ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 951 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 316,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 234 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 951 名订阅者。

根据 21 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 408,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.79%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.92% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 113 次浏览,首日通常累积 1 742 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 29。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 22 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 951
订阅者
+124 小时
+1627 天
+40830 天
帖子存档
#አንኳን_አደረሳቹህ ኅዳር ፲፪፤ #ቅዱስ_ሚካኤል በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡ #በዓለ_ሢመቱ_፥#ወበዓለ_መራኄ_ፍኖቱ_ለቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት_፨ ፨፨፨ #Share ያድርጉ ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ) ፠ #፩ በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡ ፨፨፨ ፠#፪ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ #Share ያድርጉ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

#ኀዳር_11 በዚህችም ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች ቅድስተ ሐና ዐረፋቷ ነው፡፡ #share ያድርጉ #ቅድስት_ሐና በኢየሩሳሌም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነው የማጣት ልጅ ናት፡፡ ____ #ማጣትም 3 ልጆች አሉት እነርሱም ፤ #የመጀመሪያይቱ ስሟ ማርያም ናት፤ አዋላጅ የነበረች ስተሆን ቅድስት ሰሎሜን ወልዳለች ፤ ሰሎሜም እመቤታችን መድኃኒታችን ከተወለደችው ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ያገለገለቻት ናት፡፡ #ሁለተኛይቱ ስሟ ሶፍያ ፤ ይህቺ ቅድስተ ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እናት የሆነችውን ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች፡፡ #ሦስተኛይቱም ስሟ ሐና ነው፤ ይህች ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙም ኢያቄም ከሆነ ጋር ተጋብታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት፡፡ ሰሎሜና ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን እናት ለሆች ለቅድስት ሐና እኀትማማች ናቸው፡፡ _____ ቅድስት ሐና መካነ እያለች አምላክን ልጅ እንዲሰጣት እጅግ አብዝታ ትለምን ነበር፡፡ እግዚአብሄርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኀነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችን የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡ ቅድስት ሐና ከሴቶች ሁሉ የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን አምላክን ለወለደችልን ለቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም እናት ሆና አይተናል፤ ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ጸጋ ባልተገባት ነበር፡፡ _____ ምልጃዋ አይለየን ፡፡ ሃገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ትጠብቅልን አሜን! በቦታው ሄዳቹ በዓሉን ማክበር ለምትፈልጉ👇🏼 ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. ና በሌሎች የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያተ ክርስቲያናት ... ፠ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤ/ክ ፠ ኮተቤ መካነ ቀረዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ እንዲሁም፡ ፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና:: ሌሎች በዓሉ የሚከብሩባቸውን ቦታዎች ይጠቁሙን ፨፨፨ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

እንኳን ለቅድስት ሐና በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ፡፡ ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያተ ክርስቲያናት ፠ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤ/ክ ፠ ኮተቤ መካነ ቀረዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ እንዲሁም፡ ፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና::

