EECSF
前往频道在 Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
显示更多508
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
508
📌 ምስል 2
በ2009 ዓ.ም በአዳማ⛰ በተካሄደው Break mission ላይ የተሳተፉ መልካም ሰዎች ናቸው።😃
በነፍስ-ወከፍ ለመጥቀስ፡
አማን ፣ ረዱ ፣ ህሪት ፣ ቹቹ ፣ ዮኒ
እና በጊዜው በታላቅ ሁኔታ ወንጌል ተሰብኳል ጌታ በብዙ ረድቷቸው ነበር።
በዚህ ወንጌል ስርጭት የተባበሩንን የገንደጋራ ሙሉወንጌል ቤ/ክ(ሙልዬ) ሳናመሰግን አናልፍም።
📱 Photo Credit : Aman
508
📌 ምስል 1
🤔 ጊዜው ቆየት ብሏል(ከ7-8ዓመት በፊት)
ፕሮግራሙ የፋሲካ ምሽት ነበር ✝
እና ከመርሀግብሩ አንዱ በሆነው ማዕድን 🍱 በህብረት የመቁረስ ጊዜ ላይ የነዞላ ፣ ምሬች ፣ ገሬ ፣ ቢኒ እና ሌሎችም ቡድን ምግቡን ጥርግርግ አድርጎ ከበላ በኋላ ለፎቶ ሲባል😁 እጃቸውን ዘርግተው✋ የተነሱት ምስል ነው።
📸 Photo Credit : Unknown
508
Tadese Eshete - አትቸኩልም አንተ
ጥቂት ጊዜ አለፈ ከተናገርካቸው
አብርሃምና ሳራን ተስፋ ፈጠናቸው
ከዚህ የተነሳ እርምጃን ወሰዱ
አንተንም ቀደሙ እስማኤልን ወለዱ
ግን አንተ ጌታችን ስለተስፋህ ብለህ
ይስሐቅን አምጥተህ ቃልህን ፈጸምህ (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም
ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም
ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ
በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ
ውልህን ትገልጻልህ
ወንድሞቹ ሲሰግዱ ዮሴፍ ህልምን አየ
ግን የኖረው ኑሮ ከዚህ የተለየ
ቃልህ እስኪመጣለት እርሱም ተፈተነ
በእርኩሰት በኃጢአት ላይ ሁሌ እየጨከነ
የሚጐበኝበት የእግዚአብሔር ቀን መጣ
ከእዛ ጉስቁልና ከመከራ ወጣ (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም
ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም
ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ
በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ
ውልህን ትገልጻልህ
ሃና መካኗ ሴት ብዙ አለቀሰች
በወገኖች ሳይቀር እየተነቀፈች
እርሷም እንደሰው . (1) . ዘመኗ ደረሰ
እምባዋ በአንተ ጸና ታሪኳም ታደሰ
አቤት የእግዚአብሔር ስራው ያስደንቃል
የምስኪኑን እንባ በጊዜው ያደርቃል (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም
ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም
ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ
በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ
ውልህን ትገልጻልህ
በጣም የምትወደው አልዓዛር ታሟል
የሚል ድምጽ ከሰማ አራት ቀን ሆኖታል
የሞተውን ሊያስነሳ እንባቸውን ሊያብስ
በራሱ ጊዜ መጣ ጌታችን ኢየሱስ
ዛሬም ብንጠበው በመጠበቂያችን
እግዚአብሔር ቅርብ ነው ክብሩን ሊገልጽልን (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም
ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም
ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ
በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ
ውልህን ትገልጻልህ
@AdadisSongs
508
🎺#AdadisNeger
አስደናቂ ዝማሬ #ከዘማሪ_ታደሰ_እሸቴ "አትቸኩልም አንተ" በሚል ርዕስ::
ስለ እግዜአብሔር ጊዜ የዘመረው ድንቅ ዝማሬ ነው ።
ዝማሬውን እና ግጥሙን ከታች ያገኙታል ተባረኩበት ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#YedroSongs
@AdadisSongs
@AdadisSongs
508
📝 "1ኛ ዮሐንስ ምዕ.1 ማጠቃለያ"
🔐 "ቃሉን ማወቅ እና በእርሱ መኖር "
📌 በዚህ ምዕራፍ ሁለት ዋና ሀሳቦች በጥምረት ተገልፀዋል። ይህም ቃሉን ማወቅ እና በቃሉ እንደሚገባ መመላለስ ነው(በብርሀን መመላለስ)
📌 ቃል (refer: John 1)
👉 የተቀበልነው (የዳንንበት) ቃል የህይወት ቃል ነው
👉 ይህ ቃል ቀድሞም ከአብ ዘንድ የነበረ ነው
👉 ይህ የህይወት ቃል "የተገለጠላቸው" ተቀብለውታል
👉 የተቀበሉትም የህይወት ቃል ለኛ ተነግሮናል
👉 ይህን ቃል የቀድሞ ሀዋርያት አይተው፣ ዳስሰውትና ሰምተው የተቀበሉ ሲሆን እኛ ደግሞ በእምነት ተቀብለነዋል
👉 ይህን ቃል በመቀበላችን ያገኘነው ትልቁ ነገር ህብረት ነው
👉 ህብረት የምናደርገው ከወንድሞች ጋር ቢሆንም በወንድሞች ውስጥ ያለው እግ/ር ስለሆነ ህብረታችን ከስላሴ(አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ) ጋር ነው
👉 ይህ ህብረት ቀላል አይደለም ፤ እግዚአብሔር value ያደርገዋል ፤ እርስ በራስ መዋደድ፣ መደጋገፍ እና መተናነፅ ያለበት ነው
📌 በቃሉ መመላለስ
❗️ይህን part በሚቀጥለው ምዕራፍ በስፋት እናየዋለን
👉 “ኢየሱስ እንደ ገና ለሰዎቹ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።”
ዮሐንስ 8፥12
👉 እርሱ በብርሀን የሚኖር ሳይሆን እራሱ ብርሀን ነበር። ብርሀን የሁሉ ነገር ወደ ገሀድ መገለጥ ነው። የክርስቶስ በዓለም መገለጥ በዓለም ያለውን እርኩሰት እና ክፋት ለመኮነን ነው። ስለዚህ በብርሀን መመላለስ ማለት በክርስቶስ ህይወት ዓለምን መኮነን ማለት ነው።
👉 በብርሀን መመላለስ የመኖር ጉዳይ እንጂ የመናገር ጉዳይ አይደለም
👉 የሚገርመው ነገር ሀጥያት የለብኝም የሚል ሰው እራሱን ዋሽቶ ቃሉንም ውሸታም ያስብለዋል
👉 በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ቃሉ እንኳን በእኛ ውስጥ እየኖረ አይደለም ማለት ነው
👉 እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር ይህን ሀጥያታችንን ብንናዘዝ ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ የሚያወጣን እና የሚያድነን ፃድቅ ሊቀ ካህን አለን
👉 እጅግ እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር ይህን አድርገን በብርሀን በመመላለሳችን ከሉዓላዊ እግዚአብሔር ጋር ህብረት አለን
508
#Online Fellowship 😮
🎸ዘወትር ማክሰኞ ወደ እናንተ ልዩ ፕሮግራም ይዘን እንቀርባለን ፕሮግራሙ እጅግ አዝናኝ አስተማሪ ወቅቱን የጠበቀ መልዕክት የሚተላለፍበት 🎸
👇👇👇 በሰዓቱ ያሉን 👇👇👇
👇👇👇 ፕሮግራሞች 👇👇👇
1 የፀሎት ግዜ 🙏🙏🛐
2 Worship time 😍😍👬
3 የቃል ግዜ 😍😍✝✝
4 ግጥም 😄😄😄😄
5 ጥያቄ 😳😳❓❓
የእርሶ #online መሆን ለበረከት ነው😄😄
👉 ዕለተ ማክሰኞ ቀን 11:30 ከ እኛ ጋር ይሁኑ::
👉 ይህንን ዝግጅት ስፓንሰር በማድረግ ምርትና አገልግሎቶን ያስተዋወቁ 😱😄
ስንቶቻችሁ ለመሳተፍ እና ለማገልገል ለመሸለም ዝግጁ ናችሁ??
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Only on EECSF
🔴🔴🔴ይ🀄️ላ🀄️ሉ🔴🔴🔴
—Built on Christ—
Join & share our channel:
@EECSF
@EECSF
@EECSF
508
* Bible study and prayer title*
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
📌 #week-1 (ሚያዚያ 19-25)
ርዕሰ: ሕይወትና ሕብረት 1 ዮሐ 1፥1-10
#Day_1(ሚያዚያ 19)
ርዕሰ: ምስጋና
👉 በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የድነት ስራ በማመናችን ስላገኘነው አዲስ ሕይወት
❝ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤❞
*1ኛ ዮሐንስ 1: 2
👉 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሰራልን የማስታረቅ ስራ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ስለታደሰ ፤ እንዲሁም በሰዎች መካከል ተበላሽቶ የነበረው ሕብረትና ሰላማዊ ግንኙነት ስለታደሰ
❝እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።❞
*1ኛ ዮሐንስ 1: 3
📌 በቃል የሚጠና ጥቅስ ፦ ❝ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤❞
*ዮሐንስ 1: 12
"If there is a will; there is a way!!!”
🔺በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ ሰው ሁሉ አሁን ኩነኔ የለበትም።
🙏🙏🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ::
Join and share EECSF Channel:
@EECSF
@EECSF
@EECSF
508
#Chain_prayer(Chain48)_update
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
የፀሎት ሰንሰለት (Prayer Chain)
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
👉 “በጸሎት የሚያምን ሰው ይጸልያል፡፡”🤷
🔺 በምድራችን፣ በአህጉራችን
ብሎም በአለማችን እየተሰራጨ ያለውን የcovid-19 ኮሮና ቫይረሰን አስመልክቶ በያለንበት በአንድ ልብና በአንድ ሀሳብ እንዲሁም በተመሳሳይ ርዕሶች በጋራ የምንፀልይበት የሰንሰለት_ጸሎት መጋቢት 25 #እንደጀመርን ይታወቃል ፤
🔺 በቀን #ለ 30_ደቂቃ በእግዚአብሔር ፊት በመሆን ይህንን የጸሎት ፍልሚያ #እንቀጥላለን፡፡
🔺 በየሳምንቱ በተወሰነ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል በተወሰኑ ሀሳቦች ላይ በ የዕለቱ የምንፀልይ ይሆናል ።
📌 የሰንሰለት ፀሎቱ ዋና ዋና #አላማዎች:
👉 #ሕብረት ፦ሁሉም ሰው በግል ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ሕብረት እንዲቀጥል ማበረታታት (ተማሪዎች ከዚህ የህብረት ፀሎት በተለየ ሁኔታ ወይም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የግል የፀሎትና የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜ እንዲኖራቸው ይበረታታል)
➢ መሰባሰብ ባንችልም በያለንበት እርስ በእርስ ያለንን ሕብረት ማጠንከር እንችላለን::
👉 #ኃላፊነትን ማሳደግ ፦ ለወቅታዊው የሀገሪቱ ሁኔታ ዋነኛ የሆነውን የፀሎት ሀላፊነታችንን መወጣት::
🔺 በጌታ ፊት ለመንበርከክ የፈቀዱ ቢያንስ 48 ተማሪዎችን እንጠብቃለን
👉 እያንዳንዱ ተማሪ ቀጥሎ ለሚፀልየው ተረኛ #በመደወል ማንቃት::
👉 የፀሎት ሰንሰለቱ እንዳይቋረጥ እያንዳንዱ ሰው #ማንቂያ ደውል(alarm) በስልኩ ቢሞላ የተሻለ ይሆናል::
😱 ተጨማሪ ለመፀለይ ፈቃደኛ ለሆኑ ተማሪዎች በመረጡት ሰዓት ከተመደበው ሰው ጋር በተጓዳኝ በመሆን መቀላቀል ይችላሉ::
🔺 በ የቡድኑ ያሉ አስተባባሪዎች እነዚህ ተማሪዎች እንዴት እንደሚቀጥሉ የመምራት ሀላፊነት ይወስዳሉ::
👉 ማን መደወል አለበት የሚለውን ውሳኔ ጭምር::
📌 የፀሎት መርሆዎቻችን
❖ ግልፅነት
❖ በቅዱስ ቃሉ መመሥረት
❖ እምነት
📝 መነሻ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል:
👉 ( የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የዮሐንስ መልዕክት)
👉 በየሳምንቱ ዕለተ ሰኞ ከ 9:00--9:30 #online Bs(Bible study) ሁሉም ተማሪ ያካሂዳል:: ይህንንም የ Team Smart coordinators ያስተባብራሉ::
