ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 042 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 280,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 240 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 042 名订阅者。

根据 29 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 518,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.50%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.35% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 090 次浏览,首日通常累积 1 660 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 30 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

16 042
订阅者
+124 小时
+917 天
+51830 天
帖子存档
የአርሲ ሰማእታት እና የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን አስመልክቶ ወቅታዊ መልእክት። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፤በአርሲ በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ሊገታ ያልቻለ እና ከልካይ የሌለው ተከታታይ ግድያ ምክንያት እጅግ አዝነናል ። በዚህም ለኦርቶዶክሳውያን ይልቁንም ለሰማእታት ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን። የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሞት ፣ መፈናቀልና ስደት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶ ይገኛል። በቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የወደቁትን፤ የሚታደጋቸው ሸተው በጭንቀት ያሉትን ቤት ይቁጠራቸው። ሃይማኖታቸው ምክንያት ሆኖ ግድያ ፣ ጥቃት ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ የሚደርሰባቸው ወገኖቻችን ጩኸት ተበራክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለውን የኦርቶዶክሳዊያን ሞት ፣ ስደት እና የአቢያተ ክርስቲያናት ቃጠሎን አስመልክቶ የወግዘትና የሐዘን መግለጫ ቢያወጣም መከራውን አልቆመውም ። ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣትም አልተቻለም። በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ይኸን ተከታታይ ማቆሚያ የሌለው ዕልቂት አስመልክቶ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሊቃውንት ፣ ምዕመናን እና ወጣቶች ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ በመሰየም በአርሲና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸሙትን ኢሰብዓዊና ሰይጣናዊ ድርጊቶችን በጥናት በመለየት ፤ ምክንያታቸውን በመተንተን የአደጋ መከላከልና የተጎዱትን የማበርታት ሥራ እንዲሁም የአንድን ዜጋ በነጻነት የመኖር እና የማምለክ ህገ መንግሥታዊ መብቱን ባላስጠበቁ የመንግስት አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ መንግስትን በመጠየቅ እና ኃላፊነትን ባለመወጣት ተጠያቂነት እንዲሰፍን በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ በትህትና በልጅነት መንፈስ እናሳስባለን ። ከዚህም በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ ሩፉኤልን የሚመሩት ኢህጉረ ስብከት አስመልከቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሰፊው መወያየቱንና በርካታ ማስራጃዎችን ጉባኤው ማዳመጡን ተረድተናል። በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተፈጸሙ የተባሉ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰቶች ለመስማት የሚዘገንኑ እንኳን አማንያኑን ኢአማንያንን የሚያስደነግጡ ፤ አንገትን የሚያሰደፉ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን በሚገባ ተገንዝበናል ። የተፈጸመውን አስተዳደራዊ እና ቀኖናዊ ጉዳዮች ጥሰት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ ያለ ልዩነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የማስጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል። ጥቂት የሀሳብ ልዩነቶች መፈጠራቸውን ታዝበናል። ይኸ የሀሳብ ልዩነት ቀኖና እና ህገ ቤተክርስትያንን ከመጠበቅ አንጻር የቀረበ እንዳይደለ ተረድተናል ። በተፈጸሙ አሳፉሪ ድርጊት አንገታችንን የደፋነው ሳያንሰን የአደባባይ ምስጢር በሆነው ጉዳይ ላይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ያለ ልዩነት አልመወሰን ራሱን የቻለ የቀኖና ጥሰት ነው ። ይህን ጉዳይ በሕገ ቤተክርስትያን መሠረት አድርጎ አለመወሰን ለነገም የሲኖዶስን ልዕልና ያሳጣል ሥርዓት አልበኝነትን ያነግሳል ። ስለሆነም ምልዐተ ጉባዔው ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የማስጠበቅ ፍጹም የማይሽራረፍ መንፈሳዊ ግዴታውን በምልዐት እንዲውጣ በትህትና እናሳስባለን ። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

🔷አለሁ እኔ ለወገኔ🔷 ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ ሕይወታቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ቤተሰቦች እንዲሁም በድርቅ የሚገኙ ወገኖችን ለመደገፍ አስቸኳይ ጊዜያዊ ድጋፍ እያሰባሰበ ነው። ክርስቲያናዊና ወገናዊ ድጋፍ ለማድረግ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 👇👇👇 CBE - 1000309803648 Ahadu - 0025393810901 Wegagen - 0837331610101 Abysinia - 37235458 Awash - 01329817420400 Dashen- 5171156335011 Telebir 0975005994 Wegen Fund https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ • 0943000403 / 0962171717/0966636363 🔷ያደረጉትን ድጋፍ🔷 👇👇👇 https://t.me/ArsiSupport ይላኩልን።

# ዜና ዕረፍት በደብራችን በቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም እና በደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ለረጅም ዓመታት #በትሩፋት ሲያገለግሉ የኖሩት መምሬ ግዛዉ ከበደ ከዚህ ዓለም ድካም አረ
+1
# ዜና ዕረፍት በደብራችን በቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም እና በደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ለረጅም ዓመታት #በትሩፋት ሲያገለግሉ የኖሩት መምሬ ግዛዉ ከበደ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ ። ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና በአገልግሎት ለሚመስሏቸው እንዲሁም ለመንፈስ ልጆቻቸው መጽናናትን ያድልልን ።

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በርካታ ክርስቲያኖች እየተገደሉ፣ ከቀዬአቸውና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ሲል ሀገረ ስብከቱ አስታወቀ። የሚመለከታቸው አካላት ለመፍትሔው እንዲሠሩ ሀገረ ስብከቱ አሳስቧል። (#EOTCTV ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም) በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በርካታ ክርስቲያኖች እየተገደሉ፣ ከቀዬአቸውና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ሲል ሀገረ ስብከቱ አስታወቀ። በአርሲ ሺርካ ክርስቲያኖች ላይ በታጠቁ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መጥቷል። ይህም ትልቅ ሀዘን ፈጥሮብናል። ይህንን ችግር ለመፍታት ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ እና የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር በመሆን በተደጋጋሚ ውይይቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል ብሏል ሀገረ ስብከቱ ። ​ይሁን እንጂ ችግሩ ሊቆም አልቻለም። ከጊዜ ወደ ጊዜ በአርሲ ሀገረ ስብከት ወረዳዎች ውስጥ ተመሳሳይ ችግር እየተከሰተ ይገኛል። በዚህም በርካታ ክርስቲያኖች ተገድለዋል፤ አሁንም እየተገደሉ ይገኛሉ። ሌሎቻቸውም ከቀዬአቸውና ከንብረታቸው እየተፈናቀሉ ነው። ይህም ችግሩን ለመፍታት ብዙ ጥረቶች ቢደረጉም ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም ያለው ሀገረ ስብከቱ  ዛሬም በሺርካ ወረዳ በተመሳሳይ መልኩ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል። ​ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ ለዚህ ችግር ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቷቸዋል፤ ለዚህም ሲሉ ከታች ካሉት የመንግሥት አካላት እስከ ሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጉዳዩን በተደጋጋሚ እያሳወቁ ይገኛሉ፤  እስካሁን ድረስ ግን የተሰጠ መፍትሔ የለም ብሏል ሀገረ ስብከቱ። ​የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ  ለዚህ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ከባድ ሀዘን ውስጥ በመግባት ማነጋገር የሚገባቸውን አካላት ሁሉ በማነጋገር እና ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል። የአርሲ ሀገረ ስብከት  ፣  ቅዱስ ሲኖዶስ ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው  የመንግስት አካላትም ይህንን የከፋ የጸጥታ ችግር በመቆጣጠር ለችግሩ እልባት እንዲሰጡት ሀገረ ስብከቱ ጠይቋል ። © Arsi Diocese ​የአርሲ ሀገረ ስብከት