Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 789 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 373,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 257 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 789 名订阅者。
根据 16 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 239,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 9.68%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.16% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 528 次浏览,首日通常累积 1 605 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 14。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 17 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 789
订阅者
+124 小时
+1667 天
+23930 天
帖子存档
በወርኀ ክረምት እና በወርኀ መስከረም ለተመረቃችሁ
ለሰ.ት.ቤት አባል ወንድምና እና እህቶቻችን በሙሉ፤
👩🏻🎓«እንኳን ደስ አላችሁ»👨🏻🎓
የማኀሌተ ጽጌ ትርጓሜ
ማኀሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቀፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕይ ፤
አመ ቤተ መቅደስ ጌሥኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፡፡
ንዒ ርግብየ ትናዝዘኒ እምላህ ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከሚኪ ርኀሩኀ፡፡
#share
#ትርጉም
ጌታ ከወፎች ሁሉ በመረጣት ርግብ የተመሰልሽ መልካሚቱ ርግብ ማርያም ሆይ (ዕዝ 3.26 ) #ነጭና #ቀይ መልክ ያለው (በአምላክነቱ ነጭ ፣ በሰውንቱ ቀይ የተባለ ) #አበባ ልጅሽን (መኃ 5.10) ታቅፈሽ ፤ #በ40 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እንደገባሽበት ጊዜ ሁሉ ፣ ደስ ካለው ከገብርኤልና እንዳ አንቺ ረኀሩኀ ከሆነ ከሚካኤል ጋር ፣ ከኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዩ፡፡
ትርጓሜ
፨ጌታችን ወደ ቤተ መቅድስ የገባው በ40 ቀኑ ነው የገባውም ከርግብ እና ከዋኖስ ጋር ነበር የታቀፈውም ካህኑ ዘካርያስ ነው ዕለቱ ም የካቲት 8 ነበር፡፡
፨እንደ ርግብ የዋህ ሆና የተፈጠረች ሔዋን የዲያቢሎስን ተንኮል በለማወቋ ስታለች [1]፡፡
፨ዳግሚት ሔዋን የተባለች #ማርያም ግን በንጽሕና በቅድስና ተሸልማ መልኳማ ርግብ እየተባለች ትመሰገናለች፡፡
ቅዱስ #ገብርኤል #ደስተኛ መልአክ መባሉ ፣ ጌታ ማርያምን አብስራት ሲለው ደስ እያለው መጥቶ ፣ ደስተኛይቱ ማርያም ሆይ #ደስ_ይበልሽ እይለ በማብሠሩ ነው [2]
፨ቅዱስ #ሚካኤልም እንዳ አንቺ #ሩኀሩኀና አዛኝ ነው መባሉ እመቤታችን የምህረት እናት #አዛኝ እንሆነች ሁሉ ፣ ወሚካኤል አሐዱ እመላእክት እም ቀዱሳን ቀደምት እስመ በዲበ ሠናይቱ ለሰብእ ተአዛዚ ፣‹‹ ቅዱሳን ከተባሉ መላእክት አንዱ የሆነው ሚካኤል ፣ ከጌታ #በተሰጠው_ቸርነት ለሰው ሁሉ ታዛዥና ምሕረትን የሚለምን ስለሆነ ነው ፡፡ [3] ሠለስተ የተባለው የቅዱስ #ያሬድ ድረሰትም ይህንን ያስረዳል ፡፡
____________________________________________
1.መቃ 2.18 ፣ 2. ለቃ 1.26-29 . ፣ 3. ሄኖ.1.6 ፣5-6
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
የማኀሌተ ጽጌ ትርጓሜ
እንዘ ተሐቀፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕይ ፤
አመ ቤተ መቅደስ ጌሥኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፡፡
ንዒ ርግብየ ትናዝዘኒ እምላህ ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከሚኪ ርኀሩኀ፡፡
#ትርጉም
ጌታ ከወፎች ሁሉ በመረጣት ርግብ
የማኀሌተ ጽጌ ትርጓሜ
እንዘ ተሐቀፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕይ ፤
አመ ቤተ መቅደስ ጌሥኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፡፡
ንዒ ርግብየ ትናዝዘኒ እምላህ ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከሚኪ ርኀሩኀ፡፡
ትርጓሜ
ፌስቡክ ገጻችን ላይ ያግኙ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/posts/3020737471577664
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡
ጥቅምት 5 በዓለ ዕረፋቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት
ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ ይህንንም ስርዓት አባቶታችን ሰሩልን
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤
* ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ)
፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)
ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤
*ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡
*ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤
፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡
፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡
፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)
፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥
ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡
፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤
ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡
አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ ካህኑ መልከጼዴቅ፣ አፄ ገብረመስቀል፣ አፄ ቴዎድሮስ ቀዳማዊ፣ …) እግዚአብሔርንም ሰውንም ያገለገሉ ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ ቅድስናን ከሐናፄ ቤተመቅደስነት ጋር ደርበው የያዙም ጭምር ናቸው፡፡ በዚህም በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሏቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው፤ ጽላት የተቀረጸላቸው፥ ገድል የተጻፈላቸው፤ (ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ የኾኑ) ቅዱሳን ናቸው፡፡
ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 364 ዓ/ም አጽብሐ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓ/ም በሞተ ሥጋ አርፈዋል፡፡
ክብረ በዓላቸው በትግራይ ባለ ውቅር ገዳማቸው፤
በአዲስ አበባ ደግሞ፤
* * በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ
**በየካ ተራራ ዋሻ ተክለ ሐይማኖት
**በአያት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
