Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 392 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 586,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 200 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 392 名订阅者。
根据 01 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 22,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 21.30%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.19% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 278 次浏览,首日通常累积 1 569 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 17。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 02 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 392
订阅者
-724 小时
+227 天
+2230 天
帖子存档
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፣
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡
አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው #ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት #ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም #በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት #ድል በማድረጉ ነው፡፡
የንጉሥ #ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት #እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር #መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ #ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት #ጭሱም ሰማይ ደርሶ ቅድመ ሥላሴ ሰገዶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው #መስከረም_16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡
#መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ #ቁፋሮውን_ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ #ዕፀ መስቀልም በዓፄ #ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በተለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ #ማርያም፣ ጋራ #መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ #ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
* "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ #ያሬድ/
* ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ #ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/
፠፠፠ #የመስቀል_ክብረ_በዓላት_
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
#መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤
#መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
፠፠፠
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፣
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡
አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንተ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡
የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ቅድመ ሥላሴ ሰገዶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው #መስከረም_16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡
#መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ #ቁፋሮውን_ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ ዕፀ መስቀልም በዓፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በተለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ ማርያም፣ ጋራ መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
* "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/
* ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/
፠፠፠ #የመስቀል_ክብረ_በዓላት_
#መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤
#መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤
#መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤
#መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
፠፠፠
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
የመስቀል ምልክት ምስጢራት
የመስቀልን ምልክት ስንጠቀም በርካታ ሃይማኖታዊ ምሥጢራትን እናስታውሳለን፡፡ ከእንዚህም ውስጥ የተወሰኑት
1. #ስናማትብ የምሥጢረ ሥጋዌና ድኅነት እምነታችንን እንገልጻለን.
በመስቀል ምልክት ከላይ ወደታች ስናማትብ እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወደ ምድር መምጣቱን ፤ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ መንሳቱን እናስታውሳለን ፤ ከግራ ወደ ቀኝ ባማተብን ጊዜ ደግሞ በይሁዳ አውራጃ ማስተማሩን ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት ፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን ፤ ከሲዖል ወደ ገነት እንደወሰደን እናስባለን፡፡
2. ፨ #እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር እናስታወሳለን .
በመስቀል ላይ የተገለጸውን ፍቅር ከራሱ ከመስቀሉ በላይ ለመግለጽ የሚችል ማን ነው ? መስቀል እግዚአብሔር ዓለሙን እንደወደደ የገለጸበት ቋንቋ ነው ስለዚህም ይህን ቅዱስ ዓርማ ባየን ቁጥር በትዝታ ፍቅሩን እናስባለን ፡፡ የሐ 3 ሮሜ 5 ዮሐ 15
3. ፨ #መስቀል ምልክትን በመጠቀም የክርስቶስ መከራ ተከታዮች መሆናችን እንገልፃለን.
መስቀልን በአንገታችን ላይ በማሰር፣ በመሳላም ፤ በልብሳችን ላይ በመጥለፍ፤ ከእንዚህም በላይ በቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ በመትከል በወጫዊ ሥርዓት የክርስቶስ ተከታዮች መሆናችን በግልጽ ይታወቃል፡፡ በዚህም የማናፍርበት መሆናችንን እና ትምክህታችን መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
4. ፨ #የቅድስተ ሥላሴን ስም በመጥራት እናመሰግንበታልን፡፡
በጸሎታችን ላይ አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴን ስም እየጠራን ዘወትር እናመሰግናለን ፡፡ እንደዚህ ዓይነት የዕለት ተዕለት ምስክርን ግን የምንፈጽመው ስናማትብ ነው፡፡
5. ፨ #ጠላት ሰይጣንን ያርዳል
ሰይጣን የሰውን ልጅ ላይ ለረጅም ጊዜ ያስከተላቸው ጥፋቶች በመስቀል ተደምስሷል ስለዚህም ይህን ምልክት አጥብቆ ይፈራዋል ፡፡ይህንን ምልክት በመጠቀም ዘወትር ለእኛ ጥፋት የማይተኛውን ሰይጣን እናርቅበታለን፡፡
6. ፨ #ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን በምንፈጽምበት ጊዜ መስቀልን አንጠቀማለን .
