ch
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ላይ ዉይይት ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2018 በጀት አመት እቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጆ ጋር የዉይይት መድረክ በዛሬዉ እለት አካሂዷል። በመድረኩም በ2018 በጀት አመት መሪ እቅዶችን እና የበጀት አመቱ ያለፉት ሁለት ወራት የስራ አፈፃፀም የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተካሂዶበታል። በመድረኩ በቢሮ ሀላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለፁት የጽ/ቤቱ የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ያለፉት ሁለት ወራት የስራ አፈጻጸሞች አገልግሎቱን ከመምራት፣ከማስተባበር፣ ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ፣ የተሳለጠና ፍትሃዊ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መሰጠቱን ከማረጋገጥ አንፃር በቀጣይ ጊዜያት ካሁኑ በላቀ ትጋት ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ ገልጸዋል። አክለውም ይህንኑ በ2018 በጀት አመት በላቀ ብቃት ተግባራዊ ለማድረግ የመዲናችን ነዋሪዎች በቴክኖሎጅ የዘመነ አገልግሎት ፣ ቀልጣፋ፣ግልፅና ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ስማርት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ግንባታን በማፋጠን የተቀናጀ ሞዴል የመፍጠር ስራዎችን በሁሉም ተጠሪ ተቋሞቻችን ላይ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። በተያያዘ ባለፋት ሁለት ወራት በየክፍለ ከተሞች በተከናወኑት ተግባራት መልካም እንደሆነ ተገልጾ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን በፍጥነት በ24/7 በልዩ ትኩረት በመስራት በቀሪ ስራዎች ላይ በርብርብ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የጳጉሜ ቀናትን እና በቀጣይ ያሉ በአላት ላይ አከባበር ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

