ch
Feedback
ራስን መለወጥ

ራስን መለወጥ

前往频道在 Telegram

እንዴት ናችሁ? ቢዝነስ ፕላን(ቢዝነስ ዕቅድ) እንዲሰራለት የሚፈልግ በተመጣጣኝ ዋጋ  ቢዝነስ ፕላን እንሰራለን! በውስጥ መስመር ያናግረን! ለውጥ በትክክልም ይመጣል። 💪ዕድገታችንም ይሳካል!!! Hello everyone, we make best Business plan. In good price contact us inside! just pick a what kind of business plan! We can chang

显示更多
9 785
订阅者
无数据24 小时
-337 天
-8230 天
帖子存档
photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

ራሳችንን እንድናስተውል የሚያደርጉ ምክሮች! ተገኘ ከማህበራዊ ሚዲያ ኤዲት በማድረግ t.me/changeitwow
ራሳችንን እንድናስተውል የሚያደርጉ ምክሮች! ተገኘ ከማህበራዊ ሚዲያ ኤዲት በማድረግ t.me/changeitwow

👉በ20መጨረሻ ዕድሜ እየደረሰ ነው። እነዚህ ነገሮች በህይወት ተግብራቸው‼️ 👂👂👂👂🧠🧠🧠🧠👂👂👂👂 1. የትኛውም አይነት ጎጂ ሱስ ካለብህ አሁኑኑ አቁም። ህይወትህን እስከወዲያኛው ያመሰቃቅለዋልና። ይህ ማለት ቁርጠኛ ሆን ነው። 2. አሁን የጉብዝና ጊዜ ከዚህ በኋላ ቢበዛ 15 ዓመት ነውና ጠንክረህ መስራት የምትችለው ማድረግ ስለምትፈልገው ነገር አተኩረህ አስብ ህይወት 2ኛ ዕድል ላትሰጥህ ትችላለችና። 3. ራስህን ከሰዎች ጋር ማወዳደርህን አቁም። ይህ ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚያስደስትህን ነገር የምታደርግበት ወቅት ነው። 4. በ20ዎቹ ዕድሜህ መጀመሪያ ሳትሰራው ስላለፍከው ነገር አትፀፀት። ያለፈ አልፏል አሁንም ቢሆን ከ20ዎቹ ዕድሜህ ባልተናነሰ ጠንክረህ የምትሰራበት ረጅም ጊዜ አለህ። 5. በፍቅር ግንኙነትህ መቀለድ የምታቆምበት ጊዜ ላይ ነህ። እዛም እዚም ማለት አቁም አንዷ ላይ ማምረር ግድ ይልሀል። 6. social media ላይ ጊዜ አታባክን። አሁን ጊዜህን ለወደፊቱ መሠረት የምታሲዝበት ወሳኙ ጊዜ ላይ። መጠቀም ግድ ከሆነብህም ጥቂት ሰዓት ብቻ ይሁን። ምርጫህም  በጥንቃቂ ይሁን። 7. መቆጠብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግድ የሚልህ ሰዓት ላይ ነህ በዚህ እንዳትቀልድ። የምትቀፍልበት ጊዜ ላይ አይደለህም። 8. የህይወት ዘመን ጓደኞች የምታፈራበት ወሳኙ ጊዜ ላይ ነህ መልካም ጓደኞች ይኑሩህ ለመልካም ህይወትህ ስትል። 9. አንድ ነገርን ሳትፈልግ እንድታደርግ የሚያደርግ የጓደኛ ወይም ሌላ ግፊት ካለ No ማለት ጀምር ይሉኝታ አይያዝህ። ከዚህ በኋላ ሌላ ዕድል አይኖርህምና። 10. ወላጆችህ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንተን ይፈልጉሀል። ዕድሜያቸው እየመረሸ ነው።  ምርጡ ጊዜህን ከነሱ ጋር አሳልፍ። 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 t.me/changeitwow

ኢንተርፕሪነር (ስራ ፈጣሪ) ምን ማለት ነው? EED መጋቢት 10/2017ዓ.ም ኢንተርፕርነር ማለት በራሱ ተነሳሽነት ያሉትን የንግድ ስራ አጋጣሚዎችን በመፈተሽና በመለየት በአካባቢ ያሉ ሃብቶችን በአግ
ኢንተርፕሪነር (ስራ ፈጣሪ) ምን ማለት ነው? EED መጋቢት 10/2017ዓ.ም ኢንተርፕርነር ማለት በራሱ ተነሳሽነት ያሉትን የንግድ ስራ አጋጣሚዎችን በመፈተሽና በመለየት በአካባቢ ያሉ ሃብቶችን በአግባቡ በመጠቀም በውጤት ላይ ያተኮረ ስራ ላይ የተሰማራ እና ሊመጡ የሚችሉ ችግሮችን ከወዲሁ በመገመት አስፈላጊውን ጥንቃቄ የሚያደርግና የተሰላ ሃላፊነት (calculated risk) መውሰድ የሚችል የንግድ ሰው ነው፡፡ ኢንተርፕሪነር (ስራ ፈጣሪ) እና በፈጠረዉ ስራ ከራሱ አልፎ ሌሎችን መቅጠር የሚችል ነዉ:: የጀመረዉን የንግድ ስራ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግር እና በዚህ የሽግግር እንቅስቃሴዉ ሁሉ ተጨማሪ የስራ እድሎችን የሚፈጥር፤አዲስ ምርትንና ሃብትን መፍጠር የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚያተኩር የንግድ ሰዉ ነዉ፡፡   ራዕይ ያለዉ የተጠና ንግድ ስራ ላይ ጊዜዉን፣ ገንዘቡንና ዕዉቀቱን የሚያዉል እና በእቅድ የሚመራ ያቀደዉን ራዕይና አላማ እዉን ለማድረግ የሚያስችል የፈፃሚነት ኃይልና ብቃት ያለዉ ነዉ፡፡   ለሚሰሩ ስራዎች የተሻሉ መንገዶች አሉ ብሎ የሚያምንና የሚሰራ እና ለዘመናዊ የንግድ ስራ ዘርፎች ላይ አብዛኛዉን ጉልበቱን፤ እዉቀቱንና ጊዜዉን የሚያዉል ነዉ፡፡   ኢንተርፕረነር ህብረተሰቡን የሚያነቃንቅና በሚፈጥራቸዉ አዳዲስ ነገሮች ህብረተሰቡን  የሚያንቀሳቅስ ነዉ  (Entrepreneurs are movers and shakers of the society) በአጠቃላይ ኢንተርፕረነሮች በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በፖለቲካዊ የሀገር እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ጉልህ ለዉጥ የሚያመጡ ሥራ ፈጣሪዎች ናችዉ፡፡ ራስን መለወጥ t.me/changeitwow

