1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ማስታወቂያ ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ‹‹ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት›› በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የፊፎርም ቀን አስመልክቶ በእለቱ በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም ተቋማት ሙሉ ቀን ለአገልግሎት ክፍት ሆነው የሚውሉ መሆኑን እያሳወቀ ተገልጋዬች በእለቱ ወደ ሚፈልጉት ተቋም ሄደው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን !
አዲስ ዓመት ያለቀውን ዓመት ሸኝቶ አዲሱን ከመጀመርም ባለፈ ከአስቸጋሪው ደመናማ የዝናብ ወቅት ወደ ብሩህ ተስማሚ ወራት መሻገርን የሚያበስር፣ በአዲስ አስተሳሰብና በብሩህ ተስፋ የምንቀበለው የአዲስ ምዕራፍ መባቻ ነው።
የተገባደደው ዓመት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ በበርካታ መስኮች የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የማረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ ያላቸው ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ያስመዘገብንበት እንዲሁም ከድህነት ወደ አስተማማኝ የብልጽግና ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚያስችለንን መሰረት የጣልንበት አንጸባራቂ የስኬትና የእድገት ዘመን እንደነበረ ግልጽ ነው።
ይህ ዛሬ የምናከብረው የመሻገር ቀንም፣ ባለፈው ዓመት ካለፍናቸው ትላልቅ ፈተናዎችና በድል ከተሻገርናቸው እንቅፋቶች ተገቢውን ትምህርት ወስደን በዚህ ሂደት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን አስተዋጾ ያደረጉና ያገዙን አካላትንና መላው ህዝባችንን ከልብ የምናመሰግንበት፣ ብሎም የቀጣዩ ዓመት የርብርባችን ማዕከል የሆነውን ብልጽግናን የማረጋገጥና ህዝባችንን ወደ ላቀ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እመርታ የማሻገር ራዕይ እውን ለማድረግ በጋራ ለመትጋት ቃል የምንገባበት እለት ነው።
በመሆኑም፣ ባሳለፍናቸው የለውጥ ዓመታት በአጭር ጌዜ ያስመዘገብናቸውን ተአምራዊ የልማት ስኬቶችን ተስፋ ሰጪነት አይቶ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሁሉ በመሳተፍ ሲያግዘንና ሲያበረታን የነበረው ህዝባችን ላሳየን አጋርነትና ትብብር ሁሉ ልባዊ ምስጋና እያቀረብን ቀጣዩ ዓመትም ካሳለፍነው ዓመት የተሻሉ ግዙፍ ድሎችን በማስመዝገብ ህዝባችንን ወደ ብልጽግና የምናሻግርበት እንደሚሆን በመተማመን ይህን ታላቅ አገራዊ ራዕይ ለማሳካት ህዝባችን አብሮን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን።
መልካም አዲስ አመት!!
Qaammee 1 Guyyaa Cehuumsaa!
Barri haaraan waggaa dhumate geggeessee waggaa haaraa jalqabuu irras dabree yeroo rakkisaa duumeessaa'aa gara ji'a ifaa mijitaatti cehuu kan labsu,ilaalcha haaraa fi abdii ifaa kan itti simannu jalqaba boqonnaa haaraati.
Barri xumurame akka biyaa fi magaalaattis dameelee baay'een guddina hawaasumaa fi diinagdee uummata keenya dhugoomsuuf faayidaa guddaa kan qaban milkaa'inota dameelee baay'ee kan itti galmeessine akkasumas hiyyummaa irra gara boqonnaa amansiisaa badhaadhinaa nu ceesisuu bu'uura dandeessisu kan itti keenye bara ifaa milkaa'inaa fi guddinaa akka ta'e ifaadha.
Guyyaan cehuumsaa har'a kabajaa jirru kuni,qormaatilee gurguddoo bara dabre dabarsine fi gufuuwwan injifannoon ceene irraa baruumsa barbaachisu fudhannee haala kana keessatti haga humni hayyameen qaamota gumaachaa nuuf taasisanii fi nu gargaaran akkasumas guutuu uummata keenyaa onneerraa kan itti galateeffannu,akkasumas bara itti aanuu giddu gala tumsa keenyaa kan ta'e badhaadhina dhugoomsuu fi uummata keenya gara fooyya'iinsa hawwasummaa fi diinagdee guddaatti galma ceesisuu dhugoomsuuf waliin hojjechuuf guyyaa waadaa itti seennuudha.
Kanaafuu baroota jijjiiramaa dabarsineen abdii kennummaa bu'aalee misoomaa dinqisiisoo yeroo gabaabaa keessatti galmeessine ilaalee dhimmoota barbaachisaa ta'an hunda irratti hirmaachuun nu gargaaraa fi nu jajjabeessaa kan ture uummata keenya tumsaa fi walooma nutti mul'ise hundaaf Galata guddaa dhiheessaa barri itti aanuus bara dabrsine irra injifannoowwan gurguddoo galmeessuun uummata keenya gara badhaadhinaa kan itti ceesisnu akka ta'u amanuudhaan galma biyyaalessaa guddaa kana dhugoomsuuf uummatni keenya nu waliin akka dhaabbatu yaamicha dabarsina!
