ch
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች እየተወሰዱ ያሉ የማቅለያ ዕርምጃዎች በኮሚሽኑና ክፍለ-ከተማ አመራሮች ተጎበኘ። በአዲስ አበባ እየጣለ ያለዉን የበልግ ዝናብ ተከትሎ ሊያጋጥም የሚችልን የጎርፍ አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ለጎርፍ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩና በአካባቢዎቹ እየተከናወኑ ያሉ የማቅለያ ስራዎችን አስመልክቶ የኮሚሽኑና የክፍለ ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የመስክ ምልከታ አካሂደዋል። አመራሮቹ ለጎርፍ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችንና የአደጋ ስጋቱን ለማቅለል እየተወሰዱ ያሉ የመፍትሄ እርምጃዎችን ተዟዙረዉ የተመለከቱ ሲሆን በምልከታቸዉም በአደጋ ስጋትነት የተለዩ ቦታዎች በአብዛኛዎቹ ላይ መፍትሄ እየተሰጠ ቢሆንም ቀሪ ያልተጠናቀቁ ስራዎች መኖራቸዉን የጉብኝቱ ተሳታፊ አመራሮች አሳታዉቀዋል። አያይዘዉም የተጀመሩት የማቅለያ ስራዎች የበልግ ዝናቡና በቀጣይ የሚኖረዉ የክረምት ጊዜ ሳይጠነክር በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አመራሮቹ ገልጸዋል። የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ፉፋ እንዳስታወቁት ጉብኝቱ እየተካደ ያለዉ በሁሉም ክፍለ-ከተሞች መሆኑን ጠቅሰዉ በቀሪ ቀናትም ጉብኝቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ጎን ለጎንም ተጋላጭ ለሆኑ የአካባቢ ነዋሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ተናገረዋል። በጉብኝት መርሀ ግብሩ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነርና ም/ኮሚሽነሮች የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የክፍለ-ከተሞች ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ የጎርፍና የእሳት አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን የልየታ ስራ ተሰራ፡፡ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ኮሚሽን በመቀናጀት ከፍተኛ የጎርፍና የእሳት አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን የልየታ ስራ በዛሬው እለት ተሰርቷል፡፡ በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ደሳለኝ ፉፋ፤የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ እንዲሁም የኮልፌ ቅርንጫፍ አደጋ ስጋት ኮሚሽን አመራሮችና ባለሞያዎች በተገኙበት የጎርፍና የእሳት አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን የልየታ ስራ ተሰርቷል፡፡ የስጋት ቦታዎችን መለየታቸው በቀጣይ መፍትሄዎችንና አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና በእቅድ ተይዘው ባለቤት ለመስጠት እንደሚረዳም በልየታው ወቅት የተገለፀ ሲሆን በተለይም መጪው የክረምት ወቅት በመሆኑ መንግስትና ህብረተሰቡ በጋራ ተቀናጅቶ የቅድመ ስጋት ቅነሳ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡ Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ሰላምን በተመለከተ መንግስት ለትችት ክፍት ነው። በሚያነሳው ሃሳብ ምክንያት የታሰረ አንድም ሰው የለም። ነገር ግን በአንድ እጅ ሰላማዊ ትግል፤ በሌላ እጅ በጦርነት መንግስት ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። ይህ ህግን መጣስ ነው። ነጻነትን በአግባቡ የማስተዳደር ችግር አለ። ነገር ግን መንግስት አሁንም ለሰላም ጽኑ አቋም አለው። ችግሮች በድርድር እንዲፈቱ ነው የምንሻው። ባለፉት 7 ዓመታት ከየትኛውም የጎረቤት ሀገራት ጋር ጦርነት ያላካሄደ መንግስት አሁን ያለው መንግስት ነው። ይህም ከሀገር ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ያለንን አቋም የሚያሳይ ነው። #የጠሚሩምላሾች… See more

