ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁
前往频道在 Telegram
👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor
显示更多1 896
订阅者
-324 小时
-57 天
-2930 天
帖子存档
የማህጸን ኢንፌክሽን ምንድን ነው?
በጥቅል መጠሪያው የማህጸን ኢንፌክሽ (pelvic inflammatory disease, PID) የሚባለው የሴቶች የመራቢያ አካላትን (ስረዓትን) የሚያጠቃ በሽታ ነው። የሴቶች የመራቢያ አካላት ስንል የሚከተሉትን በውስጡ ያቀፈ ነው።
🔹 ማሕፀን፦ ሴት ልጅ ነፍሰ ጡር ስትሆን ልጅ የሚሸከመው አካል
🔹 ኦቫሪዎች፦ በየወሩ እንቁላል የሚያዘጋጁ አካላት
🔹 የፋሎፕያን ቱቦዎች፦ ኦቫሪዎችን ከማህፀን ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች
🔹 ብልት፦ ማህፀን ከውጭ ጋር የሚያገናኝ።
የማህጸን ኢንፌክሽን ሲከሰት መለስተኛ የሆኑ ምልክቶች ሊታዩ አሊያም ምንም አይነት ምልክት ላይታይ ይችላል። በዚህም ምክንያት አንዲት ሴት ይህ የጤና ችግር እንዳለባት ሳታውቅ ልትቆይና ችግሩ እየቆየ ውስጥ ውስጡን ተባብሶ ለማርገዝ እስከመቸገርና ከፍተኛ ለሆነ የዳሌ ህመም እስከማጋለጥ ሊደርስ ይችላል።
☑️ ምልክቶቹ ምንድናቸው?
🔸 የማህፀን እና የወገብ ህመም
🔸 በወሲብ ጊዜ የሚያጋጥም ህመም
🔸 ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ (ሽታ ያለው)
🔸 ሽንት በሚሸናበት ጊዜ የሚያጋጥም ህመም
🔸 ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት
🔸 ድካም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ
🔸 በወር አበባ ጊዜ የሚመጣ ህመም መጨመር
☑️ የማህጸን ኢንፌክሽን በምን ምክንያት ይከሰታል?
ብዙ የባክቴሪያ ዓይነቶች የማህጸን ኢንፌክሽንን ሊያስከትሉ የሚችሉ ቢሆንም በዋነኝነት የዚህ በሽታ መንስዔ ተደርገው የሚጠቀሰው gonorrhea የሚባለው የባክቴሪያ ዓይነት ነው። ይህ ባክቴሪያ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ወደ ሴቷ ማህጸን ሊገባና በሽታው እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።
ከዚህም በተጨማሪ በወር አበባ ጊዜ፣ በወሊድ ጊዜ እንዲሁም በማህጸን የሚቀመጡ የእርግዝና መከላከያዎችን በምንጠቀምበት ጊዜ ከሚኖር የጥንቃቄ ጉድለት ይህ ባክቴሪያ ወደ ማህጸን ሊገባና በሽታውን ሊያስከትል ይችላል።
☑️ የሚያስከትለው ጉዳት
የማህጸን ኢንፌክሽን በጊዜ ካልታከመ ብዙ የጤና መቃወሶችን ሊያስከትል ይችላል። ከነዚህም መካከል…
🍀 ከማህጸን ውጪ እርግዝና (Ectopic pregnancy)፡ - የማህጸን ኢንፌክሽን በሽታ በፋሎፒያን ቲዩብ ውስጥ ጠባሳ ኡእንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም ጠባሳ ለጽንሰት የደረሰው የሴቷ እንቁላል ጽንስ ወደሚፈጠርበት ማህጸን እንዳይሄድ በማገድ ጽንሱ ከማህጸን ውጪ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል።
🍀 መሃንነት (infertility)፦ በማህጸን ኢንፌክሽን በተደጋጋሚ የተጠቃች ሴት የመራቢያ አካላቷ ስለሚጎዱ ለመሃንነት የመጋለጥ እድሏ ከፍተኛ ይሆናል።
🍀 የተራዘመ የዳሌ ህመም (chronic pelvic pain)
☑️ የማህፀን ኢንፌክሸን ህክምና
አንዲት ሴት የማህፀን ኢንፌክሽን እንደያዛት የሚታወቀው ወደ ሃኪም ጋር ሄዳ አስፈላጊ የሆኑ ምርመራዎች ከተደረጉላት በኋላ ነው፡፡ ከነዚህ ምርመራዎች መካከል የሽንት/የደም ምርመራ፤ የማህፀን ምርመራ ወይም አልትራሳውንድ ይጠቀሳሉ፡፡ ከምርመራዎቹ በኋላ ሃኪሙ አስፈላጊ የሆኑ ፀረ- ባክቴሪያ መድሃኒቶችን ሊያዝ ይችላል፡፡
የሚታዘዝልንን መድሃኒት በትክክል እና በሰአቱ ካልወሰድን በስተቀር የማህፀን ኢንፌክሽን አይድንም፡፡ በተቻለ አቅም የፍቅር ጓደኛም አብሮ ቢታከም ይመረጣል፡፡ እንዲሁም መድሃኒቱን በትክክል ከወሰዱ በኋላ እንደገና ተመርምሮ ነፃ መሆን አለመሆን እስኪታወቅ ወሲብ አለመፈጸም ይመከራል።
☑️ ለማርገዝ ብፈልግስ?