Bara Haaraa Gaarii!! See less
ከአፍሪካ ከተሞች ፎረም ጎን ለጎን ከናሚቢያዋ ዋና ከተማ ዊንድሆክ ከንቲባ ኦማግኖ ካማቲ ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ውይይት በማድረግ የእህትማማች ስምምነት ተፈራርመናል።
የውይይት ቆይታችን ወሳኝ የትብብር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የስምምነት ሰነድ ያካተተ ሲሆን በተለይም በፍሳሽ አወጋገድና በውሃ አቅርቦት፣ በከተማ ፕላን፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ ዘላቂ ትብብር መፍጠር የሚያስችል እና በሁለቱ ከተሞች መካከል ጠንካራ ግንኙነት የሚፈጥር ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
እዚህ የደረስነው ብዙ ነገሮችን ተሻግረን ነው። ያልተመዘዘ ሰይፍ፣ ያልተሰበቀ ጦር፣ ያልተተከለ ወጥመድ፣ ያልተሤረ ሤራ፣ ያልተቆፈረ ገደል አልነበረም። በፈጣሪ ርዳታ ሁሉንም እየተሻገርነው ነው።
ጦርነትን፣የኮሮና ወረርሽኝን፣ ግጭትን፣ የአንበጣ መንጋን፣ የሕዳሴ ግድብ ውጣ ውረድን፤ ተሻግረናቸዋል። ሌሎችንም እየተሻገርን ነው።
ተሻጋሪዎች ነን። አሻጋሪያችንም የማይሰበር ነው። ከማዶ አንቀርም። በመሐልም አንወድቅም። በድል እንደምንሻገር ቅንጣት ጥርጥር የለንም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የደረቅ ቆሻሻ የማጓጓዝ ስርአት ውጤታማነትን እና የጽ/ቤቱን እና የተጠሪ ተቋማት የህግ ማእቀፎች ላይ በማተኮር ባካሄዳቸው ጥናቶች ላይ ከተቋማት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ.።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ ሮ ቆንጂት ደበላ በዛሬው እለት ነሃሴ 30 ቀን 2016 አ.ም የተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ጽ/ ቤቱ የከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የተሳለጠ እና ቀልጣፋ በማድረግ ረገድ የተለያዩ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በማካሄድ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ባጎለበተ መልኩ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዛሬው እለት በመድረኩ የቀረቡት ሁለት ጥናቶችም የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ከመኖሪያ ቤቶች ጀምሮ እስከ ማስወገጃ ድረስ ያለውን የምልልስ መጠን ከመቀነስ፣ የትራንስፖርት ስርዓቱን ከማሻሻል፣ ቴክኖሎጂን ከማዘመን፣ማነቆ የሆኑ የህግ ማዕቀፎችን ከማስቀረት፣ በስታንዳርድ ከመስራት፣የነዳጅ ወጪ ከመቆጠብና ከመሳሰሉት አንፃር ጥናቶቹ መፍትሄ አመላካች ሆነው የቀረቡ ሲሆን በተሳታፊዎች ዘንድም ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል።
የውይይት መድረኩን ወ/ ሮ ቆንጅት ደበላና የዋና ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ እስማኤል መርተውታል።
በዚሁ መድረክ ላይ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ እንደገለፁት ጥናቱ የከተማችንን ፈጣን እድገት መሰረት ያደረገና ከተማዋን ጽዱ፣ ሳቢ እና ምቹ አድርጎ በማስቀጠል ሂደት አዳዲስ አሰራሮችን የሚያመላክት እንደመሆኑ ጥናቶቹ ለዘርፉ ከፍተኛ ሚናና አስተዋጽኦ እንዳላቸው አመልክተዋል።
ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ አክለው እንደገለፁት ጥናቶች ከጥናትነት አልፈዉ መሬት ላይ ወርደዉ ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ሁሉም ባለድርሻ አካል የእቅዱ አካል እያደረገ ወደ ተግባር ለማስገባት በጋራ ተረባርቦ መስራት አስፈላጊ ነዉ ሲሉም አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ዛሬ በተጀመረው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን ላይ በከተማችን አዲስ አበባ ለጎብኚዎች ከቀረቡ ስራዎች ውስጥ በከፊል:-
የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ከተሞች መነቃቃትን የፈጠረ፤ የህዝብ እና መንግሥት ትብብር ውጤት ነው:: - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባን ከመሰረቱ ለማደስ እና በሁለንተናዊነት ለማልማት በተጀመረው ስራ ተጨባጭ የሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ከተሞች ፎረም መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን-አፍሪካን አዳራሽ በዛሬ ዕለት በተጀመረው የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስኬት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ከተሞች መነቃቃትን የፈጠረ የህዝብ እና መንግሥት ትብብር ውጤት ነው ብለዋል።
ያለ ከተማ ፕላን የተገነቡ ያረጁና ያፈጁ ሰፈሮችን ለአኗኗር ምቹ በሆነ ደረጃ እንደገና ማደስ፣ ለሰውና ለትራንስፖርት የማይመቹ መንገዶችን ደረጃቸውን ጠብቀው መገንባት፣ እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ያለ ልዩነት የሚጠቀሙበትን የህዝብ መዝናኛዎችን በማስፋፋት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውንም ከንቲባዋ ጨምረው ገልፀዋል።
ለአብነት ያህል የሳይክል መንገዶችን እና መሮጫ ትራኮችን የመገንባት ስራ፣ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎቶችን እርስበርሳቸው መናበብ በሚያስችላለው ሁኔታ ተደራሽ የማድረግ ስራ የኮሪደር ልማቱ ትሩፋቶች ናቸው ብለዋል።
እነዚህ መደበኛ እና ኮሪደር ልማቶች የአዲስ አበባን ውበት፣ ተወዳዳሪነትና ምቹነት ከማሳደጋቸው በተጨማሪ የነዋሪዎቻችንን ፍትሐዊና እኩል ተጠቃሚነት እውን ማድረጋቸውን ያነሱት ከንቲባዋ በከተማው ውስጥ እየተሰሩ ያሉት ፕሮጀክቶች ለብዙ ሺ ዜጎቻችን የስራ ዕድል መፍጠራቸውን እና የንግድ ተቋማትን ማነቃቃታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