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህልን በተመለከተ “በኢትዮጵያ ሁለት መሰረታዊ ስብራቶች አሉ፤ አንደኛው የመጠፋፋት ባህል ነው። መንግስታት ወደ ኃላፊነት ሲመጡ ሳይደራጁ ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ ማለት ነው። ይህ በበርካታ የኢትዮጵያ መንግስታት ታሪክ ተሞክሯል። ሁለተኛው ከሶሻሊስት እሳቤ ጋር በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በሽታ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ያመጣው ችግር ፍረጃ ነው። የጠላትና የወዳጅ ፍረጃ ማለት ነው። ይህም ለሰላማዊ ድርድር ቦታ አይሰጥም። ይህም በኃይል ስልጣን የመያዝ አባዜን አምጥቷል።ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውም ችግር ይህ ነው። በምርጫ የተመረጠን መንግስት በኃይል ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። የሚገርመው ነገር ግን የሚያሰቃዩት እንታገልልሃለን የሚሉትን ህዝብ ነው።”… See more

የኮሪደር ልማትን በተመለከተ "የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው። በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካኝነት ከ200 ኪሎሜትር በላይ መንገድ ተሰርቷል። ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም ተከናውነዋል። በኮሪደር ልማቱ ለተነሱ ዜጎችም በቂ ካሳ ተከፍሏል። እስካሁን ባለው ሂደትም ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏል። በሁሉም የክልል ከተሞችም አስደማሚ ስራ እየተከናወነ ነው፤ ለአብነትም በሐረር ከተማ በዜጎች ተሳትፎ የተከናወነው ስራ ለሀሉም ከተሞች ምሳሌ የሚሆን ነው።" #የጠሚሩምላሾች… See more

የአፈር ማዳበሪያን በተመለከተ “እንደ ህዳሴ ግድብ ሁሉ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ታላቅ ስራ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ነው። ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመር አለብን ብለን ስራ ጀምረናል። ይህን ስራም በተለይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተሳሰር ለመስራት እየተጋን ነው። አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ በየዓመቱ 24 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ የሚያስፈልጋት ሲሆን፤ ይህን ፍላጎት ለሟሟላትም በየቀኑ 150 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እያጓጓዝን ነው።” #የጠሚሩምላሾች… See more

የዋጋ ንረትን በተመለከተ መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ድጎማ በማድረግ የዋጋ ንረቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እንዳይጎዳ በጥንቃቄ እየሰራ ነው። ለአብነትም መንግስት በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 3 ሺህ 700 ብር ይደጉማል። ለነዳጅም 72 ቢሊዮን ብር ተደጉሟል። በዚህም በሊትር 28 ብር እንደጉማለን። የደሞዝ ጭማሪ በማድርግም ቋሚ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ገቢያቸው እንዲያድግ እየተሰራ ነው። ይህ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል። #የጠሚሩምላሾች… See more

ገቢን በተመለከተ ባለፉት ስምንት ወራት 580 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል። ነገር ግን መንግስት የሚሰበስበው ገቢ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት አንጻር ከ7 በመቶ አይበልጥም። ይህን ማሻሻል አለብን። በየአከባቢው የሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ የምንችለው ገቢያችንን በበቂ ሁኔታ ማሳደግ ስንችል ብቻ ነው። #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ መንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ሁለት ዋና ዋና ስራዎች መከናወን አለባቸው። አንደኛው በቀበሌ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ሲሆን፤ እያንዳንዱ ቀበሌ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅሞችን መገንባት ነው። በዚህም ሁሉም ቀበሌዎች ያላቸውን ሃብት በቁጥር ለይተው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሁለተኛው መሶብ የተሰኘ አገልግሎት ሲሆን በሙከራ ደረጃ በሲቪል ሰርቪስና በፕላንና ልማት ሚኒስትር በሲስተም ይጀመራል። አገልግሎቱም በአንድ መስኮት ሁሉንም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia