ch
Feedback
EECSF

EECSF

前往频道在 Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

显示更多
508
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1

2

3

ቀድሞ የመለሰ ተሸላሚ ነው

ጥያቄውን ልልከው ነው

የተመቸው እና ለቀጣዩ ጥያቄ የተዘጋጀ

ሱራፌል ሀይለማርያም - እጠብቀዋለው ዋና መዝሙር - ዳኒኤል አምደሚካኤል አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ እጮሀለሁኝ እኔ አልታክትም እስኪጎበኘኝ ተስፋ አልቆርጥም እንባዬን ካይኔ እስኪያብስልኝ እጠብቃለሁ እስኪደርስልኝ ጌታ እስኪያየኝ (፫x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ እስኪ እንደሀና እንባዬን ላፍስስ መሪር ሀዘኔን በፊቱ ልግለፅ ጨካኝ እንዳይደል እኔ አውቀዋለሁ ከእግሩ ስር ሆኜ ልማፀነው ደጅ ልጥናው (፫x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ ፈተናው በዝቶ ቢያዝለኝም ለሰይጣን ሀሳብ እጄን አልሰጥም እርዳኝ እላለሁ በፊቱ ሆኜ ድንቅ እንዲሰራ በእርሱ ታምኜ በረድኤቴ (፫x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ እታገሳለሁ ምልስ ይሆነኛል ጌታ ጨክኖ መች ይተወኛል የልመናዬ ፅዋዬ ሞልቶ ይጎበኘኛል በጊዜው መጥቶ በቃ ብሎ (፫x) @AdadisSongs @AdadisSongs

ከዛ በመቀጠል 1 የሽልማት ጥያቄ ይኖረናል

ከዚህ በመቀጠል 1 የዝማሬ ግብዣ ይኖረናል ከ @AdadisSongs

እንዳነበባችሁትና እንደተባረካችሁበት ተስፋ አደርጋለው

Part : 2 🔐 "Anti-Christዎች - ባህሪያቸው " 👉 እንደ እንክርዳድ ከስንዴው ጋር ተቀላቅለው ይኖራሉ(አብረዋቸው ነበሩ) 👉 በቀጥታ ውሸትን ተናግረው አይጀምሩም ፣ ለብዙ ጊዜ ያስመስላሉ 👉 ክርስቶስ እስከ መኸር ጊዜ ተዉዐቸው እንዳለው ፣ የሚለዩበት ጊዜ ይመጣል 👉 ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም + አምላክ አይደለም + ጌታ አይደለም ብለው ይክዳሉ 🔐 የሚታወቁ ኢ-ክርስቶሳዊ አስተምሮዎች 💣 የአርዮስ ትምህርት : የክርስቶስኝ ሁለትዮሽ ባህርያት መካድ 💣 ኢቦናውያን : የክርስቶስን አምላክነት መካድ 💣 ሰባልዮስ : የክርስትስን ፍፁም ሰውነት የሚክዱ 📌 በአጠቃላይ ወልድን የሚክድ አብን ማመኑ ከንቱ ነው ስለዚህ ማንም እዳያስተን በውስጣችን ያለውን የእግዚአብሔር መንፈስ በማዳመጥ እና በመከተል እርሱን ወደማወቅ ማደግ አለብን።

📝 "1ኛ ዮሐንስ ምዕ.2 ማጠቃለያ" Part 1 🔐 "በቃሉ መመላለስ" 📌 ባለፈው ሳምንት እንደተነጋገርነው እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር ኃጥያትን ብንሰራ ከኃጥያታችን ሊያነፃን ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን። ይህ ማለት ግን ኃጥያትን እንድንሰራ የሚገፋፋን መሆን የለበትም። 📌 እኛ በብርሀን የምንመላላለስ (ከኃጥያት ልምምድ ውጭ) የብርሀን ልጆች ስለሆንን 📌 ስለ እግዚያብሔር ያለን እውቀት በኃጥያት ላይ ለምንወስደው እርምጃ ወሳኝ ሚና አለው 📌 የምንመላለሰው እግዚአብሔርን ባወቅነው እና በቀረብነው ልክ ነው 📌 ስለዚህ እግዚአብሔርን አውቃለው የሚል ትዕዛዙን መጠበቅ ግዴታው ነው 🔖 አውቃለው : የእግዚአብሔር ህይወት በእኔ ውስጥ አለ (በክርስቶስ የሚያምን) ብሎ የተቀበለ እንጂ ሉዐላዊውን እግዚአብሔር የማወቅ ሚስጥር አይደለም። 📌 ትዕዛዙን የሚጠብቅ 👇👇👇👇 👉 ትዕዛዙን በመጠበቅ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ፍፁም ይሆናል 👉 ትዕዛዙን መጠበቅ የራሱ የእግዚአብሔር መሆናችን ማረጋገጫ ነው 👉 ኢየሱስ እንደተመላለሰ ይመላለሳል : ይህ ማለት የመንፈስ ፍሬዎች በእርሱ ይገለጣሉ ማለት ነው 👉 ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል።”(my fav) 1ኛ ዮሐንስ 2፥6 👉 ከወንድሙ(ባለንጀራው) ጋር በፍቅር ይኖራል : ይህ ስለ ወንድሙ እራሱን መስጠትን ያካትታል 📌 እነዚህ ሁሉ ትዕዛዛት ከዚህ ቀደም የነበሩ ናቸው ለምሳሌ ፦ ቃየል አቤልን ገድሎታል። ያው ሰውን የገደለ ነፍሰ ገዳይ ነው😁 ነገር ግን ይህ መግደል የመጣበት ምንጭ (Source) ከመጥላት/ከቅንዓት/ከልብ መደንደን ነው። ስለዚህ አሁን ያው ህገጋት(Principle) ነው የተደገመው። አሁን ግን ሀጥያተኛ የሚያደርገው ውጤት(Output) ሳይሆን ምንጩ(Source) ነው። ሀጥያቱ የሚጀምረው ከመጥላቱ ስለሆነ ፤ ዝሙትም የሚጀምረው ከመመኘት ስለሆነ። እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከድርጊት የቀደመው የልባችንን ሀሳብ ይመለከታል። 📌 በእኛ ውስጥ ያለው የአብ ፍቅር የአለምን ምኞት የሚያስክድ ነው 📌 እግዚአብሔር ከሁሉም ነገር ቅድሚያ እንድንወደው ይፈልጋል ፣ የምናደርገውን ሁሉ ከፍቅር የተነሳ እድናደርግ ይፈልጋል። 📌 አለምን መውደድ ጊዜአዊ ጥቅም እና ጊዜአዊ ምኞትን መፈፀም ነው ፤ እግዚያብሔርን መውደድ ግን ዘላለማዊ ነው 📌 ቁ 12 - 14 ያለው በየትኛውም የዕድሜ ደረጃ ላይ ያሉት ሰዎች ይህ ቃል እንደሚመለከታቸው ለማመልከት የተፃፈ ነው። አለምን ማሸነፍ እና በብርሀን መመላለስ የሚቻለው በፀጋው እንጂ በእኛ ብርታት እንዳልሆነም ይመለከታል።