መንፈሣዊ ምስጢራት ሁሉ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የጌታችን ክቡር ደም ዋጋ ናቸው ፡፡ ያለ መስቀል በልጅነት ክብር ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የለም ከተቀደሰው የክርስቶስ ሥጋና ደም እና ከማንኛቸውም ምሥጢራት መሳተፍ ዕድልም አናገኝም ፡፡ ሮሜ 5
7. ፨ #መስቀልን ስንሸከም ዳግም ምጽዓትን እናስባለን
ጌታችን እንደገና ስለመምጣቱ ሲናገር ‹‹ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል ፤ .. የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል ›› ብሏል ፡፡
ሐዋርያው ‹‹ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በልባቹህ ተቀርጻል ›› በማለት ክርስቶስን ባሰብን ቁጥር አንድ ምልክት እርሱም መሰቀልን በዓይነ ሕሊናችን እንደሚመጣ አብራርቷል ፤ ሰለዚህም የሰው ልጅ ምልክት የተባለው መስቀል ነውና በዳግም ምጽአቱም በሰማይ ይህን ምልክት እንጠብቃለን፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
#በአዲስ አበባ እስከ ቅርብ ጊዜያት በብቸኝነት ከቀድሞ ጀምሮ #የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ( መስከረም 17) በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን #ይከብራል፡፡
#በዚሁ ደብር በቀደሙት ዘመናት አገልጋዮች የመድኀኔ ዓለምና #የመስቀል አገልጋዮች ተብለው በሁለት ምድብ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ነበሩ ፤ የመስቀል አገልጋዮችም ደመዛቸውም #ከቤተ መንግሥት ይከፈላቸው ነበር፡፡
በመድኀኔ ዓለም ፈቃድ #በዋይዜማ ፣ #በሰርክ ጕባኤ፣ #በሰዐታቱ ፣ #በኪዳኑ፣ #በቅዳሴ እና #በዑደተ_ታቦተ ሕጉ እንገናኝ፡፡
#share #share
#መስከረም 10 ተቀጸል ጸጌ ፤
#ግማደ_መስቀሉ ከእስክንድርያ በንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ቀን
፨
ተቀጸል ጽጌ የሚለውን ምስጢራዊ መዝሙር የጀመረው የዜማና የቅኔ መሰራች የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
የመሠረተውም በ6ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን #በአጼ #ገብረ_መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው
የክረምቱና የልምላሜው ጊዜ አልፎ የአበባውና የፍሬው ጊዜ በሚተካበት በመስከረም 25 ቀን ቅዱስ ያሬደ ውደ ንጉሡ ዙፋን ቀረቦ #ተቀጸል_ጽጌ _ገብረ_መስቀል_አጼጌ በማለት ዘምራል ፡፡