አንድ ተማሪ... ከፊቱ የተቀመጠ ልጅ ጀርባዉ ላይ "ደደብ" የሚል ፅሁፍ በወረቀት ላይ ፅፎ ይለጥፍበታል።ማንም እንዳይነግረዉ ሌሎች ተማሪዎችን ያስጠነቅቃቸዋል። ተማሪዎቹም ከጀርባው ላይ የተለጠፈዉን
አንድ ተማሪ... ከፊቱ የተቀመጠ ልጅ ጀርባዉ ላይ "ደደብ" የሚል ፅሁፍ በወረቀት ላይ ፅፎ ይለጥፍበታል።ማንም እንዳይነግረዉ ሌሎች ተማሪዎችን ያስጠነቅቃቸዋል። ተማሪዎቹም ከጀርባው ላይ የተለጠፈዉን ወረቀት እየተመለከቱ ሲስቁበት ዋሉ።በመጨረሻም የሂሳብ መምህራቸው ክፍል በመግባት ከባድ ጥያቄ ቦርዱ ላይ በመፃፍ "ይህን ጥያቄ የሚመልስ እጁን ያዉጣ?"ሲል ይጠይቃል። ይህንን ከባድ ጥያቄ ለመመለስ እጁን ያወጣዉ፣ጀርባዉ ላይ ስድብ የተለጠፈበት ልጅ ብቻ ነበር።ተማሪዎቹ እሱን እያዩ ለምን እንደሚስቁ ባይገባዉም፣ ወደ ብላክ ቦርዱ በመዉጣት ጥያቄዉን በአግባቡ መለሰ።መምህሩም ተማሪዎቹን እንዲያጨበጭቡለት አዘዛቸዉና ጀርባዉ ላይ ያለዉንም የተለጠፈ ስድብ አስወገደለት። መምህሩም ተማሪዎቹን እንዲህ አላቸዉ..... "ሰዎች እድገታችሁን ለማቅጨጭ በጀርባችሁ ላይ ማንነታችሁን የማይገልፁ ብዙ ቆሻሻ ነገሮችን ይለጥፉባችኋል።ይህ ከጀርባዉ ላይ ስድብ የለጠፋችሁበት ልጅ፣ የተለጠፈበትን ስድብ ተመልክቶት ቢሆን ኑሮ አሁን መልሱን ባልመለሰዉ ነበር። በህይወትም ዉስጥ ማድረግ ያለባችሁ ይህን ነዉ !!!ሰዎች ብዙ እንዳትጓዙ የተለያዩ መጥፎ ስሞችን ሊሰጧችሁና ከጉዟችሁ ሊገቷችሁ ይሞክራሉ።ስለዚህም ንቃችሁ እለፏቸዉና እያንዳንዷን አጋጣሚ ወደ ስኬት ለዉጧት።የሌሎችን ህይወት በማበላሸት የእኛን ህይወት መገንባት አንችልም።" ሰዎች ላይ ማንነታቸዉን በማይገልፁ ተለጣፊ ስሞች ተሰጥቷቸው ስንቶች መንገዳቸዉን ስተዉ ይሆን......? ከማህበራዊ ሚዲያ ራስን መለወጥ t.me/changeitwow

<ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ‼️> =+=+=+=+=+=+=+=+= ከላይ ያለው ምስል ታዋቂዋ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች maria Sharapova በዊምበልደን የቴኒስ ሻምፒዮና ላይ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኟ
<ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ‼️> =+=+=+=+=+=+=+=+= ከላይ ያለው ምስል ታዋቂዋ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች maria Sharapova በዊምበልደን የቴኒስ ሻምፒዮና ላይ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኟን ሴሪና ዊሊያምስን አሸንፋ ዋንጫ ያገኘችበት ቅፅበትን የሚያሳይ ምስል ነው ። እና ሴሪና ምንም እንኳን በማርያ ብትሸነፍም የማርያ መደሰት ሳይጎረብጣት አብራት ደስታዋን እየገለፀች ትታያለች ። ከስር ያለው የማርያ የተከፋ ፊት የሚታይበት ምስል ደግሞ እንደዚሁ በሌላ ወቅት ተገናኝተው ሴሪና ዊሊያምስ ባሸነፈችበት ወቅት የተነሳ ነው ። ... እና ይህን ምስል ያጋራው ዌብሳይት. .. " (There are two types of people in this world ) ከሚል ፅሁፍ ጋር ነበር ። አጋራን ዋሲሁን ተስፋዬ t.me/changeitwow

ድንቅ ታሪክ ከአሌክስ ገፅ 👍👍👍 ኤሊወች ትልቁ የደህንነት ዋስትናቸው የድንጋይ ልብሳቸው ብቻ አይደለም፤ የቆሙበትን መሬት ቆንጥጠው የመያዝ ብቃታቸውም ጭምር እንጅ። ጠላት ሲመጣባቸው ድንጋያቸው
ድንቅ ታሪክ ከአሌክስ ገፅ 👍👍👍 ኤሊወች ትልቁ የደህንነት ዋስትናቸው የድንጋይ ልብሳቸው ብቻ አይደለም፤ የቆሙበትን መሬት ቆንጥጠው የመያዝ ብቃታቸውም ጭምር እንጅ። ጠላት ሲመጣባቸው ድንጋያቸው ውስጥ ገብተው በቆሙበት መሬት በፅናት ከተቸከሉና መሬት ከያዙ ማንም አያነቃንቃቸውም። አንዳንዴ ታዲያ እርስ በእርስ ይጣላሉ። ያኔ "አወኩሽ ናቅኩሽ" ድንጋያቸው ውስጥ አይገቡም ፣መሬትም አይዙም። እርስ በእርስ ሲገፋፉና አንዱ አንዱን ለማሸነፍ ሲታገሉ አንድኛቸው ወይም ሁለቱም ይገለበጣሉ። ሲገለበጡ የደህንነት ከለላቸው የነበረው የድንጋይ ልብስ ከታች ስለሚሆን ራሱ ጠላታቸው ይሆናል። እንዳይነሱ በክብደቱ ይይዛቸዋል። እንኳን ሌላውን መግፋት እራሳቸውም ተመልሰው በእግራቸው ለመቆም የሌሎች እርዳታ የሚያስልጋቸው ደካማ ይሆናሉ። ያኔ ከወፍና አይጥ ጀምሮ ቀላል እንስሳት ሳይቀሩ ይጫወቱባቸዋል። አይናቸውን ያወጡታል፣ እግራቸውን እንደድንች ይፈረፍሩታል። በራሳቸው የድንጋይ ሳህን ለጠላቶቻቸው የቀረቡ ምግቦች ይሆናሉ። በሌሎች ይበላሉ። በቆማችሁበትን ፀንታችሁ ቁሙ፣ በአጉል መናናቅ አትገፋፉ። አንዳንዴ ከተገለበጥን ኋላ መነሳት እንደምናስበው ቀላል አይሆንም። በራሳችን አመለ ቢስነትና ትዕቢት ከስራችን የምንጥለው ዋስትና መከራችን ይሆናል። t.me/changeitwow

ጨካኙ የእግር ኳስ አለም ። .... ምግብ አይበላም ፡ በቂ እንቅልፍ ካገኘ ቆይቷል ፡ ከጭንቀት ጋር በተያያዘ የምግብ መፈጨት ችግር ስላጋጠመው ፡ ለሳምንታት የሚወስደው ሾርባ ብቻ ነው ። ..... ይህ ሰው በማንቸስተር ሲቲ ታሪክ ትልቁን ስኬት ያስመዘገበ ፡ ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ የሻምፒየንስ ሊግ ፡ ኮሚኒቲ ሼልድ ፡ ሱፐርካፕ. .  በአጠቃላይ 18 ዋንጫዎችን ለማንቸስተር ሲቲ ክለብ  ያስገኘ ፡ ምርጡና ውጤታማ አሰልጣኝ ነበር ። ...... ሆኖም ይህ ድል ብቻ የለመደ አሰልጣኝ ፡ ነገሮች እንዳሰበው ሳይሆን ቀርቶ በዚህ የውድድር አመት ውጤት ከሱ ራቀ ። ከዛስ. ... የሌላውን ተውት ፡ ትችትና ጥላቻው በራሱ ክለብ ደጋፊዎች ባሰ ። ለአመታት ባለድል እንዳላደረገ ያ ሁሉ ሙገሳ ከመቅፅፈት ወደ ጥላቻና ስድብ ተሸጋገረ ፨ እየደገፉ  ያሉት ማሸነፍና ፡ መሸነፍ ግድ የሆነበት የእግር ኳስ ጨዋታን ፡ መሆኑን የረሱ እስኪመስል ለአመታት ባለድል ሲያደርጋቸውን የቆየውን አሰልጣኝ ፡ በስድብ አሸማቀቁት ። ..... ይህ የደጋፊዎች ጭካኔና  ስድብ ከታዳጊ ልጁ ጋር እየሄደ ሁሉ የሚያጋጥመው ነገር ሆነ ። ....... እርግጥ ነው ማንም መሸነፍ ደስ አይለውም ። በተለይ እንደ ፔፕ ጋርዲዮላ አይነት ውጤታማ አሰልጣኝ ፡ አደለም የደጋፊ ትችትና ስድብ ተደምሮበት ይቅርና ፡ ውጤት ማጣቱ በራሱ ህመም ሆኖ ሳለ ፡ ሰውየው የሚያደርገው እስኪጠፋው ማዋከብ እና  የተደረገለትን የማይቆጥር ፡ ይሉኝታ የሌለው ደጋፊ መሆን ብዙም ደስ አይልም ። ..... ፔፕ ጋርዲዮላ በቅርቡ አድርጎት በነበረው ኢንተርቪው ፡ ወደፊት ወደ ሌላ ክለብ ሄዶ ማሰልጠን እንደማይፈልግ እየተንገሸገሸ ተናግሯል ። ማረፍ እፈልጋለሁ ፡ ሌላ ክለብ ለማሰልጠን ምንም ሀሳብ የለኝም ነበር ያለው ። ..... እንደው የቅርብ ጊዜ ስለሆነ የዚህን ሰው ነገር አነሳን እንጂ ፡ ውጤት ሲጠፋ ፡ ተጫዋቾችንና አሰልጣኞችን ፡ መፈጠራቸውን እስኪጠሉ ድረስ መስደብና ማማረር ፡ በእግር ኳሱ አለም እየተለመደ ያለ የጭካኔ ተግባር ነው ።  ..... ይህን ነገር ከኳስ አውጥተን ወደ ህይወት ስንወስደው ደግሞ ፡ የተደረገልንን እናስብ ። እንደማለት ይሆናል ከዋሲሁን ተስፋዬ ራስን መለወጥ t.me/changeitwow

