ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 622 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 302,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 181 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 622 名订阅者。

根据 08 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 67,过去 24 小时变化为 14,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.25%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.62% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 288 次浏览,首日通常累积 721 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 09 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 622
订阅者
+1424 小时
+867 天
+6730 天
帖子存档
ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡ በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡ የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡ በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል። ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ቤተ ክርስቲያን መብት እንዲያስከብር ስትጠይቅ በዝምታ የሰነበተው መንግሥት ከደቂቃዎች በፊት ከሳሽ ሆኖ መግለጫ አውጥቷል። የኢፌዴሪ የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙዩኒኬሽን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ተቋማት አንድነታቸውን ጠብቀው እንዲዘልቁ የሚጠበቅበትን ሲወጣ ቆይቷል ብሏል። ነገር ግን ደስ ሲላቸው ሀገር ናት እያሉ የሚያንቆለጳጵሷት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነቴ ላይ ፈተና ተደቅኗል ብላ አንድነቷን ለመሸርሸር የሞከሩ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ብትጠይቅም ጆሮ አልሰጣትም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሕግ የማስከበር ፍላጎት እንደሌላቸው በጥር 23ቱ ንግግራቸው ገልጸዋል። ሌላው በዛሬው መግለጫ መንግሥት የተፈጠረው ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ መክሯል። መልሶ ደግሞ በቤተ ክርስቲያኗ ሥርዓት መሠረት ይላል። ይህ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኗን መመሪያ ካለመረዳት የመነጨ ይመስላል። ቤተ ክርስቲያን በሥርዓቷ መሠረት በጉዳዩ ላይ ቀኖናዊ ውሳኔ በመወሰን ችግር ፈጣሪዎቹን ለይታለች። ቀጥሎ የሚደረገው የሚያደርጉት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ መንግሥት እንዲያስቆም መጠየቅ ነው። ነገር ግን ዛሬ ከሳሽ ሆኖ የመጣው መንግሥት ያንን ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። ሁለት እኩል ኃይላት እንደሆኑ በማስመሰል ተወያዩ ማለት አሳዛኝ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስም በጥር 24ቱ መግለጫ ይህንኑ አሳውቋል። ሌላውና በመጨረሻ ልናነሳ የወደድነው ሚዲያዎች ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማቅረብ መቆጠብ አለባቸው ያለውን ነው። ነጻ ሆነው እንዲዘግቡ ኃላፊነት ያለባቸው የመንግሥት ሚዲያዎች በጉዳዩ ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ሰንብተው ዛሬ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መግለጫን ለመዘገብ መጣደፋቸው ያስተዛዝባል። ከዚያ በተለየ መልኩ ግን ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ነገር ከቤተ ክርስቲያኗ ሚዲያዎች ጀምረው የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ሚዲያዎች ከፍተኛ ሽፋን ሰጥተውታል። የተፈጠረውን ነገር አትዘግቡ የማለት አምባገነንነት ወዴት ያደርሰን ይሆን?

አስቸኳይ መረጃ፡፡፡ የመንግስት አካላት ዛሬ እሑድ 4ስዓት ተደራደሩ ወይም ለሕገ ወጡ ቡድን ንብረት አስረክቡ ብለው አባቶችን እያስገደዱ ይገኛሉ። _--------- በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ/አሰበ ተፈሪ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾሙት አካላት በጥር 27/2015 ዓ/ም እንደሚመጡ በቂ መረጃ ለሕቡ ሰለደረሰ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን ከሕገ ወጦች ወረራ በንቃት እንዲጠብቁ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ መዋሉ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል፡፡ ከቀኑ 11፡45 ስዓት ላይ የመጡት ሕገወጥ ቡድን ለመንግሥት አካል እንደማይመለሱ ሲነግሩት ሙሉ ወጪ ችሎ እንዲያድሩ አድርጓል። በዚህ መሀል 10 የማይሞሉ ዱላ ይዘው እየዘፈኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ እነሱን ትቶ ቤተክርስቲያ እየጠበቁ ባሉት ላይ ተኩስ ተከፈተ። በተኩስና አስለቃሽ ጭስ እስከ 2ስዓት ምዕመናን ሲያዋክብም አምሽቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ከበው ህዝቡን በተኩስ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ በዱላ እያሰቃዩ ሙሉ ህዝቡን እንዳስወጡና የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊዎች ሞታችን በልደታ ብለው ግቢ ውስጥ ቀርተዋል፡፡ እስከምሽቱ 4ስዓት ላይም ቤተክርስቲያን ማን እንደሚገባ መመሪያ ከመንግስት እንጠብቃለን ብለው ከቆዩ በኋላ እና 5 ሰዓት ላይ ከሆቴል ጠርተው ሕገወጡን ቡድን አስገብተዋል፡፡ የጸጥታ እና የመንግስት አካላት ዛሬ እሑድ 4ስዓት ተደራደሩ ወይም ለሕገ ወጡ ቡድን ንብረት አስረክቡ ብለው አባቶችን እያስገደዱ ይገኛሉ። አባቶች ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የምንመራ እንጂ በግል ምንወስነው አይደለም ብለዋል። የጸጥታ ኃይሎች ተደራድረው ገብተዋል ለማለት ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ የመምሪያ ኃላፊዎችን አስገድደው ፎቶ ለማንሳት ሲሞክሩ እንደነበረ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መረጃውን ያደረሱን ገልጸዋል።