አሁን በ"1ኛ ዮሐ 2" ማጠቃለያ እንጀምራለን

በፕሮግራሞቹ መሃል ሽልማቶች ይኖራሉ በጥሞና የተከታተለ ሰው አሸናፊ ይሆናል

የዛሬውን ፕሮግራም ስፖንሰር ያደረገችውን መልካም ሴት ሳላመሰግን አላልፍም

የመጀመሪያው የ1ኛ ዮሐ ም.2 ማጠቃለያ ነው ያላነበባችሁ ሰዎች አሁን ብታነቡት እመክራለው

🙌 የዛሬ ፕሮግራሞቻችን 🙌 1⃣ የ1ኛ ዮሐንስ መልዕክት ም.2 ማጠቃለያ 📖 2⃣ የዝማሬ ግብዣ ከ @AdadisSongs 🎶 3⃣ ከዚህ ቀደም በዚህ ህብረት የነበሩ ተማሪዎች ከተነሷቸው ምስሎች መካከል የተወሰኑትን 📸 4⃣ የቃለ መጠይቅ እና ልምድ የማካፈል ጊዜ 🎤🤹‍♂ 5⃣ የመፀሀፍ ግብዣ 📚 6⃣ ይመልሱ፣ ይሸለሙ 🗣 💸 #StayHome #StayTuned

. 👉 ዛሬ ማታ 👈 "መልካም ሰኞ ሾው" ❗️የዕለቱን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ማንበብ እንዳትረሱ ❗️ በጊዜው መገኘት እንዳትዘነጉ ❗️ ጥያቄና አስተያየት የተፈቀደ ነው ❗️ ማታ 2:30 ❗️ #Stay
. 👉 ዛሬ ማታ 👈 "መልካም ሰኞ ሾው" ❗️የዕለቱን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ማንበብ እንዳትረሱ ❗️ በጊዜው መገኘት እንዳትዘነጉ ❗️ ጥያቄና አስተያየት የተፈቀደ ነው ❗️ ማታ 2:30 ❗️ #Stay_Tuned and #Share @EECSF @EECSF

#Chain_prayer(Chain48)_update 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥   መነሻ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል - የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የዮሐንስ መልዕክት 📌. 2ተኛ ሳምንት (ሚያዚያ 26 -ግንቦት 2)   ርዕስ- በብርሀን መመላለስ 1 ዮሐ 2፥1-29 ፤ መዝሙረ ዳዊት 119 ቀን 1 ፦ ምስጋና 👉ጽድቅን ለማድረግ ከጨለማ የኃጢአት ኑሮ ስለዋጀን 👉በኃጢአታችን ሊፈረድብን ሲገባ የኛን ፍርድ ክርስቶስ ስለወሰደልን 👉ሰይጣን እንዳይከሰን አንድ ጊዜ ስለፈሰሰልን እና ሁልጊዜ ስለሚታይልን የክርስቶስ ደም 👉ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊድኑ ለፈቀዱ ሁሉ ስለሆነው የኃጢአት ድነት 📌 በቃል የሚጠና ጥቅስ፦ ❝እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤❞  —1ኛ ጴጥሮስ 2: 9 ************************** የሕንፃ ኮሌጅ(EiABC) ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት 2012 ዓ. ም.                             Join and share: @EECSF