ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 529 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 411,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 215 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 529 名订阅者。

根据 27 九月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -9,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 16.78%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.35% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 606 次浏览,首日通常累积 1 297 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 17。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 28 九月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 529
订阅者
无数据24 小时
-167 天
-930 天
帖子存档
የ2017 ዓ.ም በዓለ ጥምቀት ፎቶ ማስታወሻ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719 #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord #በዓለ_እግዚእነ #በዓለ_ጥምቀት #Holy_Ephipany

የ2017 ዓ.ም በዓለ ጥምቀት ፎቶ ማስታወሻ  የዘንድሮ አዘጋጅ ደብር ፤ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም/ 5ኪሎ ቀጣይ ዓመት ተረኛ አዘጋጅ ደብር - ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም + ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር በመዝሙር፡፡ #እግዚአብሔርን_በመዝሙር_አመስግኑት፡፡ መዝሙረ ዳዊት ፻፶ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719 #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord #በዓለ_እግዚእነ   #በዓለ_ጥምቀት  #Holy_Ephipany

ጥር 13 | #አቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ ዐረፉ። አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጎዳና የተለዩ አባት ናቸው። በጥቂቱ፦ ፩. ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው፣ ብዙ ምሥጢ
+2
ጥር 13 | #አቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ ዐረፉ። አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጎዳና የተለዩ አባት ናቸው። በጥቂቱ፦ ፩. ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው፣ ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል ፪. ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል። ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል፣ ፫. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል። ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ5 ዓመት አቁመዋል፣ ፬. ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት 12 ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። ጻድቁ የተወለዱት በ16ኛው መ/ክ/ዘ በጎጃም ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ፣ እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ። በንጉሥ ሱስንዮስ ዘመን ካቶሊክ ብሔራዊ እምነት ሲደረግ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳን ወጥተው ተሰየፉ። በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ። ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጥለው ተሻገሩ። ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ። በጨለማ እስር ቤትም 5 ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር። እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም። ከ5 ዓመት በኋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል። ከተፈቱ በኋላ ጻድቁ በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል። ብዙ ተጋድለው ዐርፈዋል። ታኅሣሥ 13 ቀን ልደታቸው ነው።

በቃና ዘገሊላ፤ ዘገሊላ ከብካብ ኮነ፨ ሥርዐተ ማኅሌት ዘጥር ፲፪፥ ዘቃና ገሊላ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719

#የጥምቀት_በዓል_አከባበር_በአዲስ_አበባ_ከእንጦጦ_ጋራ_ጥግ_እስከ_ጃንሆይ_ሜዳ_ በአዲስ በአበባ ያሉ ገዳማትና አድባራትም በቦታ ርቀት እስከ ተለያዩበት ቀን ድረስ በእንጦጦ ጋራ ጥግ በአንድ ላይ በመፈናኘት ያድሩ ነበር፤ ኋላ ከቦታ ርቀት በኋላ የተቀሩት በጃንሆይ ሜዳ ማደር ጀምረዋል፡፡ እያደረም ሌሎች ገዳማትና አድባራት ሲመሠረቱ ከጃንሆይ ሜዳ በተጨማሪ ለአጥቢያቸው በሚቀርብ ቦታ ማደር ጀመሩ፡፡ ፠ በዓለ ጥምቀት በጃን ሜዳ (ጃንሆይ ሜዳ) መከበር የጀመረው ከ1887 ዓ.ም. አንስቶ መሆኑ ይነገራል፡፡ ስያሜውምና አጀማመሩም ጃንሜዳ የሚለው ጃን፥ ጃኖ ከሚለው ጋራ የተዛመደ ሲሆን ነገሥታት ለመሾም ለመሻር፣ ዳኝነት ለመስጠት፣ ሊቃውንትን ለመሾምና፣ ዐዋጅ ሲያስነግሩ በቤተ መንግሥታቸው አቅራቢያ በሚገኝ ሜዳ ላይ የጃኖ ድንኳን ተክለው ያስነግራሉ፤ ይህም ሜዳ ከጃኖ ጋራ እየተናበበ የቦታ መጠሪያ ሁኗል፡፡ ለምሳሌ፤ ‹‹ጃን ተከል›› በጎንደር ነገሥታት፤ ‹‹ጃን መራቂ›› በላስታ ነገሥታት፤ ‹‹ጃን ተራራ›› በአማራ ሳይንት በአፄ በዕደ ማርያም ‹‹ጃን ሜዳ›› በደብረ ታቦርና በአዲስ አበባ ናቸው፡፡ ፠ አዲስ አበባ መዲና በሆነችበት ሰዓት ‹‹መሐል ሰፋሪ‹‹ የሚባሉ የመኳንንት ጕባኤ በዚሁ በጃንሜዳ በስውር ዐድማ የሚያደርጉበት ሆነ አድማውን ሲያደርጉም በጃን ሜዳ ያለው የጃኖው ድነኳን ከሩቅ እንዳይታይ በማቅ ይሸፈን ነበር፡፡ እቴጌ ጣይቱ ይህን የመሰለ ሜዳ የክፉ ምክር መምከሪያ ሆኖ ከሚኖር ተባርኮ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቢሆን ብለው ለአፄ ምኒልክ ሃሳብ አቀረቡላቸው፤ አፄ ምኒሊክም ማለፊያ ብለው ሐሳባቸውን በመቀበል ጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ እንዲሆን አዘዙ፡፡ እንዲሁም የአፄ ምንሊክ አልጋ ወራሻቸው ልጅ ኢያሱ መሆኑን በግንቦት 10 ቀን 1901ዓ.ም. ዐዋጅ ያስነገሩበት፤ ‹‹ንሥረ ተፈሪ›› የተባለው የመጀመሪያው አውሮፕላንም በ12921ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ያረፈውም በዚሁ ሜዳ በመሆኑ ጭምር ስያሜው ጃንሆይ ሜዳ ተባለ፡፡ ፠ በ1887ዓ.ም. በዓለ ጥምቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ በጃን ሜዳ በሕብረት ያከበሩት የመካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን፣ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነበሩ፡፡ ፠ እስከ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ መን ድረስ ግን ታቦታቱ ወደ ቀበና ወንዝ (አፈ ንጉሥ ጥላሁን ሰፈር፤ ከፈረንሳይ ኤምባሲ በታች) ከከተራው አንስቶ አድረው በጥምቀት ዕለት ወደ ጃንሜዳ ይመለሱ ነበር፡፡ ሌሎችም በየሰበካቸው በሚገኝ አምች ቦታ ሲያከብሩ ቆይተው በ1939ዓ.ም. ከንሜዳ እጅግ በጣም ብዙ ያልራቁት (የካ ሚካኤልና ቅዱስ ዑራኤል) በንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደርጎ ወደ ጃናሜዳ እንዲመጡ ተደርጎ ነበር፤ ሆኖም ሕዝብ እየበዛ ስላስቸገረ በየአቅራቢያቸው እንዲያድሩ ተድርጓል፡፡ ፠ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኀይለ ሥላሴ በ1936 ዓ.ም በስፍራው የውኃ ቧንቧ እንዲዘረጋ፣ ባሕረ ጥምቀት ገንዳ በግንብ እንዲሰራ፣ የኤሌክትረክ መብራት በቦታው እንዲገባ አድርገዋል፡፡ ዙሪያውን በግንብ ተሰርቶ በቧንቧ የብረት ማገር ውብ ሆኖ እንዲታጠርና በዐፀድና በአበባዎች እንዲያጌጥ አድርገዋል፡፡ ይህ ቦታ ኋላ በ1994ዓ.ም. እድሳት ተደርጎለታል፡፡ ፠ እስከ ቅርብ ጊዜያትም ድረስ ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱ ታቦታት ከነድርባቸው ነበር፤ ለምሳሌ ቀቀጨኔ ደብረ ሰላም ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነበረ፤ ኋላ ግን ድርብ ታቦታት ቀርተው ዋናውን ይዘው የሚወርዱ ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ እስከ 2010ዓ.ም ድረስ ….. ባሕረ ጥምቀት (አብሕርተ አጥማቃት) አሉ፡፡ ፠ እስከ 1958ዓ.ም. በምስካየ ኅዙናን ተምሮ ማስተማር ማኅበርና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የታሪክ ድርሰትና ስብከት ክፍል አስተባባሪነት ከኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ሐዋርያዊ ድርጅት፣ ከሊቃውንትና ከመምህራን፣ ከሰዋስወ ብርሃንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተውጣጡ መምህራን በባሕረ ጥምቀቱ የስብከተ ወንጌልና፣ የመዝሙርና የድራማ መርሐ ግብር ያቀርቡ ነበር፡፡ በ1959ዓ.ም. አካባቢ ጥቂት ሰንበት ት/ቤቶች የደንብ ልብስና ነጠላ በማድረግ ታቦታቱን አጅበው አውጥውና አጅበው በመመለስ የበዓሉ ድምቀት እየሆኑ መጡ፡፡ በአሁኑ ወቅት በጃንሜዳ የሚያድሩ ታቦታት 12 ናቸው እነርሱም፤ 1ኛ. መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤ 2ኛ. ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፤ 3ኛ. መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤ 4ኛ. መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ.፤ 5ኛ. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.፤ (የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ታቦተ ወደ ጥምቀተ ባሕር ስለማይወጣ ሕዝቡና ሰ/ት/ቤቱ አብሮ ነው የሚያከብረው) 6ኛ. መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም 7ኛ. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.፤ 8ኛ. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (አብሮም ቅዱስ ሚካኤል ይወርዳል)፤ 9ኛ. ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ.ክ.፤ 10ኛ. ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ.ክ.፤ 11ኛ. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ 12ኛ.  ፈለገ ሰላም ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡተ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ (ቀበና 18 ፓርክ አጠገብ)፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719