ተቀጸል ጽጌ ብዙ ምስጢር ሲኖረው ጽጌ (አበባ) የተባለ የንጉሠ ነገሥቱ #ዘውድ ነው ፤ እግዚአበሔር የንጉሡን ዘመን እንዲባርክለት ዘውዱን እንዲቀድስለት ፤ ተቀጸል ጽጌ አጼጌ ፤ #ንጉሥ_ሆይ_ዘውድን_ተቀዳጅ_እያሉ_ለንጉሡ_ይጸልዩለታል ፡፡
ሌላዉ ትርጓሜ ደግሞ ጽጌ የተባለች #ሃይማኖት ናት ፡፡ በኦሪት ቤተ መቅድስ #ያቁምና #በለዝ የሚባሉ ሁለት አዕማዶች በቀኝና በግራ ተተክለው የቅዱስ #ጴጥሮስና #ጳውሎስ ምሳሌ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ በሁለቱ አዕማድ ራስ ላይ አንዲት አባባ ተቀርጻ ትታይ ነበር እሷም #የሃይማኖት ምሳሌ ነበረች፡፡ በዚሁ ዕለት በመዘምራኑ የሚነገረው ቀለም ፤ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሃይመኖት እልፍ ክርስቲያኖችን ማፍራታቸውን በጉልህ ያስረዳል፡፡በሃይማኖተ አበው ላይ ፤ አሕዛብ አስተጋብኡ ጽጌ ረዳ ወሦኩሰ ተረፈ በኃበ አይሁድ ( አሕዛብ አበባ ሰበሰቡ እሾህ ግን በአይዱ ዘንድ ቀረ ) ተብሎ ስለተጻፈ ጽጌ የሚለውን ቃል ሃይማኖት ተብሎ እንደሚተረጐም ታሞኖበታል ፡፡
ከዚህም በመነሳት ሊቃውንት መዘምራን ሁል ጊዜ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይህን ዝማሬ ለንጉሡ ያቀረባሉ ሊቃነ ጳጳቱም ከቤቱ መንግሥቱ የቀረበላቸውን የተጐነገጐነ አበባ በመስቀላቸው ባርከው ያማረውን አበባ ለንጉሡ #ያድላሉ ከዛም ደግሞ ለሌሎች አገልጋዮች እንደየ ማዕረጋቸው ይታደላል ፡፡
ይህ ስርዓት #ከአፄ_ገብረ_መስቀል ዘመነ መንግሥት እስከ #አፄ_ዳዊት_ዳግማዊ ድረስ በየዓመቱ መስከረም 25 ሲፈጸም ቆይቶ በአፄ ዳግማዊ ዳዊት አማካኝነት ግማደ መስቀሉ መስከረም 10 ወደ ኢትዮጵያ ባስገባበት ቀን እንዲከበር በሊቃውንት ተወስኖ የአፄ መስቀል ( መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት )ና የተቀጸል ጽጌ በዓል እስከ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይል ሥላሴ ድረስ በቤተ መንግሥት እና በቤተ ክህነት ሲከበረ ቆይቶ ኃላ ደግም በቤተ ክህነት እስከ አሁን ድረስ እየተከበረ ይገኛል ፡፡
ለመጨረሻም ጊዜ ለንጉሠ ነገሥቱ የተዘመረው #ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲሆን #ተቀጸል_ጽጌ_ኃይለ_ሥላሴ አጼጌ ተብሎ ተዘመሮ ሲያበቃ ለሊቀ ጳጳሳቱ ድግሞ ጸሎቱን ማቅረብ ቀጥሏል፡፡
በዓሉ በቅድስት ሥላሌ ቤተክርስቲያ አሁን ድረስ ስርዓቱ በዓመት በዓመት መስከረም 10 እየተፈጸመ ይገኛል ፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ
፨፨፨ ፨፨
#መስቀሉ እንዴት ወደ ኢትዮጵያ እጅ ገባ ??
የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ #አባ ሚካኤል በአሕዛብ ንጉሥ በነበረው መርዋን ታሰሩ ይህ ንጉሥም ክርስቲያኖችን ማሰቃየትም ጀመረ ፡፡
በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ #ሠይፈ አርዓድ የግብጽ ክርስቲያኖች ላይ መከራ እንዳበዛባቸው በሰሙ ጊዜ ፤ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ወደ ግብጽ ዘመቱ ፡፡ ንጉሡ ከመድረሱም በፊት ደብዳቤ ጻፋ ፤ ሊቀ ጳጳሱን እንዲፈታና ክርስቲያኖችን እንዲተው አስተነቀቁት ፤ ደብዳቤውን ካየ በኃላ እጅግ ፈርቶ ሊቀ ጳጳሱን ከእስራት ፈታቸው ንጉሱም ለበረከት እንዲሆናቸው ከጌታ ወርቅ(የሰበዓ ሰገል ወርቅ ) ጋር እንዲቀመጥ የእጅ መንሻ ወርቅ ለሊቀ ጳጳሱ ላኩላቸው ከዛ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ ፡፡
ከዚህ በኃላ እርሳቸው ሞተው የእመቤታቸን ወዳጅ የሆነው ልጃቸው ዳግማዊ ዳዊት ነገሠ ፡ አሕዛቡ ንጉሥ ሞታቸውን በሰማ ጊዜ አባ ሚካኤልን ዳግመኛ አሰራቸው ፤ ከዚያም የሮም የቁስጥንጥንያ የሶርያ የአርመን ፣ የግብፅ ክርስቲያኖች በአንድ ሆነው ለኢትዮጵያው ንጉሥ ለዓጼ ዳዊት፤ የክርስቶስን ሃይማኖት ለማጥፋት የአህዛብ ነገሥታት ቆመዋል የሚል መልእክት ላኩ ፡ ዓጼ ዳዊት ይህን በሰሙ ጊዜ መሃላ በመማፋረሱ ተናደዱ ፡፡መንፈሳዊ ቅንዓትም አድረባቸው፡፡
ክተት ሠረዊት ብለው ለጦር ዘምተው ካርቱም ሲደረሱ #ግዮን (አባይ )ን መልስው ወደ ካሩተም በረሐ ሰደዱት የግብፅ ሰዎች ከእርሱ በቀር የሚጠጡት የለምና ፡፡
የምስሩ ንጉሥ እና መኳኳንንቶች ይህን በሰሙ ጊዜ ያረጉት ስህተት እንደሆነ ተረዱ ደንግጠው ሊቀ ጳጳሱን አባ ሚካኤልን ፈቱዋቸው ከሞት የተረፉትን ምእመናን ነጻ አወጧቸው ፡፡ ለዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ያማልዱት ዘንድ ለመነ። ክርስቲያኖችም ይህንን በሰሙ ጊዜ ነጻ ላወጣቸው ንጉስ አመላካቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ ፡፡
የግብፁ መኳንንት እጅ መንሻ ወደ ንጉሡ ላኩ ፡ ንጉሥ ዳዊትም ሊቀ ጳጳሱ መፈታታቸውን በሰሙ ጊዜ አስዋን ድረስ ወረዱ ይህም በጊዜው ለኢትዮጵያ እና ለግብጽ የወሰን ድካ የነበረው ነው ፡፡
ሰኔ 10 ቀን ከሊቀ ጳጳሳቱ እና ከመኳኳንንቱ ጋር ተገናኙ ፡፡ የአባይን ውሃ እንዲመልሱላቸው እልፍ ወርቅና ይዘው ቢጠይቋቸው ይህ ለኔ ነፍስ ለማዳን አይጠቅመኝም አሉ ፡፡ እኔ የምፈልገው የጌታቸንን መስቀል ነው አሉ ፡፡ እነርሱም ከተመካከሩ በኃላ መንፈሳዊ ንጉሥ መሆኑን አይተው ይገባዋል አሉ ፡፡
መስቀሉንም አስረከቧቸዉ እርሱን ብቻ ሳይሆን #ሉቃስ የሣላቸውን ሰባቱን #የእመቤታችንን ሥዕሎች ፣ #ዮሐንስ ወንጌላዊ የሣለውን የጌታቸንን #የኵርዓተ ርእሱን ሥዕል ጭምር እንጂ ፡፡
ይህ ሁሉ የሆነው #መስከረም 10 ቀን ነው በዚችም ዕለት በመላው ኢትዮጵያ ብርሃን ሆነ ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ እያሉ ዘመሩ ይህን ልማድ በማድረግ አሁን ድረስ በዓሉ ይከበራል የበዓሉም ስም #አጼ_መስቀል እየተባለ ይጠራል፡፡
ከዚህ ቦኃላ ወደ ጥንት ላማዱ እንዲሄድ የአባይን ወንዝ መለሰው ለግብጻዊያኑ ለቀቁላቸው ፡፡
ከቅዱስ መስቀሉ ረድኤት በረከት ይክፍለን አሜን!
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
