕኩ እስዐሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት ወኢከመ እንስቶሙ አላ ዳዕሙ ዘእንበለ ከመ ከመ እፈጽሞሙ ይቤ እግዚእ በወንጌለ ሰላሙ አማኑኤል ስሙ ማርያም እሙ።
በሉቃስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ይቤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዘ ይሜሕረነ በወንጌለ ሉቃስ ወባሕቱ ይቀልል ሰማይ ወምድር ይኅልፍ እምትደቅ አሐቲ ቃል እምኦሪት።
በዮሐንስ ወንጌል:-
ሃሌ ሉያ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በወንጌል ለዘመሐረነ በኦሪት ወበነቢያት ለዘናዘዘነ በከመ መሐረነ እግዚእነ ስብሐት ለእግዚአብሔር ከመ ናምልኮ ለዘፈጠረነ።
ይህ ሦስት ጊዜ ተመላልሶ ከተዘለቀ በኋላ "ለከ ኃይል" የሚለውን በመቀባበል ፲፪ ጊዜ ይበሉ : በመጨረሻም በ፲፫ኛው ከ "ለከ ኃይል" እስከ "እብል በአኮቴት" ድረስ አንድ ጊዜ በኅብረት ይበሉ:-
ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤
አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤
ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት፤
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስመከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኲሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
ከዚህ በመቀጠል "ለአምላክ ይደሉ" የሚለውን መጀመሪያ በመሪ እየቀደሙ በአንሺ እየተከተሉ አንድ ጊዜ ይዝለቁ: በሁለተኛው ክፍል ደግሞ እያስተዛዘሉ አንድ ጊዜ ይበሉ:-
ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለምኲናኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም:
ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም (በአርብ):
ለከ ይደሉ ኃይል:
ወለከ ይደሉ ስብሐት:
ወለከ ይደሉ አኮቴት:
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም።
ከዚህ በመቀጠል የኦሪትና የነቢያት መፃህፍት ይነበባሉ: ቀጥሎም ከተአምረ ማርያም መቅድም እና ተአምር ጀምሮ ሎሎች ተአምራት ዘወትር በየጠዋቱ እንደተለመደው ይነበባሉ: መርገፋቸውን (የምንባባቱ የመግቢያ ጸሎታቸውና የመጨረሻ ጸሎታቸውን) ከሆሣዕና ሠርክ እስከ ዐርብ ሌሊት በአራራይ ዜማ ያድርሱ: ዐርብ ከጠዋት ጀምሮ ግን በዘወትር እንደተለመደው በዕዝል ዜማ ያድርሱ: ተአምረ ኢየሱስ ከተነበበ በኋላ ከወንጌል በፊት ዲያቆኑ ለሰዓቱ የተሰራውን ምስባክ መጀመሪያ በንባብ ቀጥሎም በዜማ ይበል: ሕዝቡም በአንድነት በዜማ ይቀበሉ።
ከዚያም ሁለተኛው ሥርዓተ ስግደት ይጀመራል: ዜማው የሚጀምረው አሁንም በቀኝና በግራ በመቀባበል ነው: አንዱ ይመራል ሌላው ይቀበላል:-
በመሪ:- ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዘወነ:
በተመሪ:- ንሴብሖ ወናልዕል ስሞ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ:
ኪርያላሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያላይሶን:
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን ኪርያላይሶን።
ኪርያላይሶን የሚለውን ብቻ በመሪ ወገን ፳፩ ገዜ በተመሪ ወገን ፳ ጊዜ ይበሉ: ድምሩ ፵፩ ጊዜ ይሆናል።
4 374
#በእንተ_ስቅለቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
✞ #እስመ_ለዓለም_ምሕረቱ ✞
እስመ ለዓለም ምሕረቱ /፪/
አያልቅም ብዙ ነው የአምላክ ቸርነቱ /፪/
#አዝ•••••••
አመስግኑት ጌታን ሁላችሁ በአንድነት/፪/
መሐሪ ነውና ለሰው ልጆች ሕይወት /፪/
#አዝ•••••••
የማይሞተው ሞቶ የተቀበረው /፪/
ከገሃነም እሳት እኛን ሊያድን ነው /፪/
#አዝ•••••••
ከማርያም የነሳው ያ ቅዱስ ስጋው/፪/
ቀራንዮ ሲውል የሚያሳዝን ነው /፪/
#አዝ•••••••
በፈጠረው ፍጥረት እጅግ ተሰቃይቶ /፪/
ነፍሳትን አወጣ ከሲኦል ጎትቶ /፪/
#አዝ••••••
•••✞ #በህይወቴ_በዘመኔ ✞•••
ሕይወቴ ሲመራ ጌታ በቃልህ