photo content

#ድንቅ_ለሙያ_ያለ_ፍቅር💚 " ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝን ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም " - ዶ/ር በየነ አበራ በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች ከጠሩት የመልስ ፕሮግራም ላይ ላይ ተነስቶ በመሄድና የተሳካ ቀዶ ሕክምና በማድረግ እናትና ልጅን የታደገዉ የማህፀንና ፅንስ ስፖሻሊስቱ ዶክተር በብዙዎች ምስጋና ተችሮታል። ይህ የሚያስመሰግን ተግባር የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው። በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር በየነ አበራ በትላንትናው ዕለት በሰርጋቸው ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች በጠሩት የመልስ ዝግጅት ላይ ነበሩ። በዚህ ዝግጅት ላይ እንዳሉ ነው ከሚሰሩበት ሆስፒታል የስልክ ጥሪ የደረሳቸው። የስልክ ጥሪውም እናትና ልጅን እንዲታደጉ የቀረበ ነበር። ዶክተር በየነ ስለሁኔታው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ " መልስ በሀገራችን ባህልና ወግ ትልቅ ቦታ እደሚሰጠዉ አዉቃለሁ በዕለቱ አማቾቼ አክብረው ጠርተዉን ፕሮግራሙ እየተካሄደ ነበር ስልክ የተደወለልኝ " ብለዋል። " የመጀመሪያውን ዙር አላነሳሁም ፤ በድጋሚ ሲደወልልኝ አነሳሁት አንዲትን እናት ምጥ እንዳስቸገራትና ቀዶ ሕክምና የግድ እንደሚያስፈልጋት  ተነገረኝ፤ ለመሄድ አላመነታሁም " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል። በኃላም ዶክተር የመልስ ዝግጅቱን አቋርጠው የእናት እና ልጅን ሕይወት ለመታደግ እየከነፉ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ይወስናሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ጉዳዩን እንዴት ለሙሽሪት እንዳስረዱና ሙሽሪትን እንዳሳመኗት ጠይቋቸዋል። እሳቸውም ፤ " በፍቅር ሕይወታችን ወቅት የትዳር አጋሬን በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ እነግራት ነበር፤ በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር " ብለዋክ። " ለሙሽራዋ ባለቤቴና ለሚዜዎቼ ነገርኳቸዉና ወደ ሆስፒታሉ አመራሁ። ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝ ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም " ሲሉ ተናግረዋል። ዶክተር በየነ " ቤተሰቦቿን ግን ተመልሼ ይቅርታ ለመጠየቅ ወስኜ ነበር ወደ ሆስፒታል የሄድኩት " ብለዋል። " ወደ ሆስፒታሉ ስደርስ የቀዶ ሕክምና ቲሙ ዝግጁ ስለነበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌ ቀዶ ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል " ሲሉ ተናግረዋል። ዶክተር በየነ አበራ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሕክምና ትምህርት ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያገኙ ሲሆን የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ደግሞ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል። TikvahEthiopia ራስን መለወጥ t.me/changeitwow

