Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 369 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 619,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 193 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 369 名订阅者。
根据 24 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -18,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.10%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.16% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 551 次浏览,首日通常累积 1 254 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 25 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 369
订阅者
+124 小时
+477 天
-1830 天
帖子存档
ጉባኤ ሲኖዶስ ተጠርቷል። የኾነውን ኹሉ ኅብረት እንሰማል ።
ትክክለኛውን መረጃ ከቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ።
ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ክስተት ጋር በተያያዘ የእምነቱ ተከታዮች መታሰራቸውን እና አብዛኞቹም ወደ አዋሽ ሰባት የጦር ካምፕ መወሰዳቸውን የቤተ ክርስቲያኗ ጠበቆች ለቢቢሲ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አያሌው ቢታኔ እስካሁን ባላቸው መረጃ ከ200 በላይ ምዕመናን መታሰራቸውን ተናግረዋል።
ሆኖም በተጨባጭ ደረጃ ቁጥሩ በትክክል እንደማይታወቅ እና በሚቀጥሉት ቀናትም ለዚህ ተግባር የተዋቀረው የመረጃ አካልም ዝርዝሩን ያቀርባል ብለዋል።
እስሩ በአብዛኛው የተከናወነው በአዲስ አበባ እና በአጎራባች አካባቢዎች ሲሆን ወደ አዋሽ ሰባት የተወሰዱ ምእመናን ቁጥርም በርካታ ስለመሆናቸው መረጃ አለን ብለዋል።
አዋሽ ሰባት ውስጥ ምን ያህል ግለሰቦች እንደታሰሩ በትክክል ባያውቁም ከ100 አስከ 200 የሚሆኑ የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ስፍራው መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ከቢቢሲ አማርኛ የተወሰደ
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልዑካን ቡድን በሞስኮ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ውይይት መድረክ ላይ ...።
በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራውና በሩሲያ ቆይታ እያደረገ የሚገኘው ልዑክ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአባ ሰርግዮስ የታነጸውን የቅድስት ሥላሴ ገዳምን እንዲሁም የሞስኮ መንፈሳዊ አካዳሚን ጉብኝት
አባ ንዋየ ሥላሴ ከሕገ ወጡ ሲኖዶስ ጋር በድጋሚ በመሰብሰብ ፡፡
በመግለጫቸውም አፍነው በግድ ይቀርታ እንዲጠየቁ እንደተደረጉ አረገው ዋሽተዋል ፡፡
"ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ስምዖን አረጋዊ
የካቲት 8 ፤ የጌታችን ከከበርች ልደት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ የገባበት ዕለት ኾነ ፡፡ በዓሉ ከጌታችን ንዑስ በዓሎች መኻከል አንዱ ነው ፡፡
++++
የካቲት 8 ፤ ልደተ ስምዖን አረጋዊው ፣ ካህን ፣ ጻድቅ ፣ ነቢይ ፡፡
በዓሉ የመድኀኔዓለም ቢሆንም ስምዖን አረጋዊ አማናዊ ድኅነት አግኝቶበታልና ፣ በእርጅና ምክንያት ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ሲኖር ታድሶበታልና እንደ 30 ዓመት ጎልማሳም ዘሏልና በዓሉ ይከብራል ። ስምዖን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሁሉ የድኅነት ባለቤት ኾኖበታልና በዓሉ ይከብራል ።
++++
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ የኦሪትን ሕግ ለመፈጸም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ ። ይህም ሕግን ሊፈጽም እንጂ ሊያፈርስ አለመምጣቱን በቃልም ፣ በግብርም የገለጠበት በዓል መኾኑን ያስረዳናል። ሥርዓቱን ለመፈጸም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጌታቸውን ይዘው፣ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ ።
++++
የስምዖን አረጋዊ ነገርም እንኽ ነው ..
