ch
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በመተባበር ችለናል!!… See more

ኢትዮጵያ ችላለች"በሚል መሪ ቃል የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ድጋፉንና ደስታውን ለመግለፅ በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ነው:: #ኢትዮጵያ ችላለች!!!

የብርሃን አሻራ ህዳሴ የብርሃን አሻራ ህዳሴ

ከታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ምን ተማርን፣ ባለፈው ዓመት ምን አሳካን፣ ምን ፈተነን፣ በቀጣይስ ምን አቅደናል - ከኢቲቪ ጋር የነበረኝ ቆይታ እነሆ፤… See more

የህዳሴ ግድብ በጋራ ስንተም ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደምንችል ማሳያ ነው!- አቶ ጃንጥራር አባይ የህዳሴ ግድብ በጋራ ስንተም ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደምንችል ማሳያ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለፁ፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። የውይይት መድረኩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በጋራ ስንተም ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደምንችል ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም የግድቡ መጠናቀቅ ትልቅ ድል ነው፤ ለዚህ ስለበቃን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በፓናል ውይይቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 14 ዓመታት ያለፈበትን ውጣ ውረድ፣ የተገኙ ድሎች፣ የውሃ ፖለቲካ ምንነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽሁፎች ቀርበው ወይይት እየተካሄደባቸው ነው። ከፓናል ውይይቱ ጎን ለጎን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ ከተቀመጠለት ጊዜ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለፈበትን ሁኔታ የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይም ክፍት ተደርጓል። #aa_prosperity #የኩስመና_ታሪክ_ማብቅያ #GERD #Ethiopia #addisababa #በህብረት_ችለናል

ኢትዮጵያ ችላለች ! ዛሬ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን የ14 ዓመት ጉዞ፤ በተለይም የህዝቡን ተሳትፎ የሚያሳይ የፎቶ፣ የስዕል እና በአባይ ዙሪያ የተፃፉ መፃህፍት አውደ ርዕይ እና ፓናል ውይይት አካሂደናል። በፖናል ውይይቱ የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያለዉ ፋይዳ፣ ከጂኦስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና መሸጋገር፣ የህዝብ አንድነትና ተሳትፎ ትርጉም አስመልክቶ በምሁራን ትንታኔ ቀርቧል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 14 ዓመታት ያለፈበት ውጣ ውረድ፣ የተገኙ ድሎች፣ የውሃ ፖለቲካ ምንነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽሁፎች ቀርበው ወይይት ተካሂዷል። ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከትዉልድን ትዉልድ የተሸጋገረዉን የዘመናት ቁጭትን ፀሎት ተመልክቶ በሳቅና እልልታ የሞላዉ ፈጣሪ አምላክ ይመስገን ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"በህብረት ችለናል "…

በአዲስ አበባ ከተማ የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም ተከብሮ አልፏል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሃመድ እንደገለፁት የዘንድሮው የዘመን መለወጫ በዓል ያለ ምንም አደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ በከተማ አስተዳደሩና በኮሚሽኑ ህብረተሰቡን ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተገንዝቦ አስፈላጊዉ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶች ሲተላለፉ ቆይቷል። ኮሚሽነር አህመድ አክለውም በዚህም የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ህብረተሰቡ በአሉን ባማረና በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ተግባራት የሚከናወኑበት ቢሆንም ሊኖር ከሚችል የአደጋ ተጋለጭነት አንጻር ያለ ምንም አደጋ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ለህብረተሰቡ የተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን በመተግበራቸው አመስግነዋል። ይሁንና በጳጉሜ 5 ሌሊት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ብሄረ ጽጌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መጠነኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በፍጥነት ቦታው ላይ ደርሰው በቁጥጥር ስር በማዋላቸው አደጋው በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሱን ኮሚሸነር አህመድ ገልፀዋል። ኮሚሽነር አህመድ አክለውም በአሉ ያለምንም አደጋ ክስተት እንዲከበር በሚዲያዎችና በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች የጥንቃቄ መልእክት በማስተላለፍ ወደ ህብረተሰቡ ያደረሱ አካላትን አመስግነው ለህብረተሰቡም በበዓላት ጊዜ የተደረጉ የጥንቃቄ ተግባሮች በመደበኛና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችም ባህል እንዲያደርጋቸው ጥሪ አቅርበዋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ ! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው። ‎"በህብረት ችለናል " በሚል መርህ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

‎የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው። ‎"በህብረት ችለናል " በሚል መርህ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።