የማህጸን ኢንፌክሽን ይዞት ከነበረ ለማርገዝ ሊቸገሩ ይችላሉ ። ምክንያቱም በሽታው በፋሎፕያን ቱቦዎች ላይ ጠባሳ ሊያስከትል ስለሚችል ነው። እርግዝና እንኳን ቢፈጠር ከማህጸን ውጪ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። በመሆኑም ለማርገዝ በሚሞክሩበት ግዜ በማህጸን ኢንፌክሽን ተጠቅተው እንደነበር ለሃኪምዎ መንገር አይዘንጉ።
የማህጸን ኢንፌክሽን ምልክቶች ከታዮ ባፋጣኝ ሃኪም ጋ በመቅረብና አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ በመራቢያ አካልዎ ላይ በማህጸን ኢንፌክሽን ምክንያት ሊፈጠር ከሚችል ጠባሳ ይጠበቁ።
☑️ መከላከያ መንገዶች (prevention)
የሚከተሉትን በማድረግ የማህጸን ኢንፌክሽንን መከላከል ይችላሉ።
🦋 ወሲብ በሚያደርጉበት በማንኛውም ጊዜ የላቴክስ ኮንዶም መጠቀም
🦋 የአባላዘር በሽታ ምልክቶች ካለው ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አለመፈጸም
🦋 ወሲብ አለመፈጸም(መታቀብ)
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍️ #የግለ-#ወሲብ #የጎንዮሽ #ጉዳቶች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
🔵 #ብዙ ወጣቶች ግለ-ወሲብ ለብልታቸው ማደግና ለወሲብ ህይወታቸው ማማር እንደሚጠቅም ያስባሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በተደጋጋሚ መጠቀሙ የጎንዮሽ ጉዳትም አለው፡፡ ለምሳሌ በወንዶች ላይ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳቶች መካከል
🔹 በሰውነት ውስጥ ያለውን ፕሮቲንና ካልሲየም እንዲቀንስ በማድረግ አቅምን ያዳክማል
🔹 የብልት መነሳት ችግርን ያስከትላል
🔹 ሱስ በመሆን ህይወታቸው ይቆጣጠራል
🔹 ድብርት ውሰጥ እንድንገባ ያደርገናል
🔹 ፈጥኖ መርጨት (premature ejaculation) እንዲከሰት በማድረግ በራስም ሆነ በፍቅር አጋር ላይ አለመርካትን ያስከትላል
🔹 የወንድ የዘር ፈሳሽ እንዲቀንስ በማድረግ እርግዝናን አዳጋች ያደርጋል
🔹 የማስታወስና የማሰብ አቅምን ያዳክማል
🔹 የጸፀት ስሜት መሰማት
🔹 ከፍቅር አጋራችን ጋር ወሲብ ለማድረግ ያለንን ፍላጎት ቀስ በቀስ ይቀንሳል
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍️ #ትዳርና #ወሲብ
**
#ዕድሜያቸዉ #18እና #ከዚያ #በላይ #ለሆኑ #አንባቢዎች
📌 ከጋብቻ በኋላ ወሲብ ለብዙዎች ቀዝቃዛ ወላፈን ነው። የጋብቻ ቀለበት አጠለቃችሁ ማለት ወሲብን ልጅ ለመውለድ ብቻ ተጠቀሙበት ማለት አይደለም። ከጋብቻ በፊት በቀን ሦስት፣ አራት ጊዜ ሲደረግ የነበረው ወሲብ፤ ከጋብቻ በኋላ በቀን አንዴ፣ በሳምንት ሁልቴ፣ በሁለት ሳምንት አንዴ፣ በወር አንዴ፣ በስድስት ወር አንዴ፣ በአመት አንዴ እያለ ደብዛው ይጠፋል። የልጆች ኃላፊነትና ሥራ ሲደራረቡ የወሲብ ጣሙ መረሳት ይጀምራል።
📌ብዙ ወንዶች ካገቡ የወሲብ ጥማታቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚፈስበት አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን ጋብቻ የወሲብን ወላፈን የሚያጠፋ ቀዝቃዛ ውሃ አይደለም። የወሲብ ጥማት ሳይበርድ ለብዙ ዓመታት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን የባልና ሚስትን ያላሳለሰ ጥረት ይጠይቃል። ያ ካልሆነ በሆነ ሰዓት ከሁለቱ አንዱ ወደ ውጭ ማየት ይጀምራል። ይህ ደግሞ ጋብቻን ለአደጋ ያጋልጣል። ቃልኪዳንን ያስፈርሳል። ታማኝነትን ያስረሳል።
📌 የወሲብ ህይወትን በማደስና እንደድሮም ጣፋጭ ለማድረግ ዘዴዎችን በማፈላለግ ትዳር እንዳይፈርስ ማድረግ ይቻላል።
📌 እሷን እንደሚስትህ ብቻ አትያት። እርግጥ ነው በህግ ያገባሃት ሚስትህ ነች። ግን የወሲብ ህይወታችሁን ለማጣፈጥ እሷን እንደ ሚስትህ ብቻ ማየት አቁም። እንደዚያ ካደረግህ ከሷ ጋር ለዘላለሙ ከርቼሌ የገባህ አድርገህ ራስህን ከማየት ትቆጠባለህ። ስለሆነም እሷን ከሚስትነት ባሻገር የወሲብ ንግስትህ እንደሆነች ቁጠራት። መንገድ ላይ እንዳየሃት ቆንጆ ልጅ ባምሮህ ቅረጻት። በአዕምሮህ ያልሆነችውን ነች ብለህ ሳል። እሷም እንደዚያው። የተለያዩ ገጸባህርያትን ተላብሳቹ አብራችሁ ተውኑ። አዳዲስ የአወሳሰብ ዘዴዎችን ሞክሩ። በየጊዜው ለየት ወዳለ ቦታ ይዘሃት ሂድ። ከልጆች ከጓደኛ ከዘመድ ከሥራ ርቃችሁ ለብቻችሁ ጥሩ ጊዜን አሳልፉ። ቤት ስትሆኑ ደግሞ ክፍላችሁን የግላችሁ አድርጉት። ልጆቻችሁን ከክፍላችሁ ውጭ አግኟቸው።
📌 ፒጃማ ለብሰህ አትተኛ። አንቺም እንዲሁ። ሰዎች ከተጋቡ በኋላ ፒጃማ ለብሰው መተኛት ያዘወትራሉ። አይታወቃቸውም እንጂ በቆየ ቁጥር የወሲብ ፍላጎታቸውን ይቀንሳል። ሁሌም ፒጃማ እየለበስክ የምትተኛ ከሆነ እንደድሮው ማራኪ ሆነህ አትታያትም። ዕድሜዋ እየገፋ መምጣቱን ነው የምታስታውሳት። ሳትጋቡ በፊት የነበረህን የአልጋ ውስጥ ባህሪ ብዙም አትቀይር። በፓንት (ቦክሰር) ብቻ ከነበረ የምትተኛው አሁንም በፓንት ብቻ ተኛ። እሷ የምትወደውን ከነቴራ ለብሰህ ከነበረ የምትተኛው አሁንም ያንኑን ከነቴራ የሚመስል ለብሰህ ተኛ። ፒጃማ ደራርበህ የምተኛ ከሆነ ግን አንተም እንቅልፍ ይወስድሃል እሷም የወሲብ ፍላጎቷ አይቀሰቀስም።
📌 ከሁሉም በላይ ጋብቻን ከሌላው ግንኙነት የሚለየው ዘላቂነቱ አስተማማኝ መሆኑ ነው። ስለሆነም ባለቤትህን ልታምናት ይገባል። እሷም አንተን ልታምንህ ይገባል። እናም የወሲብ ምኞትህንና ፋንታሲህን ሳትደብቅ ንገራት። እሷም የራሷን ፋንታሲ ትንገርህ። ከዚህ በኋላ የሚቀረው ነገር ፋንታሲያችሁን በፈለጋችሁት ሰዓት እውን ማድረግ ነው። ፋንታሲህን እውን ካደረገችልህ አንተም የሷን እውን ካደረግህላት ሌላ ፍለጋ ሾልኮ መውጣቱ የማይታሰብ ይሆናል። የማትተማመኑና የወሲብ ፍላጎታችሁን ግልጽ አውጥታችሁ የማትወያዩ ከሆነ የወሲብ ወላፈናቹ ሳይቆይ እየተዳፈነ ይሄዳል
ትዳራችሁም መቀዝቀዝ ይጀምራል።
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍ #በተደጋጋሚ #ውርጃ #ለምን #ይከሰታል ??
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
👉 #በተደጋጋሚ የሚከሰት ውርጃ ማለት በተደጋጋሚ 3 ጊዜ ጽንሱ ከሃያኛው ሳምንት ሳይሞላው ሲጨነግፍ የሚከሰት የችግር ዓይነት ነው ፡፡ይህንን ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ ምክንያቶች በግልጽ አይታወቁም ፡፡ ብዙ የሚባሉና በመጀመሪያዎቹ ሶስት የእርግዝና ወቅቶች የሚታየው ግን በክሮሞዞሞች ጤነኛ አለመሆን ምክንያት የሚከሰት ነው ፡፡
በመውለድ እድሜ ውሰጥ ያሉ ሴቶችን ከ 1% እስከ 2% እንደሚያጠቃ ጥናቶች ያመላክታሉ
👉 #ተደጋጋሚ #ውርጃን #ሊያስከትሉ #የሚችሉ #ምክንያቶች
🔵 የክሮሞዞም አለመጣጣም
🔵 የሆርሞን መዛባት
🔵 የእድሜ መግፋት
🔵 በሽታ የመከላከል ስርዓት መዛባት
🔵 ስር የሰደደ የልብ ህመም
🔵 በበሽታ አምጪ ተዋህሲያን መበከል
🔵 ለመርዛማና ጨረር በሰፊው መጋለጥ
🔵 ከመጠን ያለፈ ውፍረት
🔵 የታይሮይድ ህመም
🔵 አንዳንድ የመድኃኒት ዓይነቶች
🔵 የተመጣጠነ የምግብ ንጥረ ነገሮችን አለማግኘት
🔵 አልኮል አብዝቶ መጠጣት
🔵 ጭንቀት
🔵 ከመጠን በላይ ካፌን ይዘት ያላቸውን ነገሮች መጠቀም
👉 #የማስወረድ #ምልክቶች
🔵 ከትንሽ እስከ ስር የሰደደ የደም መፍሰስ ችግር
🔵 ጠንከር ያለ የሠውነት መሸምቀቅ
🔵 የጀርባ ህመም
🔵 የሆድ ህመም
🔵 ትኩሳት
🔵 ድካም
👉 #በተፈጥሯዊ #ሁኔታ #ተደጋጋሚ #ፅንስ #ማስወረድ #እንዴት #መከላከል #እችላለሁ? #ለጤናማ #እርግዝና #ምክሮች
🔵 ፎሊክ አሲድ መውሰድ
🔵 ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ይከተሉ
🔵 ጤናማ ክብደት እነዲኖር ማድረግ
🔵 ከበሽታዎች ለመከላከል ጥንቃቄ ያድርጉ
🔵 የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ግብር ስጋ ግንኙነት አለማድረግ
👉 #ውርጃን #የሚያስከትሉ #ምግቦች
🔵 አናነስ
🔵 ፓፓያ
🔵 እረንጓዴ ሻይ እና ካፌን ይዘት ያላቸው መጠጦች
🔵 ጥሬ እንቁላል
🔵 ያልፈላ ወተት
🔵 ቅመማ ቀመሞች
🔵 አልኮል መጠጣት
👉#ህክምና
🔵 እንደ ችግሩ አምጪ ምክንያቶች ምክንያቶቹን ማከም
🔵 ቀዶ ህክምና
🔵 የኑሮ ዘይቤን መቀየር
🔵 የጄኔቲክ ምርመራዎችን ሊያካትቱ ይችላል።
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍ ወንዶች #ላይ #የመውለድ #ችግር #እንዴት #ይፈጠራል
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
👉👉 #ለመካንነት መፈጠር ወንድ እና ሴት እኩል የሆነ ድርሻ አላቸው። ይህ ማለት ምንም እንኳን ጥንዶቹ ያለ ምንም የ እርግዝና መከላከያ በተደጋጋሚ ለ 1 ዓመት ያህል ግንኙነት ቢፈፅሙም ማርገዝ አይችሉም፡፡
👉 👉#አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ነፍሰጡር ለማድረግ ጤናማ የሆነ የወንድ የዘር ህዋስ ወይም ስፐርም እንዲኖረው ያስፈልጋል። ይህም መደበኛ የስፐርም ቁጥር ተብሎ ይጠራል። የማስረገዝ ችግር ያላቸው ወንዶች በዘር ህዋሳቸው ማለትም በስፐርማቸው ውስጥ የሚከተሉት ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ ፡-
👉 ዝቅተኛ የሆነ የወንድ ዘር ህዋስ መመረት
🔵 ወንዶች ያልተለመዱ የወንድ የዘር ህዋስ ቁጥር እንዲኖራቸው የሚያደርጋቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ
👉 በተለያዩ ምክንያቶች (ኢንፈክሽ ፣ ጨረር፣ወዘተ) በደማቸው የሚዘዋወረው የቴስቴስትሮን መጠን ዝቅተኛ መሆን ߹ በጄኔቲክ ችግር ምክንያት በቂ የወንድ የዘር ህዋሳት ማምረት አለመቻል ߹ ስፐርም የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ። በዚህም ምክኒያት ምንም እንኳን በወሲብ ጊዜ ማፍሰስ ቢችሉም ፣ የወንዴ ፈሳሽ ውስጥ ስፐርም አይኖርም ። በመሆኑም ማስረገዝ አይችሉም ።
👉 አጥጋቢ የሆነ እንቅስቃሴ የሌላቸው ወይም ትክክል ያልሆኑ ቅርፆች ያላቸው የወንድ ዘር ህዋሶች መኖር
👉 ስፐርም ከብልታቸው መፍሰስ ሳይችል ሲቀር
🔵 የዚህ ምክንያት በአባላዘር በሽታዎች ወይንም በቀዶ ጥገና (ቫሴክቶሚ) የወንድ የዘር ህዋስ መተላለፊያ ቱቦዎች በመጎዳት ሊሆን ይችላል።
👉 👉 ምልክቶች
🔵 በግኑኝነት ላይ ያሉ ችግሮች - ለምሳሌ፣ የብልት የዘር ፍሳሽ መፍሰስ ችግር ወይም አነስተኛ መጠን ያለው ፈሳሽ መኖር
🔵 የግኑኝነት ፍላጎት መቀነስ፣ ወይም ያለመነሳት ችግር
🔵 ብልት አካባቢ ህመም
🔵 ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን
🔵 ማሽተት አለመቻል
🔵 ያልተለመደ የጡት እድገት (gynecomastia)
🔵 የፊት ወይም የሰውነት ፀጉር መቀነስ ወይም ሌሎች የክሮሞሶም ወይም የሆርሞን መዛባት ምልክቶች
🔵 ከመደበኛው የወንድ የዘር መጠን ያነሰ (በአንድ ሚሊ ሊትር የዘር ፈሳሽ ከ15 ሚሊዮን ያነሰ ወይም አጠቃላይ የወንድ የዘር ፈሳሽ ቁጥር ከ39 ሚሊዮን ያነሰ)
👉 👉 #አጋላጭ #ሁኔታዎች
🔵 ትንባሆ ማጨስ
🔵 አልኮል አዘውትሮ መጠቀም
🔵 አንዳንድ ሕገ-ወጥ መድሃኒቶችን መጠቀም
🔵 ከመጠን በላይ ውፍረት
🔵 የወንድ የዘር ፍሬን ከመጠን በላይ ማሞቅ
🔵 ብልት ላይ ጉዳት መድረስ
🔵 ከፍተኛ የሆድ ወይም የዳሌ ቀዶ ጥገና ማድረግ
🔵 ያልወረደ የዘር ፍሬ መኖር
🔵 በቤተሰብ የመውለድ ችግር መኖር
🔵 አንዳንድ መድሃኒቶችን መውሰድ
👉👉 #ዶክተር #ማየት #ያለብዎ #መቼ #ነው?
🔵 ባልና ሚስት ያለመከላከያ በቂ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እየፈጸሙ ለ 1 ዓመት ከቆዩ በኋላ ማርገዝ ያልቻሉ ከሆነ
🔵 የትዳር ጓደኛዎ ከ 35 ዓመት በላይ ከሆናት እና ከ 6 ወራት በኋላ እርግዝና ካልተፈጠረ
🔵 የሚያሳስብ ነገር ካለዎት ግን በማንኛውም ጊዜ ሃኪምዎን አማክረው ምርመራውን ቀደም ብለው መጀመር ይችላሉ።
👉👉 #ምን #ምን #ምርመራዎች #ይደረጋሉ?
🔵 የወንድ የዘር ፈሳሽ ናሙና ምርመራ
🔵 የደም ምርመራዎች (የሆርሞን ምርመራ)
🔵 የዘር ፍሬዎ መጠን የመለካት ምርመራ
🔵 በዘር መተላለፊያ ቱቦዎች መዘጋታቸው ለማረጋገጥ የሚደረግ ምርመራ
👉👉 #መከላከያ #መንገዶች
🔵 አለማጨስ
🔵 አልኮል አለመጠጣት
🔵 ከህገ-ወጥ መድሃኒቶች ይራቁ
🔵 ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ
🔵 የወንድ የዘር ፍሬ ሙቀት ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ ነገሮች መራቅ
🔵 ጭንቀትን ይቀንሱ
🔵 ለፀረ-ተባይ መድሃኒቶች, ለከባድ ብረቶች እና ለሌሎች መርዛማ ነገሮች መጋለጥን ያስወግዱ
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍#የሀሞት #ጠጠር #ምልክቶችና #መፍትሔዎቻቸው
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
⏩ #የሀሞት ከረጢት ጉበት የሚያመርተውን ሀሞት የሚይዝ ከጉበት ሥር የሚገኝ አነስተኛ ከረጢት ሲሆን ቅባታማ ምግቦችን እንዲፈጩ ያግዛል ። የሀሞት ጠጠሮች የሀሞት ከረጢት ውስጥ ተፈጥረው የሀሞት ከረጢት ትቦን እስኪዘጉ እና ሕመም እስኪፈጥሩ ድረስ በቀላሉ የማናቃቸዉ ትንንሽ ጠጣር ነገሮች ናቸው።
⏩ # ሁለት ዓይነት ዋና ዋና የሀሞት ጠጠሮች አሉ
1. ኮሌስትሮል ጠጠር፦ አረንጓዴ-ቢጫ ቀለም ያለው ነው 80% የሚሆነው የሀሞት ጠጠርም የዚሁ ዓይነት ሲሆን ከሴት ፃታ፣ ውፍረት፣ እርግዝና፣ በፍጥነት ክብደት ከመቀነስ ጋር ይያያዛል።
2. ቀለማማ ጠጠር ሲሆን ጥቁር ቀለም ያለው የቀይ ደም ሕዋስ ጉዳት ሲጨምር የሚፈጠር ሲሆን ቡናማ ቀለም ያለው ደግሞ የሀሞት ፍሰት ሲቀንስ የሚፈጠር ነው።
⏩ #ለሀሞት ጠጠር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
🔺 የቤተሰብ ታሪክ
🔺 ብዙ የቅባት መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዝወተር
🔺 ውፍረት
🔺 እርግዝና
🔺 ኮሌስትሮል መጠን መብዛት
🔺 በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደትን በመቀነስ
🔺 የስኳር ሕመም
🔺 የእድሜ መግፋት
🔺 በጾታ ሴት መሆን
🔺 የጉበት ችግር
🔺 ኢስትሮጅን ያለው የወሊድ መቆጣጠሪያ ተጠቃሚ መሆን
⏩ #የሀሞት ጠጠር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
🔺 አብዛኞቹ የሀሞት ጠጠሮች በጊዜ ምልክት የማያሳዩ ሲሆን የሚታዩት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸዉ እነርሱም፦
🔺 ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች
🔺 የሆድ መነፋት፣ ቃር፣ ማቃጠል እና ጋዝ የመሳሰሉትን ናቸው።
🔺 ድንገተኛና አጣዳፊ ህመም በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ይሰማል።
🔺 የጀርባ ህመም በሁለቱ ትከሻ መሀል ይሰማል
🔺 ማጥዎልዎል እና ማስመለስ
🔺 ህመሙ ከደቂቃ እስከ ሰአታት ሊቆይ ይችላል
🔺 ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
⏩ #የሀሞት #ጠጠር #ለምን #ይከሰታል?
