የስንኝ ቋጠሮ
前往频道在 Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
显示更多2 046
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
2 046
ሰላም እንዴት ናችሁ የተለያዩ ቪዲዮችን ለማህበራዊ ሚዲያ ቀርፃችሁ Edit ለማድረግ የጊዜ እጥረት እና የክህሎት ማነስ ላጋጠማችሁ Content Creater መልካም ዜና አለኝ በዝቅተኛ ዋጋ የቀረፃችሁትን Video ለእይታ በሚያምር መልኩ Edit አድርገን የእርሶን Social Media እናሳድጋለን
0932675770 ይደውሉ!!
2 046
መች እረሳሀለው አልወጣህ ከልቤ❤
ለሰከንድ ለአፍታ አልራክም ከሀሳቤ🧠
ለብቻዬ ስነድናፍቆት አይሎብኝ🙍♀️
አታየኝም 👀አባ ፍቅርህ አጓሳቁሎኝ🔗🖇
በእውነት አልተመቸኝአልደላውም ጎኔን
ችላ አትበለኝ ባክህ አታሳንስ ፍቅሬን
እኔ ሰበበኛ ሀዘን የማያጣኝ😭
ፍቅርህ አስከንፎ ካንተ ደጅ አመጣኝ🚶♀️🚶♀️
ተው ✋ይቅርብኝ ተዋብሽ አትበለኝ🥀
ከጎኔ ከሌለህ ምንም አያምርብኝ
ባይሆን ስትመጣ አንተ እቅፍ ስታደርገኝ🤗
የነጠፈው ወዜ ዳግም ተመልሶ የዛኔ ያስውበኝ👩
ያንን ቀን ወደድኩት አንተን ያጋመደኝ💏💑
ደስ የሚል ስቃይ😌 በላዬ ሾመኝ 😊
ደሞም ናፈኩት የተስፋውን ቀን
አብረን ምንውለው ማንም ሳያሳቀን👫
ለተራበው ልቤ ባክህ ቶሎ ናለት🚶♂️
መኖር አቅቶታል ትዝታህ አዳክሞት🙇♀️
ወይ አላገኘውህ ወይ ትቼ አልተውኩ
እማኝ በሌለበት ልቤን ላንተ ተውኩ 😌😌
❤❤❤❤ገጣሚ @gitmv ማህሌት
2 046
እውነት እየዘቀጠ ስፍራን እያጣ ሀጥዕ እየለመለመ እና ስፍራን እያገኘ በመጣበት በዚህ አለም የህይወት ፍርድ ተገማድሎበት መንገደኛው በሙሉ ብቻውን ቢያወራ እና እብዱን ከ ጤነኛው መለየት ቢያዳግት ተአምር አይደለም ሰው ሁሉ አብዷል! ነገር ግን የሚያስደንቀው ነገር የሰው የእብደት ምክኒያት በሙሉ ምድራዊ መሆኑ ነው! አዳሜው ሄዋኔው በሙሉ ትኩረቱን አፈር ላይ ሰፍቶታል ማበድ ብርቅ ባይሆንም ያበደበት ምክኒያት ግን እብደቱን ልዩ ያደርገዋል! ንጉስ ዳዊት በንግስናው ወራት እርቃኑን ሲዘምር መቼስ ንጉስ ነው ሁሉ በ እጁ ሁሉ በደጁ የሆነለት ሚፈልገውን ነገር ሳይንቀሳቀስ አዞ ማስመጣት የሚችል በኑሮ ቀውስ ነው ጨርቁን የጣለው ብንል ውሃ የማያነሳ ብይን ይሆንብናል።
ጨርቅ መጣል የ እብደት መገለጫ መሆኑ አያከራክርም ሆኖም የዳዊት ጨርቅ መጣል ግን መንሰኤው ከላይ ነው። ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛው ሰው የሆነ % አብዷል ኑሮ በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ ሁላችንም ማበዳችን አይቀርም። የኔ ጥያቄ ግን ማበዳችን ካልቀረ ለምን እብደትን አንቀድመውም? የሚል ነው! ለዳዊት የአቻ ነገስታቶች ስጋት ሳይበግረው የሚስቱ ማፈር ሳይበግረው አንድ አንድ ትኩረቱን የሳበ አምላክ ነበረው! ከ አምላኩ አንፃር ሌሎች ጉዳዮች በሙሉ ቀለሉበት ዘመን ሲከፋ ነገር ሲቀያየር ሁኔውታዎች ሲለወጡ የማይናጋ መሰረት እንዲኖረን ትኩረታችንን እርሱ ብቻ ይውሰደው ተባረኩ! ወንድማችሁ ሞገስ ነኝ! @gitmv
