1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
እኔም የአካባቢዬ ፅዳት ባለቤት ነኝ!"
ብሎክን መሰረት ያደረገ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
በዚሁ የጽዳት ንቅናቄ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ፣ የክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አመራሮች እና የወረዳ አመራሮች፣ የከተማ የጽዳት አምባሳደር አርቲስቶች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች፣ የጸጥታ አካላት እና የወረዳው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
መርሃ-ግብሩ በኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀረ ሲሆን በታዋቂ አርቲስቶች በኪነ ጥበብ የተደገፈ በጽዳት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በመሪዎቻችን ትጋትና ብርታት አዲስ አበባን በውበት እና በብልጽግና የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት ለሊት እና ቀን እየተሰራ እንደሆነና በክፍለ በከተማችን በሁሉም ዘርፍ ውጤት እየተመዘገበ ነው በማለት ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደተናገሩት የአንድ ከተማ ማደግና መበልጸግ የሚመዘነው ጽዱና ውብ ስትሆን ነው። በዚህም ሁሉም ነዋሪ የፅዳት አምባሳደር መሆን ይገባል በማለት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ በሁሉም ዘርፍ ለውጥና ውጤት እያስመዘገበ ነው ብለዋል።
የጽዳትን ስራ ለአንድ ወገን ብቻ ባለመተው ሁሉም በመረባረብ ሞዴል መንደር እና ብሎኮችን መፍጠር እንደሚገባና የኃይማኖት ተቋማት፣ ዕድሮች እና የትምህርት ተቋማት ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግና ነዋሪው የሚሰጠውን ግንዛቤ በተግባር ላይ በማዋል ቆሻሻን ለይቶ መያዝና ማስወገድ እንዲሁም መልሶ መጠቀም እንደሚገባና ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚጥሉ ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ በበኩላቸዉ በጽዳት ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሆነ እና ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ሀብት የመፍጠር ደረጃ ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለስራ ኃላፊዎች የምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ሚያዚያ 25 / 2017 ዓ.ም
የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በከተማችን በፍጥነት እና በጥራት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶንን እየጎበኙ ነው !
የአዲስ አበባ ፈጣን ዕድገት በህዝባችን ብቻም ሳይሆን ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው ፣ አንዳንድ ሀገራትም ተሞክሮውን ለማስፋትም እንደሚፈልጉ እየተናገሩለት የሚገኝ አንፀባራቂ ድል ነው።
የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የተረዳው ህዝባችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት እንዲፋጠን ቀን እና ሌት 7/24 እየተጋ ከሚገኘው አመራራችን ጎን ተሰልፎ ርብርቡን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህም ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ ሲሆን በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በሌሎችም በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች የቅርብ ክትትል የተጠናቀቀው የካዛንችስ ኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ደግሞ በቅርቡ በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለምርቃት በቅቷል።
ካዛንችስ አሁን ላይ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች። ከጥልቅ ጉስቁልና ተላቅቃ የከተማችን ድምቀት መሆን ችላለች።
በካዛንችስ እና አካባቢው የተገነቡ 40 ነጥብ 9 ኪ /ሜ የአስፓልት ፣ 81 ነጥብ 9 ኪ /ሜ የእግረኛ ፣ 20 ኪ /ሜ የሳይክል መንገዶች የህዝባችንን እና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን አሳልጠዋል።
ለካዛንችስ የልማት ተነሽዎች በተሻለ የመኖሪያ አካባቢ የተሻለ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ሲሆን ፤ በንግድ ስራ ተሰማርተው ለነበሩት ደግሞ ለካዛንችስ አዲስ ገፅታ የተሻለ የኢኮኖሚ መነቃቃት መፍጠር የሚያስችሉ ሱቆች ተገንብተዋል።
በካዛንችስ እና በአካባቢው የነበሩ የመሰረተ ልማት ችግሮችን የሚያቃልሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን የህዝብ መናፈሻ ፓርኮች ፣ 15 የህፃናት መጫዎቻ ፣ 40 የመኪና ማቆሚያ ፣ 19 መፀዳጃ ቤቶችም ፣ የስፖርት ፓርክ ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች እና ሌሎችም ተገንብተዋል።
የአዲስ አበባ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አመራሮች እና አባላትም የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ እያሻሻሉ የአዲስ አበባን ስምና ግብር እያገናኙ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።
"እኔም የአካባቢዬ ፅዳት ባለቤት ነኝ!"
ብሎክን መሰረት ያደረገ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
በዚሁ የጽዳት ንቅናቄ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ፣ የክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አመራሮች እና የወረዳ አመራሮች፣ የከተማ የጽዳት አምባሳደር አርቲስቶች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች፣ የጸጥታ አካላት እና የወረዳው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
መርሃ-ግብሩ በኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀረ ሲሆን በታዋቂ አርቲስቶች በኪነ ጥበብ የተደገፈ በጽዳት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በመሪዎቻችን ትጋትና ብርታት አዲስ አበባን በውበት እና በብልጽግና የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት ለሊት እና ቀን እየተሰራ እንደሆነና በክፍለ በከተማችን በሁሉም ዘርፍ ውጤት እየተመዘገበ ነው በማለት ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደተናገሩት የአንድ ከተማ ማደግና መበልጸግ የሚመዘነው ጽዱና ውብ ስትሆን ነው። በዚህም ሁሉም ነዋሪ የፅዳት አምባሳደር መሆን ይገባል በማለት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ በሁሉም ዘርፍ ለውጥና ውጤት እያስመዘገበ ነው ብለዋል።
የጽዳትን ስራ ለአንድ ወገን ብቻ ባለመተው ሁሉም በመረባረብ ሞዴል መንደር እና ብሎኮችን መፍጠር እንደሚገባና የኃይማኖት ተቋማት፣ ዕድሮች እና የትምህርት ተቋማት ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግና ነዋሪው የሚሰጠውን ግንዛቤ በተግባር ላይ በማዋል ቆሻሻን ለይቶ መያዝና ማስወገድ እንዲሁም መልሶ መጠቀም እንደሚገባና ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚጥሉ ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ በበኩላቸዉ በጽዳት ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሆነ እና ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ሀብት የመፍጠር ደረጃ ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለስራ ኃላፊዎች የምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ሚያዚያ 25 / 2017 ዓ.ም
ዉጤታማ የስራ አፈፃፀማችንን በማጠናከር ክፍተቶችን እየዘጋን የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከለውጡ በፊት የከተማዋ ነዋሪዎች ፅዱና ልምላሜን አካባቢ ለማዬት ሲፈልጉ ለጉብኝት ከከተማዋ ራቅ ብለው ወደሚገኙ አካባቢዎች ነበር የሚወጡት። ዛሬ እናንተ ወጣቶች ታድላችሁዋል።ፅዱና ልምላሜ ቦታዎች በመዲናችን ተፈጥሮላችሁዋል።"
ሃጂ ሸምሱ አባስ
የመዲናችን የፅዳት አምባሳደር
መንግስት የአዲስ አበባ ከተማን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ እያደረገ ያለውን ተግባር ለማገዝ ነዋሪው ፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ እንዳለበት ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መድረክ በማዘጋጀት፣ በቤት ለቤት፣ በሻይ ቡና ፕሮግራም፣ በንቅናቄ እና በተለያዩ ስልቶች ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አሳዉቋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት፣መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳትና የጎርፍ መከላከል ንቅናቄ ዕቅድ ዙሪያ ለብሎክ ካውንስል አመራሮች፤ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣አስተባባሪና ቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናየ ጫኔ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት የሚሰጠውን ግናዛቤ ወደ ተግባር ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግና በጽዳት ስራው የኃይማኖት ተቋማት፣ዕድሮች፣ድርጅቶችና ተቋማት በንቃት ልትሳተፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ እንደተናገሩት ቀደም ሲል በመኖሪያ አከባቢ በተቋማትና በብሎክ የጽዳት ንቅናቄ ስናካሄድ የቆየን ሲሆን መጪው ክረምት በመሆኑ የፍሳሽ መውረጃዎችን ማጽዳት ይገባል ብለዋል።
በጽ/ቤቱ የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪ ወ/ሮ እቴነሽ አበራ እና አቶ ጌቱ ኩምሳ የክፍለ ከተማው ጽዳት ስራዎች አስተባባሪ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።
በክፍለ ከተማው በሚፈጠር ግንዛቤ የህብረተሰቡ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደመጣና ቆሻሻን የመለየትና መልሶ መጠቀም እየተለመደ መምጣቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ አያይዘውም መንግስት የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ውብና ማራኪ እየደረገ ያለውን ተግባር ነዋሪውም በየአከባቢው የፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም ጨለማን ተገን በማድረግ ቆሻሻ በመነገድ ላይ የሚጥሉና የሚያዝረከርኩ ህገ ወጦችን መከታተልና የወጡ ህግና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ በቅጣት ማስተማር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሚያዝያ 24/ 2017
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የምንላቸው የከተማችን ነዋሪዎች በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያቸው ጋር የተገናኙ መሠረታዊ አገልግሎቶች በመሆናቸው ህዝቡ በቂ ግንዛቤ ኖሮት በሂደቱ ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርግ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወን እንገኛለን።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሠጡት ምላሽና ማብራሪያ
ህዝብን በማዳመጥ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች እና ዝርዝር መረጃዎችን መስጠት የተጠያቂነት ስረአትን ግንባታ አካል ነዉ።
መዲናችን አዲስ አበባ ለአብዛኞች የአፍሪካ አገራት ከተሞች የጽዳት ተምሳሌት እየሆነች ትገኛለች"
"በየቤታችን እኛ አንፈልገውም ብለን የምንጥለው ቆሻሻ 50 በመቶ የሚሆነው ለመልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችልና ለዜጎቻችን የስራ እድል የሚፈጥር ነው።"
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
ዛሬ ከከተማችን ነዋሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት አማካኝነት ቀርበው ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተናል።
ህዝባችንን ማዳመጥ እና ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን እና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት የአመራራችን መገለጫ፣ የአገልግሎታችን አንዱ እና ትልቁ አካል በመሆኑ ከነዋሪዎቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም ሃሳቦች በሙሉ ምላሽ እና ማብራሪያዎችን ሰጥተናል።
ለተነሱልን ጥያቄዎች የተሰጡ ማብራሪያዎችን እና ዝርዝር መረጃዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲሁም በዚህ ገፅ የምንለቅ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው ለ2017 ዓ.ም ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እና ልዩ ልዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቅቋል:: በዚህም መሰረት:-
1. ወ/ሮ ቆንጆት ደበላ - የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ(በሽግሽግ)
2. አቶ አወሌ መሐመድ ኦመር - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
3. ወ/ሮ አይሻ መሐመድ አደን - የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
4. ኢ/ር ሕይወት ሣሙኤል ጸጋዬ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
5. ሲ/ር ሶፊያ አለሙ - የሴቶች፣ የወጣቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ ሆነው ተሹመዋል::
በሌላ በኩል ተጨማሪ በጀቱ በከተማዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