Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 369 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 633,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 187 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 369 名订阅者。
根据 19 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -46,过去 24 小时变化为 37,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.37%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.87% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 438 次浏览,首日通常累积 1 210 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 20 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 369
订阅者
+3724 小时
+367 天
-4630 天
帖子存档
✤ ቅዱስ #ቂርቆስ እድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት እየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው። የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት። መኮንኑም ቅድስት አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት። ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ፡ እድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። መኮንኑም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕጻን ቅዱስ ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው። አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታየም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው። እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ። ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ። መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ስቃይ፡ ታላላቆች አንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው። እናቱ ቅድስት እየሉጣንምከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት። እግዚአሔብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር። ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር። ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር
። ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የነሃስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ። የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር። ይህን ያየችና የሰማች እናት ቅድስት እየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት። ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት እየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ጸለየ። ያን ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት። ቅድስት እየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች። እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው። ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። ቅድስት እየሉጣም ለልጇ ያች የተወለድክባት እለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት አለችው። የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት እየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወደያውኑንቀዘቀዘ። ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ። ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው። መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው። ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝ ቃል ኪዳን ሰጠው ። እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣን በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን አሜን።
ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት በእሳት ከመጣል በንፍር ውሃ ከመለብለብ ከዳኑ በኋላ እለስክንድሮስ መከራውን ፈርተው ይመለሳሉ ብሎ በሀብለ ሰናስል እያሰረ በችንካር እየቸነከረ ሲያሰቃያቸው ቆየ፡፡ የማይሆንለት ሲሆን እጅ እግራቸውን አስሮ ከዝግ ቤት አስቀመጣቸው፡፡ ጌታም የመከራቸውን ጽናት የትዕግስታቸውን ብዛት አይቶ ከመከራ ሊያሳርፋቸው ሽቶ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ፤ በመጣ ጊዜ “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ቂርቆስ” ወዳጄ ቂርቆስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፤ ብሎ ሠላምታ ከሰጠው በኋላ የመከራህን ጽናት፣ የትዕግስትህን ብዛት አይቼ ቃል ኪዳን ልገባልህ ነው።” “ዘመጠነዝ ገድለ ተጋዲልየ ምንተኑ ትዔስየኒ” በሕፃንነቴ ይህን ያህል ተጋድዬ የምትሰጠኝ ምንድነው?” አለው። “አዐሥየከ ዘሀሎ ውስተ መልብከ” በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። እንኪያስ በስሜ ቤተ ክርስቲያን ከታነጸበት ረሃብ፣ ቸነፈር፣ የሰው በሽታ፣ የከብት እልቂት፣ የእኅል የውሃ ጥፋት፣ አይሁን አለ። ጌታም ይሁንልህ በማለት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ደግሞም “ኢትቅብር ሥጋየ በዲበ ምድር” ሥጋዬ በምድር አይቀበር አለው። “አልቦ ዘይፈደፍደከ ዘእንበለ መንበረ መንግሥትየ ወማርያም ወላዲትየ ወዮሐንስ መጥምቅየ” (ከመንበረ መንግስቴ፣ ከማርያም እናቴ ከዮሐንስ መጥምቅም በቀር በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥህ የለም።)
“ወዓዲ ከመ ኢይስማን ሥጋከ ዲበ ሠረገላ ኤልያስ አነብረከ”