ብርታት አገኛለሁ ሲያድሰኝ ፍቅርህ
ያንተ ጸጋ ጌታ ስለበዛልኝ
ጨለማው ተገፎ ብርሃንህ መራኝ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
በሕይወቴ በዘመኔ ደስ የሚለኝ ለእኔ በወንጌል ማመኔ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ወዴት እሄዳለሁ የእጅህ ጥበብ ሆኜ
ፍቅርህ እያደሰኝ ሞተህልኝ ድኜ
ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለኔ ያለህ
ምን ይከፈልሀል ለፍፁሙ ፍቅርህ
#አዝ•••••••
ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለኔ ያለህ
ምን ይከፈልሀል ለፍፁሙ ፍቅርህ
ደጅህ ላይ ተጥዬ ደጅህ ላይ ልሙት
ቃልህን ልጠብቅ በፍፁም ፍርሃት
#አዝ•••••••
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•
•••✞•••✞•••✞•••
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)
•••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ
#አዝ•••
✞✞✞ #ጌታ_ሆይ ✞✞✞
•••✞•••✞•••✞•••
ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/
የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል
የሄዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ
መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ/2/
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለሙ ጌታ
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/
በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል
ሃሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ
አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
•••✞ #ተይ_ተመከሪ ✞•••
ተይ ተመከሪ ነፍሴ ሆይ ተይ ተመከሪ /2/
በዓለም መድኃኔት ነፍሴ ሆይ በእግዚአብሔር ታመኚ /2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ለሥጋ መገዛት ነፍሴ ሆይ ምነው ቢቀርብሽ
ውርደት ነው ፍጻሜው ነፍሴ ሆይ የሚያከናንብሽ
መልካም የሆነውን ነፍሴ ሆይ ጽድቁን ተከተይ
ክርስቶስን መስለሽ ነፍሴ ሆይ ቸርነትን ሥሪ
#አዝ•••••••
ሞትን ማን ይመርጣል ነፍሴ ሆይ ሕይወትን በመጥላት
ከእንግዲህ መራቅ ነው ነፍሴ ሆይ ከስርቆት ከዝሙት
ጸጋ እንዲበዛልሽ ነፍሴ ሆይ የቃሉ በረከት
ከቤቱ አትጥፊ ነፍሴ ሆይ ፍቅር ከሞላበት
#አዝ•••••••
ለአንቺ ነበር ጌታ ነፍሴ ሆይ ደሙን ያፈሰሰው
ተሰቅሎ ሞቶ ነው ነፍሴ ሆይ ፍቅሩን የገለጸው
በፍቅሩ ለሰበኝ ነፍሴ ሆይ ለአፈቀረኝ ጌታ
ምስጋና አቀርባለሁ ነፍሴ ሆይ ዘወትር ጠዋት ማታ
#አዝ•••••••
ብወድቅ ምርኩዝ ድጋፍ ነፍሴ ሆይ ጋሻ ይሆነኛል
ለፍርድ አይቸኩልም ነፍሴ ሆይ በፍቅሩ ያየኛል
ማን እንደ እርሱ አለ ነፍሴ ሆይ የሕይወቴ ቤዛ
#አዝ•••••••
ተይ ተመከሪ ነፍሴ ሆይ ተይ ተመከሪ /2/
በዓለም መድኃኔት ነፍሴ ሆይ በእግዚአብሔር ታመኝ /2/
#ቢፈልግባትም_መልካሙ_ገበሬ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ፤
#አዝ•••
ለስልሶላት ነበር ሀይማኖት መሬቱ፤
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ፤
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ፤
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ፤
#አዝ•••
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች፤
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች፤
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ፤
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ፤
#አዝ•••
ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት፤
ጠባቂ መልዐኳ ተማጸነላት፤