I am sharing 'ነሐሴ 2017' with you

ነሐሴ 2017.pdf1.91 MB

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአጭር ጊዜ የሚተማመኑበት ተቋም ሆኗል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት እና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የፊርማ ስነስርዓቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ያከናወኑ ሲሆን፤ ስምምነቱ የነዋሪውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ላቅ ያለ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አጀንዳ በማደራጀት ውጤታማ መሆኑን ጠቁመው፤ ተቋሙ በአጭር ጊዜ የሚተማመኑበት ተቋም ሆኗል ብለዋል፡፡ ሚዲያ ህዝብ እና መንግስትን የሚያገናኝ ድልድይ ነው በማለት፤ ስምምነቱ የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት የሚያከናወናቸውን ስራዎች ወደ ህዝብ ለማድረስ ብሎም ህዝብ ጋር ያለውን ሃሳብ ለማድመጥ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ወደ ህዝቡ የሚደርስበት በርካታ ፕላትፎርሞች ያለው መሆኑም ይህንን ለማከናወን ይረዳልም ብለዋል፡፡ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፤ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በከተማዋ ልማት ውስጥ ያላቸውን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ እና የከተማዋን ነዋሪ እርካታ ለማረጋገጥ ይረዳል ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ከፍ ብላ እድትታይ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አበርክቶ ላቅ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ እነዚህን ስራዎችም ማሳየት እንደሚገባ እና በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኃላፊነት ጉልህ መሆኑን አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአቀራረብ እና ይዘት ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ሆኗል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ተቋሙ ትክክለኛ ሜትሮፖሊታን ሚዲያ የመሆን ግቡን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በመንግስት እና ህዝብ መካከል ድልድይ በመሆን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ብልሹ አሰራሮች እዲጋለጡ የማድረግ እና ህዝቡ የሚፈልገውን ነገር በአግባቡ እንዲያገኝ በማድረግ ተግባር ውስጥ በስፋት እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡ ኤ ኤም ኤን በቴክኖሎጂ እራሱን በማደራጀት፣ ብዝሃነትን በማስረጽ በተለያዩ ቋንቋዎች ህዝቡ ጋር እየደረሰ ያለ ተቋም መሆኑን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በአሁኑ ወቅት በ5 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች እና ሁለት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች በድምሩ በ7 ቋንቋዎች በተለያዩ አማራጮች ህዝብ ጋር እየደረሰ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሆን ለተሻለ ነገር እንደሚሰሩም አቶ ካሳሁን ጠቁመዋል፡፡ AMN-Addis Media Network ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ላምን ማጽናት የጸጥታ ተቋማት ዋነኛ ተልዕኳቸው ነው የኢፌዴሪ የጸጥታ ተቋማት ዋነኛው ተልዕኮ ሰላምን በመላ ሀገሪቱ ማጽናት ነው፡፡ ይሄን በተመለከተ ከጸጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት ዛሬ ተጠቃልሏል፡፡ የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ሰላምና ጸጥታ አስቻይ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው ግብዐትም ነው፡፡ ይሄን ለማስከበር ሕዝባችን በባህሉና በዕሴቱ ላይ ተመሥርቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ፣ የጸጥታ ተቋማት ሚና የማይተካ ነው፡፡ የአሻጥር፣ የከተማና የገጠር ውንብድና፣ የኮንትሮባንድ፣ የሙስና፣ ሕገ ወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር እና የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመከላከልና በመቆጣጠር የሕዝቡን ሰላም ማስከበር እንደሚገባ በውይይቱ ላይ በስፋት ተነሥቷል፡፡ የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውር ለብልጽግናችን ወሳኝ ናቸው፡፡ ስለዚህም በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ዝርፊያዎችን፣ እገታዎችን እና መሰናክሎችን በተጠና መንገድ መቆጣጠር ይገባናል፡፡ የጸጥታ ኃይላችን ሕዝቡን በየደረጃው በማስተባበር እነዚህን አካላት ከእኩይ ተግባራቸው መግታት፣ ብሎም ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ አጽንዖት ተሰጥቶበታል፡፡ ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን፣ የማዕድን ቦታዎችን፣ ኢንዱስትሪዎችን፣ የመኖሪያ አካባቢዎችን እና የሕዝብ መገልገያዎችን ደኅንነት ለመጠበቅና አገልግሎታቸው ያለ እንከን እንዲፈጽሙ ለማስቻል የጸጥታ አካላትና የየአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብር ወሳኝ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተነሥቷል፡፡ ሕዝቡ ሰላሙን በራሱ እጅ የማስከበር ፍላጎቱ፣ ዝግጁነቱና ዐቅሙ በየጊዜው እያደገ መምጣቱ ተገምግሟል፡፡ ባህላዊና መንፈሳዊ ዕሴቶቹን በመጠቀም የታጠቁ አካላት ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ እያደረገ ነው፡፡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተባብሮ የአካባቢውን ሰላም እያስከበረ ነው፡፡ የጸጥታ አካላት ለሚያከናውኑት ሥምሪትም የመረጃና የሎጂስቲክስ ድጋፍ እየሰጠ ነው፡፡ ይሄን የሕዝቡን ዐቅም ይበልጥ በሥልጠና በማጎልበት ለዘላቂ ሰላም መጠቀም እንደሚገባ በውይይቱ ማጠቃለያ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ በማሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል የሽብር ተግባር የሚፈጽሙትን ትኩረት ሰጥቶ መከታተል እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት የተነሣ ሲሆን፣ በሳይበር ቴክኖሎጂ በኩል መከናወን የሚገባቸው የመከታተልና የመቆጣጠር ሥራዎች ይበልጥ መጠናከር እንደሚገባቸው በውይይቱ ተመልክቷል፡፡ በአንድ በኩል የቴክኖሎጂ የመከላከያና መቆጣጠሪያ ሥራዎችን ለመሥራት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሽብር ፈጣሪዎቹን ለሕግ ለማቅረብ የጸጥታ አካላት በጽኑ መሥራት እንዳለባቸው መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ የጸጥታ ተቋማት ወትሮ ዝግጁነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር በሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱን በውይይቱ ተገምግሟል፡፡ ኢትዮጵያ ከዘመን ጋር የዘመኑ እና በሕገ መንግሥታዊ ዕሴቶች ላይ የተገነቡ የጸጥታ ተቋማት እየገነባች መሆኗ ተረጋግጧል፡፡ ይሄንን ግንባታ የዘወትር ተግባር በማድረግ መቼም፣ የትም፣ ለምንም ዓይነት ሁኔታ ዝግጁ የሆኑ የጸጥታ ተቋማትን እየገነባን እንድንሄድ የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካዊ ኩስመና ባከተመበትና ቁመናዋ እየተስተካለ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የጸጥታ ተቋሞቻችን የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ ነጻነት፣ ዳር ድንበር፣ ሰላምና ደኅንነት፣ ብሎም የብልጽግና ጉዞ ለማስከበር በሚችሉበት ዐቅም እና ዐቋም ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ ይሄንኑ ወትሮ ዝግጁነት ይበልጥ በማጠናከር፣ የውስጥና የውጭ ችግር ፈጣሪዎችን አደብ አስገዝቶ፣ ሰላምን በሚያጸና ልክ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ የጸጥታ ተቋማት ዋና ተልዕኮ ሰላምን ማጽናት ነውና፡፡ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን"… See more

የ1500ኛው የመውሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሙሉ እድሳት የተደረገበትየአቅመ ደካማ ቤት የቁልፍ ርክክብና መዓድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄደ … See more

ከለዉጡ በፊት አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን ሁሉም ከተሞች የተረሱ ነበሩ አሁን ግን በተለይም በመዲናችን እየተሰራ ያለዉ ስራ በፊት የነበሩ ችግሮችን ታሪክ አድርጎ ያስቀረ ነዉ።- በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከኢቢሲ ዳጉ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያስተላለፉትን መልእክት በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!…

download.htm1.28 MB

የ2017 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት ስያሜ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager