ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 123 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 232,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 221 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 123 名订阅者。

根据 01 十一月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 598,过去 24 小时变化为 74,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.12%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.46% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 729 次浏览,首日通常累积 1 686 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 29。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 02 十一月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

16 123
订阅者
+7424 小时
+847 天
+59830 天
帖子存档
የሰ/ት/ቤታችን የሕፃናት ክፍል አባላት ለጥቀምት 14 ለበዓሉ ተስማሚ የኾነውን ወረብ እያቀረቡ፡፡
የሰ/ት/ቤታችን የሕፃናት ክፍል አባላት ለጥቀምት 14 ለበዓሉ ተስማሚ የኾነውን ወረብ እያቀረቡ፡፡

ጥቅምት 14፤ ✤ ቅዱስ ገብረክርሰቶስ በዓለ እረፍቱ፤ ✤ በጋዛ ምድር ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው ረድኡ ሐዋርያ ቅዱስ ፊሊጶስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ✤ አቡነ አረጋዊ ወደ ደብረ ዳሞ በዘንዶ የወጡበት፤ ✤ ቅዱስ ሙሴ እግዚአብሔር በዓለ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ✤✤ ጥቅምት 14 በአ.አ. ክብረ በዓል የሚከበርባቸውን አብያተ ክርስቲያናት እንጠቁማችሁ፡፡ ✤ በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን (የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አቡነ አረጋዊና ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር ታቦት በድርብነት ከጥንት ጀምሮ ይከብራል) ✤ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ባለውለታችን የኾነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሐዲስ ኪዳን የእግዚአብሔርን ቃል የተናገረን፤ የክርስትና ጥቀምት አባትና አጥማቂያችን ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የኾነው ቅዱስ (ሐዋርያው) ፊልጶስ በሀገራችንን ውስጥ ብቸኛ በኾነውና በአ.አ ኮልፌ አጠና ተራ በሚገኘው ቤ.ክ. ደብረ ምጥማቅ ቤ.ክ በዓለ ዕረፍቱ ይከበራል፡፡ ✤ በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤ.ክ /ዘነበ ወርቅ/ ✤ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (የአቡነ አረጋዊ ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ በሽሮ ሜዳ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን (የአቡነ አረጋዊ ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ.ክ. (የአቡነ አረጋዊ ታቦት በድርብነት ይገኛል)

ዘጥቅምት ፲፩፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፯ኛ ዙር ዓመት፤ ፫ኛ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፲፩) በዓለ ቅድስት ሐና ወጲላግያ ወቅዱስ ኢያቄም ወያሬድ፡፡ ✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤  የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤  የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

ዛሬ ጥቅምት 7 እንዳያመልጥዎ፤ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ በዛሬው ልዩ ሳምንታዊ የረቡዕ የሠርክ ጉባኤያችን ላይ ቀድሞ በጉባኤያችን ላይ አስተማሪ በነበሩትና ዘማሪ በኾኑት መምህርና ዘማሪ ዘበነና ልዑል ሰገድ ይቀርባል፨

ሰላም ለሁላችሁም ይሁን፤ 3ኛው የባለ ትዳሮች ልዩ ጉባኤ እሑድ ጥቅምት 4/2011 ዓ.ም. ጠዋት ከ3:00 ጀምሮ በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ይካሄዳል፤ እርስዎም በመርሐ ግብሩ እንዲሳተፉ ጋብዘንዎታል የፍ/ሕ/ሰ/ት/ቤት

እንኳን ለአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ) ክብረ በዓል አደረሰን፤ *እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ *እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ *ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ *ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ *በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ *60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የአራዊቱ ምግባቸው የእግራቸው ትቢያ የኾነላቸው፤ *ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ (ለቅዱስ ላሊበላ፥ ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ታላቅ አባት ፠፠፠ ምድረ ከብድ (ዝ ምድር ክቡድ ውእቱ) ወዝቋላ (ዝ ቆላ)፤ **ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ ዝቋላ (ዝ ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባህር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ተመልሰው ወደ ምድረ ከብድ በነበረበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ፣ አባ አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ (አፋር)፣ አባ ብንያም ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፤ በግብፅ 300ዓመታት፥ በኢትዮጵያ 262ዓመታት ከኖሩ በኋላ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባትም ምድረ ከብድ ገዳም ራደች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ በሌሊቱ 6 ሰዓት አረፉ፤ ምድረ ከብድም ራደች ተንቀጠቀጠች ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከባድ/ ትብለሽ ተጠሪ አላት፡፡ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነጿት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ዋሊያውያን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ በኪደተ እግራቸው ከረገጧቸው ዋና ዋና መካናት አንዱ የኾነው የምድረ ከብድ ጕዞ እንዳያመልጣችሁ፡፡!! አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ /የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

የ2ኛ ሳምንት፥ የጥቅምት 4 ሥርዐተ ማኅሌተ ጽጌ፤ በዓለ አብርሃ ወአጽብሃ፥ ወዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፨