photo content
+1

ኢ/ር ቢጃይ ናይከር እንደፃፈው ✍️ 🕹ትምህርት ወይሥ ሥልጠና? (ኑሮህን የሚደጉም በቂ ገቢ ከየትኛው?) ትማር.....ትማርና ተመርቀህ ወደ ሠፈርህ/ወደ ቀዬህ ትመለሣለህ....! በኛ ግዜ ሥትመረቅ.... እንደ ሠርግ ይደገሥልሃል።ሢጠብሽህ የምትሾተው የአንገት ሃብልና የ ጣት ቀለበት ፤ለ ሥራ ቅጥር ኢንተርቪው የምትጫማው ሹል ጫማ፣የምትታጠቀው ባለ ጠቃጠቆው ቀበቶ፣ሽክ የምትልበት የተተኮሠ ሸሚዝ .... ከሠፈርተኛው፣ከጓደኞች፣ከእድር፣ከዘመድ አዝማድ በሥጦታ ወደፊት በብድራት የምትመልሠው (የመለሠ ያለ አይመሥለኝም) ይበረከትልሃል!! ሃይሥኩል አብረሃት የተማርክ ለርኪ ፣ማትሪክ ቁሥለኛ አድርጎ ያሠናከላትና ሠፈር የቀረች፣ማህበረሠቡ የሚዘባበትባት.... ድሮ ትንሽ የተመቻቻችሁ - ደግሞ 'congratulation የኔ ፍቅር' የሚል የድሮ ፖሥት ካርድ ትገጭሃለች።ከዚህ ሃሜተኛ ማህበር መሃል ይዘሃት እንድትጠፋ ኦፈር ትሠጥሃለች። ትተማመንብሃለች 😂 ግና የተመረቀ ሁሉ ሥራ አይዝምና ...አራት ኪሎ የሥራ ማሥታወቂያ ለማንበብ ጆሊጋ ትኮለኮላለህ፣ሥራ ከየት ይምጣ? ዘመድ ከሌለህ፣አሪፍ ካድሬ ካላወቅህ፣የቀበሌ ሥብሠባ አተኩረህ ካልተሣተፍክ፣እንትን ካልሆንክ.... የተሠጠህን ሃብሉን፣ቀለበቱን፣ቀበቶውን፣ሹሉ ጫማህን፣የተመረቅህበት ሡፍህን ተራ በተራ ፒያሣና መርካቶ እየወሠድክ .... እየፖሸርክ ትቅ*ምበታለህ፣ ትጠ*ጣበታለህ፣ታጨ*ሥበታለህ፣ት***ታለህ። ¤¤ ሥራ እንዳገኘህ አይነት የሚያሠማህን የሥራ ማሥታወቂያ በ15 ሣንቲም ተከራይተህ ከ .... አዲሥ ዘመን፣ ወደ አዲሥ አድማሥ፣ ከ ፎርቹን፣ ወደ ሪፖርተር ......ትገለባበጣለህ....ሥራ ኢንጅሩ!😂 ትፈልግ ትፈልግና ትደክማለህ 6 ወር፣አንድ አመት፣ሁለት አመት ወዘተ ሥራ ፈት ትሆናለህ።አንተም ኮሚኒቲውም ትሠለቻቻላችሁ። በዜሮ አመት የሥራ ልምድ ማን ይቀጥርሃል? ኮታ እሥካልመጣ ድረሥ!? ለመሠደድ ሁሉ ታሥባለህ። 15 ሣንቲም የጋዜጣ ክራይ መክፈል ፣መ*ጠጫ፣ መ*ቃሚያ፣ማ*ጨሻ...ምናምን ይጠርርብሃል።ከዛሥ አይንህን ጨፍነህ ቤትህ ትቀራለህ፣ትነጫነጫለህ...ማሚህ፣ዳዲህ በድግሡ ግዜ እንዳልተደሠቱ ልባቸው ይሠበራል። በለሥ የቀናው ...አብራችሁ ተመርቃችሁ ደሞዝ ያለው ጀለሥህ በወር አንዴ ይለቅብሃል። እሡም ከበቃው። ¤¤ ይህ ማለት ተመርቀህ ኳሊፋይድ ሆነህ ነው።የሥራ አጥ ዳታቤዝ ማሞቂያ ትሆናለህ። ክህሎት(ሥኪል) የለህማ...... እዚጋ ነው....ከገባህበት አዝእቅጥ ለመውጣት ክህሎቶችን ባጋጣሚ በማየት ትሠለጥናለህ። ታቅፈህ ጥበቃ ትሠራህ፣ተመልክተህ ጋሪ ትነዳለህ፣ተደራጅተህ ኮብል ትፈልጣለህ፣ባጃጅ ትሾፍራለህ፣ሰልጥነህ ራይድ ትነዳለህ፣የሆቴል አሥተናጋጅ ትሆናለህ፣የሥፓ ጠባቂ ትሆናለህ፣ፓርኪንግ ትሠራለህ፣ትላላካለህ፣....መዝረፍ አትችልም!