ch
Feedback
EECSF

EECSF

前往频道在 Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

显示更多
508
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF

EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF

እግዚያብሄርን ለመስማት፣ ለመታዘዝ እና ለመመለስ የተዘጋጀ ልብ ይኑረን ለክብሩ የሚኖሩ ሰዎች የምንጸና ሰዎች እግዚያብሄር ያድርገን የዛሬው ኘሮግራማችን በዚህ አልቋል እግዚያብሔር ይባርካችሁ

God bless you bro!

🔎 ስለተሃድሶ ስናነሳ እኛ ጋር ብዙ ጊዜ ሚከሰት ነገር አለ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረታችንን አደስን ብለን ጥሩ መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ሆነን ሳናስበው ትንሽ ቆይተን ደግሞ የምንረሳበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ። እኔ ጋር ይከሰታል🤷 ✅ተሀድሷችን የፀና እንዲሆን በመጀመራያ ይሄንን ጥያቄ ራሳችንን መጠየቅ አለብን 🤔? እግዚአብሔር በኔ ህይወት ምን አይነት የፈረሰ፣ የደከመ፣ የተበላሸ ተሀድሶ የሚያስፈልገው ህይወት አለ? 🤔? ከዚህ ህይወት አንጻር እግዚአብሔር እኔን ምን ይለኛል? 🤔? ለዚህ ድምፅ እኔ ምን ምላሽ አለኝ? ለእውነተኛ ተሀድሶ መምጣት መሰረታዊ ነገሮች፦ ✅ በመንፈስ መነሳሳት ዕዝ 5፥7 ✅ የለውጡን ጉዳይ መረዳት ዕዝ 2 ✅ ህብረት ማድረግ ዕዝ 3፥1 ✅ በተግዳሮት መፅናት ዕዝ 4፥1-7 ✅ በስፍራ መፅናትና መቆም ዕዝ 6፥17 ✅ የጌታን ቃል መረዳት ዕዝ 7፥10 ✅ በህልውናው ውስጥ መሆን ሃጌ 1፥5 ✅ ስለበደለኝነት መፀፀት ✅ መፆምና መፀለይ ዕዝ 9፥5 ✅ መለየት ዕዝ 9፥11 ለምን ተሀድሶ አስፈለገ ✅በአእምሮ መታደስ ጌታን ለማክበር ሮሜ 12፥2 ✅የጌታን ፈቃድ አውቆ ለመኖር ✅ለጌታ ጊዜ ለመዘጋጀት ኤፌ 6፥5 ✅የጌታን ፈቃድ ለማድረግ ዕዝ 9፥9 ኤፌ 6፥5 የፀና ተሀድሶ እንዲኖረን እግዚአብሔር ይርዳን🙏 እግዚአብሔርን ወደ መምሰል እለት እለት እንጠጋ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ 🖐

