ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

前往频道在 Telegram

↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya

显示更多
3 819
订阅者
-524 小时
+1617 天
+15530 天
帖子存档
«إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَ
«إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا الْعَذَابَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمًا» እነዚያን በተአምራታችን የካዱትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን፡፡ ስቃይን እንዲቀምሱ ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ አል-ኒሳዕ፣56 ═════ ❁✿❁ ══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም አል-ሀፊዝ ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝አላህ ለታማኝ ባሮቹ ላቅ ያለ የክብር ደረጃዎችን  አዘጋጅቶላቸዋል ይህንንም ደረጃ በስራዎቻቸው ብቻ አያገኙትም ነገር ግን በሚደርስባቸው ፈተናዎችና ችግሮች ሰበብ ያገኙት ቢሆን እንጂ።❞         📚فتح الباري ص - 7 / 433 ═════ ❁✿❁ ══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- ❝ታላቅና ምስጉን የሆነው የአላህ ልምድ ነው የባሪያውን ደረጃ ከፍ ሊያደርገው በፈለገ ጊዜ በተለያዩ  መከራዎችና ችግሮች መፈተኑ አይቀሬ ነው ከችግሮቹና ከፈተናዎቹ ካለፈ በኋላ ወደ ትልቋ ደረጃ እንዲደርስ ሰበብ ይሆኑታል።ልክ የጀነት ሰዎች ከሞቱ በኋላ ወደ እርሷ ወደ ጀነት እንደሚገቡት ሁሉ እንዲሁም የቂያማ ቀን አስፈሪ ክስተቶች ከሞት በኋላ እንደሚሆኑት ሁሉ።❞         📚إغاثة اللهفان (1 / 817) ═════ ❁✿❁ ══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝አላህ ይዘንላችሁና እወቁ ከመካከላችሁ በአንድ የዲን እውቀት በሚሰጥበት ስብስብ ውስጥ የተገኘ እና ከዚያም የዲን ትምህርት ከሚሰጥበት ስብስብ አንዲት እውቀት ያወቀና የሰራባት ከዚያም ለወንድሞቹ ያስተማረ ሰው በዚያች ባስተማራት ዕውቀት ተጠቃሚ መሆኑን እወቁ። በዚያች በአንዲት ዕውቀት ብዙ መልካም ነገርን ይቀዳጃል የዚያኛው ሰው ምንዳ ሳይቀነስበት እስከ ቂያማ ቀን ድረስ  የሰራበትን ሰው ምንዳ ያገኛል።የእውቀት መልካምነት የሚመጣው ብዙ በተማረ ሰው ብቻ ነው ብለህ አታስብ።ለሰራተኛ ሁሉ ትንሽም ብትሆን ለሰራው ስራ አላህ ከፋይ ነው ምክንያቱም አላህ ማንም ቅንጣት ታህል በዳይ ጌታ አይደለምና።ነብዩﷺ ከእኔ የሰማችሁትን አንዲትም አንቀፅ ብትሆን አድርሱ"ብለዋል።❞ 📚 المصـدر : الضياء اللامع من الخطب الجوامع :(8/1) ═════ ❁✿❁ ══ https://t.me/Mohammedseid21

قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله : إعلموا رحمكم الله أنّ من حضر منكم مجلسًا واحدًا من مجالس العلم فاستفاد مسألة، عمل بها وعلّمها إخوانه، فإنه يحصّل خيرًا كثيرًا ، ويجرىٰ له أجرها وأجر من عمل بها إلىٰ يوم القيامة، ولا تظنوا أن فضل العلم لا يحصل إلاّ لمن تفقه كثيرًا،‏فإن الله تعالىٰ سوف يجزي كل عامل بعمله وإن قل، ولا يظلمون نقيرًا، قال النبي صلى الله عليه وسلم : « بلغوا عني ولو آية » 📚 المصـدر : الضياء اللامع من الخطب الجوامع :(8/1)