🔺 ትክክለኛ ምክናየቱ ባይታወቅም የሚከተሉት ከታዩ ጠጠር ይፈጠራል
🔺 የሀሞት መብዛት
🔺 የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
🔺 የብሉሪብን መጨመር
🔺 በሀሞት ከረጢት ውስጥ ሀሞት፡ ኮሌስትሮልና ቢሊሩቢን ለረጅም ጊዜ ሲቆይ
⏩ #የሀሞት #ጠጠር #መከላከያ #መንገዶች
🔺 በቂ ውሀ #መጠጣት
🔺 ስብን መቀነስ
🔺 ምግብን በሰአቱ መመገብ
🔺 ክብደት መቀነስ
🔺 ጥራጥሬ፡ ፍራፍሬና ቅጠላቅጠል መመገብ
🔺 የስኳርና የኮሌስትሮል መጠን መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
⏩ #የሀሞት ጠጠር መፍትሄዎች
🔺 አብዛኛውን ጊዜ የሀሞት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ቀዶ ጥገና በማድረግ ጠጠሩን ያስወጣሉ።
🔺 ጠጠሩን ማሟሟት የሚችሉ መድኃኒቶችንም መውሰድ ሌላኛው መፍትሄ ነው።
🔺 ቅባታማ ምግቦችን መቀነስም ይገባናል።
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍#በእርግዝና #ወቅት #መመገብ(#መዉሰድ) #የሌለባቸዉ #የምግቦች
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
🔵#በደንብ ያልበሰለ/ጥሬ ስጋ እና የዶሮ ዉጤቶችን
🔹 በእርግዝናዎ ወቅት ነፍሰጡር ካልሆኑት አንፃር ሲታይ በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የምግብ መመረዝ የመጋለጥ እድል ከፍ ያለ ነዉ፡፡ ስለሆነም ከምግብ ወለድ ህመሞች እራስን ለመከላከል ሁሉንም የስጋና የዶሮ ተዋፅኦዎችን ከመመገብዎ በፊት በሚገባ ማብሰል እንቁላል ነጩ እና አስኳሉ በደንብ እስኪጠነክሩ ድረስ በደንብ መቀቀል(ጥሬ እንቁላል አደገኛ በሆኑ ባክቴሪያዎች ሊበከል ይችላል)፡፡ ከጥሬ ወይም በደንብ ካልበሰ እንቁላል የተዘጋጁ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ተገቢ ነዉ፡፡
🔵# የማህጸን መኮማተር የሚያመጡ ምግቦች
🔹 በእርግዝና ወቅት ፓፓዬ ፣አናናስ፣ተልባ፣አብሽ እና የሞሪንጋ ሻይ እንዲወሰዱ አይመከርም ምክንያቱም በውስጣቸው የሚይዙት ንጥረ ነገር የማህጸን መኮማተርን ስለሚያስከትል ለውርጃ ያጋልጣል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህን መሰል ምግቦች አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት የመዉለጃ ጊዜዋ ሲደርስ(ወሯ ሲገባ) ብትጠቀማቸዉ ምጥ ቀለል ሊያደርግላት ይችላል፡፡
🔵#ፓስቸራይዝድ ያልተደረጉ ምግቦችን
🔹 ብዙዎቹ መጠናኛ ስብ የያዙ እንደ ክሬም የወጣለት ወተትና ማንኛዉም ፓስቸራይዝድ ያልተደረገ ወተት የያዙ ምግቦችን መመገብ ለምግብ ወለድ ህመሞች ሊዳርግዎ ይችላል፡
🔵#በደንብ ያልታጠቡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን
🔹 ጤናን ሊጎዱ ከሚችሉ ባክቴሪዎች እራስን ለመከላከል በደንብ ያልታጠቡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ያለመመገብ
🔵#ከመጠን ያለፈ ካፊን/ caffeine/
🔹 ካፊን ያላቸዉ ምግቦች እንደ ቡና፣ሻይ እና ቸኮሌት አዘዉትሮ/አብዝቶ መመገብ እትብትን በማለፍ በዉስጣቸዉ የያዙት አነቃቂ ንጥረ ነገር (ካፊን) ፅንስን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ምንም እንኳ ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከመጠን ያለፈ ካፊን ያላቸዉን ነገሮች መጠቀም ለዉርጃ የመጋለጥ እድሉን ሊጨምር እንደሚችል ያሳያል፡፡
🔵#አልኮል
🔹 በእርግዝናዎ ወቅት ምንም አይነት አልኮል መዉሰድ የተከለከለ ነዉ፡፡ በእርግዝና ወቅት አልኮል መዉሰድ ፅንሱን የአፈጣጠር ችግር እና ከተወለደ በኋላም የአእምሮ እና የአካል እድገት ዉስንነት ያስከትላል፡፡ እንዲሁም አልኮል የሚጠጡ እናቶች ለዉርጃ እና በማህጸን ዉስጥ የፅንስ ሞት ያጋጥማቸዋል፡፡
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍ #ለፎሮፎር #በቤት #ውስጥ #ምን #ማድረግ #ይቻላል?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
🔺 የኮኮናት ኦይል መቀባት:-ራስዎትን ከተቀቡ በኋላ 30 ደቂቃ -1ሰአት አቆይተው ይታጠቡት፤ይህንን በሳምንት እስከ ሶስቴ ያድርጉ።
🔺 እርጎ መቀባት:-እርጎ ራስዎትን ተቀብተው ከ 10 - 15 ደቂቃ ይቆዩ፤ ከዛ በኋላ በሻምፖ ይታጠቡ።
🔺 ራስዎትን የሎሚ ጭማቂ መቀባት:-የሎሚ ጭማቂ ራስዎትን ተቀብተው ለትንሽ ጊዜ ያህል ቆይተው ራስዎትን በደንብ ይታጠቡ፡፡
🔺 ራስዎትን vinegar/አቼቶ መቀባት:- ሁለት የሾርባ ማንኪያ አቼቶ ራስዎትን ተቀብተው ትንሽ ጊዜ ይቆዩና በደንብ ይታጠቡት፡፡
🔹 ሁለት የሾርባ ማንኪያ አቺቶ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት እና ከሶስት ማንኪያ ውሀ ጋር መደባለቅ እና መቀባት፡፡ ከ10 ደቂቃ በኋላ በሻንፖ መታጠብ፡፡ ይሄንንም በሳምንት አንዴ ይሞክሩት፡፡
🔺 በዚንክ እና በቫይታሚን ቢ 6 የበለጸጉ ምግቦችን መብላት:- ቀይ ስጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ የወተት ውጤቶች አንዳንዶቹ ናቸው።
🔺 እንደ ጄል እና ጸጉር ላይ የሚነፉ ስፕሬዎች የመሳሰሉትን ኬሚካል ያላቸው ነገሮች መጠቀም መቀነስ
🔺 ጭንቀት መቀነስ
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍️ #የስንፈተ #ወሲብ #መድሐኒት #የጎንዬሽ #ጉዳት
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
👉👉 #የስንፈተ ወሲብ ችግር በዋናነት ወደ ብልት የሚደርሰዉ የደም ዝዉዉር እና የነርቭ ስርአት ላይ ተፅእኖ ሲፈጠር ፤በሆርሞን መዛባት እንዲሁም የጡንቻ መዛል ሲኖር ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ያለ ባለሙያ ምክር እና ትዛዝ የተለያዩ መድሃኒቶችን ሲያዘወትሩ ይስተዋላል የነዚህን መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት
👉👉 በሚዋጥ በሚቀቡ ወይም በሌሎች መንገድ የተቀመሙ መዳኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት
🔵 የራስ ምታት
🔵 የደም ግፈት መቀነስ
🔵 የጡንቻ ህመም
🔵 የጀርባ ህመም
🔵 ማዞር እስከ ራስ መሳት የሚያስከትል ሊሆን ይችላል
🔵 የአይን ብዥታ
🔵 የሰውነት መቅላት (መቆጣት)
🔵 የአፍንጫ ማፈን
🔵 ብልት አካባቢ ጤናማ ያልሆነ እብጠት
🔵ብልት አካባቢ ኢንፌክሽን
👉👉 #በጣም #ያልተለመዱ #ወጣ #ያሉ #የጎንዮሽ #ጉዳቶች
🔵 የብልት ከ 4 ሰአት በላይ መነሳት ይህም በብልት አካባቢ ያሉ የደም ስሮች እስከ መበጠስ ሊያደርስ ይችላል
🔵 የእይታ መጣት (አይነ ስውርነት)
🔵 የመስማት ችግር
🔵 ድንገተኛ ሞት
👉👉 ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች የስንፈተ ወሲብ መዳኒቶች ሙሉ ለሙሉ ከስሩ ችግሩን የማፈታ አይደለም በተጨማሪም ሌሎች ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ይህን መዳኒት መውሰድ ፈፅሞ አይችሉም እስከ ሞት የሚያደርስ ውስብስብ ችግሮችን ይዞ ይመጣል፡፡
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
ከውርጃ በኃላ መቼ እርግዝና ይፈጠራል?
https://youtu.be/qYaxzygbI54
ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ምስሉን ወይም ሊንኩን ይጫኑ!!
✍️ #በእርግዝና #ወቅት #የአልትራሳውንድ #ጠቀሜታ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
🔵 #የመጀመሪያ የእርግዝና ክፍለጊዜ
🔹 እርግዝናው መከሰቱን ለማረጋገጥ
🔹እርግዝናው ማህጸን ውስጥ ወይም ከማህጸን ውጪ መከሰቱን ለማረጋገጥ
🔹 የጽንሱን እድሜ ለማወቅ
🔹 ጽንሱ የልብ ምት እንዳለው ለማረገጋገጥ
🔹 አካላዊ ግድፈት ካለ ለማየት
🔹 ዳውን ሲንድረም የተባለው ህመም የመከሰት እድሉን ለማወቅ
🔹 በማህጸን እና እንቁልጢ አካባቢ የሚከሰቱ ያልተለመዱ ሁኔታዎችን ለመለየት
🔵#ሁለተኛው የእርግዝና ክፍለጊዜ
🔹 የጽንሱን አእምሮ ጤንነት ለማረጋገጥ
🔹 የጽንሱን የፊት ገጽታ አካላት ለማረጋገጥ
🔹 የጽንሱን የውስጥ አካላት ለማየት( ልብ፤ሳምባ፤አንጀት፤ጉበት፤ኩላሊት፤የሽንት ፊኛ)
🔹 የእግርና የእጅ እድገትን ለመቆጣጠር
🔹 የጀርባ እና አከርካሪ አጥንትን አቀማመጥ ለማየት
🔹 የጽንሱን ጾታ ለመለየት
🔵 #ሶስተኛው የእርግዝና ክፍለጊዜ
🔹 የጽንሱን ክብደት ለማረጋገጥ
🔹 የጽንሱን አመጣጥ እና የእንግዴ ልጁን አቀማመጥ ለማወቅ
🔵 #በመጨረሻ
🔹 የሚፈጠሩ ጤነኛ ያልሆኑ እድገቶች ካሉ እሱን ለመለየት
🔹 ሀኪሙ ጤነኛ ያልሆነ የጽንስ እድገት እንዳለ ከጠረጠረ ይህን ለመለየት ዶፕለር በተባለ መሳሪያ የደም ስሩን ጤንነት መመርመር
🔹 የሽርት ውሃ መጠንን ለመለካት
👉👉 #ስለጤናዎ ለመመካከር 8809 ላይ እየደወሉ ባለሞያዎችን በቀጥታ መገናኘት ይችላሉ፡፡ ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✍ 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
ፅንስ ማስወረድ እና አደጋዎቹ
https://youtu.be/ZRNH_xmmG14
ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ምስሉን ወይም ሊንኩን ይጫኑ!!