📖የውስጥ መታደስ📖 ሐጌ ምዕ 1- ምዕ 2 ዕዝራ ምዕ 1- ምዕ 10 🖐 ሰላም የEiABC የቅዱሳን በግቢም፣ከግቢ ውጪም በየቤታችሁ ያላችሁ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ 🙏 በአካል ላያችሁ ዘንድ እናፍቃለሁ። አለ ጳውሎስ...😊 🔎 ዛሬ ከእኔ ጋር የእግዚአብሔርን ቃል እንከፋፈላለን ጌታ ይረዳኛል። ዛሬ ማካፍላችሁን ሀሳብ ከቀናት በፊት ለጓደኞቼ ያካፈልኳቸው ሰፋ ያለ ሀሳብ ነው አሁን አሳጥሬ ሀሳቡን ለማካፈል ሞክራለሁ 📖 ሐጌ 1፥7-9 ⁷ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ። ⁸ ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ⁹ እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው። ሮሜ 12፥2 “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” 📌 ከላይ ያለው የሐጌ መፅሃፍ ከመፅሐፈ ዕዝራ ምዕራፍ 5 የቀጠለ ነው። የዕዝራ መፅሃፍ 10 ምዕራፎች አሉት፤ እስራኤል በባርነት እያለ እግዚአብሔር የፋርስ ንጉስ ቂሮስን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሰራ ልቡን ያስነሳበትና ለእስራኤል የተሀድሶ ዘመን ነበረ። እስከ ምዕራፍ 4 ድረስ በዘሩባቤልና እያሱ እንዲሁም ሌሎች የእምነት አባቶች መላው እስራኤልን በማነሳሳት እግዚአብሔርን ቤት ስራ አስጀምረው ነበረ። unfortunately ምዕራፍ 5 ላይ ሁሉም በየፊናው ተበትኖ እግዚአብሔርን ቤት ስራ የተስተጓጎለበት ጊዜ ነበረ። በዚህ ጊዜ ነው እግዚአብሔር በሐጌ በኩል የተመለሱ መልእክት የተናገረው። የተናገረውንም ሰምተው በንስሃ ተመልሰው ከዕዝራ ምዕራፍ 6 ጀምሮ እንደገና እግዚአብሔርን ቤት መስራት ሲጀምሩ እናያለን። 🗒 ሁላችንም እንደምናውቀው እስራኤላውያን ላይ የተለመደ አንድ cycle አለ 🏷 ከእግዚአብሔር ጋር ይስማማሉ 🏷 ትንሽ ቆይተው ከእግዚአብሔር ጋር ይጣላሉ, በራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ 🏷 እግዚአብሔር ተመለሱ ይላል፤ በቁጣ ይገለጥባቸዋል 🏷 ይፈራሉ በንስሃም ይመለሳሉ 🏷 እንደገና ከእግዚአብሔር ጋር ይስማማሉ then it goes round... በዚህ ክፍል (ሐጌ) የምናየውም የዚህን ሀሳብ short version ነው። 📌 እግዚአብሔር ተቆጣ ፦ሐጌ 1፥4-6 📌 ያደረጉትን ተናገረ ሐጌ 1፥4-9 📌 የደረሰባቸውን ተናገረ ሐጌ 1፥10-11 📌 ተመለሱ አለ ሐጌ 1፥10-12 📌ፈሩት ሐጌ 1፥12 📌 ከእናንተ ጋር ነኝ አለ ሐጌ 1፥13 📌 ልባቸውን አነሳሳ ሐጌ 1፥14 📌 እግዚአብሔርን ቤት ሰሩ ሙሉ ክፍሎቹን አጥኑት ዕዝራን ጭምር በጣም ወሳኝ ክፍሎች ናቸው

አሁን ደግሞ የእግዚያብሄርን ቃል የምንከፋፈልበት ጊዜ ነው ከወንድማችን ሳሙኤል ጋሻው (ሳሚ) ጋር

Meskelih Sir(MP3_70K).mp34.91 MB

አሜን አሁን ደግሞ እግዚያብሔርን በዝማሬ እናመልከዋለን

ሁሉን የምትችል ሰማይና ምድርን የፈጠርክ የዘላለም አባት ሆይ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን! ስለሁሉ እናመሰግንሀለን! ጌታ ሆይ ፀጋህ ለኛ የተሰጠጠ ውድ ሀብት መሆኑ ገብቶናል። ስለዚህ ስጦታ እናመሰግንሀለን። በጌታ በኢየሱስ ስም ጨለማ ውስጥ ያሉት ከጨለማው መውጣት ይሁንላቸው, ኢየሱስን ያላወቁ ነብሳት ዛሬ እንፀልያለን ከዛ ከጨለማ ሕይወት የዘላለም ሞት ካለበት ወጥተው ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲመጡ, ለእኛ የበራልን ለእነሱም እንዲበራላቸው እንፀልያለን። በጨለማ የታሰሩ ሁሉ ይፈቱ በጌታ በኢየሱስ ስም ነፃ ይውጡ። የጠላት ዲይብሎስ ስራ በጌታ በኢየሱስ ስም የፈረሰ ይሁን። ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳይበራላቸው ያሰወረ በኢየሱስ ስም የፈረሰ የይሁን! በጌታ በኢየሱስ ስም ስለ ሐገራችን ስለኢትዮጵያ ደግሞ እንጸልያለን።  መሪዎች እግዚአብሔር ካልመራቸው እኛን መምራት አይችሉምና ጌታ ሆይ ለምድራችን ድረስ, ለሕዝቡም ራራለት, ለመሪዎቻችንም መፈራትህን ጥበብን ምሪትህን ማስተዋልን ስጣቸው, እግዚአብሔር ሆይ ምድራችንን አስብ, እግዚአብሔር አምላክ ምድራችንን በምህረትህ ተመለከት, መልካም እንዲሆንላት ለምድራችን አንተ የተናገረን ብቻ እንዲፈጸም አጥብቀን እንፀልየያለነን, መለያየት ዘረኝነት ጥላቻ መገዳደል ጭንገፋ ከምድራችን አርቅልን። "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።" እንዳልከው ሰላም ያጣችው  እና በጭንቀት ውስጥ ያላችው አገራችንን አስባት, በናዝሬቱ ጌታ በኢየሱስ ስም አሜን!🙏