2 046
#3_ሰአት_ሙሉ_የ_ቲክቶክ_ተንቀሳቃሽ_ምስል_እያየን_3_ደቂቃ_መፃፍ_ማንበብ_ተራራን_የመግፋት_ያክል__ሚከብደን_ለኛ_ለዘመኑ ወጣቶች አጭር መጣጥፍ መፃፍ ራሱ ድንጋይ ላይ ውሃን እንደማፍሰስ የሚቆጠር ቢሆንም ድሮ ልጆች እያለን አምሳ ሳንቲም ይዘን ዘፈኑን፣ ኮሌክሽኑን፣ እና ሙሉ የ ህንድ ፊልም ከ 3-4 ሰአት የሚያህል ቁጭ ብለን ለማየት የነበረን #ትዕግስት አሁን ስም ብቻ ሆኖ መቅረቱን ሳስብ ይገርመኛል። አሁን ላይ ላለን ወጣቶች አንድ ነገር ላይ ረጅም ሰአት መቆየት የንገፈግፈናል ቤተክርስቲየን ገብተን 20 ደቂቃ ስንቀመጥ የሚያፍሽገን መፅሃፍ ቅዱስን ወይም ሌሎች መፅሃፍትን ለማንበብ ስንቀመጥ ከሶስተኛው ገፅ በሁአላ የሚያቁነጠንጠን ትምህርት ለማጥናት ስንቀመጥ አይናችን ውሃ የሚቋጥረው ነገር ለምን ይሆን? አሁን ላይ በ ሃገራችን ሆነ በ አፍሪካ ብሎም በ አለም ላይ ለተጋረጠብን ድቅድቅ ጨለማ ብርሃን መሆን የምንችለው በ አንድ ነገር ላይ ጥልቅ የሆነ እውቀት እና መረዳት ሲኖረን ለዛ ነገር ፈላጊ(demand) አቅርቦት(supply) እንሆናለን። ለ አንድ ነገር ጥልቅ የሆነ መረዳት ሊኖረን የሚችለው በዛ ነገር ላይ መቆየት ስንችል ብቻ ነው። ስለዚህ እዚህም እዚያም እየረገጥን ወደ ጎን ከምናሰፋ የተወሰነ ቦታ መርጠን ወደ ጥልቅ ብንቆፍር ምንጭ እናገኛለን ተገፍተን የማንወድቅ ስር የሰደድን እንሆናለን። እንታገስ! እንቆይበት! ወንድማችሁ ሞገስ ነኝ። ከታዘብኩት @gitmv
2 046
ቃል ነበረ በሰው የተሰበረ
እንደ አሞራ ገደል የተሸረሸረ
ለሰው የተሰጠ በሰው የተሻረ
ቃል ነበረ!
እንደ ወርቅ የነፃው ከውሃ እኩል የጠራው
ድብልቅልቅ ብሎ
ዛሬ ላይ ቢያጣ ከውሸት ሚያጠራው
ቃሎች?
ክብራን ነበሩ ልክ እንደ እንቁ
ዛሬ ላይ ተገፍተው ተጥለው ቢወድቁ
ዛሬ ላይ!
ሚያነሳቸው አጥተው ቢመስሉ ትቢያውን
ውስጣቸው ንፁ ነው አይመስሉም ጣይውን
ጣይውን ቢመስሉ ከድሮም አይኖሩ
ለኛም አይሰጡን ከላይ ከእግዜሩ
✍️🏽በሰለሞን
2 046
ለምን ቀረሽ
ሳልኖር ካንቺ ጋር፣
ሳላቀው ስሜቱን ሳልኖር በቅፍሽ ውስጥ፣
ሳለየው ጠረንሽን ሳይቀር ልቤ ውስጥ።
ላክሽኝ ተስፋ ሞልተሽ ከማላቀው ሰው ጋር።
ጉንጮቼን ደባብሰሽ አቅፈሽ ስትስሚኝ፣
እንባዬን ጠራርገሽ በስስት ስታይኝ፣
መች ገባኝ እማዬ ቻው እንደምትይኝ፣
እመጣለሁ ልጄ መሸት ሲል ቀኑ ነበር እኮ ያልሽኝ።
ቀኑም መሸት ሲል ጀንበር አዘቅዝቃ ወደ ቤቷ ገባች፣
ተረኛ ጨረቃም በከዋክብት መሀል አሸብርቃ ወጣች።
እኔም ወጣሁ ከቤት መምሸቱን አይቼ፣
ከበራፉ ቆሜ እጠብቅሽ ጀመር እስካይሽ ጓጉቼ፣
አቅፌ ልስምሽ አጆቼን ዘርግቼ።
ግን ግን ግን
አልመጣሽም እማ
ለምን እንደቀረሽ ሚነግረኝ አጣሁ፣
የኔንም መጠበቅ ላንቺ የሚነግር ተላላኪም አጣሁ።
ታዲያ ለምን ቀረሽ እመጣለሁ ብለሽ?