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት፤
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት፤
#አዝ•••
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ፤
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ፤
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች፤
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች፤
#ኦ__የማይሞተው_ሞተ
•••✞•••✞•••✞•••
ኦ የማይሞተው ሞተ /2/
ሄደ ቀራንዮ እየተጎተተ
ወድቆ እየተነሳ እንዲያ እየቃተተ
ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ /2/
•••✞•••✞•••✞•••
እጅና እግሩ ታስሮ ሄደ አደባባይ
እየተገረፈ ታግሶ ስቃይ
አለቀሰች ቆማ ድንግል ማርያም
ተሰቀሎባት ልጇ መድሐኒዓለም
#አዝ•••••••
በአይሁድ አደባባይ ፍርድ ተንጋደደ
ወንበዴ ተለቆ ንፁህ በግ ታረደ
የማይሞተው ሞተ ለሰው ፍቅር ብሎ
ዋ ለቀራንዮ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ
#አዝ•••••••
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ስጋውን ለመኑ
እንዲፈቅድላቸው ሂደው ተማፀኑ
ገንዘው ቀበሩት በአዲስ መቃብር
ቅዱስ ቅዱስ ሃያል እያሉ በክብር /2/
•✞ #አለምን_ለማዳን ✞•
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞
ዓለምን ለማዳን የተሰቀለው
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው /፪/
#አዝ•••••••
ጌታችን ተሰቅሎ ሲያዩት መላእክት
በዝማሬ ፈንታ አለቀሱለት
ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው
አምላኩ እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው/፪/
#አዝ•••••••
ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም
ለጠላት የሚሞት በጭራሽ አይኖርም
ጠላቶቹ ስንሆን ለኛ የሞተው
ክርስቶስ ልዩ ነው ወደርም የለው/፪/
#አዝ•••••••
እውርን ቢያበራ የሞተን ቢያስነሣ
በመመስገን ፈንገታ ሆነበት አበሳ
ሰማያዊው ዳኛ ሊፈረድበት
ተከሶ ቀረበ በጲላጦስ ፊት /፪/
#አዝ•••••••
አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው
ሥጋና ደሙንም ለእኛ የሰጠው
ፍቅር አስገድዶት ለኛ የሞተው
መልካሙ እረኛችን መድኃኔዓለም ነው/፪/
#አዝ•••••••
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
☞ @EOTC2921 Channel
☞ @Ethio_Orthodox1 Group
4 374
#ጌታችን_መድሃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_በመስቀል_የተጓዛቸው_ጉዞዎች
☞✞ ጌታችንን ወደቀራኒዮ ሲወስዱት የተነሱብት ቦታ ገበታ/ገበጣ/ ይባላል፡፡ ይህ የጲላጦስ አደባባይ ነው፡፡ከዚህ ተነስቶ መስቀሉን ተሸክሞ እስከ ቀራኒዮ የደረሰበት ፍኖተ መስቀል ይባላል፡፡
#1ኛ_ምዕራፍ_የጲላጦስ_አደባባይ_ገበታ(ገበጣ)፦ ጌታችን ለፍርድ ከጲላጦስ የቀረበበት ምዕራፍ ነው ስሙም በዕብራይስጥ ገበታ በግሪክ ሊቶስትራ ይባላል፡፡
#2ኛ_ምዕራፍ_ጌታ_የተገረፈበት፦ ከሊቶስትራ ወደ ጌቴሴማኒ የሚወስደውን መንገድ ተሸግሮ ጲላጦስ ጌታን ገርፎ ይህ ሰው ያውላችሁ ያለበት ቦታ ነው የቦታው ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌታ የተገረፈበት ይባላል፡፡ ላቲኖች ገዳም ሰርተውበታል፡፡
#3ኛ_ምዕራፍ_ጌታ_መጀመሪያ_የወደቀበት_ቦታ፦ የቀድሞውን ስፍራ ወደግራ ትቶ ወደ ምዕራብ የሚወስደውን መንገድ ይዞ በደማስቆ በር መግቢያ የአርመን ቤተ ክርስቲያን ያለበት በሩ በሩ በብረት የታጠረ ትንሽ ክፍል ነው፡፡ ስሙም ጌታ የወደቀበት ቦታ ይባላል፡፡
#4ኛ_ምእራፍ_እመቤታችን_እያለቀሰች_ልጇን_ያገኘችበት_ቦታ፦ ከ3ኛ ምዕራፍ ትንሽ ዝቅ ብሎ ከአርመን ገዳም በስተግራ ካለው ማዕዘን ሲደርሱእናቱ ድንግል ማርያም እያለቀሰች ከላጇ ጋር የተገናኘችበት ቦታ ነው፡፡