ኘሮግራማችንን በጸሎት እንጀምራለን ከወንድማችን ናታን ጋር አብረን እንጸልይ

ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድ
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድርገን የምንተናነጽባቸውን ፍሬ ነገሮች እንከፋፈላለን፤ አብራችሁን ቆዩ።

EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF

EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF

EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF

የዛሬው ኘሬግራማችን በዚህ አልቋል እግዚያብሄር ይባርካችሁ

በሁሉ ነገር አልፈን እግዚያብሄርን ማየት ይሁንልን ሰዎችን ተጠቅሞ እግዚያብሄር ይሰራል ስርዐቶች ወይም ሰዎች እግዚያብሄርን አይጋርዱብን

የEiABC እህት ወንድሞቼ እንደምን አላችሁ። አበባየሁ ነኝ✋ ዛሬ አንድ የእግዚአብሔር ቃል ክፍለ ሀሳብ ላካፍላችሁ።👇 ✨ "ጥላ እና አካል"✨ 👉ወደ ቆላስዩስ ሰዎች 2:16-17 "እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ። እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።" በዚህ ቃል ስለ ጥላ እና አካል እውነተኛ ምሳሌነት አጠር ባለ መንገድ እናያለን። በመጀመሪያ የጥላና የአካልን ባህሪያት እንመልከት። 📌ጥላ ማለት አካልን የሚመስል ማለት ነው ነገር ግን አካል ነው ማለት አይደለም። 📌ጥላ በቅርፅ እና በእንቅስቃሴ አካልን ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ጥላ ሁኔታ ላይ የሚደገፍ ነው። 📌ፀሀይ በቀረበችና በራቀች ቁጥር የማጠርና የመርዘም ባህሪያትን ይለብሳል። ከዚያም አልፎ ምናልባትም ፀሀይ ከጠፋች አበሮ ሊጠፋ ይችላል። 📌ነገር ግን ግን አካል ፀሀይ ራቀች ወይም ቀረበች ወይም ደግሞ ጠፋች ብሎ ባህሪውንና መልኩን አይቀይርም። ✔️ልክ እንደዚሁ ደግሞ በዘመናችን እየሆኑ ያሉት ነገሮች ትምህርቶች፣ ትዐምራቶች፣ ድንቆች፣ ፈውሶች፣ መገለጦች፣ የመሳሰሉት ጥላ ናቸው። 🔸እነዚህ ጥላዎች አካሎች አይደሉም ነገር ግን አካሉን የሚመስሉ ናቸው።🔸 ሀዘን ቢሆን የምድር ደስታ፣ ተቀባይነት ወይም ደግሞ መገፋት እነዚህ ሁሉ ጥላ ናቸው ፀሀይ በሌለችበት ጊዜ ይጠፋሉና። 🔸ነገር ግን እኛ አካሉን ክርስቶስን እንጂ ጥላውን አንከተልም። አካሉ ሁኔታዊ አይደለም የፀሀይ/የጊዜው ሁኔታ በእርሱ ላይ ለውጥን አይፈጥርም። ፀሀይ ወጣች ወይም ጠለቀች እርሱ ግን ሳይቀየር ይኖራል። 📌ስለዚህ በሚያልፈው ጥላ ላይ አንደገፍም። ነገር ግን ፀንቶ በሚኖረው በአካሉ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደገፋለን።🤗 ተባረኩልኝ!

አሁን ደግሞ የእግዚያብሄርን ቃል የምንከፋፈልበት ጊዜ ነው ከወንድማችን አበባየሁ ጋር

04 Track 4(1).mp35.88 MB