ምን እንቅፋት ያዘሽ ልጅሽ እንዳታይሽ።
MW
13-07-2015
2 046
ቶሎ ና🏃💨
ቆሜያለው ከደጁ 🏠ናፍቆትን አርግዤ😔
ትመጣለህ👣 የሚል ትንሽ ተስፋን ይዤ
ከብርዱ እንድሸሸግ እቅፍን ናፍቄ
ከጉያዬ ውስጥ ፍቅርን ❤አምቄ
እየጠበኩህ ነው👤
.
.
ብርዱ ሳይጠናብኝ እባክህ ቶሎ ና
ብቻዬን እንዳልሆን ስጎዝ በጎዳና
ትመጣልኛለህ ከቅፍህ እንድኖር
ከአለም እርቀን በፍቅር እንድንበር💓
አሰብከው አለሜ💑
.
.
አነስ ባለ ጎጆ በእሳት በሞቀ
በ'ቅፍህ ውስጥ ሆኜ ፍቅርን ባመቀ
ልባችን ታድሞ ከጣፋጩ ዜማ
ከእሳቱ ዳር🔥 ሆነን መውደድን ስንሰማ
ለማይደገመው ለዚ ጣፋጭ🍯 ጊዜ
ዝናብ ☔ብርዱን ችለህ ቶሎ ና በጊዜ⏳ Be Mahi
2 046
አትሳቅ
መክነፌ ሳያንሰኝ በአይኖችህ 👀ውበት
መድከሜ ሳይበቃኝ ውሉን ሳላውቅበት
በፍቅርህ ቀንበር ውስጥ የተያዘ ልቤን 🫀
ላስመልስ ሰታገል የወሰድከው ቀልቤን
ትቼህ እንዳልተውህ በሀሳቤ 🧠እንዳልፀና
ስቀህ አታለልከኝ ጥርስህ ይርገፍና😁
በ ማህሌት
2 046
አትሳቅ
መክነፌ ሳያንሰኝ በአይኖችህ 👀ውበት
መድከሜ ሳይበቃኝ ውሉን ሳላውቅበት
በፍቅርህ ቀንበር ውስጥ የተያዘ ልቤን 🫀
ላስመልስ ሰታገል የወሰድከው ቀልቤን
ትቼህ እንዳልተውህ በሀሳቤ 🧠እንዳልፀና
ስቀህ አታለልከኝ ጥርስህ ይርገፍና😁
ተፃፈ በ ማህሌት
2 046
Repost from የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
በማለዳ የዚህችን ወጣት ሴት፣ በዚኹ በፊት ገጿ(facebook) ላይ እንደምትሰናበት ጽፋ ራሷን ማጥፋትዋን ሳነብ ከልብ አዝኛለሁ። አብሮ በተያያዘ ጉዳይ ግን፣ በረጅም የጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶች፣ በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ሊያልፉ፣ ለከባድ ጭንቀት ሊጋለጡ፣ ብሎም ሳይናገሩ ራሳቸውን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ሳስብ ይሰቀጥጠኛል።
ምድርን እግዚአብሔር የሰጠን እንድንከባከባትና እንድንጠብቃት፤ እንድንኖርባትም እንጂ ለሰዎች የማትመች "ደባሪ ስፍራ" እንድናደርጋት አይደለም። የአገር መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶች ... ቢቻላችኹ ምድራችንን ከጭንቀትና ከጦርነት ዐሳርፋችኹ በሰላም እንድንኖርበት "ፍቀዱልን"።
2 046
ድል ነው
ያመደ ቢወዛ ድፍርሱ ቢጠራ
ያለቀሰ ቢስቅ ፅልመቱ ቢበራ
እድል ሳይሆን ድል ነው የ አምላኩ ውጊያ
የጭንቅ ቀን ፀሎት መልስ ነው ማብሰሪያ
2 046
ትዝታ ሲናፍቅ