ኅዳር ፱፤ የሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) ክብረ በዓል ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ፤ ሐመረ ኖኅ ሠለስቱ ምዕት ቤ.ክ፤ በሃገራችን በሠለስቱ ምዕት (በ318ቱ ሊቃውንት ስም) ብቸኛ የሆነውና በአሁኑ ሰዐት ከ4ቱ የመጻሕፍት ጕበኤያት በኢትዮጵያ ደረከጃ የመጻሕፍተ መነኰሳት ዋና ማስመስከሪያ የሆነ ነው፡፡ ፠ በሃገራችን በሠለስቱ ምዕት (በ318ቱ ሊቃውንት ስም) ብቸኛ የሆነውና ከ311 ዓመታት በፊት በአፄ ቴዎፍሎስ (ስመ መንግሥት አጽራር ሰገድ) ታንጾ የነበረ ሲኾን ንጉሡ ሲያንጹትም የሠለስቱ ምዕት የአእላፍ መላእክትና የነቢያት ቤተ ከርስቲያን አድርገው ነው፤ ድርቡሽ ጎንደርን ከ130 ዓመታት በፊት በወረረ ጊዜ ጠፍ ኹኖ ቆይቶ በ2007 ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያኑ ድጋሚ ተሠርቶ፤ እነሆ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡ ፠ ይህ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጕባኤ ቤትም ሲኖረው፤ ቀድሞ የ4ቱ ጕባኤያት ዋና ማስመስከሪያ ኹኖ ቆይቷል፤ ከአፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ መነኰሳት ዋና ማስመስከሪያ ኹኖ ይገኛል፡፡ ፠ ፎቶ ላይ የምትመለከቱት የሠለስቱ ምዕት የመጻሕፍተ መነኰሳት ጕባኤ ቤት ከዋናውና ከጥንቱ የመጻሕፍተ መነኰሳት ጕባኤ ማሄጃ ብራና መጻሕፍት ጋር በእሳት አደጋ በተቃጠለበት ወቅት፤ በጎንደር የሚገኙ፤ በኢትዮጵያ ደረጃ ዋና የመጻሕፍተ ብሉያት ምስክር መምህር ዘዐቢየ እግዚዕ ኪዳነ ምሕረት (መምህር ኤልያስ)፤ በኢትዮጵያ ደረጃ ዋና የመጻሕፍተ ሐዲሳት ምስክር መምህር ዘግምጃ ቤት ማርያም (ሊቀ ማዕማራን ወመጋቤ ሐዲስ ወልደ ሰንበት ባይነሳኝ)፤ በኢትዮጵያ ደረጃ ዋና የመጻሕፍተ ሊቃውንት ምስክር መምህር ዘመንበረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም (ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ) በአንድ ላይ ሁነው፤ ፠ በኢትዮጵያ ደረጃ ዋና የመጻሕፍተ መነኰሳት መምህር ዘሠለስቱ ምዕት የሆኑትን (መጋቤ ምሥጢር ወመጋቤ ምክር መምህር ተሾመ ታደሰን)ና ቀደ መዛሙርቶቻቸውን ሲያጽናኑ የሚያሳይ ነው፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

#ኅዳር_፰ #ተዝካረ_አበው_(ኅዳር ፮-፰) share ያድርጉ ፠፠ በታላቁ ገዳም በዋልድባ/ዋሊ/ ብቻ ለሚደረገው የተዝካረ አበው (የዋልድባ አባቶች መታሰቢያ) አደረሳችሁ ፥ አደረሰን፨ በኢትዮጵያ በብቸ
#ኅዳር_፰ #ተዝካረ_አበው_(ኅዳር ፮-፰) share ያድርጉ ፠፠ በታላቁ ገዳም በዋልድባ/ዋሊ/ ብቻ ለሚደረገው የተዝካረ አበው (የዋልድባ አባቶች መታሰቢያ) አደረሳችሁ ፥ አደረሰን፨ በኢትዮጵያ በብቸኝነት ጌታችን በመሠረተው በዚህ ታላቅ ገዳም በዋልድባ ብቻ ከሚደረጉ ሥርዐቶች መካከል አንዱና ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው መካከል፤ ከሰኔ ፳፩ ጀምሮ የወጣ ሳይገባ፥ የገባ ሳይወጣ (መርፌም ቢኾን ከሱባዔው በፊት ወደ ገዳሙ ካልገባ ሱባዔው እስኪያልቅ ጥቅም ላይ አይውልም)፨ የ158 ቀናት ሱባዔ ይደረጋል፤ ከ140 ቀናት በኋላ ከኅዳር ፮ - ፰ ተዝካረ አበው ይደረጋል፤ በሱባኤ የቆዩ አባቶች በማኅበር ደረጃ ይሰባሰባሉ፤ መልሰው ከኅዳር ፱ ጀምረው ደግሞ እስከ ኅዳር ፳፬ ወደ ሱባዔ ገብተው በ፳ወ፬ቱ ካህናተ ሰማይ ትልቁ ሱባዔ ያበቃል፤ ከኅዳር ፳፬ ጀምሮ ወደ ገዳም መግባት መውጣት ይፈቀዳል፨ በእነዚህ 158 የሱባኤ ቀናት (ከሰኔ ፳፩ - ኅዳር ፳፬ ድረስ)፤ ከቀባሪ በስተቀር ወደ ገዳሙ መግባትም አይቻልም፨ ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ለዘይሴኒ እምወይን፤ ወእምነ ሐሊብ ጣዕሙ እንተ ይሠምዮ ልሣን፡፡ አበው ቀደምት ዘአብረንታንት ቅዱሳን፤ እለ ሕገክሙ ዘእንበለ ፍሬ ምኑን፤ ከመ ኢያብኡ እክለ በዛቲ መካን፡፡ ፠፠ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ከአርጋብ ጸዓድዒድ ቅዱሳን አበው አንድነት፥ ከአቡነ ሳሙኤል ልጅነት፥ ከገዳመ ዋሊ ረድኤት በረከት ይክፈለን፨ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w