ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

前往频道在 Telegram

↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya

显示更多
3 819
订阅者
-524 小时
+1617 天
+15530 天
帖子存档
🌴ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ  እንዲህ ብለዋል፡- ❝ጂኒዎች ብዙ ጊዜ ሰዎችን ያግታሉ ከሰዎችም እይታ ይሰውሯቸዋል በአየር ላይ ይዘዋቸው ይበርራሉ ለመግለጽ ብዙ ጊዜ የሚፈጁ ጉዳዮች አጋጥመውን ያቃሉ።❞ 📚مجموع الرسائل الكبرى (٣٠٧/٢) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሰለፎች """" ❝ከፊል ቀደምቶች አላህ ለረመዷን ወር እንዲያደርሳቸው ለስድስት ወራት ያህል አላህ ይለምኑ ነበር ከዚያም ፆማቸውን እንዲቀበላቸው ለስድስት ወራት ያህል ዱዓ ያደርጉ ነበር።❞ 📚لط
🌴ሰለፎች """" ❝ከፊል ቀደምቶች አላህ ለረመዷን ወር እንዲያደርሳቸው ለስድስት ወራት ያህል አላህ ይለምኑ ነበር ከዚያም ፆማቸውን እንዲቀበላቸው ለስድስት ወራት ያህል ዱዓ ያደርጉ ነበር።❞       📚لطائف المعارف(٢٠٩)] ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ  እንዲህ ብለዋል፡- ❝መልካሞችን ሁሉ ከያዙ ዱዓዎች መካከል አንዱ በአነስ (ረ ዐ) ዘገባ  የጠቀሰው ሐዲስ ሲሆን ነብዩ ﷺ ዱዓ በሚያደርጉ ጊዜ ይህንኑ ዱዓ በብዛት  ይሉ ነበረ፡-«ጌታችን ሆይ በቅርቢቱ ዓለም መልካምን በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሙን ለገሰን ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን»።«ጌታችን ሆይ በቅርቢቱ ዓለም መልካምን ለገሰን»የሚለው፦ በዱንያ ላይ ያለ መልካምን ሁሉ ያካትታል  ለምሳሌ ያህል፦ እንደ ጥሩ ሚስት፣ጥሩ መጓጓዣ፣ ሰፊና ጥሩ መኖሪያ ቤት  ሌሎችንም መልካሞችን ያጠቃልላል።በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሙን ስጠን ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን"።ይህም በመጨረሻው ዓለም ያለን ሁሉንም ያጠቃልላል።ለምሳሌ፦ ቀላል ምርመራ፣ መፅሃፉን በቀኝ እጅ መስጠት ፣ሲራጥን በቀላሉ ማለፍ  ከመልእክተኛውﷺ ሃውድ መጠጣት  ጀነት መግባትና ሌሎች መልካሞች ሁሉ ይካተቱበታል። ይህ ዱዓ ከሁሉም ዱዓዎች የበለጠ  የዱዓ ዓይነቶችን አሟልቶ የያዛና እጅግ በጣም ሰፊ የሆነ ነው። 📚شرح رياض الصالحين(مـ٦/صـ١٦) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

የጁሙዓ ሳምንታዊ ምክር.. 🌴ሸይኽ አብደላህ ሰኢድ 🕌ከሃዋ መስጂድ

«فَمِنْهُم مَّنْ آمَنَ بِهِ وَمِنْهُم مَّن صَدَّ عَنْهُ ۚ وَكَفَىٰ بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا» ከእነሱም (ከይሁዶች) በእርሱ ያመነ አለ፡፡ ከእነርሱም ከ
«فَمِنْهُم مَّنْ آمَنَ بِهِ وَمِنْهُم مَّن صَدَّ عَنْهُ ۚ وَكَفَىٰ بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا» ከእነሱም (ከይሁዶች) በእርሱ ያመነ አለ፡፡ ከእነርሱም ከእርሱ ያፈገፈ አለ፡፡ አቃጣይነትም በገሀነም በቃ፡፡ አል-ኒሳዕ፣55 ═════ ❁✿❁ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሰሙራ ቢን ጁንዱብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳስተላለፈው፡- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- " أحب الكلام إلى الله أربع ؛ سبحان الله، والحمد لله، ولا إله إلا الله، والله أكبر، لا يضرك بأيهن بدأت " . ወደ አላህ ዘንድ በጣም የተወደዱ ቃላቶች አራት ናቸው፦«ሱባሃን አላህ" አልሃምዱሊላህ" ወላ ኢላሃ ኢለላህ" ወሏሁ አክበር» በየትኛውም ብትጀምር ምንም ችግር የለውም።      📚رواه مسلم 2137 ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- 👉አላህ ጭንቀትና መረበሽን ከሚያስወግድባቸው ታላላቅ መንገዶች መካከል፦ 1-ኃያሉን አላህን ማስታወስ። 2-ቁርኣንን አብዝቶ ማንበብ። 3-በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን ማብዛት። እነዚህ ጭንቀትንና መረበሽን ለማስወገድ ትልቅና ዋናዎቹ ምክንያቶች ናቸው።             📚نور على الدرب ١/ ٣٣٣] ═════ ❁✿❁ https://t.me/Mohammedseid21

«أَمْ لَهُمْ نَصِيبٌ مِّنَ الْمُلْكِ فَإِذًا لَّا يُؤْتُونَ النَّاسَ نَقِيرًا» በእውነቱ ለእነሱ ከንግሥናው ፋንታ አላቸውን ያን ጊዜ ለሰዎች በተምር ፍሬ
«أَمْ لَهُمْ نَصِيبٌ مِّنَ الْمُلْكِ فَإِذًا لَّا يُؤْتُونَ النَّاسَ نَقِيرًا» በእውነቱ ለእነሱ ከንግሥናው ፋንታ አላቸውን ያን ጊዜ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ ያለችውን ነጥብ ያህል አይሰጡም ነበር፡፡ አል-ኒሳዕ፣53 ═════ ❁✿❁ ═ https://t.me/Mohammedseid21

🌴አል-ቁረዚይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- ❝አንድ ሙእሚን  ባለቤቱና ልጆቹ ለታላቁ አላህ ታዛዥ ሆነው እንደማየት የበለጠ የሚያስደስተው ነገር የለም።❞        📚تفسير البغويّ - ٢/٤٩٥ ) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማሙ ሙጃሂድ ቢን ጃቢር ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝አዋቂ ማለት አላህን የሚፈራ ነው ኢልሙ ትንሽ ቢሆንም እንኳ  አላዋቂ ጃሂል ማለት ደግሞ አላህን ያመፀ ነው እውቀቱ የቱንም ያህል ቢደርስም እንኳ።❞ 📚البداية والنهاية (٩/٢٥٥)] ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

«أَمْ يَحْسُدُونَ النَّاسَ عَلَىٰ مَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۖ فَقَدْ آتَيْنَا آلَ إِبْرَاهِيمَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَ
«أَمْ يَحْسُدُونَ النَّاسَ عَلَىٰ مَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۖ فَقَدْ آتَيْنَا آلَ إِبْرَاهِيمَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَآتَيْنَاهُم مُّلْكًا عَظِيمًا» ይልቁንም ሰዎችን (ሙሐመድን) አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን ታላቅንም ንግሥና ሰጠናቸው፡፡ አል-ኒሳዕ(54) ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል፡- ❝እነእርሱ አይቀበሉኝም አይሰሙኝም እኮ አትበል! ነገርግን አንተ ማድረግ ያለብህ ማስተላለፍ ብቻ ነው አንተ ዘንድ ያለችውን ጥቂት ብትሆንም እንኳ አስተላልፍ አላህ ያደርስልሃልና።❞       📚الجامعة الإسلامية ٢٨-٥-١٤٣٧هـ ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ፉደይል ኢብኑ አል-ኢያድ ረሒመሁሏህ አንድ ሰው እንዲህ አላቸው፡- ❝እከሌ የሚባል ሰው እኔን በክፉ ያነሳኛል ያማኛል” አላቸው።"እርሳቸውም" በእርግጥም እሱ ትልቅ የሆነ መልካምን ሃሰና አምጥቶልሃል። "አሉት"።❞ 📚 [ حلية الأولياء لأبي نعيم (18801 ) ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ለአል-ሐሰን አል-በስሪ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ተባሉ፡- ❝እከሌ እናንተን በክፉ ያነሳችኋል። ተባሉ” (እርሳቸውም) “እንኳን ደህና መጣህ  የማላውቅህ  "ሃሰና" መልካም ስራዬ ሆይ! ባንተም ላይ ምንም ያልደከምኩብህ ስትሆን ባንተም ላይ ይዩልኝ እና ኩራት የሌብህ የመልካም ስራ ውጤት ነህና።❞     📚 [ حلية الأولياء لأبي نعيم (18801 ) ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡- ❝አንድ ወንድምህ ሲንሸራተት «ሲሳሳት» ባየኸው ጊዜ አስረዳው  አስተምረው አላህም ተውበትን እንዲለግሰው ዱዓ አድርግለት አንተም  በወንድምህ ላይ ለሸይጧን አጋዥ እንዳትሆን።❞              📚حلية الأولياء(٩٨/٤ ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝በአንድ ሰው ላይ ጅኖች/ የተለያዩ ቆሻሻ ነፍሶች በሰውዬው ላይ የመከሰታቸውና የማጥቃታቸው ምክንያት ሰውዬው በዲኑ ላይ ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ነው ቀልቡና አንደበቱ አላህን ከማስታወስና በእርሱም ከመጠበቅ በመዘንጋቱ ሰበብ ነው።ምክንያቱም እነዚህ ጂኖች/ ቆሻሻ የሆኑ ነፍሶች ይህን ሰው ምንም መከላከያ መሳሪያ ሳይኖረው  ያገናኙታል እረ እንደውም እርቃኑን ከዚያም (በአላህ ፈቃድ) ተፅዕኖ ያደርሱበታል።❞             📚 زاد المعاد (٩٤/٤) ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- ❝እኔ የምመክራችሁ አላህ በረካ ያድርጋችሁና፦ ከእነዚህ ጨካኝ አረመኔ ከሆኑት  ጅኖች ክፋት ሰላም እንድትሆኑ ነው በቁርኣን እና በሃዲስ የመጡትን አዝካሮች ዘወትር በመጠባበቅ ማድረግ አለባችሁ ከእነዚህም መካከል አያተል-ኩርሲን አንድ ሰው ከልቡ አምኖ በቀራ ጊዜ አላህ በእርሷ ሰበብ ይጠብቀዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- እርሷን በሌሊቱ ክፍል ያነበበ ሰው አላህ ሌሊቱን ሙሉ ጠባቂ ያደርግለታል እስከሚነጋ ድረስ ሸይጧን ፈፅሞ አይቀርበውም። ሰዎች ሸሪዓዊ ከሆኑ አዝካሮች ቸል ባሉ ጊዜ ጂኖች በመካከላቸው ይበዛሉ ከዚያም እንደፈለጉ ይጫወቱባቸዋልና።❞             📚لقاء الباب المفتوح [197] ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና ሰለ ሸይኻቸው ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ሰዎችን በመርዳት ላይ እጅግ በጣም ጠንካራና ፈጣን  ነበሩ ምክንያቱም አንድ ሰው ሰዎችን በሚረዳበት ጊዜ ሁሉ ቻይ የሆነው አላህ እርሱን እንደሚረዳው ስለሚያውቅ ነውና።❞      📚روضة المحبين (1/ 168) ═════ ❁✿❁ ═════ https://t.me/Mohammedseid21