1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ስኬታማ ዝግጅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሚኒስትሮች እና ርዕስ መስተዳድሮች የተካሄደ የእውቅና መርሐ-ግብር በምስል፦
የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማስተሳሰር የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ በፍጥነት እንዲጓዝ ያግዛል።
Piroojektoota gurguddoo eegalaman walitti hidhuun, jalqabbiin bara bayyanachuu Itoophiyaa saffisaan akka adeemu ni gargaara.
See less
19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ነገ ለማክበር የተዘጋጀችው እንግዳ ተቀባይዋ የአርባ ምንጭ ከተማ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ለከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርጋለች።
ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደአርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው።
እንደ ሀገር የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለከተሞችም ሆነ ለገጠር አካባቢዎች ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ዛሬ በመጎብኘት ላይ እንዳለነው አይነት የሙዝ ልማት ሥራዎችን በገጠር አካባቢዎች በማሳዎች ላይ የኩታ ገጠም እርሻ አሰራረን ጀምረናል። እነዚህን ጥረቶች የሚደግፈው የሌማት ትሩፋት ሥራ በየአርሶአርብቶአደሩ ቤት የእንቁላል ምርትን ከአሳ እና ከብት ርባታ ብሎም ንብ ማነብ ጋር ምርት በማሳደግ ላይ ይገኛል።
እነዚህ መርሃግብሮች በጥምር የገጠሩ እና የከተማው ነዋሪዎች ከትሩፋቱ እንዲካፈሉ አልመው ሰርተዋል። በተለይ የኩታ ገጠም እርሻ በአርባምንጭ ታላቅ ተስፋ የሰነቀ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የቴክኖሎጂ ሙያተኞቹን የ5 ሚልዮን ኮደርስ ስልጠና እና ሰርተፍኬት እንዲወስዱ ተቋሙ አስገዳጅ አቅጣጫ አስቀመጠ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያስጀመሩትና የኢትዮጵያ መንግስት ከተባበሩት አረብ ኢምሬት ጋር በመተባበር የተቀረፀው ይህ ፕሮግራም 5 ሚሊዮን ፕሮግራመሮችን በቀጣይ ሶስት ዓመታት ለማፍራት እቅድ ተይዟል።
በዚሁ መሰረት የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ 5 ሚሊዮን ፕሮግራመሮችን ለማፍራት የሚያስችለው ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ የሚገኙ የአይሲቲ ባለሙያዎች የዝግጅት ስልጠና ኦሬንቴሽን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲዔታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ በእንግድነት ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንዲሁም የከተማው ኢኖቬሽን እና ቴክኖሌጂ ልማት ቢሮ የስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ቱሉ መንግስቱ በተገኙበት ሰጥቷል።
የዲጂታል ኢትዮጵያን ለመፍጠር የቴክኖሎጂ ሙያተኞች ያላቸውን እውቀት ማስፋት እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን ከማንነት አስተዳደር ጋር ያለው ስራ ቁልፍ የዘርፉ ምሶሶ በመሆኑ ተቋማችን የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣት እንዲችል ሙያተኞቹ እራሳቸውን ማብቃት ይኖርባቸዋል ሲሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በዕለቱ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ እና የስማርት ሲቲ ዋና ሃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የስልጠናውን ኦሬንቴሽን በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት የሲቪል ምዝገባ ሪፎርም ላይ ያለ ተቋም በመሆኑ አገልግሎቶችን በማሻሻል (ዲጂታላይዝ በማድረግ) የተገልጋይ ህብረተሰብ ኑሮ ቀላል ማድረግ አስፈላጊ እና የስማርት ከተማ ግንባታ አንዱ ግብ ነውም ብለዋል።
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲዔታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ
የስልጠናው አስፈላጊነት እና ወሳኝነት ላይ አፅንኦት በመስጠት አሁን ያለንበት ዘመን የእውቀት ዘመን በመሆኑ መንግስት ያለማውን ሃገሪቱን ወደ ዲጂታል የማሸጋገር ውጥን ሰልጣኞች እራሳቸውን አብቅተው ለሃገር በመስራት በዓለም ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ ሃገር ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ አስተዋፆዖ እንዲያደርጉ መልዕክት ለሰልጣኞች አስተላልፈዋል።
ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ህዳር 28/2017ዓ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል።
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበር ላይ ለመሳተፍ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል።
እንግዶቹ አርባምንጭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የጋሞ አባቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የካሳንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት
Koriidarii Kaasaanchesii fi deebisanii misoomsuu.!