ዓለም በተፈጠረ በ5,200 ዓመታት በጥሊሞስ የተባለ ንጉሥ በግሪክ ነግሦ ነበር። ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጦ፣ እንደ ገል ቀጥቅጦ የገዛው መሆኑን ገልጦ፣ የቀረው ነገር አለመኖሩን ሲናገር ባለሟሎቹ በእሥራኤል ጥበብ የመላባቸው 46 መጻሕፍት ስላሉ እነርሱን አላስተረጎምክም አሉት። እስራኤልን አስገብሮ ስለነበር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ72 የአይሁድ ሊቃውንት ጋር አስመጣ። አይሁድ ተንኮለኛ መኾናቸውን ስለሚያውቅ 36 ድንኳን እንዲዘጋጅ አድርጎ ኹለት ኹለቱን መድቦ፣ የየድንኳኑን ሊቃውንት የሚቆጣጠሯቸው አንዳንድ ጠባቂዎች ጨምሮ እንዲተረጕሙ አዘዛቸው።
በዚህ ምክንያት በ284 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት 46ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ወደ ልሳነ ጽርዕ (ግሪክ) በ70ው ሊቃናት ተተረጐሙ። ከ70 ሊቃናት በመኻከል አንዱ የነበረው #ስምዖን ምሁረ ኦሪት ነበር። ይተረጕም ዘንድ መጽሐፈ ኢሳይያስ ደረሰው። ታዲያ ይህ ሊቅ የትንቢቱን መጽሐፍ እየተረጎመ ሳለ ምዕራፍ ፯ ላይ ሲደርስ የሕይወቱን አቅጣጫ ወደ ዘላለማዊ በረከት የሚያሳድግ ልዩ ገጸ ንባብ ገጠመው ። እርሱም
“ ስለዚኽ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነኾ ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳ 7፥14 የሚል ነበር።
ስምዖንም "እንዴት ድንግል ትፀንሳለች?" ብሎ "ድንግል" የሚለውን "ሴት" ብሎ ቀይሮ " ሴት ትፀንሳለች " ብሎ ለማረም ይሞክርና አመሻሽ ላይ ስለነበር እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት ሲነቃ የቀየረው ተቀይሮበት " ድንግል ትጸንሳለች" የሚል ሁኖ ያገኘዋል። ተሳስቼ ነው ብሎ አሁንም ሊያበላሽ ሲሞክር መልአኩ ሦስት ጊዜ አርሞበት በሦስተኛው መልአኩ ራሱ ተገልጦለት "ይህችን ድንግል ሳታይና ልጇንም ታቅፈህ ሳትባረክ አትሞትም"
( የተጠራጠርከውን ሳታይ አትሞትም ብሎ ብሎ ነግሮት ) ተሰወረ። አረጋዊ ስምዖንም ከዚያች ዕለት ጀምሮ መድኅን ክርስቶስ እስከሚወለድ ለ284 ዓመታት ከአልጋ ጋር ተጣብቆ ኖረ።
አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ወጡ ። በዕለቱም መልአከ እግዚአብሔር አረጋዊ ስምዖንን ቀስቅሶ ተስፋ የሚያደርገው አዳኝ ክርስቶስ መምጣቱን ነገረው። በዚህ ጊዜ አረጋዊ ስምዖን አካሉ ታድሶ፣ እንደ 30 ዓመት ወጣት እምር ብሎ ከአልጋው ተነሣ። በፍጥነትም ወደ መቅደስ ገባ። መድኀኔዓለምን ከድንግል ማርያም ተቀብሎ በመታቀፍ "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው"
(" ጌታ ሆይ፥ አን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤
ይኽም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ፳ኤል ክብር ነው።" (ሉቃ 2÷29-32) )
በማለት ጸለየ።
አምላኩም ጸሎቱን ሰምቶት በዛሬው ዕለት ዐረፈ። ከበዓሉ በረከት ይክፈለን። አሜን!!
የሊቁ ስምዖን አረጋዊ በረከት እና ምልጃ አይለየን !
በዓለ ስምዖን በዐይቢይነት ሜላት ደብረ ገነተ ኢየሱስ ይከብራል ፡፡
ጐንደር -- › አንዳቤቴ ወረደ -- › ገነተ ኢየሱስ
በ13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ መንግስት
ልዕልት ሜላተ ወርቅ ያሰተከለችው ደብር ነው ፡፡
+++
በዓሉ በኢየሱስ ስም የተሰየሙ አድባራትና ገዳማት ላይ ይከበራል !
+++
አንዲት ቤተክርስቲያን ፣ አንድ ሲኖዶስ ፣ አንድ ፓትርያርክ ፡፡
+++
/ በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ /
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
ሥርዓተ ቀብራቸው በቀ.ደ.መደኀኔዓለም ከ5 - 6 ነው ።
#ዜና_ዕረፍት
ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም
ከ1971 - 2015 ዓ.ም በአገልግሎት
‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ ፥ 38
* የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ፡፡
* ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸው የሚፈጸምበትን ዕለት እና ሰዓት እናሳውቃለን ።
*የአባታችንን ነፍስ ፥ አምላካችን መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሓቅ ጋር ይደምርልን !
#የሥርዓተ ቀብር ሰዓቱን የምናሳውቅ ይኾናል ።
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።
በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሁኑን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።
#ሰበር_ዜና #ይቅርታ ጠየቁ
፨፨፨፨፨፨፧፨ ፨፨፨፨፨፨
ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ ለማስገባት ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚገኙ ሰምተናል።
ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
