685
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
I hate when people refer to single parents as having a "broken home"…
It's not.
You know what's a broken home. Having a house full of people who shouldn't be together and bleed that toxic energy into their kids.
That is a broken home.💯
ታላቁ ማንነትህ!
ማይክል አንጀሎ ታላቅ የሆነ የዕምነበረድ ቅርፅ ሰርቶ አስመረቀ፤ ሰዎች ተገረሙ አንዳንዶች በእጅ ጥበቡ ውበት ተደንቀው 'ታይቶ የማይታወቅ' አሉ። እሱ ግን ተጠየቀ "ይሄን የዳዊትን ቅርፅ እንዴት እንዲህ ድንቅ አርገህ ሰራኸው" ተባለ፤ ከዛ መለሰ "አንድ ትልቅ ዕምነበረድ አመጣሁና የማያስፈልገውን ሁሉ ገፍፌ ፈቅፍቄ ከላዩ አነሳሁለት፤ ምንም የተለየ ነገር አለሰራሁም" አለ።
አንዳንዴ ከህይወትህ ተቆርጠው ተገፈው የሚወጡ ሰዎች ሁኔታዎች ትዝታዎች ሁሉ ታላቁ ማንነትህን ሊያወጡት ስለሚችሉ በዚህ አለም ፈተናዎች በፍፁም አትደንግጥ!
🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣
🌹 @thinkandgrowrichF🌹
🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣
ህይወትህ እንዲቀየር መጀመሪያ አንተ መቀየር አለብህ! በዚህ አለም የሚገጥሙህ ማንኛውም ነገሮች የአንተና የአመለካከትህ ነፀብራቅ ነው ደስ የሚለው ያለንበት ክፍለ ዘመን አመለካከታችንን በመቀየራችን ብቻ ህይወታችንን መቀየር የምንችልበት ነው።
ከምንም ተነስተው ትልቅ ደረጃ ሲደርሱ፣ ሀብት ሲገነቡና ለሚሊዮኖች ምሳሌ ሲሆኑ አይተናል። ወዳጄ እንዳትጠራጠር እነሱ ውስጥ ያለው አቅም አንተም ውስጥ አለ!
🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣
🌹 @thinkandgrowrichF🌹
🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣
ጂም ሮን የተባለ ደራሲ,። ''ላንተ ብሎ ፑሽ-አፕ (ስፖርት) እንዲሰራልህ ሌላ ሰው አትቀጥርም ስለዚህ ከሌላ ሰው ብዙ አጠብቅ" ይለናል። የኛን ሸክም ማንም አይሸከምልንም፣ እንደውም እኛ ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ሸክም ማቅለል እንደምንችል ማመን አለብን።
አሪፍ ነገር ስናገኝ በልፋቴ እንደምንለው ከባድ ነገር ሲገጥመንም በጥፋቴ ማለት አለብን። የኛ ጥፋት መሆኑን ስናምን ለመፍትሄው ግማሽ መንገድ ተጉዘናል። ሰበብ እንደሚያበዛ ሰው ቆሞ የሚቀር የለም!
ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
ፋራ እኮ ነኝ
መሳቅ መጫወትን የማዉቅ
በአላማዬ ቀልድ የማላቅ
ለናቀና ላንጓጠጠኝ
በቃላቶች ላሽሟጠጠኝ
ቀና እንዳልል ለሚራገም
የዉድቀት ቀኔን ለሚያልም
ሳቅ ነዉ መልሴ
ዝምታ ነዉ እስትንፋሴ
ፓሪ ኦቨር የማያምረኝ
ጌመር መሆን ማይታየኝ
በሠዎች ፊት የሠገጥኩ
እራሴን ግን ያከበርኩ
ለሩቅ ህልሜ የታመንኩ።
ለእድሜ እኩያ የማልመች
አካባጅ ነች የተባለች
እኔ ማለት ያቺ ሴት ነች።
❤❤❤❤❤❤❤❤
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍
❤❤❤❤❤❤❤❤
🌿ከአምስት አመት በኋላ!
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖርህን ጓደኛ የሚወስነው ዛሬ ያዳበርከው አመለካከት ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖርህን የፍቅር ወይም የትዳር ግንኙነት የሚወስነው የዛሬ ወዳጅነት ምርጫህ ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖርህን እውቀት የሚወስነው ዛሬ የምታነባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የምትገባበትን አዲስ የሕይወት ምእራፍ የሚወስነው ዛሬ ለማድረግ የቆረጥከው ለውጥ ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የምትኖረውን የኑሮ ደረጃ የሚወስነው ዛሬ ያዳበርከው ልማድ ነው፡፡
ጥራት ያለው ሕይወት በአንድ ጀንበር አይመጣም፡፡ በአንድ ጀንበር ብቅ ያለ ነገር ካለም በአንድ ጀንበር ጥልቅ ማለቱ ስለማይቀር ጥራትን ዛሬ ጀምረውና በምንም ነገር እንደማይቀለበስ ሆኖ እንዲበቅል ጊዜ ስጠው፡፡
Dr. Eyob Mamo
═════❥━━━❥═════
🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣
🌹 @thinkandgrowrichF🌹
🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣
ሰላም!✌
የሰላምን ጥቅም ለማወቅ የግድ የጦርነት ቀጠና ውስጥ መሆን አይጠበቅብንም የጦርነት አስከፊነት ለማወቅም የጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ መሆን እኮ አይጠበቅብንም።
ሰላም ማለት የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም ይልቁንም ጦርነት ሳይኖር በመካከላችን የሚኖሩትን ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን በውይይትና በንግግር ፈተን [በጋራ መኖር ጭምር እንጅ...ዞሮ ዞሮ ግን ሰላም ከጦርነት ይልቅ እጅግ የተሻለ ነገር እንደሆነ አውቃለሁ አምናለሁም።
# ሀገራችን በጣም አስቀያሚ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ገብታለች በሁለቱም ጎራ ያሉት ወንድሞቻችን ናቸው አብረን በልተናል አብረን ሁሉን ነገር ተጋርተናል ዛሬ ግን ሁሉም ጎራ ከፍሎ በዚህ በቆሻሻ ፖለቲካ የሰው ልጅ በሁለቱም በኩል እየረገፈ ነው። እናም እባካቹ እዚህ ቻናል ላይ ያላቹ ቤተሰቦች ከጊዜ ወደጊዜ ጦርነቱ የሁላችንም ቤት ማንኳኳቱ የማይቀር ነው እናም #አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ቻሌንጅ እንጀምር ለጊዜው ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። በቻልነው አቅም ስለ ሰላም እንጩህ......የዘመቻው መምሪያ ቃል "Ubuntu" ይባላል በዚህ ሀሳብ የሚስማማ ሁሉ ይሄን ቃል በመጠቀም ዘመቻውን ይጀምር። #ሼር ይደረግ..!
