1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂደዋል ።
በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች ፡-
1 ኛ. የኮሪደር ልማት የግዥ ጥያቄ ፣ የግንባታ በጀት እና የግዢ ሂደት አወሳሰን በተመለከተ በፋይናንስ ቢሮ በኩል ለቀረበልን ጥያቄም፤ ለልማቱ መሳለጥ እና የሀብት መባከን እንዳይፈጠር እንዲሁም የሥራ ቅልጥፍናን በሚጨምር መንገድ ለመስራት እንዲያስችል የሚያደርግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተወያይተን አፅድቀዋል ::
2ኛ. በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የሚተዳደሩ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አያያዝ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም እና ወደ ከተማው ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ዘይቤ ማምጣት እንዲያስችሉ ተቋማቱ በትምህርት ቢሮ ይዞታ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ደንብ አስፈላጊ በመሆኑ አፅድቀዋል።
3ኛ. የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ኃይል ስምሪት በማዕከል ፣ በክ/ ከተማ እና በወረዳ ለማመጣጠን እንዲቻል በተዘጋጀው የዝውውር እና ምደባ ረቂቅ ደንብ በየተቋማቱ ያለንን የሰው ሀብት በውጤታማነት ለመጠቀም እንዲያችል የሚያግዝ በመሆኑ በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።
መስከረም 28/2017
አዲስ አበባ
ሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ከመንግስት እና ከግል ሚድያ ጋዜጠኞች ለተነሱልኝ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥቻለሁ።
በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በተሰጠን የስራ መመሪያ መሰረት የተጠኑት የሁለተኛ ዙር ኮሪደሮች ስምንት ሲሆኑ፣ ለህዝብ ያለእረፍት እየሰራን ከህዝብ የምንደብቀው ምንም ስለሌለ በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቻለሁ። ማብራሪ መስጠቱ ለወደፊትም ይቀጥላል።
የኮሪደር ልማት ዋና አላማዉ ከተማችንን ለመኖር ምቹ ማድረግ፣ ማደስ፤ ገፆታዋን ማሻሻል እና ከልማቱ ማንም ወደ ኋላ ሳይቀር ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነዉ።
ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን በአጠቃላይ 2,817 ሄክታር መሬት በሚሸፍን እና 132 ኪ.ሜ ርዝመት ባለው ቦታ ላይ የሚገነባ ሲሆን፣ በግንባታ ስራው ከተካተቱ የመሰረተ ልማት ስራዎች ውስጥ የመንገድ ግንባታ፣ የአረንጓዴ ቦታዎች ግንባታ፣ የብስክሌት መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የታክሲና አውቶቢስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንጎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የህዝብ መጸዳጃ ቦታዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ፣ ደረጃውን የጠበቀ የከተማ መብራት፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ ስራ ተጠቃሾቹ ናቸው።
ስራዉ በዋናነት በከተማው አቅም እና በጀት የሚከናወን ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፤ የመብራት አገልግሎት እና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዚህ ውስጥ መሰረተ ልማታቸውን በመዘርጋትና ከተማዋን ስማርት ሲቲ በማድረግ በኩል ትልቅ እገዛ የሚያደርጉ ይሆናል።
ሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራችንን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በቂ ቅድመ ዝግጅት ያደረግን ሲሆን፣ በመልሶ ማልማት ሲኖሩ ከነበሩበት ለመኖር ምቹ ያልሆነ ጎስቃላ አካባቢዎች ለተነሱ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤቶችን፣ በቂ የመስሪያ ሼዶችን፣ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም ከ 500 በላይ የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን ዝግጁ አድርገናል። በተመሳሳይ ምትክ መሬት እና ካሳ አዘጋጅተናል።
በሁለተኛ ዙር የተለዩት ኮሪደሮች:-
1. ካሳንቺስ- እስጢፋኖስ-መስቀል አደባባይ- ሜክሲኮ- ቸርችል-አራት ኪሎ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ (የኮሪደሩ ርዝመት 40.4 ኪ/ሜ)
2. ጫካ ፕሮጀክት (ሳውዝ ጌት)- መገናኛ- ሃያ ሁለት- መስቀል አደባባይ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 7.1 ኪ.ሜ)
3. ሲኤምሲ- ሰሚት- ጎሮ- ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል ኮሪደር እና የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 10.8 ኪ.ሜ)
4. ሳር ቤት- ካርል አደባባይ- ብስራተ ገብርኤል- አቦ ማዞሪያ- ላፍቶ አደባባይ- ፉሪ አደባባይ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 15.9 ኪ.ሜ)
5. አንበሳ ጋራዥ- ጃክሮስ- ጎሮ ኮሪደር ( የኮሪደሩ ርዝመት 3.1 ኪ.ሜ)
6. አራት ኪሎ- ሽሮ ሜዳ- እንጦጦ ማርያም- እጽዋት ማዕከል ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 13.19 ኪ.ሜ)
7. ቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 20 ኪ.ሜ)
8. እንጦጦ-ፒኮክ ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር (የኮሪደሩ ርዝመት 21.5 ኪ.ሜ)
ከላይ የተዘረዘሩ ኮሪደሮችን ምዕራፍ በምዕራፍ ከፍለን በጥራት እና በፍጥነት የምንሰራ ሲሆን፣ የከተማችን ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የትራፊክ መጨናነቅን ጨምሮ የሚኖሩ ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎችን በመቻል እንደ መጀመሪያው ዙር በትብብር ከተማችንን በጋራ እንድንገነባ አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ክብርት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ ላለፉት ስድስት አመታት የኢትዮጵያ ፕረዚዳንት በመሆን ስለሰጡን አገልግሎት እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት የተጠሪ ተቋማትን የ2017 በጀት አመት የተቋም ግንባታና ልዩ የተቋማዊ ሪፎርም ዕቅድ በጋራ እየገመገመ ይገኛል ።
የግምገማ መድረኩን በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣የጽ/ቤቱ ከፍተኛ. አመራሮች አቶ ተፈራ ሞላ እና ወ/ ሮ ቆንጅት ደበላ እየመሩት ይገኛሉ።
በመድረኩ ላይ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ የሲቪል ምዝገባና መረጃ አገልግሎት ኤጀንሲ ፣ የከተማው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን እንዲሁም የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሸን የተቋም ግንባታና ልዩ የሪፎርም እቅዳቸውን ከልማት እቅዳቸው ጋር አቀናጅተው ለውውይት አቅርበዋል::
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ዋ/ስራ/ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለጹት በተጠሪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡ ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሁም የህብረተሰቡን እርካታ የሚያረጋግጥ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከር ከማዕከል እስከ ታችኛው የዘርፉ መዋቅር ያሉ አመራሮችና እንዲሁም ሰራተኞች ቀጣይነት ባለው እና ውጥ በሆነ መልኩ የሪፎርም ስራዎቸ እንዲተገበሩ ለማድረግ ይህ አይነቱ መድረክ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት የተጠሪ ተቋማትን የ2017 በጀት አመት የተቋም ግንባታና ልዩ የተቋማዊ ሪፎርም ዕቅድ በጋራ እየገመገመ ይገኛል ።
የግምገማ መድረኩን በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣የጽ/ቤቱ ከፍተኛ. አመራሮች አቶ ተፈራ ሞላ እና ወ/ ሮ ቆንጅት ደበላ እየመሩት ይገኛሉ።
በመድረኩ ላይ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ የሲቪል ምዝገባና መረጃ አገልግሎት ኤጀንሲ ፣ የከተማው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን እንዲሁም የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሸን የተቋም ግንባታና ልዩ የሪፎርም እቅዳቸውን ከልማት እቅዳቸው ጋር አቀናጅተው ለውውይት አቅርበዋል::
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ዋ/ስራ/ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለጹት በተጠሪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡ ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሁም የህብረተሰቡን እርካታ የሚያረጋግጥ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከር ከማዕከል እስከ ታችኛው የዘርፉ መዋቅር ያሉ አመራሮችና እንዲሁም ሰራተኞች ቀጣይነት ባለው እና ውጥ በሆነ መልኩ የሪፎርም ስራዎቸ እንዲተገበሩ ለማድረግ ይህ አይነቱ መድረክ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በትላንትናው እለት በከተማችን በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶቻችንን ግንባታዎች ተዘዋውረን ገምግመናል።
በተለይም ከተማችንን የኮንፍራንስ፣ የቱሪዝም እና የስበት ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት የሚያረጋግጡ፣ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ እንዲሁም ለነዋሪዎቻችን የስራ እድልን በሰፊው የሚፈጥሩ የአዲስ ኢንተርናሽናል የኤግዚቢሽንና የኮፍረንስ ማዕከል፣ ከዚያ ጋር ተያይዞ እየተሰራ ያለውን የለሚ ፓርክ፣ አየር መንገድ-ጎሮን ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ጋር የሚያገናኘዉን መንገድ ግባታ እና የአረንጏዴ ልማት ስራዎቻችን ያሉበትን ደረጃ ጎብኝተናል።
ፕሮጀክቶቹ በተገቢ ጥራት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን በፍጥነት ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ በቅርበት ክትትል እያደረግን በመስራት ላይ እንገኛለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ምንድናቸው የሚለው ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።
👉 ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
👉በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
👉 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ- ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
👉መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽከርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም መሆናቸውን ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የፍራፍሬ ስራችን ፍሬያማነቱ መገለጫ:: የዛሬ ሶስት ዓመት በፊት የተከልናቸው::
Tattaaffiin keenya gama muduraatiin taasifne firii godhataa jira. Waggoota sadii dura kan dhaabne.
Our eff… See more
በዛሬው እለት መስከረም 25 ቀን 2017 አ.ም የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በታላቅ ድምቀት በመዲናችን አዲስ አበባ ተካሂዶ በሰላም መጠናቀቁ ይታወቃል።
ይህንንም ተከትሎ በዓሉ በድምቀት የተከበረበትን ቦታ የማፅዳት ስራ ተከናውኗል።
በፅዳት መርሐ ግብሩ ላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙባረክ ከማልን ጨምሮ የክፍለ ከተማው አመራሮች ፣የፅዳት እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ዘይዳ ነስረዲን ገልፀዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