✍ #የከሰል #ጭስ #አማካኝነት #ስለሚመጣ #የአየር #መበከል
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
👉👉 #በአል ሲሆን በከሰል የመጠቀም ነገር ይስተዋላል፡፡ከከሰል የሚወጣዉ መርዛማ ጋዝ (ካርቦን ሞኖኦክሳይድ) ቀለም፣ ሽታ እንዲሁም ጣዕም የሌለዉ ቢሆንም በአየር ላይ የበዛ ካርቦን ሞኖኦክሳይድ ካለ ወደ ዉስጥ የምንተነፍሰዉን ኦክስጅን በካርቦን ሞኖኦክሳይድ ይተካና ንጹህ ኦክስጅን ወደ ደም ስራችን የመድረስ አቅሙ ይቀንሳል፡፡
👉👉 #በካርቦን #ሞኖኦክሳይድ #መመረዝ #ምልክቶች
📌 ራስ ምታት
📌 ድካም
📌 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
📌 የትንፋሽ ማጠር
📌 የጭንቅላት መቅለል
📌 የእይታ መደብዘዝ
📌 ግራ መጋባት
📌 ድብርት
📌 ለማስታዎስ መቸገር
📌 ራስን መሳት
👉👉 #ለችግሩ #በይበልጥ #ተጋላጭ #የሚሆኑት #እነማን #ናቸዉ
📌 ነፍሰጡር
📌 ህጻናት
📌 በእድሜ የገፉ
📌 ልብ እና ሳንባ ላይ ችግር ካለ
⏩ #መልካም #በአል!!!
👉👉 #በካርቦን ሞኖኦክሳይድ ጋዝ መብዛት እንዳይኖር ከሰል በምንጠቀምበት ጊዜ በር እና መስኮት መክፈትዎትን አይርሱ ሆኖም ግን ችግሩ ከተከሰተ ወዲያዉኑ ንጹህ ኦክስጂን ማግኘት መቻል ምልክቶች ካልጠፉ እና ከተባባሱ ወደ ጭንቅላት የሚሄደዉን ደም በመመረዝ ምክንያት የጭንቅላት ጉዳት፤ የልብ ድካም፤ዉርጃ ብሎም ሞት ስለሚያስከትል ወደ ህክምና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነዉ፡፡
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
የቴሌግራም ቻናላችን👇 ለሌሎች ያጋሩ
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
የጡት ህመም እንዴት ይከሰታል? | ከጡት ካንሰር ጋር የሚያገኛኘው ነገር አለ?
✅ ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
https://youtu.be/HHu0mUnRY8w
✍️ #ትንታ/ #መታነቅ (chocking)
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
⏩ # ትንታ በላይኛው የመተንፈሻ አካል ማለትም በጉሮሮ ውስጥ ምግብ ወይም ሌሎች ባዕድ ነገሮች ሲገቡና የተጎጂውን የመተንፈሻ አካል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመዝጋት የመተንፈስ ችግር ሲያስከትሉ ትንታ/መታነቅ (choking) ደረሰበት ይባላል፡፡
⏩ #መንስኤዎቹ
🔺 ምግብ በደንብ አኝኮ አለመዋጥ
🔺 ምግብ በሚበሉበት ጊዜ ማውራት ወይም መሳቅ
🔺 በአንዳንድ የጤና ሁኔታዎች ወይም ድክመቶች ምክንያት ምግቦችን የመዋጥ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል
⏩ #ምልክቶቹ
🔺 ከፍተኛ ሳል ማሳል
🔺 የእጅ ምልክቶች እና ሽብር (አንዳንድ ጊዜ ወደ ጉሮሮ ይጠቁማሉ)
🔺 በድንገት ለማውራት(ለመናገር) መቸገር/ የተቆራረጡ ቃላትን መናገር
🔺 በጉሮሮዎ ጀርባ ላይ የሆነ ነገር መሰማት
🔺 የመተንፈስ ችግር ወይም መተንፈስ አለመቻል
🔺 ወደ ሰማያዊነት መለወጥ - (በፊቱ ፣ በከንፈሮቹ እና በጥፍር)
🔺 የንቃተ ህሊና ማጣት
⏩ #መከላከያዎቹ
🔺 በተለይ ከ4ዓመት በታች ህፃናት ያገኙትን ነገር ወደ አፋቸው ስሚወስዱ ህፃናት በሚጫወቱበት እና በሚገኙበት አካባቢ እንደ፡- ጥራጥሬ፣ ሳንቲም፣ ቁልፍ፣ ብሎን፣ ፍራፍሬ እና የመሳሰሉት እንዳይኖር ማድረግ በመጫዎቻነትም አመስጠት
🔺 በህፃናት አመጋገብ ዙሪያ ጥንቃቄ ማድረግ ፤ በንደብ የላመ ምግብ መመገብ
🔺 በጨዋታ ጊዜ በአፋቸው የሚበላ ነገር ይዘው መሯሯጥ መከልከል
🔺 ሕጻናት በሚመገቡበት ጊዜ ብቻቸውን አለመተው
🔺 ማንኛውም ሰው ምግብ በሚመገብበት ጊዜ በደንብ አኝኮ መዋጥ አለበት፡፡ በተለይ ጥሬ ስጋና አትክልት በደንብ ካልታኘኩና በትንሹ ካልተቆራረጡ የተወሰነ ጫፍ በጥርስ ላይ ተጣብቆ ሲቀር ሌላው ጫፍ በጉሮሮ አከባቢ ሲደርስ ወደታች እንዳይወርድ በመያዝ መታነቅን ያስከትላል
🔺 እያወሩ እና እየሳቁ መመገብ ለመታነቅ ይዳርጋል
⏩ #የመጀመሪያ #እርዳታ #ለትንታ
🔺 በተቻለዉ መጠን በመደጋገም እንዲያስል ማበረታታት
🔺 ያነቀው ምግብ ወይም ባዕድ ነገር ሙለ በሙለ መውጣቱንና ተጎጂው ህሊናውን ወይም ራሱን በደንብ የሚያውቅ መሆኑን ሳያርጋግጡ ምንም ነገር ፈሳሽ ጭምር በአፍ መሰጠት አይገባም
🔺 ተጎጂው ማሳል እና መተንፈስ ካቃተው ተጎጂው ሙለ በሙለ ታንቋል ማለት ስለሚሆን ቀጣዩን ዕርዳታ ይስጡ፤ እርዳታ እየሰጡ አምቡላንስ ያስጠሩ
⏩ #ሙሉ #በሙሉ #ሲሆን
🔹ተጎጂዉ መተንፈስ መናገር ወይም መሳል አይችልም ስለሆነም በሁለት እጆቹ አንገቱን ጥርቅም አድርጎ በመያዝ እርዳታ ፍለጋ እራሱን ሲያንቀሳቅስ ይታያል
🔹ይህ ምልክት ሲያጋጥም የአየር ቧንቧዉ ሙሉ በሙሉ የተዘጋ መሆኑን ተረድተን በሚከተለዉ መንገድ ለመርዳት መሞከር ይኖርብናል
🔺 የእርዳታ ጥሪ ማድረግ
🔺 ባእድ ነገር ወደ ጉሮሮዉ ገብቶ የታነቀን ሰው አፉን በማስከፈት ባዕድ ነገሩ የሚታይ ከሆነ ብቻ
ጣቶችን አስገብቶ ለማውጣት መሞከር፤
🔺 ያነቀው ነገር የማይታይ ከሆነ የታነቀውን ሰው በማስጎንበስ በሁለቱ የጀርባ አጥንቶች መካከል
ፈጠን ብለን 5 ጊዜ ብንመታው የገባው ነገር ሊወጣ ይችላል
🔺 በዚህ እርዳታ ተጎጂው ከችግሩ መዉጣት ካልቻለ ከተጎጂዉ በስተጀርባዉ በመቆም አንደኛዉን እጅ በመጨበጥ ሌላኛዉን እጅ በላዩ ላይ በመደረብ በተጎጂዉ እንብርትና ከታችኛዉ ደረት መካከል አድርገን ወደ ዉስጥና ወደ ላይ በተከታታይ በመጫን መርዳትና በየመሀከል መዉጣቱን መመልከት
🔺 በድንገት እራሱን ከሳተ በቀስታ በጀርባዉ ማስተኛትና ደረቱን ቢያንስ በደቂቃ መቶ ጊዜ ያህል
በመደጋገም በመጫን የደም ዝዉዉሩንና አተነፋፈሱን ማገዝ
⏩ #ነፍሰ ጡር #ሴት #ወይም #ወፍራም #ሰዉ
🔺 በእርግዝናዉ መግፋት ወይም በዉፍረት ምክንያት እጃችንን ሆድ ላይ ማረግ ስለማንችል ከሆድ ከፍ ብለን ከጡት ስር በግራ እና በቀኝ ደረት በኩል በተከታታይ መጫንና ሚወጣ ነገር ካለ መመልከት
⏩ #ሕጻን #ልጅ
🔺 ሕጻን ልጅ ላይ ከሆነ ደረቱን በአንድ እጃችን ጉልበታችን ላይ አድርገን በሌላኛዉ እጃችን ጀርባዉን መታ መታ ማድረግና ከዚያም ወደ ሌላኛዉ እጃችን
በማዘዋወር ደረቱን ጫን ጫን ማድረግ
⏩ #ብቻዎን እያሉ ይህ አይነቱ ችግር ከገጠመዎት በወንበር ራስጌ ጠርዝ ላይ ሆድን በማስደገፍ ሆድዎን ጫንጫን በማድረግ እራስዎን ይርዱ
የቴሌግራም ቻናላችን👇 ለሌሎች ያጋሩ
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
✍#የቶንሲል #ህመም
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥
👉 👉 #የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ቫይረስና ባክቴሪያዎች በአፍና በአፍንጫችን አድርገው በመግባትም ጭምር የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላሉ፡፡
👉 👉 #የህመሙ #ምልክት #ምንድን #ነው?
🔵 ቀይ ያበጠ ቶንሲል
🔵 በቶንሎች ላይ ነጭ ወይም ቢጫ ሽፋን
🔵 በጉንፋን የተዘጋ ጉሮሮ
🔵 ለመዋጥ መቸገር
🔵 ትኩሳት
🔵 ያበጡ ሊምፍ ኖዶች መኖር
🔵 መጥፎ የአፍ ጠረን
🔵 የሆድ ቁርጠት
🔵 የአንገት ህመም
🔵 ራስ ምታት
👉 👉 #አጋላጭ #ነገሮች
🔵 ወጣት ዕድሜ፡- ብዙውን ጊዜ የቶንሲል በሽታ በልጆች ላይ የሚከሰት ሲሆን በባክቴሪያ የሚከሰተው የቶንሲል በሽታ ከ 5 እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ላይ ባሉ ልጆች ላይ በጣም የተለመደ ነው፡፡
🔵 በተደጋጋሚ ለጀርሞች መጋለጥ፡- እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ከእኩዮቻቸው ጋር በቅርበት የተገናኙ እና ብዙ ጊዜ የቶንሲል ህመም ሊያስከትሉ ለሚችሉ ቫይረሶች ወይም ባክቴሪያዎች ይጋለጣሉ።
👉 👉 #የቶንሲል #ህመም #የሚያመጣው #ውስብስብ #ችግር
🔵 በእንቅልፍ ወቅት ለመተንፈስ መቸገር
🔵 ወደ ታችኛው የጉሮሮ አካባቢው የሚዛመት ኢንፌክሽን
🔵 መግል የቋጠረ የቶንሲል እጢ
👉 👉 #ሕክምና
🔵 የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ሕመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት ይለያያል፡፡ በቫይረስ ምክንያት የሚመጣን የጉሮሮ ሕመም ሰውነታችን ባለው የበሽታ መከላከል አቅም የሚዋጋ ሲሆን መድኃኒት መውሰድ አስፈላጊ አይሆንም፡፡ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰትን የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ቦታ በመሄድ ባክቴሪያ አጥፊ መድኃኒቶችን (Antibiotics) መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
👉 👉 #ከዚህ #በተጨማሪ #የሕመሙን #ሁኔታ #እንዲያስታግስልን፤
🔵 በቂ ዕረፍት መውሰድ
🔵 ትኩስ ፈሳሽ መውሰድ፡- ሻይ፤ ወተት፤ አጥሚት
🔵 ለስለስ ያሉ ምግቦችን መመገብ፡- ሾርባ
🔵 ለብ ባለ ውሃ በጨው እና ዝንጅብል መጉመጥመጥ
🔵 አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አራት ማንኪያ ማር፣ ሩብ ማንኪያ ጨው እና የሎሚ ጭማቂ ጨምረን በማዋሃድ በቀን ከ2 እስከ 3 ጊዜ መጠጣት ጥሩ ወጤት ያስገኛል።
የቴሌግራም ቻናላችን👇 ለሌሎች ያጋሩ
https://t.me/DrJano
https://t.me/DrJano
እርግጠኛ ነኝ ፎቶ ለመነሳት ፈልገው የአነሳስ style ጠፍቶብዎት ተቸግረው ያውቃሉ።የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው።
https://t.me/+RPX65IKfSq81BF0C