ተምረሃላ! በቃ qualification and skills የተራራቁበት ባህር ውሥጥ ትዘፈቃለህ። የመጀመሪያው ምታውቀውን እንዴት እንደምታሣይ ሢያደርግህ፤ሁለተኛው ክህሎት ደግሞ መሥራት የምትችለውን ነው። ለዚህ ሤናሪዮ ከኳሊፊኬሽን በበለጠ ክህሎት ረጂ ነው! ክህሎት በፍጥነት እና በተግባር ይለውጥሃል።ክህሎትን ለማግኘት ብዙ አመት እንደ ትምህርት አታሣልፍም።በሦሥት ወርበ ሁለት ወር ....ኮዲንግ ትሠለጥናለህ፣ሽያጭ ትሠለጥናለህ፣ሹፍርና ትሠለጥናለህ፣ወጥ መሥራት ትሠለጥናለህ፣ኢንትሪየር ዲዛይን ትሠለጥናለህ፣ብየዳ ትሠለጥናለህ ወዘተ :: ሪል ወርልድ ቻሌንጆችን በክህሎት ትወጣዋለህ።ጂያንቶች እንደነ ጎግል፣አፕል ክህሎት እንጂ ዲግሪ አይቀጥሩም።ሥንት ሢቪል፣ቢዝነሥ፣ሜካኒካል ወዘተ ተምረው አሜሪካ ገብተው ፕሮግራሚንግ በአጭር ግዜ ሠልጥነው የእለት እንጀራቸውን የሚዘጉ ነፍ ናቸው። ሞር ....ክህሎት ወደ ኢንተርፕሩነር የሚያሸጋግር ሃይል አለው።የእውነት አለም፣ገበያ ውሥጥ ልምምድ ሥለሚኖርህ። ከደሞዝ ይልቅ ንግድ ትርፍን ለማጣጣም የተሻለው...ክህሎት ላይ የተመሠረተ ተፍ ተፍ ፣በት በት ሢኖርህ ነው። የቻይኖች ተረት ...'ጦጣ ፊት ሙዝና ገንዘብ ብታሥቀምጥ...ሙዙን ይመርጣል። ጦጣው ገንዘብ ሙዝ እንደሚገዛ ሥለማያውቅ።' ይላሉ። በፊትህ ከደሞዝ ወይንም ከንግድ ትርፍ (wage or profit) ምርጫ ቢሠጥህ ...ከቅጥር ሥራ እና ከንግድ እንደ መምረጥ ያህል ነው። ብዙ ሠው የሚያውቀው ደሞዝ እንጂ ቢዝነሥ ብዙ ገንዘብ አለማምጣቱን ነው። ችግር የማይፈታ ትምህርት ያመጣው በዲግሪ ለአብዛኛው ጀማ... ድህነት እንዲነግሥብህ ፣አካባቢን እንዳታውቅ እና ፍርሃት እንዲጣባህ፣ ኢንተርፕሩኒያል ማይንድ ሤት እንዳይኖርህ ያደርጋል። የንግድ ኦፖርቹኒቲን እንዳታይ ያደርግሃል።ለጥቂቱ ይሠራል (ከጥቂቱ ከሆንክ እለፈው) ችግር የማይፈታ ትምሮ.... ብዙህ ግዜህን ት/ቤትና ምርምር ላይ እንድታሣልፍ ያደርግሃል።በዚህ ሃገር ትምህርት ቤቱም ለደሞዝ እንድትሠራ አድርጎ ቀርጾ ያወጣሃል።ለዛ ነው ብዙ ባለሃብት ያልተማረ.. ብዙሁን የተማረን ተቀጣሪ ያደረገው።...ጥሬ ሃቅ። ደግሞ መማር...የኢጎ፣የወረቀትና የድህነት ማማ ላይ ሠቅሎህ ቁጭ ይላል።ለራሥህ ችግርን የማይፈታ ትምህርት ራሥህን ሃሣብህን ከመሥራት ይልቅ ለሠው /ለሢሥተም እንድትሠራ ዘዴን ያሥተምርሃል። የንግድ ትርፍ ከላብ ምንዳ/ደሞዝ መብለጡንና አንተም አኳየር ማድረግ እንደምትችል አይነግርህም። ምንዳ ይደግፍሃል ትርፍ ግን ሃብትን ያመጣል። አብዝተህ ክህሎትን ፈልግ።ሠልጥን። ዲፕሎም፣ዲግሪ፣ማሥተርሥ፣ፒ ኤች ዴ እራሥህን እንዲሁም ማህበረሠብ ላይ ተቆጣሪ ለውጥ ካላመጣ የብላኔ ጥበብ ነው።ለኢጎ እና ለፎቶ ከመሆን አያልፍም። ትምህርት ላይ አጫጭር ተግባራዊ የክህሎት ሥልጠና ብትወሥድበት ሙሉ ይሆናል።ብቻውን ግን....😂👌 ትምህርት ወይሥ ሥልጠና? በርቱ! ከማህበራዊ ሚዲያ ራስን መለወጥ