#5ኛ_ምዕራፍ_ቀሬናዊ_ስምዖን_የጌታን_መስቀል_የተሸከመበት_ቦታ፦ ከ4ኛው ምዕራፍ 20ሜትር ያህል ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከተጓዙ በኋላ ወደቀኝ የሚታጠፈው መንገድ ነው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ ስምዖን ቀሬናዊ የሚባል ሰው ከእርሻ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ወታደሮች አግኝተውት አስገድደው እየጎተቱ ወስደው የጌታን መስቀል ያሸከሙበት ቦታ ነው፡፡ በዚህ ቦታ ላቲኖች ትንሽ መቅደስ ሰርተውበታል የሰምዖን መቅደስ ይባላል፡፡ይህ ስምዖን የተባለ የእስክንድሮስ እና የሩፎን አባት ነው ማር፡5፥21 ፣ ሮሜ፡16፥13 የእነዚህ ልጆች ቁጥር ከሰባ ሁለቱ አርድዕት ነው፡፡
#6ኛ_ምዕራፍ_ቤሮና/ስራጵታ/፦ በመሐረብ የጌታን ፊት የጠረገችበት ቦታ
ቤሮና የምትባል ሴት ከግፋቱ ጽናትና ከመስቀሉ ክብደት (እርጥብስለሆነ) የተነሳ ፊቱ የደም ወዝ አልብሶ ስታየው አዝና ፊቱን በነጭ መሐረብ ስትጠርግለት ወድያዉኑ አምላክነቱንየሚገልጥ ለበጎ ስራዋም ተስፋ የሚሰጥ ፣ሐይማኖቷን የሚያበረታታ የፊቱ መልክ እንዳለ በመሐረቡ ላይ ተገኘ፡፡ እሷም በዚህ ምክንያት እምነቷ እጅግ የጸና ሆነ፡፡ በዚህ ቦታ ላይ ግሪኮች መቅደስ ሰርተውበታል፣ በየሳምንቱ አርብ አርብ ይከፈታል፡፡
#7ኛ_ምዕራፍ_የጎልጎታ_መቃረቢያ፦ ከ6ኛ ምዕራፍ በግምት እንደ 100ሜ ያህል ተጉዞ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በሚወስደው መንገድ ከሰሜን አቅጣጫ መጥቶ ወደ ጽርሐ ጽዮን በሚያሳልፈው መካከለኛ መንገድ ላይ ነው፡፡ በጌታች ዘመን የከተማው መጨረሻ የምዕራቡ በር ይህ ነበር ይባላል፡፡ በዚህ ቦታ ትንሽ መቅደስ አለበት መቅደሱ የላቲኖች ነው ጥንት የከተማው በር ይባል ነበር፡፡
#8ኛ_ምዕራፍ_የጌታችንን_ስቃይ_ሴቶች_አይተው_ያለቀሱበት_ቦታ፦ ከ7ኛ ምዕራፍ 15ሜ ያህል ወደ ላይ ወጣ ብሎ የገኛል ጌታ መስቀሉን ተሸክሞ መከራ መስቀልን እየተቀበለ ሲሄድ ሴቶች እይተው እያለቀሱ ሲከተሉት ወደ አነርሱ መለስ ብሎ እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለኔ አታልቅሱ ለራሳችሁ አልቅሱ እንጅ ያለበት ቦታ ነው ሉቃ፡23፥27 ይህን ማለቱ ከ40 አመት በኋላ የሚመጣባቸውን መከራ በትንቢት ሲነግራቸው ነው! በዚህ ቦታ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የሆኑ መነኩሳት መኖሪያ አራት ቤቶች አሉ፡፡
#9ኛ_ምዕራፍ_መስቀል_ይዞ_የወደቀበት_ቦታ፦ አንድ የቆመ የድንጋይ አምድ አለበት በዚህ ቦታ ጌታ መስቀል ይዞ ወድቆበታል ፡፡ ይህ ቦታበወደ ጎልጎታ መውጫ በር ነው ቦታው የኢትዮጵያ ገዳማት መግቢያ ነው፡፡
#10ኛ_ምዕራፍ_የጌታችንን_ልብሱን_የገፈፉበት_ቦታ፦
#11ኛ_ምዕራፍ_ጌታችንን_የቸነከሩበት_ቦታ፦ ጌታችንን ልብሱን ገፈው እርቃኑን ካስቀሩ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በምስማር የቸነከሩበት ቦታ ነው፡፡
#12ኛ_ምዕራፍ_መስቀሉን_የቆሙበት_ቦታ፦ ጌታችንን መስቀል ላይ ከቸነከሩት በኋላ መስቀሉን ያቆሙበት ቦታ ነው፡፡
#13ኛ_ምዕራፍ_ቅዱስ_ስጋውን_ከመስቀል_ላይ_ያወረዱበት_ቦታ፦ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ኒቆድሞስ ጌታችንን ከመስቀሉ ያወርዱበትና ያሳረፉበት ቦታ ነው፡፡
#14ኛ_ምዕራፍ_ቅዱስ_ስጋውን_የገነዙበት_ቦታ፦ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ኒቆድሞስ ጌታችንን ስጋ የገነዙበት ቦታ ነው፡፡
#15ኛ_ምዕራፍ_ቅዱስ_ስጋው_የተቀበረበት_ቦታ፦ ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ኒቆድሞስ ጌታችንን ስጋውን በአድስ መቃብር ያሳረፉበት ቦታ ነው፡፡ መቃብሯ ቅዱስ ዮሴፍ ለራሱ ብሎ ከአልት ጠርቦ አዘጋጅቷት የነበረች አድስ መቃብር ናት፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
☞ @EOTC2921 Channel
☞ @Ethio_Orthodox1 Group
4 374
🌿🌿🌿 #ሆሳዕና 🌿🌿🌿
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15
የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡
የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።
⛪️✨⛪️✨ ሆሣዕና ✨⛪️✨⛪️
1⃣🌿ሆሣዕና ማለት ምን ማለት ነው?