ጅማ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ሙሉ ለሙሉ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተሰብሯል። የደብሩን ካህናት፣ ዲያቆናትና ወጣቶችን ወደ ወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አስረዋቸዋል። ዛሬ በሻሸመኔ የተከሰተው ነገ በጅማ እንዳይፈጠር ሥጋት ላይ መሆናቸውን ምእመናን ገልጸዋል።

ጅማ ደብረ/መዊ/መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት የጸጥታ ኀይሎች በራሳቸው ጉልበት ጊቢ ውስጥ ገብተው ይገኛሊ ። አንዲሁም በአከባቢው ያሉትን ወጣቶችን አፍሰው እየወሰዱ ይገኛል። ነገ በ28 ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ አዲሱን ጳጳስ የአካባቢው ምእመና ን እንዲቀበሉ እያስገደዱ የሚቃወሙትን ደግሞ እያሰሩ ነው።

ጅማ ደብረ/መዊ/መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት ፖሊሶች በራሳቸው ጉልበት ጊቢውስጥ ገብተው ይገኛል አንዲሁም በአከባቢው ያሉትን ወጣቶችኝ ቤተክርስቲያንን የሚጠብቅትን በሙሉ አፍሰው እየወሰዱ ይገኛል። በመሆኑ ይህ መልዕክት ህዝበ ክርስቲያኖች በሙሉ ለሁሉም ህዝብ እንድታስተላልፊ በእግዚዓብሔር ሰም እጠይቃችሁለው አንድ የሀይማኖታችን ግዴታ ነው። ነገ በ28 ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ አዲሱ ጳጳስ በግድ በጉልበት እንድንቀበለው ብለው ከአሁኑ የሚቃወሙትን ወደ እስር ቤት እያስገቡ ነው። ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እራሳቹን አዘጋጁ ለሀይማኖታችኝ መቆም አለብን። ነገ ከለሊቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ከደብረ/መዊ/መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም ጥያቄያችንን እናስተላልፋለን። ሼር አድርጉ

በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ

በአሰበ ተፈሪ /ጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን እየወረወሩና ተኩስ መጀመራቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጹ። ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል "በሁለታችሁ አንገባም" በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል። ነገር ግን ከመሼ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን እየወረወረ መሆኑን ምእምናን በስልክ ገልጸውልናል። መረጃውን ያደረሱን ምእመናን አክለውም የጸጥታ ኃይሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከብቦ እየተኮሰና እያወከበ ቢሆንም ምእመኑ ግን ከግቢ አልወጣም ብሏል።

መንግሥት በአስቸኳይ መልስ የማይሰጥ ከሆነ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ! ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እሑድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በመላው ዓለም ተፈጻሚ የሚሆን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አደረገ። መንግስት የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ለተነሱ ወራሪ ቡድኖች ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱ ጾመ ነነዌን መላው ኦርቶዶክሳውያን ጥቁር ልብስ በመልበስ እና ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ እንዲያሳልፉ ያዘዘ መሆኑ ይታወሳል። ሆኖም መንግስት በተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ከሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መነሻቸውን ያደረጉ እና ወደ መስቀል አደባባይ እና ወይም ወደ ባሕረ ጥምቀት ሐድረሻቸውን ያደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መመሪያ ሰጥቷል።

በአሁኑ ሰዓት የጸጥታ ኃይሉ የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ሰብሮ በመግባት ውስጥ በሚገኙት ምእመናን ላይ እየተኮሰ በመግደል ላይ እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን በእንባ ጭምር ገልጸውልናል። (c)tmc

አሰላ +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የከተማው ህዝብ በሌለበት ከበቆጂ የሌላ እምነት ተከታዮችን በአይሱዚ በማምጣት መንበረ ጵጵስናውን ሰብረው ገብተዋል። ስድስት ፓትሮል መኪና ያጀባቸው የክልሉ ልዩ ኃይል ሲሆን ከገቡ በኋላ በተሿሚው የገዳሟን ምዷየ ምጽዋት በመሥበር ለአጃቢዎቹ የፀጥታ ሰዎች ሕገ ወጥ ተሿሚው ገንዘቡን አድለዋል። የከተማው ፖሊስ ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ያሬድን አፍኖ ምሽት ከከተማው ማስወጣቱ ይታወቃል።