12 የዕውቀት ጠብታዎች ከኖህ መርከብ!     ⚓️-⚓️-⚓️_ 1️⃣ ወደ መልካም ነገር የምትወስድህ ጀልባ ስትመጣ ፈጥነህ ተሣፈር፣ የመዳንህ መርከብ ስትቀርብ በቶሎ በእርሷ ላይ ውጣ፤ በሕይወት ዘመንህ አንዴ ካልሆነ ያቺን መርከብ ደግመህ ላታገኛት ትችላለህና – በፍፁም መርከብህን አታስመልጥ! 2️⃣ ሁልጊዜ ይህን ነገር አስታውስ፡- ሁላችንም ያለነው በአንዲቱ ጀልባ ውስጥ ነው፤ ጀልባይቱ ብትሰበር ሁላችንም እናልቃለን፤ ጀልባይቱ በሠላም ብትጓዝ ሁላችን እንተርፋለን! ይሄን አትርሳ – ሁላችንም ያንዲት ጀልባ ተጓዦች መሆናችንን! 3️⃣ በህይወትህ ልታደርጋቸው የምትመኛቸውን ነገሮች አስቀድመህ ዐቅዳቸው! ልብ በል፤ ኖህ መርከቡን መገንባት የጀመረው ዝናቡ መዝነብ ከጀመረ በኋላ አልነበረም! ደመናም በሠማይ ሣይዞር፤ የዝናብ ጉርምርምታም ሣይሰማ – አስቀድሞ ነው መርከቢቱን ማነፅ የጀመረው! 4️⃣ የአካል ጥንካሬህን ሁልጊዜም ጠብቀህ ተገኝ፤ ሁልጊዜም ብቁ ሁን! ማን ያውቃል? ምናልባት በ600 ዓመትህ፤ የሆነ ሰው ድንገት መጥቶ፤ አንድን እጅግ ታላቅ ነገር እንድታከናውን ሊጠይቅህ ይችላልና! 5️⃣ መናቆርን ብቻ ሥራዬ ብለው በያዙ ነቃፊዎች ትችት በፍፁም አትበገር! መሥራት ያለብህ ትክክለኛ ነገር ካለ፤ ዝም ብለህ ሥራህን ቀጥል! ለወሬኛ መድኃኒቱ ያ ነው – ትክክለኛ ሥራህ በስተመጨረሻ ይገለጣል! 6️⃣ ወደፊት ልትደርስበት አጥብቀህ የምትፈልገውን የህይወት ራዕይ፤ በታላቅ ሥፍራ ላይ አኑረው! ታላቅን ሕልም አልም! ለከበበህ ቁጥቋጦ ሣትበገር፤ ከፍ ባለ ሥፍራ ላይ የሕይወትህን ዋርካ ቀልስ! በታላቅ ሥፍራ ላይ የራዕይህን ማደሪያ መቅደስ ለመገንባት – አልመህ፤ ቆርጠህ ተነስ! 7️⃣ ጥንድ ጥንድ ሆነህ መጓዝ፤ ለክፉም ለደጉም ይበጃልና፤ ጉዞህ የተቃና እንዲሆን፤ ከጥንድህ ጋር መጓዝን አስብበት! 8️⃣ ከፈጣኖች እንደ አንዱ ነኝ ብለህ፤ በፍጥነትህ አትመካ፤ ፍጥነት ሁልጊዜም ላያድንህ ይችላልና! በደንብ አስተውል፤ በመርከቡ ውስጥ እኮ፤ ቀርፋፋዎቹ ቀንዳውጣዎችም፤ ፈጣኖቹ አቦሸማኔዎችም – ሁለቱም እኩል ፍጥነት ባለው ቀሰስተኛ መርከብ ተጉዘው ነው፤ በህይወት የተረፉት! 9️⃣ ጭንቀት ሲይዝህ፤ ካለህበት ነገር ወጣ በል፤ ትንሽ ዘወር በል፤ ለተወሰነ ጊዜ ቅዘፍ! ከችግርህ በላይ ሆነህ ስትንሣፈፍ – ያስጨነቀህ ነገር እልፍ ማለቱ አይቀርም! 🔟 ይህን ነገር ሁሌም አስታውስ፤ የኖህ መርከብ የታነፀችው ልምድ በሌላቸው በአማተሮች እጅ ነው! እንዲያም ሆኖ፤ ታላቅን ማዕበል ተቋቁማ፤ የተጓዦቿን ህይወት አተረፈች! ታይታኒክስ?  ታይታኒክ የተገነባችው፤ አሉ በሚባሉ ዕውቅ ባለሙያዎች ነው! ግን የአንድ ቀንን ማዕበል መቋቋም ተስኗት፤ ተሣፋሪዎቿን ውሃ አስበላቻቸው! አየህ አይደል? በሙያ ልቀት ብቻ አትመካ፤ ከሌሎችም ዘንድ ከአንተ የበለጠ ጠቃሚ መፍትሄ ሊገኝ እንደሚችል ዕወቅ! የታናናሾችህ የእጅ ሥራ፤ ህይወትህን የመታደግ አቅም ሊኖረው እንደሚችል – በዘመንህ ሁሉ አስብ!   1️⃣1️⃣ ማዕበሉ የቱንም ያህል ቢናወፅ፤ አምላክህ ከአንተ ጋር ካለ፤ ማዕበሉ ፀጥ እንደሚል፤ ቀስተደመናም በሠማይህ ላይ ሊወጣ እየጠበቀህ እንደሆነ፤ በፍፁም ልብህ እመን! የማዕበሉ ወጀብ በመንገድህ ላይ በርትቶ ሲፀናብህ፤ የአንፀባራቂው ቀስተደመናህ መውጣት እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያበሥር፤ አንዳች የተስፋ ምልክት እንደሆነ ዕወቅ!! 1️⃣2️⃣ በጉዞዎችህ ሁሉ ከላይ የተነገሩት ጥንቃቄዎች አይለዩህ! የቱንም ያህል ማዕበሉ በመንገድህ ቢፀና፤ በስተመጨረሻ ጉዞህ እንደ ኖህ የተቃና ይሆንልሃል! ይህ የሚሆነው ግን፤ ጉዞህን ከራስህ አልፎ - የሌሎችንም ሕይወት የሚታደግ እንዲሆንልህ አድርገህ ስታቅደው ነው! እንደ ኖህ፤ ያሰብከው ይሰምርልህ ዘንድ፤ ሥራዎችህን፤ ጥረቶችህን፤ በረከቶችህን ሁሉ ለሌሎች የሚተርፉ አድርጋቸው! መልካም ጉዞ! ቦን ቮያዥ! ⚓️♥️ _ የእንግሊዝኛ መልዕክቱ (ከከበረ ምስጋና ጋር):- «Everything I need to know about life, I learned from Noah’s Ark». ውርስ ትርጉም አሰፋ ኃይሉ(Assefa Hailu) ራስን መለወጥ t.me/changeitwow