#መልስ🌿✍ሆሣዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው።
2⃣🌿 በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሠራችን የምን ምሳሌ ነው?
#መልስ🌿1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፦ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ።
2. ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3. ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4. ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስሐ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው።
3⃣🌿 ጌታችን በዕለተ ሆሣዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም?
#መልስ🌿ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ " አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።" ዘካ. 9፥9
🌿በአህያ መቀመጡ፦
•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል።
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤ በቀላሉ ትወጣበታለህ፤ በቀላሉ ትይዘዋለህ፤ እንደፈለክም ታዘዋለህ፤
4⃣🌿ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘንባባ የመነጠፉ ምሥጢር የምን ምሳሌ ነው?
#መልስ🌿 1. ዘንባባ፡- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃም ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግኗል።
2. ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
3. ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው፤ የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4. ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
5. ዘንባባ እሾሃማ ነው፤ አንተ ሕያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
6. ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ። ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
5⃣🌿 ሕዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት ዓይነት ቅጠል አነጠፉለት ምን ና ምን?
#መልስ🌿 ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፦ ለክብሩ መግለጫ ነው።
ሌሎችም ሦስት ዓይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤ የቴመር ዛፍ፤ የወይራ ዛፍ አነጠፉለት።
6⃣🌿 ትልቅዋ አህያ በምን ትመሰላለች ውርንጭላዋስ?
#መልስ🌿 ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ናት።
1. ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ሕገ ኦሪትም የተለመደች ሕግ ናትና።
2. የእስራኤል ምሳሌ ነው፦ ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ሕግ ለመፈጸም በሕግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው።
3. የአዳም ምሳሌ ነው፦ አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና፤
🌿✍ውርንጭላዋ
1. በሕገ ወንጌል ትመሰላለች፦ ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረታት የሠራት አዲስዋ ሕግ ናትና።
2. በአህዛብ ትመሰላለች፦ ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ሕግህን የመቀበል የለመደ አይደሉም። ለሕግህ አዲስ ናቸውና።
3. የእመቤታችን ምሳሌ ናት፦ የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰላለች። እመቤታችን ድኅነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና።
7⃣🌿 አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል የሚለው ኃይለ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል???
#መልስ🌿 ዘካ. 9፥9
8⃣🌿 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ያልታሠሩ አህዮች እያሉ ለምን የታሠሩትን መረጠ?
#መልስ🌿✍አህዮቹ የታሠሩት ሌባ ሰርቆ ነው ያሠራቸው። ወንበዴ ሰርቆ ነው ያሠራቸው አህዮቹ ለጌታ ውለታ ሠርተዋል። ጌታ ሲወለድ አሙቀውታልና ለጌታ ውለታ ልንመልስ ያልቻልነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን። የታሠሩት እዲፈቱ የመረጠበት ምሥጥር፦ እኔ ከኃጢአታችሁ ልፈታችሁ የመጣሁ ነኝ ሲል ነው። ወንበዴው አህዮቹን ሰርቆ በመንደር እንዳሠራቸው ዲያብሎስም ለሰው ልጅ በኃጢአት ሰንሰለት ከሲዖል መንደር አስሯቸው ነበርና። ሐዋርያቱ ሲልካቸው ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በልዋቸው አላቸው። የፈጠራቸው እሱ ነውና።
🌿🌿🌿🌿🌿🌱🌿🌿🌿🌿🌿መልካም የሆሳዕና በዓል ይሁንልን።
ሆሳዕና በኣርያም!
