Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 336 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 643,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 190 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 336 名订阅者。
根据 13 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -75,过去 24 小时变化为 2,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.35%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.54% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 428 次浏览,首日通常累积 1 616 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 25。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 14 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 336
订阅者
+224 小时
-47 天
-7530 天
帖子存档
፨† መነኮሳት †፨
"ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።" ማቴ ፲፱፥፳፱
ልመና ጸሎታቸው ትራዳን!
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
፠ ጥር 22 ቀን፤ #ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡
በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት፤
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡
1ኛ) #ጎንደር_ደብረ_እንጦንስ፤ በጻድቁ አፄ ዮሐንስ /ከ1659-1674/ የተመሠረተ፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፡፡ ጎንደር ከ300 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ ሆና በቆየችባቸው ዘመናት የአቡን (የጳጳስ) ቤት (መንበረ ጵጵስና) ሆኖ ያገለገለ፡፡
2ኛ) #እንጦንስ_ኢየሱስ፤ በጣና ላይ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ፡፡
3ኛ) መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም፡፡ (አሁን ቅድስት ማርያምበመባል የሚጠራ)
እንዲሁም
4ኛ) #ግብጽ_እንጦንስ_ገዳም ናቸው
‹‹ኀጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጢአታችንን እኛ ረስተን የምንጽናና ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስብብናል፡፡›› /ቅዱስ እንጦንስ/
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ እንኳን ለ፹፬ኛ ዓመት የልደት በዓልዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !
ቅዱስነትዎ በመንበረ ፕትርክናዎ ለረጅም ዓመታት በሰላምና በጤና እንዲቆዩ ምኞታችን ነው !
የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን !
#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና )
#እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡
#ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤
#ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤
#ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡
፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/
ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም)
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡
#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡
*የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡
*እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡
**ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል፡፡ (የሎዛ ማርያምና የጥር 21 በዓል አከባበሯን ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡)
፠ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ማኅሌ እነሆ ብለናል፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
+9
የብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በመንበረ ፓትርያርክ የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሥርዐተ ቀብር በታላቁ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ተፈጸመ።
ገብርኤል ሆይ ለሐና ልጅ ለማርያም ደስ የሚያሰኝ ምሥራች እንዳበሠርካት። ለኔም የምጸድቅበትን የምድንበትን የምሥራች አብሥረኝ፡፡ መልካም የምሥራች ማብሠር ለአንተ ክፍልህ ነውና።
#ሥርዓተ_ቀብራቸው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈጸማል።
ቅዱስ ሲኖዶስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እንደገለጸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ሥርዓተ ቀብር ነገ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተማሩበት በመነኮሱበት እና ለረጅም ዓመታት ባገለገሉበት በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈጸማል።
ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ እና በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል ።
የብፁዕነታቸውን ዕረፍት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የሚሰጠውን መግለጫ እንደደረሰን እናቀርባለን።
፨† ሰማዕታት †፨
"እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" ሥርዓተ ቅዳሴ
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719
እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባረ ዓፅሙ
፠ ዐላውያን ነገሥታት በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የሊቀ ሰማዕቱን ሥጋውንና አጥንቱ በመንኰራኵር ፈጭተው በነፋስ ለበተኑበት፤ ነገር ግን ለአምላካችን የታመነ ሰማዕት በመሆኑ ያረፈበት መሬትና ዕፅዋት ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እያሉ ያመሰገኑበት ነው፡፡
፠ አማን በአማን፤ አማን በአማን፤
ኮከበ ልዳ ፀሐየ ፋርስ፡፡
፠ እንደ ጎንደር አበራ ጊዮርጊስ ባሉት ክብረ በዓሉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርዶና አድሮ ነው በዓሉ የሚከበረው፡፡
፠ በጥር 18 ከዋይዜማው ጀምሮ የቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት ባሉበት በሙሉ የሚቆመውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