(ሥጋህን እንዳይፈርስ በኤልያስ ሠረገላ አኖርልሃለሁ) ብሎ ተስፋውን ነግሮታል። እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በመኮንኑ በሰይፍ ጥር ፲፮ በሰማዕትነት ያረፈች ሲሆን ቅዱስ ቂርቆስን ግን ተመለስ ቢለው አልመለስም እምነቴንም አልክድም ባለው ጊዜ ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ በጥር ፲፭ አስገድሎት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ መታሰቢያዋ ዕለት በየወሩ በ፲፮ እመቤታችን ቃል ኪዳን በተቀበለችበት ቀን በሚታሰብበት የቅድስት ኪዳነ ምህረት ቀን ይታሰባል።
የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት፤ የቅዱስ ቂርቆስና የቅድስት ኢየሉጣ በረከታቸው ቃል ኪዳናቸው ይድረሰን በእውነት ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን፨
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
እንኳን ለቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣና ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ)
#ሐምሌ_፲፱#በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል_ወቅዱስ_ቂርቆስ_ወቅድስት_ኢየሉጣ_ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡
በቀጨኔ ደ/.ሰ/መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል.ቤ.ክ የፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ
ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
✼ ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡
አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም #እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም #ድምፅ እንደ ብዙ #ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ #ኃይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ #በግምባሬ_ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፥5-9) ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክትአለቃ የቅዱስ #ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡
✤ ገብርኤል የሚለው ቃል የሁለት ቃለት ጥምር ነው እነዚህም #ገብር እና #ኤል ሲሆኑ ትርጕማቸውም ገብር #አገልጋይ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው፤ በተገኛኘ ገብርኤል ማለት #የአምላክ_አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው።
“እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች” አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፥13) ብሎ በተናገረው ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፥16) በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡
ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው #እርባብ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከ100ው ነገደ መላእክት መካከል ከበታቹ የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉት፤ ከተማቸውም በሰማየ #ራማ ነው፡፡
✼ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል፣ እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን በመቃወም ‹‹#ንቁም_በበህላዌነ_እስከ_ንረክቦ_ለአምላክነ - “አይዞአችሁ ፈጣሪያችን እስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት
#መላእክትን_ያረጋጋ_መልአክ_ነው፡፡ በተወዳጁ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል ራእ12፥7፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” (ኢሳ.1416) በማለት ገለጠልን፤ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል እና በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ነበር፡፡
✼ ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል ሉቃ 1፥19፤ ታላቁ ነቢይ ሄኖክም ስለ ነገረ
መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መስክሯል ‹‹በአበቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ #በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ #ገብርኤል ነው፡፡›› ሄኖክ 6፥7፤ ‹‹በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው››ሄኖክ 10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ነገር ግን ያደረጋቸው ተዓምራቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በመልክኡ፣ በድርሳኑ፣ በገድሉ፣ በተዓምሩ የተጻፉ ቢሆንም ሐምሌ 19 እና ታኅሣሥ 19 ያደረጋቸውን ተራዳኢነት ፡-
✤✤✤ ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቅዱስ #ቂርቆስና እናቱ ቅድስት #እየሉጣ በሰማዕትነት መከራ የተቀበሉበት፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ #ገብርኤል ደግሞ #ከእቶን እሳት ያዳናቸው እለት ነው::
✤✼፠ #ታኅሣሥ_19 አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር በዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ ላቆመው ጣዖት አንሰግድም በማለታቸው ወደ እቶን እሳት እንዲጣሉ አድርጓቸዋል ፤ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ግን ከእቶን እሳቱ የልብሳቸው ዘርፍ እንኳን እሳት ሳይነካው ድነዋል፡፡ (ይህንን በዓል የምናከብረው ታኅሣሥ 19 ስለሆነ ታሪኩን በስፋት ለመረዳት የታኅሳስ 19 ስንክሳርን ወይም የታኅሣሥ ወር ልጥፈችንን ወደ ሃሏ በመመለስ ይመልከቱ ፡፡)
#ሐምሌ_15
#በዓለ_እረፍቱ_ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
ክርክር በዕለተ ሰኑይ ተፈጽሟልና ባርክኒ ይላታል፤ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ ብላ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ትባርከዋለች። እርሱም ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል።
በረከቱ አይለየን።
#ልጆቻችንን_ስናቆርብ....
"ሁሉ በአግባብና #በሥርዓት ይሁን።" 1ኛ ቆሮ 14፥10
#በመልካም_መሬት_ላይ_የወደቀ_ዘር_ፍሬዉ_የሚታይበት_ቀን_እንሆ አንድ ቀን ብቻ ቀረው :-
ልጆቾን አስተምረን የተማሩትን ሲጠየቁ ምላሽ የሚሰጡበት በይዘቱ ልዩ የሆነ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ መርኃግብር
ሁላችሁም የአጥቢያችን ምዕመናን እሁድ ሐምሌ 14 ከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ተጋብዘዋል ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
#በመልካም_መሬት_ላይ_የወደቀ_ዘር_ፍሬዉ_የሚታይበት_ቀን_እንሆ :-
ልጆቾን አሰተምረን የተማሩትን ሲጠየቁ ምላሽ የሚሰጡበት በይዘቱ ልዩ የሆነ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ መርኃግብር
ሁላችሁም የአጥቢያችን ምዕመናን እሁድ ሐምሌ 14 ከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ተጋብዘዋል ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
#ሐምሌ_7_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤ #ወልዱ_ለአቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ልደቱና_እረፍቱ_ነው፡፡
ዕረፍቱ የኾነው በሐምሌ 7 (6,705 ዓመተ ዓለም፥ በ2ት እንድቅትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፥ በ7ት ጥንተ ዮን፥ በወንጌላዊው ማቴዎስ ዘመን በዕለተ ረቡዕ) ነው፡፡ ያረፈውም በአፄ ይስሐቅ ጥያቄ የጋራ መናገሻ መድኀኔ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ባርኮ ሲመለስ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ሲኾን ፤ አርድዕቱ ሥጋውን ይዘው ሂደው በአባቱ መካን በደብረ ጎል (አሁን በደብረ ባሕርይ) አሳርፈውታል፡፡
፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤
፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥
፠ ዐምደ ሃይማኖት
፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤
፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤
፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥
፠ አፈ በረከት
፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል
ከ40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤
1. ✼ ኆኀተ ብርሃን
2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም)
3. ✼ መዝሙረ ድንግል
4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ
5. ✼ ውዳሴ መላእክት
6. ✼ ውዳሴ ነቢያት
7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት
8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት
9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን
10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን
11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር
12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን
14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ
15. ✼ መሰንቆ መዝሙር
16. ✼ እንዚራ ስብሐት
17. ✼ ውዳሴ መስቀል
18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት
19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት
20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት
21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ
22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ
23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም)
24. ✼ ውዳሴ ስብሐት
25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ
26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ
27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት
28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት)
29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ)
30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት
31. ✼ መልክአ ቊርባን
32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን
33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም
34. ✼ ክብረ ቅዱሳን
(በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው #በደቡብ_ወሎ_በቦረና_አውራጃ ነው፡፡
(አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነው/፡፡)
አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤተ፡፡
#ኢትዮጵያ🙏
#EOTC

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።:
#ቋሚ ሲኖዶስ_ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ።
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል።
ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው እግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው።
"ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል " ያለው ቋሚ ሲኖዶስ " በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር ፦
✤ መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣
✤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣
✤ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣
✤ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።
በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል።
በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርገውት መደበኛው ሥራቸውን በያሉበት ቦታ እየሰሩ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆነው በጾም በጸሎት እንድተጉ ጥሪ ተላልፏል።
#ETHIOPIA #EOTC
#መልዕክት
" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ
✤ ሰላምን
✤ መረጋጋትን
✤ ፍቅርን
✤ አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
#ኢትዮጵያ🙏
#EOTC
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
#መልዕክት
" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ
✤ ሰላምን
✤ መረጋጋትን
✤ ፍቅርን
✤ አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
#ኢትዮጵያ🙏
#EOTC
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ።
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል።
ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው እግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው።
"ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል " ያለው ቋሚ ሲኖዶስ " በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር ፦
✤ መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣
✤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣
✤ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣
✤ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።
በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል።
በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርገውት መደበኛው ሥራቸውን በያሉበት ቦታ እየሰሩ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆነው በጾም በጸሎት እንድተጉ ጥሪ ተላልፏል።
#ETHIOPIA #EOTC
✤✤✤ #ሐምሌ_ቅድስት_ሥላሴ
ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ምሳሌ ዘየኀጽጽ) ስለኾነ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡
#ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤
#፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤
ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡
ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤
አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡
እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤
፠ ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤
፠ ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤
፠ ለዳንኤል በአረጋዊ፣
፠ ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤
፠ ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡
#፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡
#፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤
ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤
ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤
ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡
መልክአ ጴጥሮስ ወጳውሎስ pdf.pdf7.25 KB
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 