በመዲናችን አዲስ አበባ እስካሁን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ያህል ነዋሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አካሂደዋል - በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመዲናዋ እየተካሄደ ያለውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት አስመልክተው እነደተናገሩት ሁሉንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ በመሆኑ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ባሉ የተለያዩ ማዕከላት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
አክለውም የፋይዳ መታወቂያው በመዲናዋ የሚሰጡ ሁሉንም አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ እንደ ሃገር ደግሞ አጠቃላይ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገትን ከማፋጠን፣ ልማቱን ከማሳለጥ እና ህገወጥ አሰራሮችን ከመከላከል አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያው ሁሉም ዜጋ ሊኖረው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘውም በከተማችን አዲስ አበባ ባለፉት 2 ወራት በተሰራው ውጤታማ የንቅናቄ ስራ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ አካሂደዋል ሲሉም አመልክተዋል።
በመዲናችን ከወረቀት ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ እየተሰጠ ያለው የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት እስካሁን 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ያህል ዜጎች ማግኘታቸውን የገለጹት ኢንጅነር ወንድሙ አገልግሎቱን ከፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር የዜጎችን ሁሉንም መረጃ ከአንድ ቋት መቅዳት የሚቻልበት የአሰራር ስርአት እየተዘረጋ እንዳለም አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የመሬት ይዞታ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በድንገተኛ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ዋለ::
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በተሰራው ድንገተኛ ኦፕሬሽን የመሬት ይዞታ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ::
በዛሬው ዕለት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማን ጨምሮ በመላው አዲስ አበባ የትምህርት ቤት አካባቢ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዷል::
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ ለቡ በተሰራው ኦፕሬሽን የመሬት ይዞታ ካርታን ጨምሮ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ እኩይ አላማ የሚያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል::
ቤቱ ሲፈተሽ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ግለሰቡ የፅንፈኛው ቡድን አባልና በትጥቅ ትግል ጭምር ተሳታፊ እንደነበር ታውቋል።
ከፎርጂድ ሰነዱ በተጨማሪ የተለያዩ የጦር ድምፅ አልባ መሳሪያዎችም በግለሰቡ ቤት ተገኝቷል::
በዛሬው እለት በክ/ከተማው በተሰራው ኦፕሬሽን ሺሻና ጫት ቤት፣ግሮሰሪና ፔንሲዮን፣ማሳጅ ቤትን ጨምሮ የትምህርት ቤቶች ዙሪያ በሚገኙ አዋኪ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች ላይ ከ97 በላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉ የመንግስት ተቋማት ሁሉም አገልግሎቶች ላይ የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር አስገዳጅ አሰራር ተቀመጠ
የሃገር አቀፉ የፋይዳ ምዝገባ ስርዓት ለሃገር የሚኖረውን አስተዋፅዖ ከግምት በማስገባት የስርዓቱን ተፈፃሚነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስተባበር የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በጋራ መግባባት በመፍጠር እየተመራ ያለ ሲሆን ከከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አገልግሎት ጋር በተያያዘም አስገዳጅ አሰራር ተዘርግቷል።
ይህንኑ መነሻ በማድረግ በአገልግሎት ባህሪያቸው የተለዩ የከተማው ተቋማት በዋናነትም የንግድ ቢሮ፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ፣ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ የትራፊክ ማናጀመንት ኤጀንሲ ፣ የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ቁጥጥር ፈቃድ ባለስልጣን፣ የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር ዝርዝር የዝግጁነት እና አፈፃፀም ውይይት ተደርጓል።
አጠቃላይ አሁናዊ የምዝገባ ሁኔታ እና የአስገዳጅ ስርዓቱ አፈፃፀም ገለፃ በብሄራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንዲሁም የተቋማቱ የስራ ሃላፊዎች ባሉበት ቀርቧል።
ክቡር አቶ አለማየሁ የፋይዳ ምዝገባ ከከተማ ነባራዊ የእድገት ሁኔታ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ከአካታችነት፣ ከቀልጣፋ አገልግሎት ፣ ከፍትሃዊ የሃብት አጠቃቀም፣ የሃብት አስተዳደር እንዲሁም ከሰላም እና ፀጥታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ከተማዋን ስማርት የሚያደርግ የዲጂታል ምሶሶ በመሆኑ ስራው በቁልፍ ተግባር የሚመራ መሆኑን ገልፀዋል።
የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን በከተማው ያሉ የመንግስት ሰራተኞችም በዚሁ ስርዓት አስገዳጅነት እንዲካተቱ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ስራ መገባቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ
በመድረኩ ያነሱ ሲሆን ከተማዋ የፋይዳ ምዝገባ ተደራሽነትን ሙሉ ለሙሉ ባጠረ ግዜ ተደራሽ ለማድረግ ከብሄራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት ጋር ከኤጀንሲው መዋቅር የመመዝገቢያ አማራጮች በተጨማሪ አዲስ ተደራሽ ተንቀሳቃሽ መዝጋቢዎችን ለማሰማራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
ተቋማቱ የፋይዳ ምዝገባ ለአገልግሎት አስገዳጅ ያደረጉ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ አፈፃፀሙ እየተገመገመ የሚሄድ መሆኑ ተነግሯል።
ለበለጠ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