እውነት አንዳንዴ ትዝታ ምንም ክፋት የለው፣
ከዛሬ ይሻላል ድንቅ ቀለም አለው ፣
ትናንት የሆነውን ወደሗላ እያዩ፣
ስንት ደስታ አለው ትዝታ ከላዩ፣
ከላይ ካፋፍ ካፋፍ፣
ትዝታ ሲገዝፍ ፣
ትዝ ትዝ የሚለኝ ፍቅራችን ነበረ፣
በደስታ ተገምዶ በጥብቅ የታሰረ ፣
አሁን ግን ትዝታ የነበር ቃል ድርሳን ፣
ልባቺን ሊነደል ቀስ በቀስ ያሳሳን ፣
ውል የነበረበት ቃል የተፃፈበት ፣
አሁን በትዝታ ነበር የሆነበት ።።
ት
ዝ
ታ
ትዝታ ክፋትም አለበት
ላይመለስ ነገር ህመም ሆኖ ያልፋል፣
ትዝታ ህመም አለበት ውስጠት ልብ ያቆስላል፣
በትላንት ላይ እሾህ ይተክላል፣
ሰርክ እየታሰበ ደስታን ያሳድፋል ፣
ንፉግ ሀሳብ የማይመለስ ተስፋ ጥሎ ፣
ህመምን ከደስታ እኩል አስከትሎ፣
ግና ምን ይደረግ
ህይወት ነው አቀበት፣
ተራራ ቁልቁለት ፣
ሜዳ ደልዳላ ነው ስቃይና ድሎት፣
ክፉ ነው ትዝታ
✍️አቤል አረጋ
(አቡ) @son_abu
2 046
ውርደትሽ አንሷቸው ውርደት ሊጨምሩ
ይኧው አየናቸው
መጥፎ ያልናቸውን መርቀው ሲምሩ
በገዛ ራሣቸው ትውልድ እየገዙ
ጥሩ ያሉት ሥራ መጥፎ እየሆነ ስንቴ ተወገዙ
በቀል ያረገዘን የህማማት ሥቃይ
እንድንሸከመው አረጉን መርቀው አውራጅና አሰቃይ
ማነው ያደረጋቸው ነፋጊና ከልካይ
ማነው ያደረጋቸው ነቃይና ተካይ
ሁሉም በየድርሻው
ሁሉም በየእርሻው ላብ አለኝ እያለ
የማይጠፋ አሻራ ጠማማ ችግኝን አፍልቶ ተከለ
ዝቅታሽ አንሷቸው ይባሱን
ሊያዘቅጡሽ
ይኸው አየናቸው፣
መላቅጥ ጠፍቷቸው መላቅጥ ሲያሳጡሽ
ከፍ ካለ ቦታ ዝቅታውን መርጠው
የተቀጠለውን ከመሐሉ ቆርጠው
እኔ ነኝ እያለ ፎካሪም ቀራሪም
እኔ ነኝ እያለ ጨራሽ አስጀማሪም
አተኳኮስ ማያውቅ አያነጣጥርም
ምላሠ ኮልታፋ አያቀጣጥርም
ወትሮስ ዘሩን እንጅ ስንዴውን አይቆጥርም
ሕመምሽ አንሷቸው ሕማም ሊደርቡ
ይኸው ታዘብናቸው፣
ከህማም ጎተራ ሰበዝ ሲሸርቡ
ማነው የሚያቅተው ጥያቄ ማነብነብ
ማነው የሚከብደው ሠማይን ማዘነብ
ሁሉም እየሆነ አቧራ አራጋቢ
ሁሉም እየሆነ በቁስል አንገብጋቢ
ፈዋሽ ነው ያጣነው የተራበ አጥጋቢ
መሆን ቢያቅታቸው ለችግርሽ ደራሽ
እንዴት ይሆናሉ እንቅፋትን አውራሽ
መሆን ሲገባቸው ሕመምሽን ጠጋኝ
እንደምን ይላሉ የናቴ አጥር ወጋኝ
እናም
በተቆራረጠ ባረጀ ዘመን ላይ ዓመታት ያልፋሉ
እነዚያ ዓመታቶች መቼም የማይጠፋን ታሪክ ይጽፋሉ
እነዚያ ታሪኮች ዘመን ያስቀራሉ
እነዚያ ታሪኮች፣
ለአንዳንዱ ሕይወትን
ለአንዳንዱ ሞትን ይመሰክራሉ
በተበጣጠሰ ባልተቀጣጠለ
የታሪክን ሊያፋልስ ማን የኑሮ ለጠለ
ባልታከመ ሥጋ ባልደነደነ አንጀት
እንዴት ይታሰባል እየዋሉ ማርጀት
እንደምን ይሆናል የዕድሜ ጣራን መፍጀት
✍Eyuel