ብዙ መጠሪያ ስሞች ያሉት ማይክ ታይሰን የሚሉት ቡጢኛ መቼስ ጉደኛ ሰው ነው። በጉብዝናው ዓመታት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ከስፖርቱ አግኝቷል። እንደ Rolls-Royce እና ፌራሪ የመሳሰሉ ከመቶ በላይ ውድ መኪኖች፣ ስድስት ቅንጡ ቤቶች፣ በርካታ የዳይመንድ ጌጣጌጦችን ሲሰበሰብ ኖረዋል። ለልብስ ብቻ ከሶስት ሚሊየን ዶላር በላይ ያወጣ እንደነበር ይነገራል። ሲዝናና እና ሲገዛ ለነገ አይልም። ከጓደኞቼ ጋር ዎክ እያረኩ ድንገት ወደሆነ መዝናኛ ቦታ እንሂድ ሲሉኝ ለሰከንድ ሳላቅማማ ወዲያው አዲስ መኪና ገዝቼ ይዣቸው ሄዳለሁ ይላል። ብራዘር እኔ እኮ ገንዘብ አጠፋለሁ..አይበረክትልኝም አትበል። ማይክ ታይሰን አለልህ። ይበትናል ቢባል እንኳ አይገልጸውም። የሚስቱን ገላ መታጠቢያ ገንዳ በተለየ ሁኔታ ለማሰራት ያወጣውን ብትሰማ ታብዳለህ። ለልደቷ ድግስ ብቻ ከ400 ሺህ ዶላር በላይ አውጥቷል። [ያውም በእነሱ 80'ዎቹ ውስጥ]። በስፖርቱ እጅግ ስኬታማ ነበር። ከ56 ግጥሚያዎች ውስጥ 50ውን አሸንፈዋል። ያውም 44ቱን በዝረራ። የጉብዝና ወራቱ ሲያልፉ ጡረታ ወጣ። ቁጭ ብሎ ጥሪቱን መብላት ጀመረ። ሱስ አጧጧፈ። ከዕፅ ጋር ተመቸቸ። ቁማር አስከተለ። ዝነኛው ቡጢኛ በአጭር ጊዜ ቀውስ ላይ ቀውስ እየጨመረ ተቃወሰ። በዚህ ላይ አስገድዶ የመድፈር ክስ እና እስር። የሃብቱ ተራራ በፍጥነት ተናደ። የገላ መታጠቢያን በወርቅ ያሰራላት ሚስቱ 9 ሚሊየን ዶላር ወስዳ ተሸበለለች። ተለየችው። ሌላ አገባ። እሷም ሃብቱን ተካፍላ እብስ አለች። ቀሪ ሃብቱን ቁማር እና መጠጥ ቤቶች ተከፋፈሉት። ጭራሽ መኪኖቹን እና ቤቶቹን በሙሉ በመሸጥ ወደ ዕዳ ገባ። 400 ሚሊየን ዶላሩን ጨርሶ ከ30 ሚሊየን ዶላር በላይ ዕዳ ተሸካሚ ሆነ። በብድር የተገዛትን መኪና ይዞ ለማደሪያ ጓደኛው ቤት በጥገኝነት ገባ። በወቅቱ በሰጠው አንድ ቃለመጠይቅ እንዲህ አለ [ ለሰላምታ የሚጠይቀኝ ሰው አልነበረም። የሚፈልጉኝ በሙሉ አበዳሪዎቼ ናቸው። እራሴን ጠላሁ። በጥልቀት መውደቄን አየሁ። የባከነ ሕይወት መምረጤን ተረዳሁ። እንደምንም በምንም ዋጋ ዕዳዬን ከፍዬ ከሰው ዓይን ዞር ማለት..ከአሜሪካ መራቅ ፈልግኩ ] ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ አዲስ ፀሐይ ወጣች። ከሱስ አገገመ። ከቁማር እና ዕፅ ራቀ። በተቋማት ታግዞ ዕዳውን ለመክፈል ዳግም ወደ ቦክሱ ሪንግ ተመለሰ። በተለያዩ ስፖንሰሮችም ታገዘ። ዕዳውንም መክፈል ቻለ። እንዳውም አሁን እስከ 10 ሚሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት አፈራ። እነሆ... ዛሬ ንጋት በ58 ዓመቱ ከወጣቱ ጄክ ፓውል ጋር ዳግም ቡጢ ይጋጠማል። በዚህም ተጨማሪ ሚሊየን ዶላሮችን ይዝቃል። 70 ሺህ ተመልካች ፊት የሚደረገውን የቡጢ ግጥሚያ Netflix ለ280 ሚሊየን ደንበኞቹ በቀጥታ ያስተላልፋል። እኔ ጠብ፣ ጠበኞች፣ ቡጢ እና ቡጢኞችም አይመቹኝም። ሰው እንዴት በድብድብ እንደሚዝናና አይገባኝም። የሆነ ሆኖ... 👍ማይክ ታይሰን ወድቆ የመነሳት ተምሳሌት ነው። ከማህበራዊ ሚዲያ ራስን መለወጥ t.me/changeitwow

ራስን መለወጥ - Telegram 频道 @changeitwow 的统计与分析