የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 230 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 245,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 081 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 230 名订阅者。
根据 06 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 625,过去 24 小时变化为 -24,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.69%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.08% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 437 次浏览,首日通常累积 337 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 11。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 230
订阅者
-2424 小时
+2177 天
+62530 天
帖子存档
16 230
🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️
📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ
እና የሌሎችንም ...........
ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
16 230
ደስታ የት ነው ያለችው?
ደስተኛ ሕይወት መኖር የብዙ ሰው ፍላጎት ነው ሰው ከሁሉም ነገር በላይ ለደስታ ሲል እውቀቱን ጉልበቱን ገንዘቡን ያወጣል በዚሕ መልኩ ደስታውን ሲፈልግ ብዙ ሰው አያገኘውም የደስታ መገኛ ወዴት ነው? ደስታን ሰው በተለያየ ቦታ እየዞረ ይፈልጋታል አንዳንዱ መንፈሳዊ ቦታዎች በመሔድ ይፈልጋታል አንዳንዱ በእውቀት መገኛ ቦታ በትምሕርት ቤት ይፈልጋታል አንዳንዱ በሥራ ቦታ በሥራ ውስጥ ይፈልጋታል አንዳንዱ ደግሞ በመዝናኛ ቦታዎች ዘና እያለ ይፈልጋታል አንዳንዱ ደግሞ በመጠጥ ቤት እየጠጣ መጠጥ ውስጥ ይፈልጋታል አንዳንዱ በስፖርት ቤት በስፖርት ውስጥ አንዳንዱ በማሕበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ አንዳንዱ በእንቅልፍ አንዳንዱ በሀብትና ንብረት ውስጥ ይፈልጋታል ግን በሁሉም ውስጥ ደስታ አትገኝም ደስታ ለአንተ ታስፈልግሀለች እንጂ አንተ ለእርሷ አታስፈልጋትም ደስተኛ መሆን የሁሉም ፍላጎት ነው ሰው ለረጅም ዘመን ያካበተውን ሀብት ለደስታ ለማውጣት አይግደረደርም ምክንያቱም ሁሉም ለደስታ ነውና ታዲያ እቺ በሰው የምትወደድ የምትፈለግ ደስታ መገኛዎ ወዴት ነው? መገኛዎማ ራስሕ ውስጥ ነው አንተ በውጪ ትፈልጋታለሕ እንጂ ደስታ ያለቺው ውስጥሕ ነው ዎጋዎም ርካሽ ነው ደሀውም ሀብታሙም እኩል ገንዘብ ሊያደርጓት ይችላሉ ።
ደስታ ውስጥሕም ብትሆን የአንተ አያያዝና አጠቃቀምሕ ነው ሕይወት የሚዘራባት ካለበለዚያ በውስጥሕም ብትኖር ትገድላታለሕ ደስታን የምትፈልጋት ከሆኔ እኔ ልጠቁምሕ በሕሊናሕ ውስጥ ወዳለው እውነት ግባ በዛም ውስጥ ደስታሕን ታገኘዎለሕ እውነትን ተቀበል በእውነት ኑር እውነተኛ እርዳታ አድርግ በእውነት የኑሮ ደረጃሕን አምነሕ ተቀበል ገንዘብ ስትሰበስብ ሳይሆን ገንዘብን ስትሰጥ ነው ደስታ ምታገኘው በእውነት ፍረድ በእውነት ምከር በእውነት ሥራ በእውነት አግባ በእውነት ጸልይ በእውነት አግኝ በእውነት ተማር ለእውነት ተጠቀምበት በእውነት አስተዳድር በእውነት ተመራ በእውነት ውደድ በእውነት ተወደድ በእውነት ዝቅ ዝቅ በል በእውነት ድከም በእውነት አግኝ
ለእውነት ኑር ለእውነት ሙት እዛ ውስጥ ነው ደስታ የምትገኘው ።
🥰🥰መልካም ቀን ይሁንላችሁ🥰🥰
16 230
+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +
የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::
ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::
እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::
ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::
ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::
ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::
ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::
የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::
ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?
እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::
ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
16 230
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ!
ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡
"ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
ገፅ 86
16 230
አንዳንዴ እልህ የሚያሲዙህ ሰዎች ባያቁትም አብዝተው መውደቂያቸውን እያመቻቹ ነው። ግን አወዳደቃቸው ይጎዳቸዋል የ እልሁን ክፍያ ከዛ ሰው ስለሚያገኙ!
16 230
ስትጀምር ይንቃሉ!!
ስትሳሳት "ብለን አልነበር!" ይላሉ፡፡
መሐል ስትደርስ ወደ ኋላ ይጎትታሉ፡፡
ወደ መጨረሻው ስትቃረብ መንገድ ይዘጋሉ፡፡
እንደምንም ስታሳካው ግን መግቢያ ያጣሉ፡፡
ወዳጅ መስለው ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡"እንኳን ደስ ያለህ!" ይላሉ፡፡
አንተ ግን ስትጀምርም አትስማቸው፡፡ስትጨርስም አትስማቸው፡፡ራስህ ላይ እና ስራህ ላይ
ብቻ አተኩር፡፡ስኬት ሲመጣ ወደ አንተ የማይመጣ የለም፡፡
✨መጀመርያ_ስኬታማ_ሁን!!!
16 230
፡
ሰባራ ሳለች መብረር ያቃታት
ከጎጆው ወስዶ ጠግኖ አዳናት
ኖራ ኖራ ግን
ታዛው ከሞቀ
ጥላው ብትበር
በቁም ወደቀ
ያ አዳኝ ልቡ አዝኖ ሲሰበር
ቃላቱ ሁሉ
ያኔ ማዳኔ ጥፋቴ ነበር?!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
16 230
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
16 230
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
16 230
🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️
📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ
እና የሌሎችንም ...........
ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
16 230
ፈልገውህ ከመጡና ፈልገሃቸው በሔድካቸው ሰዎች መካከል ዋጋህ እኩል አይደለም! ባንዱ ስትከበር ባንዱ ቀለህ ትታያለህ ያላንዳች መገምገሚያ።
16 230
ይህንን ያውቃሉ⁉️
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሴቶች የወር አበባ ላይ በሚሆኑበት እና ከፍተኛ ህመም በሚያጋጥማቸው ግዜ ሙዝ መመገብ ከከፍተኛ ህመም ይጠብቃቸዋል ምክንያቱም ሙዝ በፋይበር እና በማግኒዥየም የበለፀገ በመሆኑ የፔሬዱን ህመም ይቀንስላቸዋል 🍌
16 230
ይህንን ያውቃሉ ⁉️
ጥናቶች እንደሚገልፁት ከሆነ አንዲት ሲጋራ የምታጨስ ሴት ጡቷ ያለጊዜው ማለትም ከሌሎች ከማያጨሱ ሴቶች አንፃር በፍጥነት ነው የሚወርደው .... ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሲጋራ ማጨስ ሴቶች ጡት ውስጥ የሚገኘውን Elastin ተብሎ የሚጠራውን Protien ስለሚያዳክመው ነው ይህም ወደ ጡት መውረድ ይመራል
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