🌴ኢማሙ ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝የዱኒያ ፀጋ ከጀነት ችሮታ ጋር እንደማትገናኘው  ሁሉ የኃያሉ አላህን ፊት መመልከት ከጀነት ችሮታ ጋር  አይገናኝም ይህም አላህ ለሚወዳቸው ባሮቹ  የዋለላቸው ታላቁና ፈፅሞ አምሳያ የሌለው ችሮታው ነው። «ጥራት ለአላህ የተገባ ነው።የቂያማ ቀን የእርሱን ፊት ለመመልከት በዱኒያ ላይ እርሱን ከመውደድ እርሱን ከማወቅና ከማምለክ ወደ እርሱ  ከመጓጓት ጋር የተቆራኘ ነው።❞       📚إغاثة اللهفان (١/٣٣) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ አሉ፡ ❝አንተ በእርግጥም ጌታህን በአይንህ  እንደምታየው ካረጋገጥክ።በአላህ ይሁንብኝ ዱኒያ ለአንተ ምንም አይደለችም ምክንያቱም ተፎካካሪዎች እና ተሽቀዳዳሚዎች የሚወዳደሩት  የአላህን ፊት ለመመልከት ነውና የሁሉም ነገር የመጨረሻው ዋናው ግቡ ችሮታ አላህ መመልከት ነውና።❞      📚الفتاوى 389/8] ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ሸይጧን እኔ ከእርሱ ከአደም የተሻልኩ ነኝ እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ የሚል ተቃውሞ አስነሳ ይህችንም ቃል ለተከታዮቹ ሁሉ አወረሳቸው። ከኢማን እና ከተቅዋ ይልቅ ማንነትና ዘርን ማስቀደም በተከታዮቹ መካከል ዋና ርስት ሆና ቀረች።❞     📚الصواعق_المرسلة ( 1003/3) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴አቡ ዑስማን አል-ነይሳቡሪ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- «إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ» «ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡» 👉የሚለው ተፍሲሩ፦ ከቢድዐ የፀዳ በሱና ላይ የፀና የተረጋጋ ልብ ማለት ነው።❞      📚تفسير ابن كثير (4/630) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ ❝ሱናን የማያውቅ ሰው ቢድዓን  ፈፅሞ ሊያውቅ አይችልም።❞     📚 سِلْسِلَةُ الْهُدَى وَالنُّورْ (٧١٥) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ሱና እራሷ ቢደዓን አትተወውም ያጠፋቺው ቢሆን እንጂ።የሱና  ፀሀይ በባሪያው ልብ ላይ በወጣች ጊዜ የቢድዓን ጭጋጎች እና ጨለማዎች ሁሉ ቆርጣ ትጥላለች።❞           📚مدارج السالكين٣٧٩/١ ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

የጁሙዓ ሳምንታዊ ምክር.. 🌴ሸይኽ አብደላህ ሰኢድ 🕌ከሃዋ መስጂድ

🌴ኢማሙ ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- ❝ከሰዎች ስህተት ይልቅ በራሱ ጥፋት ላይ ያተኮረ ሰው ምንኛ ያማረና የተባረከ ሆነ።  የራሱን ጥፋት ረስቶ በሰዎች ስህተት ላይ ለተዘናጋ ሰው ወዮለት! ምንኛ ከሰረ የመጀመሪያው የስኬት ምልክት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የኪሳራ ምልክት ነውና።❞        📚طريق_الهجرتين (271/1 ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝የሙስሊሞችን ሃጃዎች ማሟላት ከኢዕቲካፍ የበለጠ አንገብጋቢ ነው ምክንያቱም ጥቅሙ ብዙ ነውና ብዙ ጥቅም ደግሞ ከጥቂት ጥቅሞች ይበልጣልና።ነገር ግን ይህ የሚትተወው ጉዳይ ከእስልምና ግዴታዎች ዋጂቦች እስካልሆነ ድረስ ነው።❞        📚مجموع فتاوى ورسائل          العثيمين" (20/ 180) ] ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት፦ ❝የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- የተቸገረ ወንድሜን ለመርዳት ከእሱ ጋር መሄድ በዚህ መስጂዴ ውስጥ ለአንድ ወር ኢዕቲካፍ ከመቀመጥ ይልቅ እኔ ዘንድ የበለጠ ተወዳጅ ነው። ከሙስሊም ወንድሙ ጋር በችግሩ ጊዜ አብሮ የሄደ እና የረዳው ችግሩ እስከ ሚወገድለት ድረስ አብሮት የፀና ሰው አላህ እግሮቹን  ያፅናለት እግሮች  መፅናት በሚያቅታቸው ቀን።❞    📚حسنه الألباني في " الصحيحة " (906) ] ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሙሐመድ አብዱረኡፍ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፡- ❝ምላስህን ጠብቅ የማይመለከትህን ከመናገር ተጠንቀቅ ብዙ የሚናገር ሰው ብዙ ይወድቃል ብዙ የሚወድቅም ሰው ኃጢአቱ ብዙ ይሆናል ኃጢአቱም ብዙ የሆነ ሰው የጀሃነም ይሆናልና።ሰዎችን በፊቶቻቸው  ወደ ጀሀነም የሚደፋቸው ምላሶቻቸው ባመጡት እንጂ ሌላ ነገር አለን? የአላህ መልእክተኛ ﷺከመጥፎ ምላስ አደጋነትም  ህዝቦቻቸውን መክረዋል አስጠንቅቀዋልና።         📚فتح القدير ١/ ١٩٤ ) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ዑቅባ ብን አመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ፦ عن عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ قلت : يا رسول الله ما النجاةُ ؟ قالَ : امسك عليك لسانكَ و ليسعكَ بيت
🌴ዑቅባ ብን አመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ፦ عن عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ قلت : يا رسول الله ما النجاةُ ؟ قالَ : امسك عليك لسانكَ و ليسعكَ بيتكَ ، و ابك  على خطيئتك. ❝እኔ የአላህ መልእክተኛﷺ ሆይ መዳን ነጃ መውጣት ምንድን ነው አልኳቸው? እንዲህ አሉኝ፦“ምላስህን ያዝ ቤትህ ይስፋህ እንዲሁም ለኃጢአትህ አልቅስ"።❞             📚الصحيحة-  888 ) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ሸይኹል- ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝አላህን የሚወዱትና እርሱን ብቻ የሚያመልኩት በእርሱ ላይ ቅንጣትን ሳያጋሩ የሚያመልኩት የተውሂድ ባለቤቶች ብቻ ናቸው። ከእነርሱም
🌴ሸይኹል- ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝አላህን የሚወዱትና እርሱን ብቻ የሚያመልኩት በእርሱ ላይ ቅንጣትን ሳያጋሩ የሚያመልኩት  የተውሂድ ባለቤቶች ብቻ ናቸው። ከእነርሱም ውስጥ አንድም በቅጣት ውስጥ አይቀርም አይዘወትርም።ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን ጣዖታትን አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ(የሚገዙ) አልሉና፡፡በአላህ ላይ ሌሎችንም የሚያመልኩ የሺርክ ባለቤቶች  ናቸውና።አላህ እንዲህ ብሏልና፦ «አላህ በእርሱ ላይ ማጋራትን አይምርም»።❞           📚قاعدة في المحبة صـ١١-) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21

🌴ኢማም ኢብኑ ረጀብ አል-ሀንበሊ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ተውሂዱን ያሟላ ሰው ምድር የሚሞላ ወይም ሊሞላ የቀረበ ኃጢአትን ሰርቶ ጌታውን ቢገናኘው ኃያሉ አላህን በታላቅ ምሕረትን ያገኘዋል።
🌴ኢማም ኢብኑ ረጀብ አል-ሀንበሊ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ተውሂዱን ያሟላ ሰው ምድር የሚሞላ ወይም ሊሞላ የቀረበ ኃጢአትን ሰርቶ ጌታውን ቢገናኘው ኃያሉ  አላህን በታላቅ ምሕረትን ያገኘዋል። ይህ ማለት ግን አላህ ከፈለገ የወንጀሉን ያህል ይቀጣዋል ከፈለገ አላህ ወንጀሉን ሙሉለሙሉ ይምረዋል።ፍጻሜው ግን በጀሃነም ውስጥ ለዘላለም አይኖርም ይልቁንም ከጀሃነም ወጥቶ ጀነት እንዲገባ ያደረገዋል።❞       📚جامع العلوم والحكم صـ ٣٧٤) ═════ ❁✿❁ ═══ https://t.me/Mohammedseid21